Addis info
1.41K subscribers
454 photos
7 videos
181 links
Download Telegram
በመጀመሪያው ዙር የቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ባየርን ሚዩኒክ በሜዳው ከሪያል ማድሪድ ጋር አቻ ተለያይቷል። ከሁለቱ ቡድኖች ለፍፃሜ ማን ያልፋል?
Join: @felagi
በኢትዮጵያ ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ 5 በመቶ ያህሉ ሲጋራ አጫሽ ናቸው ተባለ 
 
ኢትዮጵያ የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር በመቀነስ ስኬታማ ሀገራት ከሆኑ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን ከትንባሆ ነጻ ህጻናት የተባለ ድርጅት አታውቋል፡፡ 
 
በኢትዮጵያ ከ6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከአጫሾች በሚወጣ የትምባሆ ጭስ እንደሚቸገሩ ከዚህ በፊት የተደረገ ጥናት ያሳያል ሲሉ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የተናሩት ከትንባሆ ነጻ ህጻናት ድርጅት  የአፍሪካ ፕሮግራም ዳይሬከተር ቢንቶው ካማራ ናቸዉ፡፡በኢትዮጵያ ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ 5 በመቶ ያህሉ ትምባሆ አጫሾች ሲሆኑ ኢትዮጵያ የአጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ እና የዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅ ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ በየጊዜው ስታዘጋጅ ቆይታለችም ብለዋል፡፡  
 
ህጻናትን ከትንባሆ ነጻ የማደረግ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ያለባትን የትንባሆ አምራቾች እና ተጠቃሚዎች ግፊትን ተቋቁማ ለውጥ አምጪ የትንባሆ ቁጥጥር አዋጆች ማጽደቁ ተነግሯል፡፡ውጤታማው የኅብረተሰብን ጤና መሰረት ያደረገ የትንባሆ ቁጥጥር በኢትዮጵያ ዙሪያ የሚያጠነጥን ዘጋቢ ተንቀሳቃሽ ምስል እንቅስቃሴ ከትንባሆ ነጻ ህጻናት ማዘጋጀቱን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡የተደረጉ ጥረቶችን እና የተገኙ ውጤቶችን አስመልክቶ  ያጠናቀረውን ተራኪ እና ዘጋቢ ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጓል፡፡  
 
ይህ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለትንባሆ ቁጥጥር አዋጅ እና እንቅስቃሴ ያደረገችውን በርካታ ውጣ ውረዶች ያካተተ ሲሆን፤  በሂደቱ ላይ የነበሩትን ባለድርሻ አካላት በተለይም ደግሞ ድጋፍ እና ያላሰለሰ ጥረት ያደረጉ ተቋማት በዋናነት የዓለም የጤና ደርጅትን የትንባሆ ቁጥጥር የህግ ማዕቀፍን ተንተርሰው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን ትኩረት አድርጓል።  ዘጋቢ ፊልሙ ጌትፊልድ በተባለ  እና ማኅበረሰባዊ ለውጥ ለማምጣት በሚል የተቋቋመ ኩባንያ ባለቤትነት የተዘጋጀ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ 
 
ለትምበሆ ቁጥጥር ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከልም ትምባሆ መግዛት የሚችሉት እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የመዝናኛ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ ትምባሆ ማጨስ እንደማይቻል፣ ሰው በተሰበሰበባቸው ቦታው ትምባሆ ማጨስ እና ማስጨስ መከልከሉ አስገዳጅ ህግ መደረጋቸው ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በትምባሆ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ግብር መጣሉ እና የትምባሆ ምርቶችን በብዙሃን መገናኛዎች ላይ ማስተዋወቅ እንዳይቻል መከልከሉም ኢትዮጵያ  የትምባሆ ተጠቃሚዎችን ቁጥር ከመቀነስ አንጻር ከሰራቻቸው ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸውም ተብላል፡፡  
 
ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አንጻር ከትምባሆ ነጻ የሆኑ ህጻናትን ለመፍጠር ብርቱ ጥረት እያደረጉ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ እንድትሆን አድርጓታል ተብሏል፡፡ 
 
በትግስት ላቀዉ

Join: @felagi
👍2
አርቲስት አዲስአለም ጌታነህ ከ21 ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ተፈታለች።
👍1