FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስረከበ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

የማሰልጠኛ ማዕከሉ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመልካ ሰዲ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስገንብቶ በማጠናቀቅ ለአከባቢው ማህረሰብ አስረክቧል።

ሠራዊቱ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በማጠናከር ባለበት አከባቢው ሁሉ ለማህረሰቡ በመድረስ ምን ጊዜም የማይናወጥ አቋሙን በድጋፍ እያረጋገጠ ይገኛል ።

የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለበርካታ ዓመታት በማገልገል ለመማር ማስተማር ሂደቱ ፈታኝ የነበረውን በመልካ ሰዲ የሚገኝ ሲድሃ ፋጌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ሰርቶ ለአካባቢው ማህረሰብ አስረክቧል።

በቁልፍ ርክክብ ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉ የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል አየለ ወልደ ጊዮርጊስ ምን ጊዜም ለህዝብ እና ለሀገር ቅድሚያ የሚሰጥ ሰራዊታችን ከሚከፈለው የሕይወት መስዋእትነት ጎን ለጎን በእንዲህ ዓይነት በጎ ተግባር በመሳተፍ ለሀገር እድገት ስኬት ጉዞ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሲድሃ ፋጌ ቀበሌ መስተዳድር አቶ አብዱ አሊ ሰራዊቱ ከህዝብ አብራክ ወጥቶ ለህዝብ የሚያገለግል እውነተኛ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን በተግባር አረጋግጧል ብለዋል ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍10🔥3👏2
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሜንቴናንስ የሠራዊቱን ዝግጁነት የሚያጠናክሩ ተግባራትን እያከናወነ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሜንቴናንስ የሠራዊቱን ዝግጁነት የሚያጠናክሩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል። የሠራዊቱን ግዳጅና ተልዕኮ ስኬታማ ለማድረግ የሜንቴናንስ ሙያተኞች በዕቅድ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ ውጤታማ ተግባራት እያከናወኑ እንደሚገኙ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጥገና ኃላፊ ኮሎኔል ዳምጤ አያልሰው ተናግረዋል።

የሜንቴናንስ ክፍሉ በተሽከርካሪ ጥገና  ከኃይል ውጪ የነበረ ኦራልና በመሳሪያ ጥገና ቡድን ደግሞ ከአገልግሎት ወጪ የነበረ ዙ-23 መሳሪያ  የተለያዩ ሀገራት ስሪት የሆኑ የመሳሪያ ክፍሎችን በማዳቀልና ሞደፊክ በመስራት ወደ ኃይል የመመለስ ስራ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተከናውኗል ሲሉም ገልፀዋል።

የዕዝ ኮማንድ ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል በአባላቱ ዘንድ ተነሳሽነትን ፈጥሯል ያሉት ኃላፊው ኮሎኔል ዳምጤ አያልሰው ረጅም ጊዜ ከአገልግሎት ውጪ የነበሩ የውሃ ቦቴ፣ፓትሮልና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ወደ ኃይል የመመለስ ስራ መሰራቱን ጠቁመው ውጤቱም የሠራዊቱን ዝግጁነት ከማጠናከር ባሻገር የሙያተኛውን አቅም ያሳደገ ስለመሆኑም ተናግረዋል።

የመሳሪያ ጥገና ክፍል አስተባባሪ የሆነው ሻምበል አወቀ አያሌው በበኩሉ ለረጅም ጊዜ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ወድቀው የነበሩትን በማሰባሰብ የሜንቴናንስ ክፍሉ አባላት ንብረቶችን ከመሰብሰብ እስከ ሃሳብ ማዋጣት እንዲሁም በየሞያ ዘርፉ አሻራውን ከማኖር አንፃር ተነሳሽነቱ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

የዕዙ አዛዥ ተደጋጋሚ ጉብኝትና ድጋፍ ለበለጠ ስራ አነሳስቶናል ያሉት ሻምበል አወቀ አያሌው በቀጣይም የተሻለ ስራ ለመስራት ዝግጁነታችን ከመቼውም ጌዜ በላይ የላቀ ነው በማለት ተናግሯል።
ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
44👍7🙏7👎2🔥2👏1
የአዋሽ ውጊያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት የመሠረተ ልማት ሥራዎች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን በአዋሽ አርባ ውጊያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ተገኝተው በተቋሙ እየተገነቡ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፤ የትምህርት ቤቱን የሜካናይዝድ ሃይል የማሠልጠን ሂደቱን ተመልክተዋል፡፡
    
የአዋሽ ውጊያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት የስልጠና ማኑዋሎችን በማዘመን ዘመናዊነትን የተላበሰ ዘመኑ ያፈራውን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የሚጠቀም፣ ተኩሶ የሚመታና ተዋግቶ የሚያሸንፍ የሜካናይዝድ ሃይል እያፈራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ይመር መኮነን በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ መከላከያ እያስገነባቸው ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን አምፊ ቲያትር፣ 3 ኪሎ ሜትር የአስፓልት ኮክሪት ፓራዶ የውስጥ ለውስጥ መንገድን ጨምሮ 8 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ግንባታን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ዘገባው የትምህርት ቤቱ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።  
   
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
51👏15👍14🥰3🕊1
ዕዙ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ክፍሎች የማበረታቻ ሽልማትና እውቅና ሰጠ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ በተጠናቀቀው በጀት አመት የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ክፍሎች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል። የመቆያ ጊዚያቸውን የሸፈኑ እንዲሁም የመመልመያ መስፈርቱን ላሟሉ አመራሮችም ማዕረግ የማልበስ ሰነ ስርዓት አካሂዷል።

በዕለቱ የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ክፍሎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት በመስጠትና ለማዕረግ ተሿሚዎች ማዕረግ በማልበስ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፋት የዕዙ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ሽልማቱ ጥንካሪያችሁን የበለጠ አጎልብታችሁ እንድትቀጥሉ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት የላቀ የግዳጅ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ክፍሎች እና የማዕረግ ተሿሚዎች ባገኙት የማዕረግ እድገት እና ሽልማት ተጠቅመው በቀጣይም የላቀ ጀግንነት በመፈፀም ሃገርና ህዝብን የሚያኮራ ተግባር መፈፀም እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ዕዙ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የአሸባሪና የፅንፈኛ ቡድኖችን በመደምሰስ የፀረ ሰላም ሃይሎችን ፍላጎት በማምከን የተወጣው ግዳጅ በበጀት አመቱ ህዝባዊነቱን በተግባር ያሳየበትና የማድረግ ብቀቱን ያረጋገጠበት እንደሆነ ያወሱት ዋና አዛዡ የእነዚህ ክፍሎች ሚና ከፍተኛ እንደነበርም አንስተዋል።

በተገኘው ድልና ስኬት በመበረታታት በቀጣይ 2018 አዲስ አመት ለበለጠ ውጤታማ የተልዕኮ አፈፃፀም በመዘጋጀት የፀረ ሰላም ሃይሎችን ሙሉ ለሙሉ በማጥፋት የህዝብን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ የሚጠበቅ መሆኑንም አመላክተዋል።

የማዕረግ ዕድገት ተሿሚዎች እና በበጀት አመቱ ተሸላሚ የሆኑ አመራሮችም ባስመዘገቡት ውጤትና በተሰጣቸው ሽልማት መደሰታቸውን ገልፀው በቀጣይ ክፍሎቻቸውን መርተው የተሻለ ድል በመቀዳጀት የሚሰጣቸውን ማንኛውም ግዳጅ በቁርጠኝነትና በጀግንነት እንደሚፈፅሙ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶ ግራፍ ይህአለም አታላይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3022👏4🔥3