Addis info
1.41K subscribers
454 photos
7 videos
181 links
Download Telegram
ለካ እንደዚም አለ ወገን ትላንትና ማታ ነው Apr 28 2024 በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 2:20 ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የደረስኩት business class  ካውንተር ላይ አንድ ሴት ቀጭን  የቀይ ዳማ ወጣት የኢትዮጵያ ፓስፖርቴን ሰጠሁት።

የት ነው የምትሄጂው አለኝ ? ደብሊን አልኩት በየት በኩል አለኝ በአርላንዳ ኤርፖርት በስቶኮም በኩል አልኩት።

ሲስተም ቼክ አላረገ ፓስፖርቴን አላየ መሄድ አትችይም ትራንዚት አይፈቀድም አለኝ ሁሌ የምመላለስበት መንገድ ነው እኮ ወንድሜ አውሮፖ ውስጥ እስፔሻል ቪዛ የሚያስፈልገው ለለንደን ብቻ ነው አልኩት።

በቃ ዞር በይ ሌላ ከስተመር ላስተናግድበት አለኝ እኔስ አልኩት የማውቀው ነገር የለም ሴኩሪቲ ከመጥራቴ በፊት አትረብሺኝ ዞር በይልኝ አለኝ።

እሺ ጥራ በቃ  ዞር አልልም አልኩት አንድ ኢሚግሬሽን የሚሰራ ወጣት በአጋጣሚ እያለፈ አይቶ እባክህን እየረበሸችኝ ነው ዞር አድርግልኝ አለው ወጣቱም ምንም ሳይናገር ጥሎ ሄደ እኔም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ ሄጄ ሱፐርቫይዘር ካለ አናግሩኝ ተቸግሬአለው አልኳቸው።

አንድ የአየር መንገዱ ሰራተኛም ምን ልርዳዎት አረፍ ይበሉ አለኝ የሆነውን ነገርኩት ነይ እንሂድ ብሎ ወደ ካውንተሩ ሄድን።

ምንድ ነው ይችላሉ እኮ መብረር ለምን አስቆምካቸው ብሎ ጠየቀው  እራሱ ሲስተሙ ውስጥ ገብቶ ካየ በኃላ እንቢ ያለው ወጣት እንዲሰራ አዘዘው ወጣቱም ቼክኢን አደረገኝ ቆም ብዬ ብዙ አሰብኩ።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት በመያዜ ብቻ ሲስተም ቼክ ሳያደርግ  አትበሪም በማለቱ መርህ አልባ  ድርጊት በመፈፀሙ በጣም አዝኛለው አፍሬአለዉም።

እኔ አንድ ቀንም ዜግነት ባለመለወጤ ፀፅቶኝ አያውቅም ሀገሬን ወዳታለው እንደዚ ያሉ ብራንዳችንን ክብራችንን መጠሪያችን የሆነውን ብቸኛው አየር መንገዳችን  ስሙ እንዲጎድፍ ሰዎች እንዲማረሩበት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚሰሩ ግለሰቦች መኖራቸውን አውቄአለው።

እኔ በሌላ አየር መንገድ business class ከምጏዝ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ  ቢሆን ብጏዝ እመርጣለው  ብዙ ጥሩ ሰዎች ያሉበት ቤት ነው ግን ጥቂቶቹ ስርአት አልበኞች የአየር መንገዱን መልካም ስም እያስጎደፉ ስለሆነ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል እላለው።

ሼር አድርጉ ለሚመለከተው አካል ይድረስ ውድ ኢትዮጵያን ተስፋ አትቁረጡ እስከ ጥግ ሂዱ መፍትሄ እስክታገኙ ሁላችንም የሀገራችን አንባሳደሮች ነን።🇪🇹

Via:- በረከት ገበሬዋ
👍2
በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳኤ በዓልም ምክንያት በማድረግ 188 የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ ክፍት እንደሚሆኑ ተነገረ 
 
ከትንሳኤ በዓል ጋር በተያያዘ በምርት አቅርቦት፣ህገወጥየንግድ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጣር ረገድ ለበዓሉ የተለየ እቅድ በማቀድ ፣በቢሮው ኃላፊ የሚመራ ግብረ ኃይል በማቋቋም ወደ ተግባር መግባቱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድና ግብይት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍስሀ ጥበቡ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩ ለትንሳኤ በዓል በ188 የእሁድ ገበያዎች ሰፊ የምርት አቅርቦት እንዲፈጠር በዓሉን ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደው ገበያ ሳምንቱን ሙሉ ይካሄዳል ሲሉ ተናግረዋል። 
 
