በጎጃም እና በደቡብ ጎንደር የተሰማራው ሠራዊት 81 የጽንፈኛውን ቡድን አባላት ደመሰሰ፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ምስራቅ ዕዝ እና በስሩ ያሉት ኮሮች ባደረጉት ልዩ ስምሪት የጽንፈኛው ቡድንን አከርካሪ የሰበሩ ውጤቶች አስመዝግበዋል፡፡ ጽንፈኛው የሚዲያ ግርግር ለመፍጠር በሁሉም የጎጃም እና የደቡብ ጎንደር ዞኖች ሽብር ለመፍጠር ቢያስብም ሀሳቡ መና ቀርቶ 81 አመራሩን እና ተዋጊዎቹን አጥቷል፡፡
ምስራቅ ዕዝ በደቡብ ጎንደር በእብናት ፣ በሊቦ ከምከም ፣ በፋርጣ፣ በእስቴ፣ በደራ ወረዳዎች ቀበሌዎች ባደረገው ስምሪት ጽንፈኛውን የገባበት ገብቶ ደምስሶታል፡፡ በሰሜን ጎጃም ባሉ ደቡብ ሜጫ፣ደቡብ አቸፈር፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳዎች ቀበሌዎች ውስጥ ተሰግስጎ የነበረውን ዘራፊ ቡድን የማጽዳት ግዳጅ ተወጥቷል፡፡
በአዊ ብሑረሰብ ዞን በዳንግላ፣ በፋግታ ለኮማ ፣ ድማማ አንገረብ እና በሌሎች ወረዳዎች ውስጥ ባሉ ቀበሌዎች ባደረገው ዘመቻ ጽንፈኛውን የገባበት ገብቶ ነው የቀጠቀጠው፡፡ በምዕራብ ጎጃም ቋሪት ፣ አበስቃን፣ ጉልሽ፣ ጎሽ ሜዳ፣ አየለች ገበያ ፣ ሰከላ ወረዳ ቀበሌዎች ላይ እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም አነደድ ወረዳ ጉዳለማ ከተማ ኮሮች ህግ የማስከበር ግዳጃቸውን በብቃት ተወጥተዋል፡፡
በነዚህ ስኬታማ አፕሬሽኖችን ከተደመሰሱት በተጨማሪ 44 የጥፋት መልዕክተኞች ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ አስራ አንድ ሲማረኩ ፣ አስራ ሁለት እጃቸውን ሰጥተዋል ፡፡ ሌሎች አስራ ሁለቱ ጥቃቱን መቋቋም ተስኗቸው ሲሸሹ በአባይ ወንዝ እና በጎርፍ ተበልተው ህይወታቸው አልፏል፡፡ በውሀ ከተውሰዱት መሀል አዲሱ መንበር የኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ፅ/ቤት ሃላፊ የነበረ ፣ ጉምዜ እና በዛብህ የሚባሉ የጽንፈኛው አመራሮች ይገኙበታል።
አንድ አር ፒ ጂ/ላውንቸር ከነቅንቡላው ፣ አንድ ፒ ኬ ኤም/መትረየስ ፣ 85 የድሽቃ ጥይት ፣ 27 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ፣ 60 የመትረየስ ጥይት ፣ 103 የኤ ኬ ኤም ጥይትን ጨምሮ ሌሎች ጽንፈኛው ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሸከርካሪዎች እና 22 ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በተለይም በሠራዊታችን ቁጥጥር ስር የዋለውና የጽንፈኛው መሪ ያስመረቀው "ዘሪሁን 13 የአዲሱ ትውልድ ሮኬት ሚሳዔል" በሚል ቁርጥራጭ ብረት ቀጣጥለው የሰሩት የውሸት መሳሪያ ህዝቡን ምን ያህል እንደናቁትና በውሸት ፕሮፓጋንዳ እንደሚያታልሉት ያጋለጠ ነበር፡፡ ጽንፈኛው ዘመናዊ ሮኬት ሰርቻለሁ በሚል ከህብረተሰቡ በርካታ ገንዘብ በመዋጮ ስም ዘርፎበታል፡፡
በዚህ ዘመቻ ከተደመሰሱት አመራሮቻቸው መሀል ረዳት ኢንስፔክተር ስሜነህ መለሰ የፋግታ ፖሊስ አባል የነበረ ፣ ኢንጅነር ዋሲሁን አለነ ኤፍሬም አጥናፉ የሚባል ብርጌድ አመራር የነበረ ፣ ተሻገር አደመ የዚሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረ ፣ ምህረቱ አበበ ብርጌድ ምክትል አዛዥ ፣ ግዛቸው ደሳለው ፋይናንስ ሰራተኛና የአካባቢው ፅንፈኛ መስራች ታህሳስ 2017 ቆስሎ ያመለጠ ቀንደኛ ዘራፊ ፣ ደሴ ባዜ የአባጋስ ሻለቃ አዛዥ ፣ ቃኛቸው ተበጀ የሻለቃው ሎጅስቲክስ ይገኙበታል።
