በኢትዮጵያ ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ 5 በመቶ ያህሉ ሲጋራ አጫሽ ናቸው ተባለ
ኢትዮጵያ የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር በመቀነስ ስኬታማ ሀገራት ከሆኑ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን ከትንባሆ ነጻ ህጻናት የተባለ ድርጅት አታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከአጫሾች በሚወጣ የትምባሆ ጭስ እንደሚቸገሩ ከዚህ በፊት የተደረገ ጥናት ያሳያል ሲሉ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የተናሩት ከትንባሆ ነጻ ህጻናት ድርጅት የአፍሪካ ፕሮግራም ዳይሬከተር ቢንቶው ካማራ ናቸዉ፡፡በኢትዮጵያ ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ 5 በመቶ ያህሉ ትምባሆ አጫሾች ሲሆኑ ኢትዮጵያ የአጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ እና የዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅ ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ በየጊዜው ስታዘጋጅ ቆይታለችም ብለዋል፡፡
ህጻናትን ከትንባሆ ነጻ የማደረግ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ያለባትን የትንባሆ አምራቾች እና ተጠቃሚዎች ግፊትን ተቋቁማ ለውጥ አምጪ የትንባሆ ቁጥጥር አዋጆች ማጽደቁ ተነግሯል፡፡ውጤታማው የኅብረተሰብን ጤና መሰረት ያደረገ የትንባሆ ቁጥጥር በኢትዮጵያ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ተንቀሳቃሽ ምስል እንቅስቃሴ ከትንባሆ ነጻ ህጻናት ማዘጋጀቱን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡የተደረጉ ጥረቶችን እና የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ ያጠናቀረውን ተራኪ እና ዘጋቢ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለትንባሆ ቁጥጥር አዋጅ እና እንቅስቃሴ ያደረገችውን በርካታ ውጣ ውረዶች ያካተተ ሲሆን፤ በሂደቱ ላይ የነበሩትን ባለድርሻ አካላት በተለይም ደግሞ ድጋፍ እና ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉ ተቋማት በዋናነት የዓለም የጤና ደርጅትን የትንባሆ ቁጥጥር የህግ ማዕቀፍን ተንተርሰው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን ትኩረት አድርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ ጌትፊልድ በተባለ እና ማኅበረሰባዊ ለውጥ ለማምጣት በሚል የተቋቋመ ኩባንያ ባለቤትነት የተዘጋጀ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
ለትምበሆ ቁጥጥር ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከልም ትምባሆ መግዛት የሚችሉት እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የመዝናኛ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ ትምባሆ ማጨስ እንደማይቻል፣ ሰው በተሰበሰበባቸው ቦታው ትምባሆ ማጨስ እና ማስጨስ መከልከሉ አስገዳጅ ህግ መደረጋቸው ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በትምባሆ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ግብር መጣሉ እና የትምባሆ ምርቶችን በብዙሃን መገናኛዎች ላይ ማስተዋወቅ እንዳይቻል መከልከሉም ኢትዮጵያ የትምባሆ ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከመቀነስ አንጻር ከሰራቻቸው ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸውም ተብላል፡፡
ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አንጻር ከትምባሆ ነጻ የሆኑ ህጻናትን ለመፍጠር ብርቱ ጥረት እያደረጉ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ እንድትሆን አድርጓታል ተብሏል፡፡
በትግስት ላቀዉ
Join: @felagi

👍2
በ55,000 ብር ከገዛናው በሬ በ100,000 ብር የሚገመት ወርቅ ተገኘ።
በወላይታ ዞን በዳሞት ፑላሳ ወረዳ ሻንቶ ከተማ ለትንሳኤ በዓል ለእርድ በ55,000 ብር ከተገዛው በሬ የተገኘው ወርቅ በ100,000 ብር ተሽጧል።
ከዚህ በፊት በወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ ለገና ከታረዱት በሬዎች በ235,000 ብር የሚገመት ወርቅ መገኘቱን መዘገባችን የሚታወስ ነው።
መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ።
Via:- Bonga Ethiopia
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉https://t.me/felagi

ሰበር ከስፖርቱ 🚨 ዌስትሀም ዩናይትድ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ በ 2023/24 የውድድር ዓመት ማጠናቀቂያ ቡድኑን ስለመልቀቅ በጋራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቋል ። የአሰልጣኙ ውል ማጠናቀቂያ ዓመት መሆኑም ይታወቃል ።
Join: @felagi
Join: @felagi
👍1
ይህ ወጣት ቲክቶከር በቁጥጥር ስር መዋሉን ታውቋል።
አቶ አለሙ ቢጫ ለተባሉ ግለሰብ ህክምና በቲክቶክ የተሰበሰበ 350 ሽህ ብር "ታማሚው ስለማይድን ብሩን አጥፍቼዋለሁ . . . ቲክቶክ አካውንቴን ሸጬ እከፍላለሁ"በማለት በአደባባይ የተናገረው ወጣት ዛሬ ሚያዚያ 28/2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የቅን ልቦች ከተባለ ድርጅት አቤቱታ ቀርቦለት ወጣቱን ሲፈልግ መቆየቱ ተሰምቷል።
ወጣቱ ሰሞኑን አጠፋሁት ያለውን 350 ሽህ ብር ለታካሚው አለሙ ቢጫ መመለሱ ታውቋል።ፖሊስ ጉዳዩን አጣርቶ በዋስትና እንደሚለቀ ይጠበቃል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ታላቅ የሬስቶራንት ምረቃ መርሀግብር
ጥፍጥ ያሉ በተፈጥሮ ምርት የተስሩ ለጤና የሚስማሙ ልዩ ልዩ ምግቦችን አዘጋጅቶ ፤ ልብን በሚመስጥ ውብ ዜማ በሚያሰሙ የሀገር ባህል መሳሪያዎች ፤ በልዩ የጥበብ ምሽት በአዝናኝ እና አሸላሚ መርሀ ግብር ደምቆ ሊመረቅሎት ነው።
ግንቦት 2፤3፤4 አርብ ቅዳሜ እሁድ ሁላችሁም ተጋብዛችኃል ማንም ሰው እንዳይቀር።
በአገልግል መጥተው አንድ ነገር አዘው ሲጠቀሙ 3% ለኢትዬጵያዊያን ወገኖቻችን እየረዱ እንደሆነ ይወቁ።
አገልግል ዘመናዊና እና ባህላዊ ምግብ ቤት

