FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ምስራቅ ዕዝ ሲያካሂድ የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
    
የምስራቅ ዕዝ 48ኛ አመት የምስረታ በዓል በማሰመልከት ለአስር ቀናት በአትሌቲክስ፣በእግር ኳስ እና በመረብ ኳስ እንዲሁም በተኩስ ስፖርታዊ ውድድሮችን ሲያካሄድ ቆይቷል።
  
በስፖርት ውድድሩ ፋፃሜ ላይ ተገኝተው ለአሸናፊ ቡድኖች ዋንጫ በመስጠት ንግግር ያደረጉት የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሜጀር ጀኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ የዕዙን የ48 አመታት ተጋድሎ ለመዘከር ያካሄድነው ስፖርታዊ ውድድር ለተልዕኳችን ትልቅ እገዛ የሚያደርግ፣ ለሠራዊታችን አሃዳዊ ፍቅር እና ውስጣዊ አንድነቱን ከማጠናከር አንፃር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
 
የስፖርት ውድድሩ አላማ የምስራቅ ዕዝ 48ኛ አመት የምስረታ በዓል ከማክበር ባለፈ ዕዙ ከተልዕኮው ጎን ለጎን አሃዱዎች እርስ በርስ እንዲተዋወቁና ለቀጣይ ግዳጅ የስነ ልቦና ዝግጁነትን በማረጋገጥ ከፍተኛ የሞራል መነቃቃትን እንዲፈጥሩ ለማስቻል እንደሆነም አንስተዋል።

የምስራቅ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ማርዬ ምትኩ በውድድሩ ሁሉም የምስራቅ ዕዝ ኮሮችና ስታፍ ክፍሎች የተካፈሉበት፣ የሠራዊቱ ውስጣዊ አንድነትና አሃዳዊ ፍቅር የተንፀባረቀበት፣ በዲስፕሊንና በወታደራዊ ጨዋነት የተከናወነ ውድድር መሆኑን ገልፀዋል።

ውድድሩ ውስጣዊ ፉክክር ኖሮት በውጤት እንዲጠናቀቅ የዕዙ ስፖርት ቡድንና አሰልጣኞች የሐረሪ ክልል ስፖርት ፌዴሬሽን የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ አመራርና የግቢው ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ተወዳዳሪዎች በወታደራዊ ዲስፕሊን  ታንፀው ጨዋታውን ለፍፃሜ በማድረሳቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በውድድሩም በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በመረብ ኳስና በተኩስ አሸናፊ የሆኑ ክፍሎች የተዘጋጀላቸውን ዋንጫ ከክብር እንግዶች ወስደዋል።

ዘጋቢ ሳምሶን ባህሩ
ፎቶ ግራፍ ኪሶች ኢቲቻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2824👏7🔥2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ማርችንግ ባንድ የመጀመሪያ ሥራውን አቅርቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

በሩሲያ ማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ማርችንግ ባንድ ቡድን የመጀመሪያ ሥራውን አቅርቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
38👏12👍2🫡2🔥1
ተቋማዊ የሳይበር ደህንነት ሥጋትን ለማሥቀረት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

ሳይበር በማንኛውም ጊዜና በየተኛውም ቦታ ተደራሽ መሆን የሚችል አለምን በአንድ መረብ ያሥተሳሰረ ምህዳር ነው። በመሆኑም ይህንኑ የሳይበር ምህዳር በማሥፋፋት የሠራዊቱ አንድ አካል አድርጎ ለመጠቀም እየተሠራ ነው።

በሳይበር የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የሚያሥችል አሁናዊ አለም አቀፍ የሳይበር ዕድገትን እንደተቋም ለመከተልና ከሳይበር ጥቃት ተቋሙን ከመጠበቅ እና ከመከላከል ባሻገር ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም በሚያሥችል አካሄድ የማጠናከር ሥራ እየተተገበረ መሆኑን የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ ደመቀ ተናግረዋል።

የሳይበር ደህንነትን ከውጪ ጥገኝነት በተለቀቀ አግባብ በራስ አቅምና በሀገር ብሎም በተቋም ደረጃ መጠቀም የምንችልበት አግባብ መፈጠሩ አስፈላጊ በመሆኑ ተቋሙ ለሳይበር  ደህንነት ትኩረት በመሥጠት የለውጡ አንድ አካል ሆኖ መመሥረቱን ጄኔራል መኮነኑ አሥገንዝበዋል።

የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ባለፋት ሁለት ዓመታት በመስኩ ከፍተኛ የሆነ ሙያዊ ጥናት ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ ደመቀ ከጥናት ግኝቱ በመነሳት ፅሁፎች ማኑዋሎች እና የሳይበር ደህንነት ፖሊሲውን ማዘጋጀት መቻሉን አሥረድተዋል።

የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ለተቋሙ ክፍሎች የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማሥጨበጫ ስልጠናዎች በማጠናከር ስለ ሳይበር ደህንነት፣ ከሌሎች ምህዳሮች ጋር ስላለው መስተጋብር፣ የሳይበር ምህዳር ሉዓላዊነትን እንዴት ማስጠበቅ እንደሚቻል፣ እንዲሁም የሳይበር ጥቃት አይነቶችን፣ እንደ ሠራዊት እና እንደ ተቋም የሠራዊቱን ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ከሳይበር ጥቃት እንዴት መከላከል እንደሚቻል ትኩረቱን ያደረገ ሥራ በማከናወን ላይ መገኘቱንም አንስተዋል።

የዋና ዳይሬክቶሬቱ ሙያተኞች በማሠልጠኛዎችና በሠራዊቱ ክፍሎች በመዘዋወር የጥንቃቄ ደንቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ተቋሙን ከሳይበር ጥቃት መከላከል እንዲቻል ሰፊ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል።

የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ለመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ፣ ለመከላከያ ሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት፣ ለመከላከያ ሠላም ማሥከበር ማዕከል ከፍተኛ መኮንኖች የግንዛቤ ማሥጨበጫ ሰጥቷል።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍16🔥1🥰1👏1
በጎጃም እና በደቡብ ጎንደር የተሰማራው ሠራዊት 81 የጽንፈኛውን ቡድን አባላት ደመሰሰ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

ምስራቅ ዕዝ እና በስሩ ያሉት ኮሮች ባደረጉት ልዩ ስምሪት የጽንፈኛው ቡድንን አከርካሪ የሰበሩ ውጤቶች አስመዝግበዋል፡፡ ጽንፈኛው የሚዲያ ግርግር ለመፍጠር በሁሉም የጎጃም እና የደቡብ ጎንደር ዞኖች ሽብር ለመፍጠር ቢያስብም ሀሳቡ መና ቀርቶ 81 አመራሩን እና ተዋጊዎቹን አጥቷል፡፡

ምስራቅ ዕዝ በደቡብ ጎንደር በእብናት ፣ በሊቦ ከምከም ፣ በፋርጣ፣ በእስቴ፣ በደራ ወረዳዎች ቀበሌዎች ባደረገው ስምሪት ጽንፈኛውን የገባበት ገብቶ ደምስሶታል፡፡ በሰሜን ጎጃም ባሉ ደቡብ ሜጫ፣ደቡብ አቸፈር፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳዎች ቀበሌዎች ውስጥ ተሰግስጎ የነበረውን ዘራፊ ቡድን የማጽዳት ግዳጅ ተወጥቷል፡፡

በአዊ ብሑረሰብ ዞን በዳንግላ፣ በፋግታ ለኮማ ፣ ድማማ አንገረብ እና በሌሎች ወረዳዎች ውስጥ ባሉ ቀበሌዎች ባደረገው ዘመቻ ጽንፈኛውን የገባበት ገብቶ ነው የቀጠቀጠው፡፡ በምዕራብ ጎጃም ቋሪት ፣ አበስቃን፣ ጉልሽ፣ ጎሽ ሜዳ፣ አየለች ገበያ ፣ ሰከላ ወረዳ ቀበሌዎች ላይ እንዲሁም በምስራቅ ጎጃም አነደድ ወረዳ ጉዳለማ ከተማ ኮሮች ህግ የማስከበር ግዳጃቸውን በብቃት ተወጥተዋል፡፡

በነዚህ ስኬታማ አፕሬሽኖችን ከተደመሰሱት በተጨማሪ 44 የጥፋት መልዕክተኞች ቁስለኛ ሆነዋል፡፡  አስራ አንድ ሲማረኩ ፣ አስራ ሁለት እጃቸውን ሰጥተዋል ፡፡ ሌሎች አስራ ሁለቱ ጥቃቱን መቋቋም ተስኗቸው ሲሸሹ በአባይ ወንዝ እና በጎርፍ ተበልተው ህይወታቸው አልፏል፡፡ በውሀ ከተውሰዱት መሀል አዲሱ መንበር የኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ፅ/ቤት ሃላፊ የነበረ ፣ ጉምዜ እና በዛብህ የሚባሉ የጽንፈኛው አመራሮች ይገኙበታል።

