የሜክሲኮ የምግብ አቅራቢ የአይጥ መረቅን ከ50 ዓመታት በላይ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታወቀ
በሜክሲኮ ሜርካዶ ሪፐብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ በሚሰኘው ገበያ ውስጥ በርካታ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘት ይቻላል፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ልዩ የሆነው የአይጥ ስጋን በመሸጥ የሚታወቅ የቆየ የምግብ አቅራቢ ድርጅት ታዋቂ ነው።
ለበርካታ የዓለም ህዝብ የአይጥ ስጋ በፍፁም የማይለመድ እና ነውር ቢሆንም በሜክሲኮ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ክልል ውስጥ ግን ለየት ያለ ጣዕሙ እና ለመድኃኒትነት ይውላል በሚል ለረጅም ዓመታት ጥቅም ላይ ውሏል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአይጥ ሥጋ የሚሸጡባቸው ሱቆች እና አከፋፋዮች ከአካባቢው ገበያ እየጠፉ ይገኛል።
በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ ግን አንዱ አከፋፋይ አሁንም ሁለቱንም ማለትን ጥሬ የአይጦች ስጋ እና የአይጥ መረቅ ከተለያዩ አትክልቶች እና ቅመማ ቅመም ጋር አዋህዶ መሸጡን ቀጥሏል። እያንዳንዱ የአይጥ መረቅ አንድ ሙሉ ሳህን የሚይዘው በ100 የሜክሲከ ፔሶ ወይም በ5.80 የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል።በሜርካዶ ሪፑብሊካ የመጨረሻው የአይጥ ስጋ ሻጭ ሆሴ ሬሜዲዮስ ሄርናንዴዝ "ካሚሎ" በመባልም የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየችው ወላጅ እናቱ ይህንኑ ንግድ ወርሷል።
በአንድ ወቅት በገበያው ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የአይጥ ስጋ ሻጮች እንደነበሩ ያስታውሳል፣ ነገር ግን ሁሉም ጡረታ ወጥተዋል አልያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሁን ላይ በገበያው ውስጥ ብቸማ አቅራቢ ሆኖ ቀጥሏል። ስራው እየተቀዛቀዘ በርካቶች ከዘርፉ ቢወጡን በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቤተሰብን ንግድ ለመተው እቅድ የለኝም ሲል ይናገራል። ይህው የቤተሰቡ ንግድ ለ52 ዓመታት ዘልቋል።
በስምኦን ደረጄ

🍃 መልካም ሰንበት 🍃ሆሳዕና በዓርያም
" በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ መዝሙረ ዳዊት 118:26
✟✟✟ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ✟✟
" የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።"ማቴዎስ ወንጌል 21:9

ተወዳጇ አርቲስት ሳያት ደምሴ ከለዛ ሽልማት ራሷን ማግለሏን አዘጋጁ ገለፀ
ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የሀገር ውስጥ ውድድር ራሷን ማግለሏ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ማሳወቋን ይታወቃል::
ይህንን ተከትሎ የለዛ ሽልማት እስከ አሁን ድረስ እያወዳደራት የነበረ ቢሆንም የእሷን ሀሳብ በማክበር አዘጋጁ ብርሀኑ ድጋፌ በማህበራዊ ገፁ ላይ ይህንን አስፍሯል::
ምርጥ ተዋናይት ምድብ ዕጩዎች 4 ቀርተዋል:: ይህም የሆነው ከአክብሮት ጋር በሚል ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የአገር ውስጥ ውድድር ራሴን ማግለሌ ይታወቅልኝ ባለችው መሠረት ነው ይህ የሆነው :: ሃሣቧን እናከብራለን ::
13ኛው የለዛ ሽልማት የመጨረሻ ዙር እጩዎች ድምፅ መስጠት ሚያዚያ 23 ያበቃል!
ብርሀኑ ድጋፌ
የለዛ ሽልማት

ክለቤን በገንዘብ አለውጥም ያለው ተጨዋች👏
በትናትናው ዕለት ጅማ አባ ጅፋር እና ስልጤ ወራቤ ሊያደርጉት በነበረው ጨዋታ ላይ አንድ የጅማ ተወላጅ የሆነ አሰልጣኝ ለጅማ አባ ጅፋር ተጨዋች ለሆነው ማንያዘዋል (ቻፒ) ለሚባል ተጨዋች በመደወል "ገንዘብ ታገኛላቹ ተጎድተናል በሉ..እኔ ከስልጤ ወራቤ አመራሮች ጋር አውርቻለው እንደምለው ካደረጋቹ ጥሩ ገንዘብ ታገኛላቹ" ብሎ ለተጨዋቹ ይነግረዋል ተጨዋቹ ግን ከተነገረው በተቃራኒ ድምፆቹን በመቅዳት ለአመራሮች ቅጂውን በመስጠት ሁሉን ነገር ገሀድ አውጥቶታል::

እግር ኳስ በኢትዮጵያ ተዓምራቱ እንደቀጠለ ነው።
ይህ ክስተት ጎል አግብተው ደስታቸውን እየገለፁ ይመስላል ግን አይደለም ዳኛውን ከበው እያናገሩት ነው። አንዱ ተጨዋች ለማናገር ሜዳው ሁላ አልበቃውም ተጨዋች ላይ ወጥቶ ነው የሚያናግረው።
ተጨማሪ መረጃ :-
ቴሌግራም - @felagi

በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል
#NEWS | በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል።
የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል::
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡
Via: ዳጉ ጆርናል