የሠራዊቱን የሳይበር ግንዛቤ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም
የሠራዊቱን የሳይበር ግንዛቤ በማሳደግ ለሚሰጠው ተልዕኮ ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጅ መሳሪያ በመጠቀም የመረጃ የበላይነትን በመውሰድ ግዳጁን በአሸናፊነት ለመወጣት አጋዥ መሆኑን የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ደረጀ ደመቀ ገልፀዋል ።
ጀኔራል መኮንኑ በሳይበር ደህንነት ፣ ምንነትና ሚዲያን መሠረት አድርገው ስለሚፈፀሙ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳና ቅስቀሳ ዘመቻዎች እንዲሁም የሳይበር ደህንነቱ በጥንቃቄ ካልተመራ ስለሚያስከትለው ጉዳት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተለይም አሁን ካለው የውጊያ ቴክኖሎጅ ጋር ተያይዞ የሳይበር ደህንነት አቅምን በማሳደግና በመገንባት ሃገርንና ተቋሙን ከጥቃት መከላከል እንዲቻል፣ የሠራዊቱን ንቃተ ህሊና በቀጣይነት ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የሳይበር አውድ እንደ አንድ የጦርነት አውድ እየታየ የመጣ መሆኑን የገለፁት ጀኔራል መኮንኑ ለዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደቱ የሳይበር ግንዛቤውን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶ ግራፍ ይህ አለም አታላይ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤32👍10🔥5
በብርሸለቆ ማሠልጠኛ የ42ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም
የብር ሸለቆ መሰረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 42ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች ከስልጠናቸዉ ጎን ለጎን በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ሲያካሂዱት የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቋል።
ስፖርታዊ ዉድድሩ ከሥልጠና ጎን ለጎን በተለያዩ የሥፖርት ዓይነቶች ፣በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ እንዲሁም በገመድ ጉተታ ለሦስት ወራት ሲካሄድ ቆይቶ ፍፃሜዉን ሊያገኝ ችሏል።
በፍፄሜዉ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ለአሸናፊ ቡድኖች ዋንጫ እና ሽልማት የሠጡት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምክትል አዛዥ ለሰዉ ሃብት አስተዳደር ኮሎኔል ጌታቸዉ ከበደ ስፖርታዊ ውድድሩ ሲዘጋጅ ዋና አላማዉ ሠልጣኙ እርስ በእርስ እንዲተዋወቅ፣ እንዲግባባ ፣አሃዳዊ ፍቅር እንዲኖረው እና ወታደራዊ ሙያውን እንዲገነዘብ በማሠብ መሆኑን ገልፀዋል።
የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሠራዊት ስነ - ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፍቅሬ ዳመነ በበኩላቸው በ42ኛ ዙር ስፖርታዊ ክንዉን ምልምል ሰልጣኝ ተወዳዳሪዎች ስፖርታዊ ዲሲፕሊን ተላብሰው ውድድር ማካሄዳቸው እና በስፖርታዊ ጨዋነት በብርቱ ፍክክር መጨረሳቸው ለየት የሚያደርገው መሆኑን ተናግረዋል።
በውድድሩ በገመድ ጉተታ ሃያ አራተኛ ሻለቃ ሃያ ሁለተኛ ሻለቃን 2ለ0 በመረብ ኳስ ጨዋታ ሠላሳ አንደኛ ሻለቃ አሥራ አንደኛ ሻለቃን 3ለ2 እንዲሁም በእግር ኳስ ጨዋታ ሠላሳ ሁለተኛ ሻለቃ አሥራ አንደኛ ሻለቃን 3ለ2 በመርታት የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችለዋል።
ዘጋቢ ጥላሁን ጌታነህ
ፎቶ ግራፍ እንደግ አበዛው