እንዲሁም  በለሚ ኩራ፣ በኮልፌ እና በአቃቂ ቃሊቲ የግብርና ምርቶች የገበጻ ማዕከላት በመደበኛነት የተለያዩ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡበት አሰራር መኖሩን ገልፀዋል።በተጨማሪም በማዕከላቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ትላልቅ ባዛሮችን በማዘጋጀትና ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉበት በማስቻል የገበያ ማረጋጋት ሚናውን ለመወጣት የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እያከናወነ ይገኛል። 
 
በገበያ ማዕከላቱና ባዛሮች በተመጣጣኝ ዋጋ ከሚቀርቡ የአትክልትናፍራፍሬ ፣የሰብል፣የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች በተጨማሪ በቁም እንስሳት የገበያ ማዕከላት በቂ የፍየልና የበግ እንዲሁም የዳልጋ ከብት እንዲቀርብ የሚያችሉ ትስስሮችን ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝም ገልፀዋል። 
 
በሌላ በኩል በንግድ ዘርፍ ህግና ስርዓት እንዲከበር ፣ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ሊስተዋሉ የሚችሉ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ለመቆጣጠር የሚያስችል ግብረ ሀይል ማቋቋሙን እና ጠንካራ የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎችን ለማከናወን መታቀዱን አቶ ፍስሀ ጥበቡ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ። 
 
በምህረት ታደሰ

Join: @felagi
👍1
Join: @felagi
የአዉሮፓ ህብረት ፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር" ሲል ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ አጠበቀ 
 
👉🏼 የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ መክፈል አለባቸውም ተብሏል 
 
የአዉሮፓ ህብረት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር ሲል ወቅሷል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ ማጥበቁን አስታዉቋል። 
 
ዳጉ ጆርናል ከአሶሴትድ ፕረስ ዘገባ እንደተመለከተው ፤ የአውሮፓ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ ለመስራት የሚፈጅባቸዉን ጊዜ በሶስት እጥፍ መጨመሩን ነዉ። 
 
ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊያን በ15 ቀናት ዉስጥ ቪዛ ያገኙ ነበር የተባለ ሲሆን በዚሁ ዉሳኔ መሰረት ወደ 45 ቀናት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ይህም የኢትዮጵያ መንግስትን በህገወጥ መንገድ በአዉሮፓ ይኖራሉ የተባሉ ዜጎችን እንዲመልስ ጫና ለመፍጠር ነዉ ብሏል ዘገባው። 
 
ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከታዘዙ ሶስት ሰዎች መካከልም አንዱ ብቻ መመለሱ በህብረቱ የመንግስትን ተባባሪነት ጎድሎታል የሚለዉን ክስ ለማሳያነት ቀርቧል። ይህም በፈቃዳቸዉም ይሆን ካለፍላጎታቸዉ ህገወጦችን ለመመለስ የሚደረገዉን ሂደት አጓቶታል ብሏል። 
 
በዚህ ዉሳኔ መሰረትም የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን የቪዛ ቀናቸዉም ቢያልፍ የአዉሮፓ ምድርን ለቅቀዉ እንደማይወጡ ህብረቱ ገልጿል።

Join: @felagi
የሀይማኖት አባት የማይከበርበት ሀገር ቢያንስ አያስቀድሙትም😂
👍1
ልዩ የበዓል ቅናሽ ከMiki Brand

ከታች ባለው አድራሻ
Miki brand official
call📶0966132481
🏢አድራሻ - አዲስ አበባ, ሃያሁለት(22)፡ ጎላጎል 1ኛ ፍሎር ላይ፡ የሱቅ ቁ.112
✂️ ለሱቅና ብዛት ተረካቢዎች ባስተያየት እናስረክባ
https://www.tiktok.com/@micky.brand4?_t=8kgtFvQW7D3&_r=1
ያሉበት ቦታ ያለተጨማሪ ክፍያ እናደርሳለን
https://t.me/+UqpqFfCWq2Yu_Igj