አንድ አር ፒ ጂ/ላውንቸር ከነቅንቡላው ፣ አንድ ፒ ኬ ኤም/መትረየስ ፣ 85 የድሽቃ ጥይት ፣ 27 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ፣ 60 የመትረየስ ጥይት ፣ 103 የኤ ኬ ኤም ጥይትን ጨምሮ ሌሎች ጽንፈኛው ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሸከርካሪዎች እና 22 ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተለይም በሠራዊታችን ቁጥጥር ስር የዋለውና የጽንፈኛው መሪ ያስመረቀው "ዘሪሁን 13 የአዲሱ ትውልድ ሮኬት ሚሳዔል" በሚል ቁርጥራጭ ብረት ቀጣጥለው የሰሩት የውሸት መሳሪያ ህዝቡን ምን ያህል እንደናቁትና በውሸት ፕሮፓጋንዳ እንደሚያታልሉት ያጋለጠ ነበር፡፡ ጽንፈኛው ዘመናዊ ሮኬት ሰርቻለሁ በሚል ከህብረተሰቡ በርካታ ገንዘብ በመዋጮ ስም ዘርፎበታል፡፡

በዚህ ዘመቻ ከተደመሰሱት አመራሮቻቸው መሀል ረዳት ኢንስፔክተር ስሜነህ መለሰ የፋግታ ፖሊስ አባል የነበረ ፣  ኢንጅነር ዋሲሁን አለነ ኤፍሬም አጥናፉ የሚባል ብርጌድ አመራር የነበረ ፣  ተሻገር አደመ የዚሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረ ፣ ምህረቱ አበበ ብርጌድ ምክትል አዛዥ ፣ ግዛቸው ደሳለው ፋይናንስ ሰራተኛና የአካባቢው ፅንፈኛ መስራች ታህሳስ 2017 ቆስሎ ያመለጠ ቀንደኛ ዘራፊ ፣ ደሴ ባዜ  የአባጋስ ሻለቃ አዛዥ ፣ ቃኛቸው ተበጀ የሻለቃው ሎጅስቲክስ ይገኙበታል።

በዚህ ስምሪት የተደመሰሱት የጽንፈኛው አመራሮች በቡድኑ ውስጥ ትልቅ ቦታ ነበራቸው፡፡ በተለይም ሃምሳ አለቃ ደሴ አባይነህ የዘራፊው ዋና ስምሪት ሰጪ እና ሎጀስቲክስ ፣ መሬጌታ ብርሃኑ ጌተነህ  የቀጣናው አወያይ እና ፖሊቲካ አስልጣኝ ወደ መንግስት ፅንፈኛው የሰላም ጥሪ እንዳይቀበል ቃለ መህላ የሚየስገባና እየሰበከ ሲያዋጋ የነበረ ፣ አንተነህ መሠረት ከዚህ በፊት መንገድ ትራንስፖርት ሙያተኛ የነበረ  ከመጀመሪያው ጀምሮ ፅንፈኛን ያደራጀ የመንግስት መሣሪያ ከሚሊሺያ ያስወረደ አሁን የሻለቃ ምክትል አዛዥ የነበረ በጀግኖቹ የኢትዮጵያ ልጆች ቀለባቸው አፈር ሆኗል፡፡

የሠራዊታችንን ምት መቋቋም ያቃታቸው የጽንፈኛው አመራሮች በዋሉበት የማያድሩ ፣ ህይወታቸውን ለማትረፍ በየጥሻው እና ጉራንጉሩ መደበቂያ ሲፈልጉ የሚውሉ ፣ የሠራዊታችንን መምጣት ምልክት ሲያዩ በመጨነቅ ከመሞት ለመሰንበት በመደበቅ ህይወታቸውን የሚያራዝሙ ሆነዋል፡፡