በዚህ ስምሪት የተደመሰሱት የጽንፈኛው አመራሮች በቡድኑ ውስጥ ትልቅ ቦታ ነበራቸው፡፡ በተለይም ሃምሳ አለቃ ደሴ አባይነህ የዘራፊው ዋና ስምሪት ሰጪ እና ሎጀስቲክስ ፣ መሬጌታ ብርሃኑ ጌተነህ የቀጣናው አወያይ እና ፖሊቲካ አስልጣኝ ወደ መንግስት ፅንፈኛው የሰላም ጥሪ እንዳይቀበል ቃለ መህላ የሚየስገባና እየሰበከ ሲያዋጋ የነበረ ፣ አንተነህ መሠረት ከዚህ በፊት መንገድ ትራንስፖርት ሙያተኛ የነበረ ከመጀመሪያው ጀምሮ ፅንፈኛን ያደራጀ የመንግስት መሣሪያ ከሚሊሺያ ያስወረደ አሁን የሻለቃ ምክትል አዛዥ የነበረ በጀግኖቹ የኢትዮጵያ ልጆች ቀለባቸው አፈር ሆኗል፡፡
የሠራዊታችንን ምት መቋቋም ያቃታቸው የጽንፈኛው አመራሮች በዋሉበት የማያድሩ ፣ ህይወታቸውን ለማትረፍ በየጥሻው እና ጉራንጉሩ መደበቂያ ሲፈልጉ የሚውሉ ፣ የሠራዊታችንን መምጣት ምልክት ሲያዩ በመጨነቅ ከመሞት ለመሰንበት በመደበቅ ህይወታቸውን የሚያራዝሙ ሆነዋል፡፡
ምስራቅ ዕዝ በቅርቡ በጀመረው በዚህ አዲስ ስልት ፣ ሠራዊታችን አስቸጋሪ መልክዓ ምድሮችን በቀንም ሆነ በድቅድቅ ጨለማ በጽናት በማለፍ ፣ ዝናብ ፣ ጭቃ ፣ የወንዝ ሙላት ፣ ብርድ እና ሌሎች የተፈጥሮ መሰናክሎችን በመቋቋም ባደረጋቸው እልህ አስጨራሽ ስምሪቶች ህዝብን እፎይ ያስባሉ ውጤቶችን አስገኝቷል፡፡
በዚህ ወር ከነሐሴ 9 ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናቶች በተካሔደው ልዩ ኦፕሬሽን የአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ሀይሎች ፣ የመስተዳድር አካላት እና ህብረተሰቡ መረጃ እና ሌሎች ድጋፍ በመስጠት ለሰላማቸው እንዲጸና ያላቸውን አጋርነት በተግባር አሳይተዋል፡፡
ሠራዊታችን እነዚህን የህዝብ ሰላም አደፍራሾች በጸረ-ሽምቅ ከያሉበት እያሰሰ ፣ እየከበበ እና እየመነጠረ አጽድቶ ህግ ያስከብራል፡፡ ዘመቻው ሰላም አደፍራሾች እስኪጠፉ የሚቀጥል ሲሆን ሰራዊታችን ክልሉን ከጽንፈኞች የማጽዳት ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ዘገባው የምስራቅ ዕዝ ነው፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤53👍8👎5🔥2👏2
ዕዙ ግዳጁን በስኬት በመፈፀም ለልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለፀ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የተሰማራበትን የግዳጅ ቀጠና ከፅንፈኛ ቡድኖች ነፃ በማውጣት በአካባቢው ምቹ የልማት ሁኔታ መፍጠሩን የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሠፋ ቸኮል ገልፀዋል።
ዝግጁነታችንን በማረጋገጥ ለቀጣይ ወሳኝ ግዳጅ እንዘጋጅ በሚል መሪ ቃል የዕዙ ከፍተኛ እና መካከለኛ ወታደራዊ አመራሮች የተሳተፉበት ውይይት በዕዝ ደረጃ ተካሂዷል። በመድረኩ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ2017 ዓ.ም የግዳጅ አፈፃፀም ጥንካሬና ድክመቶችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።
ውይይቱን የመሩት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል ዕዙ መንግስት እና ተቋሙ የሰጡትን ግዳጅ በብቃት ተወጥቷል ብለዋል። ዕዙ በፈፀማቸው ግዳጆች እና ባገኛቸው ድሎች የአካባቢው ማህበረሰብ ኑሮውን ተረጋግቶ እንዲመራ እና ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ነው የገለፁት።
ህዝቡ በአካባቢው የሚሽሎከለኩ ፅንፈኛ ቡድኖች ጠፍተው የሰላም አየር የመተንፈስ ፅኑ ፍላጎት ያለው መሆኑን ያነሱት አዛዡ የህዝቡ ሰላም ፈላጊነት ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ እንዲያጠናቅቅ ተደማሪ አቅም ይሆነናል ብለዋል።
