Addis info
1.4K subscribers
454 photos
7 videos
181 links
Download Telegram
አርቲስት አማኑኤል ሐብታሙ ለምን ታሰረ?

"... አስቸኳይ ነው። ለምን እንደሆነ እንጃ እቃዎቼን መልሰዋቸዋል። እኔንም እንፈልግሀለን ብለው እስከ አሁን ይዘውኛል። የአውሮፕላን መነሻ ሰዓቱም ሊያልፍብኝ ነው"

- እንዴ!.. ለምን?

"እኔ እንጃ ኤርፖርት ውስጥ ነው እስከ አሁን ያለሁት። ጉዞዬ ከደቂቃዎች በኋላ ነው። ግን እስከ አሁን ጠብቅ! ብለው ይዘው እንዳቆዩኝ ነው"

ከአማኑኤል ሐብታሙ ጋር መጠነኛ መረጃዎች ከተቀያየርን በኋላ አንድ አንድ ነገሮችን አጣርቼ በቶሎ መልሼ እንደምደውልለት ከነገርኩት በኋላ ስልኩ ተቋረጠ።

ከደቂቃዎች በኋላ መልሼ ስደውል ስልኩ ተዘግቷል። በተደጋጋሚ ብሞክርም ያው ነው።

ከቤተሰቦቹ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ይህንን ማስታወሻ እስካሰፈርኩበት ሰዓት ድረስ አማኑኤል ፖሊሶች ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ወስደውት በእስር ላይ ይገኛል።

ቤተሰቦቹ ራት እንዳደረሱለት እና በፖሊስ ስለተያዘበት ጉዳይ እርሱም ይሁን በሕግ ስር የዋሉት ፖሊሶች ምንም አይነት መረጃ እንዳልሰጧቸው አረጋግጫለሁ።

አማኑኤል ሐብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘውን ተወዳጅ አዲስ ባለ አንድ ሰው የሙሉ ሰዓት ቴአትሩን እስራኤል አገር ለሚገኙ ተመልካቾች ለማሳየት በጉዞ ላይ ሳለ ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ/ም አመሻሽ ላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በፖሊስ ተይዞ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

ለእስር ያበቃው ጉዳይ ምን እንደሆነ የተገለጸ ነገር ባይኖርም፤ እስራኤል ውስጥ ነስ ጽዮና በተባለ ከተማ ትልቅ ቴአትር ቤት የፊታችን ሐሙስ ትርዒቱን ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቆ አውሮፕላን ለመሳፈር አየር ማረፊያ ደርሶ ነበር።

ከ400 በላይ ተመልካቾች ትኬቱን በቅድሚያ ቆርጠው፣ በጠቅላላው ከ750 በላይ ተመልካቾች የሚታደሙበትን ዝግጅት ለማቅረብ በጉጉት እየተጠበቀ በድንገት ምክንያቱ ባልታወቀ ሰበብ ታስረ
👍2
ይቅርታ‼️

#UPDATE  | ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ "ያደኩበት ቤተክርስትያን ተገንብቶ በማለቁ የተሰማኝ ደስታን ለመግለፅ ሀላፊዎችን አስፈቅጄ ነው ጥይት የተኮስኩት በዚህም ያስከፋዋችሁ  ይቅርታ አድርጉልኝ" ብሏል።
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተዘገበ 
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል።  
 
ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል።  
 
በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።  እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም። 
 
Via Addis Maleda
👍1
የሜክሲኮ የምግብ አቅራቢ የአይጥ መረቅን ከ50 ዓመታት በላይ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታወቀ  
 
በሜክሲኮ ሜርካዶ ሪፐብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ በሚሰኘው ገበያ ውስጥ በርካታ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘት ይቻላል፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ልዩ የሆነው የአይጥ ስጋን በመሸጥ የሚታወቅ የቆየ የምግብ አቅራቢ ድርጅት ታዋቂ ነው።  
 
ለበርካታ የዓለም ህዝብ የአይጥ ስጋ በፍፁም የማይለመድ እና ነውር ቢሆንም በሜክሲኮ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ክልል ውስጥ ግን ለየት ያለ ጣዕሙ እና ለመድኃኒትነት ይውላል በሚል ለረጅም ዓመታት ጥቅም ላይ ውሏል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአይጥ ሥጋ የሚሸጡባቸው ሱቆች እና አከፋፋዮች ከአካባቢው ገበያ እየጠፉ ይገኛል።  
 
በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ ግን አንዱ አከፋፋይ አሁንም ሁለቱንም ማለትን ጥሬ የአይጦች ስጋ እና የአይጥ መረቅ ከተለያዩ አትክልቶች እና ቅመማ ቅመም ጋር አዋህዶ መሸጡን ቀጥሏል። እያንዳንዱ የአይጥ መረቅ አንድ ሙሉ ሳህን የሚይዘው  በ100 የሜክሲከ ፔሶ ወይም በ5.80 የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል።በሜርካዶ ሪፑብሊካ የመጨረሻው የአይጥ ስጋ ሻጭ ሆሴ ሬሜዲዮስ ሄርናንዴዝ "ካሚሎ" በመባልም የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየችው ወላጅ እናቱ ይህንኑ ንግድ ወርሷል።  
 