ምስራቅ ዕዝ በቅርቡ በጀመረው በዚህ አዲስ ስልት ፣ ሠራዊታችን አስቸጋሪ መልክዓ ምድሮችን በቀንም ሆነ በድቅድቅ ጨለማ በጽናት በማለፍ ፣ ዝናብ ፣ ጭቃ ፣ የወንዝ ሙላት ፣ ብርድ እና ሌሎች የተፈጥሮ መሰናክሎችን በመቋቋም ባደረጋቸው እልህ አስጨራሽ ስምሪቶች ህዝብን እፎይ ያስባሉ ውጤቶችን አስገኝቷል፡፡

በዚህ ወር ከነሐሴ 9 ቀን ጀምሮ ባሉት ቀናቶች በተካሔደው ልዩ ኦፕሬሽን የአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ሀይሎች ፣ የመስተዳድር አካላት እና ህብረተሰቡ መረጃ እና ሌሎች ድጋፍ በመስጠት ለሰላማቸው እንዲጸና ያላቸውን አጋርነት በተግባር አሳይተዋል፡፡

ሠራዊታችን እነዚህን የህዝብ ሰላም አደፍራሾች በጸረ-ሽምቅ ከያሉበት እያሰሰ ፣ እየከበበ እና እየመነጠረ አጽድቶ ህግ ያስከብራል፡፡ ዘመቻው ሰላም አደፍራሾች እስኪጠፉ የሚቀጥል ሲሆን ሰራዊታችን ክልሉን ከጽንፈኞች የማጽዳት ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ዘገባው የምስራቅ ዕዝ ነው፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
49👍7👎5🔥2👏2
ዕዙ ግዳጁን በስኬት በመፈፀም ለልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገለፀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የተሰማራበትን የግዳጅ ቀጠና ከፅንፈኛ ቡድኖች ነፃ በማውጣት በአካባቢው ምቹ የልማት ሁኔታ መፍጠሩን የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሠፋ ቸኮል ገልፀዋል።

ዝግጁነታችንን በማረጋገጥ ለቀጣይ ወሳኝ ግዳጅ እንዘጋጅ በሚል መሪ ቃል የዕዙ ከፍተኛ እና መካከለኛ ወታደራዊ አመራሮች የተሳተፉበት ውይይት በዕዝ ደረጃ ተካሂዷል። በመድረኩ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ2017 ዓ.ም የግዳጅ አፈፃፀም ጥንካሬና ድክመቶችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን የመሩት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል ዕዙ መንግስት እና ተቋሙ የሰጡትን  ግዳጅ በብቃት ተወጥቷል ብለዋል። ዕዙ በፈፀማቸው ግዳጆች እና ባገኛቸው ድሎች የአካባቢው ማህበረሰብ ኑሮውን ተረጋግቶ እንዲመራ እና ፊቱን ወደ ልማት እንዲያዞር ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ነው የገለፁት።

ህዝቡ በአካባቢው የሚሽሎከለኩ ፅንፈኛ ቡድኖች ጠፍተው የሰላም አየር የመተንፈስ ፅኑ ፍላጎት ያለው መሆኑን ያነሱት አዛዡ የህዝቡ ሰላም ፈላጊነት ቀሪ ስራዎችን በአጭር ጊዜ እንዲያጠናቅቅ ተደማሪ አቅም ይሆነናል ብለዋል።

ከውይይቱ በኋላ በበጀት አመቱ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ኮሮችና ክፍለጦሮች ዕውቅና እና ሽልማት የተሰጠ ሲሆን የመቆያ ጊዚያቸውን የሸፈኑና የመመልመያ መስፈርቱን ላሟሉ አመራሮችም የማዕረግ ማልበስ ሰነ ስርዓት ተካሂዷል።

ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮል በአሁኑ ሰአት እንደተቋም ሰራዊቱ በስነ-ልቦናና በትጥቅ ዘመኑን የሚመጥንና ሀገርን ወደተሻለ ምዕራፍ እንዲያሻግር ተደርጎ የተገነባና በመገንባት ላይ ያለ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ድሎችን እና ስኬቶችን ወደላቀ ደረጃ በማሸጋገር በ2018 በጀት ዓመት ለበለጠ ውጤታማ የተልዕኮ አፈፃፀም መዘጋጀት ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን የፀረ ሰላም ሃይሎችን ዕኩይ አላማ ሙሉ ለሙሉ በማጥፋት የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ የሚጠበቅ መሆኑንም አመላክተዋል።
 
ዘጋቢ የንጉሴ ውብሊቀር
ፎቶግራፍ ቀራለም አዱኛ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍13👏2🔥1