ከውይይቱ በኋላ በበጀት አመቱ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ኮሮችና ክፍለጦሮች ዕውቅና እና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን የመቆያ ጊዚያቸውን የሸፈኑና የመመልመያ መስፈርቱን ላሟሉ አመራሮችም የማዕረግ ማልበስ ሰነ ስርዓት ተካሂዷል።
ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል በአሁኑ ሰአት እንደተቋም ሰራዊቱ በስነ-ልቦናና በትጥቅ ዘመኑን የሚመጥንና ሀገርን ወደተሻለ ምዕራፍ እንዲያሻግር ተደርጎ የተገነባና በመገንባት ላይ ያለ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ድሎችን እና ስኬቶችን ወደላቀ ደረጃ በማሸጋገር በ2018 በጀት ዓመት ለበለጠ ውጤታማ የተልዕኮ አፈፃፀም መዘጋጀት ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን የፀረ ሰላም ሃይሎችን ዕኩይ አላማ ሙሉ ለሙሉ በማጥፋት የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ የሚጠበቅ መሆኑንም አመላክተዋል።
ዘጋቢ የንጉሴ ውብሊቀር
ፎቶግራፍ ቀራለም አዱኛ

❤27👍14👏2🔥1
በኤዩሶም የሴክተር 3 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ዋና ሊቀመንበር በሶማሊያ ልዩ ተወካይና የኤዩሶም ዋና ኃላፊ አምባሳደር አል ሃጂ ኢብራሂማ ዲኔ ፣ሜጀር ጀኔራል ክንዱ ገዙ የኤዩሶም ቺፍ ኦፍ ስታፍ እና የኤዩሶም ስታፍ አባላት በባይድዋ የሚገኘውን ሴክተር 3 ጎብኝተዋል፡፡
አምባሳደር አል ሃጂ ኢብራሂማ ዲኔ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በሱማሊያ ልዩ ተወካይና የኤዩሶም ዋና ኃላፊ ከነ ልዑካቸው በባይድዋ ኤርፖርት ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የሴክተር 3 ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት የሴክተሩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተመለከተም ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
ሴክተር 3 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በብቁ ወታደራዊ ዝግጅት የተደራጀ ተልዕኮውን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚፈፅም በአፍሪካ ህብረት የተጣለበትን ከባድ ሃላፊነት በአግባቡ የሚወጣና እየተወጣ የሚገኝ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ ለዚህም አመሰግናለሁ ያሉት አምባሳደር አል ሃጂ ኢብራሂማ ዲኔ መፈታት ያሉትን ችግሮች ከበላይ አካል በመነጋገር እንዲፈቱ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡
የሴክተር 3 ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተክሉ ሁሪሳ ስለ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ፣ስለጠላት እንቅስቃሴ፣ በቀጠናው ስለተገኘው ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም የሰራዊቱን ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።
ዘጋቢ ሰመረ እሸቱ
ፎቶግራፍ አይናለም ተክለፃዲቅ

❤23👍11👏2🔥1