FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.5K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

"የጀግኖች መፍለቂያ ፤ የድል ምልክት " በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 4ኛ ዓመት የኮሩ ምስረታ በዓልን ይፋዊ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓትን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያስጀመሩት የቴዎድሮስ ኮር አዛዥ ኮሎኔል ረሺድ ኢብራሂም እንዳሉት ቴዎድሮስ ኮር የተመሠረተበትን 4ኛ ዓመት ሲያከብር ተቋሙ የጣለበትን ሃላፊነት በጀግኖች አባላቱ ክቡር መስዋዕትነት በድል እየፈፀመ ነው።

የኮሩ አዛዥ በንግግራቸው እንደገለፁት ቴዎድሮስ ኮር በጦርነት ውስጥ ተወልዶ ያደገና በእሳት ተፈትኖ እንደ ወርቅ ነጥሮ የወጣ ፈተናን የሚፈትን እንጅ በፈተናዎች የማይዝል ፤ የጀግኖች መፍለቂያ እና የምዕራብ ዕዝ መተማመኛ ክንድ ነው።

እኛ የቴዎድሮስ ኮር አባላት በፈፀምናቸው ስኬታማ ተልዕኮዎችና ባስመዘገብናቸው አንፀባራቂ ድሎች የምንረካ አሊያም የምንዘናጋ አይደለንም ያሉት አዛዡ ኮሎኔል ረሺድ ኢብራሂም በተለዋዋጭና ተቀያያሪ የተልዕኳችን ባህሪ ውስጥ ከዕለት ወደ ዕለት የሚጎመራና የሚያብብ የድል ፍሬን ለሀገር እና ለህዝባችን ማበርከታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
  
የምስረታ በዓሉ በተለያዩ ኩነቶች ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት እንደሚከበር መሆኑን የገለፁት ኮሎኔል ረሺድ ኢብራሂም ፓናል ውይይት ፤ የፎቶ አውደ ርዕይ ፤ የእውቅና አሠጣጥ ስነ- ስርዓትን ጨምሮ የተለያዩ መርሃ- ግብሮች እንደሚከናወኑ ገልፀዋል። የሆሮ ጉድሩ ዞን አባገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች መድረኩን  በባህላዊ ምርቃትና ምስጋና አስጀምረዋል።

"የጀግኖች መፍለቂያ ፤ የድል ምልክት " በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው የቴዎድሮስ ኮር 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ  የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሜጄር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ ፤ የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ፤ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምሬሳ ፍጤ ፤ የሻምቡ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባን ጨምሮ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና እና የሃገር ሽማግሌዎች፤ አባገዳዎችና ሃደ ስንቄዎች ፤ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሻምቡ ከተማ ነዋሪዎችና በየደረጃው የሚገኙ የኮሩ አመራሮችና አባላት ታድመዋል።

ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3313👎7🥰6🔥1👏1
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ሪምአውክስ ክላውድ የአየር ወለድ ማሰልጠኛን ጎበኙ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሪምአውክስ ክላውድ የተመራው ልዑክ ከልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ እና ከክፍሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በቢሾፍቱ የሚገኘውን የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም አጠቃላይ የልዩ ዘመቻዎች ማሰልጠኛ ማዕከልን እና በስሩ የሚገኙትን አራት ትምህርት ቤቶች በተመለከተ የዕዙ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ለቡድኑ ማብራሪያና ገለፃ የሰጡ ሲሆን የልዩ ሀይሎች ስልጠናን የሚያሳይ አጠር ያለ ዶክመንተሪ ፊልምም ቀርቧል፡፡

በሀገራዊ ለውጡ ተቋሙ ባደረገው ሪፎርም የልዩ ሀይሎች ማሰልጠኛ ማዕከል የማሰልጠን አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ በሀገር ደረጃ የውጊያ ማሪሽ ቀያሪ የምድር ድሮን የሚል ስያሜ የተሰጣቸውን የኮማንዶ፣ አየር ወለድና ልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር ሀይል መፍጠር መቻሉን አብራርተዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ተልዕኮ እና አሁናዊ ብቃቱን ለልዑካን ቡድኑ የገለፁ ከመሆኑም በላይ ማሰልጠኛ ማዕከሉ የራሱን ብቁ አሰልጣኞች በማፍራት ለኢትዮጵያ የሚመጥናትን ሀይል እያሰለጠነ ከመሆኑም በላይ ለአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮችም በስልጠና መስክ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አውስተዋል፡፡

የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ሪምአውክስ ክላውድ በበኩላቸው ዕዙ ባደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀው የኢትዮጵያ የኮማንዶ፣ አየር ወለድና ልዩ ሀይል ፀረ-ሽብር የስልጠና ሂደት መደነቃቸውን በመግለፅ ስልጠናው የኢትዮጵያ ሠራዊት ጥንካሬ ያሳዬ ነው ብለዋል፡፡

የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወጣቶች በዚህ ደረጃ እዚህ ሰልጥነው ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውና ይህም በሁለቱ ሀገሮች ወታደራዊ ትብብር ስምምነት መሰረት እንደሚፈፀም ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል። ዘጋቢ አብዱራህማን ሀሰን ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
18👍7🔥2🏆1
የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት አካሄደ ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

በዚሁ የፓናል ውይይት ላይ የጀግናው ሠራዊታችን ዘመን ተሻጋሪ ገድሎች ተዘክረዋል። በተለይም የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር ፅናት ፤ ቁርጠኝነት እና ህዝባዊነት መሠረቶች በፅሁፍ ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
  
የፓናል ውይይቱን የመሩት የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ  የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር ስያሜውን ከጀግናው አፄ ቴዎድሮስ መውረሡ ለጠላቶቻችን እጅ የማንሠጥ ፤ የማንጨበጥ የእሳት ነበልባል ትውልድ ዛሬም ኢትዮጵያ እንዳላት የሚጠቁም መሆኑን ታሪክን አጣቅሠው አስገንዝበዋል። 

ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ቴዎድሮስ ኮር "የጀግኖች መፍለቂያ ፤ የድል ምልክት "የሚል መሪ ቃል ያነገበ ሲሆን በእርግጥም ኮሩና የኮሩ መስራች ክፍለጦሮች በሠሜኑ የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ በሠሩት ድንቅ ጀብዱ በሃገር ደረጃ የአውደ ውጊያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ እንደነበሩ አስታውሰው ቴዎድሮስ ኮርም ጀግኖች የሚፈልቁበት አሃድ ነው ብለዋል።

የፓናል ውይይቱ ተጋባዥ እንግዳ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምሬሳ ፊጤ በበኩላቸው ካለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት በፊት ምዕራብ እና ቄለም ወለጋን ጨምሮ በአራቱም የወለጋ ዞኖች ፅንፈኛ እና አሸባሪ ቡድኖች በንፁሃን ላይ ሲያደርሡት የነበረው ሁለንተናዊ ሠቆቃ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ክፉኛ ያሳዘነ እንደነበር አውስተዋል። ከማንም በላይ የወለጋ ህዝብ ደግሞ የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ያንን ወቅት ዛሬም ድረስ የጨለማ ዘመን እያለ እንደሚጠራው ተናግረዋል።

የምዕራብ ዕዝ በቀጠናው በተሠማራ አጭር ግዜ ውስጥ ታሪክ ሲዘክረው በሚኖር ጀግንነትና ወታደራዊ ብቃት የወለጋ አካባቢን ከጨለማ ወደ ብርሃን አሸጋግሯል ያሉት አቶ ምሬሳ ፊጤ የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞንም እንደ ሌሎቹ የወለጋ ዞኖች ለዓመታት የራቀውን ሠላም መልሶ እንዲጎናፀፍ አስችሏል ብለዋል።

ለዚህ ስኬት ደግሞ በተለይ የዕዙ ቴዎድሮስ ኮር ያደረገው ተጋድሎ በወለጋ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለዘለዓለም ታትሞ ሲዘከር ይኖራል ብለዋል።

የፓናል መወያያ ፅሁፉን ያቀረቡት ዕጩ ዶክተር ደረጄ ገቢሳ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለአንድ ሀገር የጀርባ አጥንት ፤ የሉዓላዊነት፤ የብሔራዊ ክብርና ጥቅም ዋልታ ምሰሶ መሆኑን ገልፀው የጀግናው ሠራዊታችን ተልዕኮዎች ሁሉ ከዚሁ መርህ የመነጩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
 
ዕጩ ዶክተር ደረጄ ገቢሳ የምዕራብ ዕዝ በወለጋ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በአጭር ግዜ ውስጥ ያስመዘገበው ድል ሠራዊቱ የተገነባበትን ህዝባዊነት እና አይበገሬነት ፍንትው አድርገው ያሳዩ ስለ መሆናቸው አብራርተዋል። የቴዎድሮስ ኮርም ለዚህ አባባል ሁነኛ ማረጋገጫ  የሆኑ ተጨባጭ ድሎችን ማስመዝገቡንም ጠቅሠዋል።

የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች በሠጡት አስተያየትም። ዛሬ እንዲህ የሠላም አየር መተንፈስ የቻልነው በእናንተ በውድ ልጆቻችን ደምና መስዋዕትነት በመሆኑ እናከብራችኋለን፤ እንወዳችኋለን የተገኘው አንፃራዊ ሠላም ተጠናክሮ ቀጥሎ አካባቢያችን የተቸረውን የተፈጥሮ ፀጋ በማልማት ለራሳችንም ለሃገራችንም የሚተርፍ እድገትና ብልፅግና እንዲመጣ በማናቸውም ሁኔታ ከጎናችሁ አንለይም ሲሉ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ  ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍7🔥2🥰1