በአንድ ወቅት በገበያው ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የአይጥ ስጋ ሻጮች እንደነበሩ ያስታውሳል፣ ነገር ግን ሁሉም ጡረታ ወጥተዋል አልያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሁን ላይ በገበያው ውስጥ ብቸማ አቅራቢ ሆኖ ቀጥሏል። ስራው እየተቀዛቀዘ በርካቶች ከዘርፉ ቢወጡን በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቤተሰብን ንግድ ለመተው እቅድ የለኝም ሲል ይናገራል። ይህው የቤተሰቡ ንግድ ለ52 ዓመታት ዘልቋል።
 
በስምኦን ደረጄ
🍃 መልካም ሰንበት 🍃ሆሳዕና በዓርያም

" በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ መዝሙረ ዳዊት 118:26

✟✟✟ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ✟✟
" የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።"ማቴዎስ ወንጌል 21:9
ቶተንሃም ሁለቱንም አርሰናልን እና ማን ሲቲን ያስተናግዳል ሲዝኑ ከመጠናቀቁ በፊት 🏟️👀

ርዕሱ እጣ ፈንታ በእጃቸው ነው 🏆 🫳🧵
ተወዳጇ አርቲስት ሳያት ደምሴ ከለዛ ሽልማት ራሷን ማግለሏን አዘጋጁ ገለፀ

ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የሀገር ውስጥ ውድድር ራሷን ማግለሏ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ማሳወቋን ይታወቃል::

ይህንን ተከትሎ የለዛ ሽልማት እስከ አሁን ድረስ እያወዳደራት የነበረ ቢሆንም የእሷን ሀሳብ በማክበር አዘጋጁ ብርሀኑ ድጋፌ በማህበራዊ ገፁ ላይ ይህንን አስፍሯል::

ምርጥ ተዋናይት ምድብ ዕጩዎች 4 ቀርተዋል:: ይህም የሆነው ከአክብሮት ጋር በሚል ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የአገር ውስጥ ውድድር ራሴን ማግለሌ ይታወቅልኝ ባለችው መሠረት ነው ይህ የሆነው :: ሃሣቧን እናከብራለን ::

13ኛው የለዛ ሽልማት የመጨረሻ ዙር እጩዎች ድምፅ መስጠት ሚያዚያ 23 ያበቃል!

ብርሀኑ ድጋፌ
የለዛ ሽልማት
መድፈኞቹ በሰሜን ለንደን ደርቢው 🔥 
 
                     
         ቶትንሃም 1-3 አርሰናል  
 
        ሮሜሮ ⚽️     ሆይበርግ ⚽️ (በራሱ) 
                         ሳካ ⚽️ 
                       ሀቨርትስ ⚽️ 
 
ጎሎቸን 👉

Join: @felagi
ክለቤን በገንዘብ አለውጥም ያለው ተጨዋች👏 
 
በትናትናው ዕለት ጅማ አባ ጅፋር እና ስልጤ ወራቤ ሊያደርጉት በነበረው ጨዋታ ላይ አንድ የጅማ ተወላጅ የሆነ አሰልጣኝ ለጅማ አባ ጅፋር ተጨዋች ለሆነው ማንያዘዋል (ቻፒ) ለሚባል ተጨዋች በመደወል "ገንዘብ ታገኛላቹ ተጎድተናል በሉ..እኔ ከስልጤ ወራቤ አመራሮች ጋር አውርቻለው እንደምለው ካደረጋቹ ጥሩ ገንዘብ ታገኛላቹ" ብሎ ለተጨዋቹ ይነግረዋል ተጨዋቹ ግን ከተነገረው በተቃራኒ ድምፆቹን በመቅዳት ለአመራሮች ቅጂውን በመስጠት ሁሉን ነገር ገሀድ አውጥቶታል::
እግር ኳስ በኢትዮጵያ ተዓምራቱ እንደቀጠለ ነው። 
 
ይህ ክስተት ጎል አግብተው ደስታቸውን እየገለፁ ይመስላል ግን አይደለም ዳኛውን ከበው እያናገሩት ነው። አንዱ ተጨዋች ለማናገር ሜዳው ሁላ አልበቃውም ተጨዋች ላይ ወጥቶ ነው የሚያናግረው።

ተጨማሪ መረጃ :-
ቴሌግራም -  @felagi
በአዲስ አበባ በዛሬዉ እለት ባጋጠመ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል

#NEWS  | በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታዉቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል::በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል::

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ህብረተሰቡ ፈጥኖ እንዲያሳዉቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Via: ዳጉ ጆርናል