FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ በጌጃ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን ፕሮጀክት ተመለከቱ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.,ም

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ በጌጃ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን የስትራቴጂክ መሳሪያዎች ኮር የክፍለጦር  መኖሪያ ካምፕ እና የጠጠር መንገድ የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ የስትራቴጂክ መሳሪያዎች ኮር ለመከላከያ ዋነኛ ድጋፍ ሰጪ እንደመሆኑ ፕሮጀክቱ ሳይጓተት በፍጥነት ተገንብቶ ማስረከብ እንደሚገባ ገልፀው ግንባታው የደረሰበት ደረጃ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

የሜሮብ ኮንስትራክሽን ድርጅት አምራችና ባለቤት ኢንጂነር ተስፋዬ ዲንሳ ሳይቱ ሁለት ፕሮጀክቶችን ያካተተ መሆኑን ገልፀው አንደኛው የክፍለ-ጦር ካምፕ አሁን ላይ 87% መድረሱንና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ፕሮጀክት ደግሞ 2.8 ኪሎ ሜትር አንደኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ አየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ከመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ጋር በመስራታቸው ደስተኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ ሻለቃ መጋቢ ባሻ ኢንጂነር ሲሳይ አበጋዝ እና ዳታ ኮሌክተር ምክትል አስር አለቃ መንፈሱ ገዴቻ የበላይ አካል ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ሰራተኞች ለሃያ አራት ሰዓት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ዲዛይኑን ጠብቆ በተቀመጠለት ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት እንዲያልቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ሃያ ብሎኮች፣ጂ+3 እና ጂ+1 ፎቆች ያሉት ነው፡፡

ዘጋቢ አዳም ወንድማገኝ
ፎግራፍ ታሪኳ ብረሃኑ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍13🔥3
የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት የሚወጡ የፈጠራ ባለቤት ጀግኖችን አፍርተናል።                   
  ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የኦርዲናንስ መምሪያ፣ የአቅርቦት መምሪያና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት፤ እንዲሁም ልዩ ልዩ ስታፍ ቡድኖች ስኬታማ እንቅስቃሴን አስመልክተው ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥተዋል።

የተቀበሉትን ግዳጅ በብቃት ከመተግበር ባለፈ ስራን የሚያቀሉ ፈጠራዎችን የሚሰሩ የሰራዊት አባላት  ማፍራታችን፤ ዕቅዶቻችን ስኬታማ እንዲሆኑ ጉልህ ድርሻ አላቸው ሲሉ በመርሃ- ግብሩ በእንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል ገልፀዋል።

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ሙስጠፋ መሀመድ የሁሉም ክፍሎች የላቀ ትብብርና ዘመናዊ አሰራር፤ ዘርፈ ብዙ እምርታ እንዳስገኘ ተናግረዋል።

በዕለቱ ሃገራቸውን ለረጅም አመታት አገልግለው በክብር ለተሰናበቱ አባላት እንዲሁም በአመቱ በስራ አፈጻጸማቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አባላት ዕውቅና እና ሽልማት ተበርክቷል።

ዘጋቢ ዳዊት ብርሃኑ
ፎቶግራፍ በድሩ መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
23👍8👏2🔥1🥰1😭1
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር የጋራ ሥልጠና ሰጡ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሀሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም 

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ያዘጋጀው ስልጠና ሰራዊቱ ተላላፊ በሽታዎችን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚረዳ እና ሰራዊቱን ከተለያየ በሽታ ለመከላከል እንደሚያስችል በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የደቡብ ዕዝ ጤና መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ግርማይ ከበደ ገልፀዋል።

ሙያተኞችን በስልጠና ለማብቃት የተቋሙና የሲቪል ተቋማት ርብርብ ማድረጋቸው የሚበረታታ መሆኑን
የሀገር አቀፍ የናሙና ቅብብሎሽ አስተባባሪ ሬድዋን መሀመድ ገልፀዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ የሰራዊት አባላትም ስልጠናውን በመውሰዳቸው ጥሩ እውቀት መጨበጣቸውን እና ወደ ክፍላቸውም ሲመለሱ ባገኙት እውቀት ሰራዊቱን ለማገልገል ዝግጁ መሆናችውን አረጋግጠዋል::

ስልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ ዕዞች፣ ማሰልጠኛዎች እና ከልዩ ልዩ ከፍሎች ለተውጣጡ የሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኒሺያን ሙያተኞች ነው።

ዘጋቢ እዮብ ሰለሞን
ፎቶግራፍ አብረሃም ወርቁ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32🥰2🔥1
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝትና ማዕረግ የማልበስ ሥነ-ሥርዓት።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ብሄራዊ ቤተ-መንግስትን ጎብኝተዋል።

ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ዛሬ የተመለከትነው የጉብኝት ቦታ ሀገራችን ተከብራ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ የዘለቀች ሥለመሆኗ ትውልድ የሚማርበት መሆኑን ገልፀዋል።

ታሪክን በአግባቡ እና ትውልድ በሚያስተምር መንገድ ሰንዶ በማዘጋጀት በዚህ መልኩ ለጉብኝት ክፍት እንዲሆን የሰራ አካል በእጅጉ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል።

አያት አባቶቻችን ያስረከቡንን ሀገር ሉዓላዊነቷንና ብሄራዊ ጥቅሟን በማስጠበቅ ለመጭው ትውልድ ለማስረከብ ሰራዊታችን ተልዕኮውን በብቃት እየፈፀመ እንደሚገኝ የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ሀገርን ከውስጥ ባንዳና ከውጭ ጠላት በመጠበቅ እና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም የማስከበር ተልዕኮውን ከመቸውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ገልፀዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ በተገኙበት የመቆያ ጊዚያቸውን የሸፈኑና ማዕረግ መልበስ የሚያስችላቸውን መስፈርት ላሟሉ የዋና መምሪያው አመራሮችና አባለት የማዕረግ የማልበስ ስነ ስርአት ተካሂዷል።

የማዕረግ ዕድገት የበለጠ ሀላፊነት በመሆኑ የዛሬ ተሿሚዎች ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት የተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም ለማስመዝገብ መትጋት ይጠበቅባችኋል ሲሉ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ አሳስበዋል።

የዛሬ ተሿሚዎች መምሪያው እየፈፀመ ለሚገኘው ሁሉን አቀፍ ስራ ተጨማሪ አቅም በመሆን የበኩላቸውን ሚና ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ዘጋቢ ማሙሸት አድነው
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
61🔥5😡3