❤43👍8🔥1
የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስረከበ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም
የማሰልጠኛ ማዕከሉ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመልካ ሰዲ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስገንብቶ በማጠናቀቅ ለአከባቢው ማህረሰብ አስረክቧል።
ሠራዊቱ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በማጠናከር ባለበት አከባቢው ሁሉ ለማህረሰቡ በመድረስ ምን ጊዜም የማይናወጥ አቋሙን በድጋፍ እያረጋገጠ ይገኛል ።
የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለበርካታ ዓመታት በማገልገል ለመማር ማስተማር ሂደቱ ፈታኝ የነበረውን በመልካ ሰዲ የሚገኝ ሲድሃ ፋጌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ሰርቶ ለአካባቢው ማህረሰብ አስረክቧል።
በቁልፍ ርክክብ ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉ የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል አየለ ወልደ ጊዮርጊስ ምን ጊዜም ለህዝብ እና ለሀገር ቅድሚያ የሚሰጥ ሰራዊታችን ከሚከፈለው የሕይወት መስዋእትነት ጎን ለጎን በእንዲህ ዓይነት በጎ ተግባር በመሳተፍ ለሀገር እድገት ስኬት ጉዞ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሲድሃ ፋጌ ቀበሌ መስተዳድር አቶ አብዱ አሊ ሰራዊቱ ከህዝብ አብራክ ወጥቶ ለህዝብ የሚያገለግል እውነተኛ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን በተግባር አረጋግጧል ብለዋል ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

❤25👍10🔥3👏2
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሜንቴናንስ የሠራዊቱን ዝግጁነት የሚያጠናክሩ ተግባራትን እያከናወነ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሜንቴናንስ የሠራዊቱን ዝግጁነት የሚያጠናክሩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል። የሠራዊቱን ግዳጅና ተልዕኮ ስኬታማ ለማድረግ የሜንቴናንስ ሙያተኞች በዕቅድ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ ውጤታማ ተግባራት እያከናወኑ እንደሚገኙ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጥገና ኃላፊ ኮሎኔል ዳምጤ አያልሰው ተናግረዋል።
የሜንቴናንስ ክፍሉ በተሽከርካሪ ጥገና ከኃይል ውጪ የነበረ ኦራልና በመሳሪያ ጥገና ቡድን ደግሞ ከአገልግሎት ወጪ የነበረ ዙ-23 መሳሪያ የተለያዩ ሀገራት ስሪት የሆኑ የመሳሪያ ክፍሎችን በማዳቀልና ሞደፊክ በመስራት ወደ ኃይል የመመለስ ስራ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተከናውኗል ሲሉም ገልፀዋል።
የዕዝ ኮማንድ ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል በአባላቱ ዘንድ ተነሳሽነትን ፈጥሯል ያሉት ኃላፊው ኮሎኔል ዳምጤ አያልሰው ረጅም ጊዜ ከአገልግሎት ውጪ የነበሩ የውሃ ቦቴ፣ፓትሮልና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ወደ ኃይል የመመለስ ስራ መሰራቱን ጠቁመው ውጤቱም የሠራዊቱን ዝግጁነት ከማጠናከር ባሻገር የሙያተኛውን አቅም ያሳደገ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የመሳሪያ ጥገና ክፍል አስተባባሪ የሆነው ሻምበል አወቀ አያሌው በበኩሉ ለረጅም ጊዜ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ወድቀው የነበሩትን በማሰባሰብ የሜንቴናንስ ክፍሉ አባላት ንብረቶችን ከመሰብሰብ እስከ ሃሳብ ማዋጣት እንዲሁም በየሞያ ዘርፉ አሻራውን ከማኖር አንፃር ተነሳሽነቱ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
የዕዙ አዛዥ ተደጋጋሚ ጉብኝትና ድጋፍ ለበለጠ ስራ አነሳስቶናል ያሉት ሻምበል አወቀ አያሌው በቀጣይም የተሻለ ስራ ለመስራት ዝግጁነታችን ከመቼውም ጌዜ በላይ የላቀ ነው በማለት ተናግሯል።
ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

❤44👍7🙏7🔥2👎1👏1