ቦሌ አየር መንገዱ ይቅርታ ጠየቀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ዛሬ ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ የታየ ቢሆንም አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገዶኞቻችንን ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ወርደዋል። በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ውድ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

በአሜሪካ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የ2.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
ጥበበ እሸቱ ሀይሌ ይባላል ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገ ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከእዚህ በፊት በተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ሲለግስ ቆይቷል።
በሠሜኑ ጦርነት ጊዜም የተፈናቀሉ ወገኖችን ከመደገፍም ባሻገር 140 ለሚደርሱ የጋሸና አካባቢ ነዋሪዎች ቤት ሰርቶ አስረክቧል ።
በቅርቡም በትግራይና በአማራ ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግሯል።
ይህ ቅን ሰው በዛሬው ዕለት ለመቄዶንያ የአረጋውያን ማዕከል ከ2.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ እና ለአረጋውያኖቹ የምሳ ማብላት ፕሮግራም አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊታደስ ነው
ለረዥም አመታት እድሳት ሳይደረግለት የቆየዉ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአዲስ መልክ ሊገነባ መሆኑ ተነገረ
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት እና የከተማ አስተዳደሩ በጋራ በመሆን ከ 40 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለዉን እና ብቸኛዉን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ሊጀመር እንደሚችል ተጠቁሟል።
የንግድ ምክርቤቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ለካፒታል እንደተናገሩት የሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎች የተወሰዱ መሆኑን በማንሳት የኤግዚቢሽን ማዕከሉን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የማልማት እቅድ መያዙንና በቀጣይ ዓመት ሊጀመር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል ።
ከ4 አስርት አመታት በላይ ያስቆጠረዉ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሀገር ዉስጥና ዓለምአቀፍ የንግድ ትርኢቶችን አሁን ላይ እያዘጋጀ ቢሆንም ማዕከሉ ያረጀና አገልግሎት መስጫዎቹም በሙሉ የደከሙ መሆናቸው ይነገራል ።
(ካፒታል ጋዜጣ)
ለረዥም አመታት እድሳት ሳይደረግለት የቆየዉ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአዲስ መልክ ሊገነባ መሆኑ ተነገረ
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት እና የከተማ አስተዳደሩ በጋራ በመሆን ከ 40 ዓመታት በላይ ታሪክ ያለዉን እና ብቸኛዉን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ሊጀመር እንደሚችል ተጠቁሟል።
የንግድ ምክርቤቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ ለካፒታል እንደተናገሩት የሌሎች ሀገራት ተሞክሮዎች የተወሰዱ መሆኑን በማንሳት የኤግዚቢሽን ማዕከሉን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የማልማት እቅድ መያዙንና በቀጣይ ዓመት ሊጀመር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል ።
ከ4 አስርት አመታት በላይ ያስቆጠረዉ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሀገር ዉስጥና ዓለምአቀፍ የንግድ ትርኢቶችን አሁን ላይ እያዘጋጀ ቢሆንም ማዕከሉ ያረጀና አገልግሎት መስጫዎቹም በሙሉ የደከሙ መሆናቸው ይነገራል ።
(ካፒታል ጋዜጣ)
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቦሌ አየር መንገዱ ይቅርታ ጠየቀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ዛሬ ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ የታየ ቢሆንም አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል በመቆም መንገዶኞቻችንን ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ ወርደዋል። በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ውድ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡
በውስጥ ይነበሩት ተሳፋሪዎች በሰአቱ የነበራቸው ሁኔታ በቪዲዬ !!!

ቦርሲያ ዶርቱመንድ በዌምብሌይ በሚከናወነው የ 2023/2024 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል
ፓሪሰንት ዠርመ 0-1 ቦርሲያ ዶርቱመንድ (0-2)
⚽ ሁመልስ 50'
Join: @felagi
ፓሪሰንት ዠርመ 0-1 ቦርሲያ ዶርቱመንድ (0-2)
⚽ ሁመልስ 50'
Join: @felagi
👍1
ከቤንዚን ውጪ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከቤንዚን ውጪ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
በዓለም ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መነሻ በማድረግ በቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ብቻ መጠነኛ ማሻሻያ መደረጉን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
በመሆኑም ከግንቦት 1 ቀን 2016 ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የአይሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።
በዚህም መሰረት:-
ቤንዚን ……………………………………… ብር 78.67 በሊትር
ነጭ ናፍጣ………………………………… ብር 79.75 በሊትር
ኬሮሲን …………………………………... ብር 79.75 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ………………... ብር 70.83 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ…………………… ብር 62.36 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ…………………. ብር 61.16 በሊትር ሆኗል።

ሪያል ማድሪድ ባየርን ሙኒክን 2-1 በማሸነፍ ለቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አልፈዋል። በፍፃሜው ቦሩሲያ ዶርትሙንድን የሚገጥሙ ይሆናል።