FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ሠላም አሥከባሪ ሻለቃው በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተረጋገጠ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ በአሥተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ። የዩናሚስ ኢንስፔክሽን ቡድን መሪ ሚስተር ካሌብ ማቹሩሬ ዝግጁነት በማረጋገጥ ሂደት ሞተራይዝድ ሠላም አሰከባሪ ሻለቃው የሠው ሃይሉን እና የተልዕኮ መገልገያ ማቴሪያሎቹን በተሟላ መልኩ ለግዳጅ ዝግጁ ማድረጉን አረጋግጠዋል።

ሚስተር ካሌብ ማቹሩሬ ለሞተራይዝድ ሻለቃው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከመኖሪያ ቤት እና ተያያዥ ጉዳዮች መሟላት የሚገባቸው አስፈላጊ ንብረቶች በፍጥነት እንዲያስተካከል የተጠየቀ ሲሆን በፍተሻው ወቅት የታዮ ጉድለቶች በስምምነቱ መሠረት በቀጣይ ማሟላት እንደሚገባም ተናግረዋል። በጥቅሉ ሲታይ ግን የሠራዊቱ የዝግጅነት ቁመናው እና የንብረት አያያዙ ከባለፈው የተሻለ እንደነበር ተገልጿል።

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ሌተናል ኮሎኔል ተፈራ ሊሞሬ ሠላም አስከባሪው የታጠቃቸው የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያዎች ፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ፣ የህክምና መገልገያዎች ፣ የሰራዊቱ መመገቢዎች  እና መፀዳጃዎች ላይ ፍተሻ መደረጉን ተናግረዋል።

ሌተናል ኮሎኔል ተፈራ ሊሞሬ ንብረቶቹ ለግዳጁ ካላቸው የላቀ ጠቀሜታ አኳያ በጥንቃቄ እና በእንክብካቤ መያዝ የሠላም አስከባሪው ሀላፊነት መሆኑን ጠቁመው ለዚህም አስፈላጊ ክትትል እንደሚደረግ አብራርተዋል።

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አከባሪ ሻለቃ የኢንስፔክሽን ሀላፊ ሻምበል ዘመናይ ደመቀ ሁሉም ንብረቶች ክፍያ እንዲያገኙ ተገቢውን ቁጥጥር መደረጉን ገልፀው ንብረቶቹ የሀገር ሀብት በመሆናቸው በእንክብካቤ በመያዝ ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ኢንስፔክሽን ቡድኑ በዌስት ኢኳቴሪያ ቀጠና ያምቢዮ ፣ ፖዙ እና ታምቡራ እንዲሀም በሴክተር ሳውዝ ጁባ ዱሩፒ ካምፕ ጨምሮ  ፍተሻ እና ቁጥጥር  በማድረግ ዝግጁነትን አረጋግጧል።

ዘጋቢ ፍፁም ተካ
ፎቶ ግራፍ ግርማቸው አብረሀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍9🔥2
የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ለውድድር አመቱ በቂ ዝግጅት እያደረገ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሀሴ 09 ቀን 2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየርሊግ ውድድር ላይ የሚሳተፈው የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ለ2018 የውድድር አመት ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር መሠረት ማኔ ገልፀዋል።

የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ለ2018 የውድድር አመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ጀምሮ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ በመቀለቀል እንዲሁም የነባሮችን ውል በማደስ ዝግጅታቸውን በቢሾፍቱ ከተማ  ከሁለት ሳምንት ቢፊት በመጀመር በርካታ የጥንካሬና ቡድኑን የማቀናጀት ስራ በመሥራት ላይ ናቸው።

የቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር መሠረት ማኔ  መቻል አንጋፋ ክለብ ነው እድሉ ተሰጥቶኝ ያለኝን ልምድ እና አቅም ተጠቅሜ  ውጤታማ እንዳደርገው ሃላፊነት ለለሰጡኝ ለክለቡ አመራሮች እና ለተቋሙ ትልቅ ክብር አለኝ ብለዋል።

ኢንስትራክተር መሠረት እንዳሉት ቡድኑ በዝግጅት ስራቸው የጥንካሬ ስራን ከኳስ ጋር አጣምረን እየሰሩ መሆኑን አንስተው በቀጣይ የተለያዩ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ለማድረግ ማቀዳቸውን ተናግረው ከአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹ ጥንካሬ እና ድክመት በመለየት ነሀሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሚጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየርሊግ ውድድር ላይ የተሻለ ውጤት እንደምናመጣ እምነት አለኝ ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

   መቻል ለኔ ሁሉ ነገሬ ነው ያለችው የቡድኑ አምበል አምሳ አለቃ ዙሪያሽወርቅ መልኬ በ2018 የውድድር አመት የተሻለ ውጤት ለማሳካት ያለን አንድነት እና ተነሳሽነት ጥሩ ነው በመሆኑ በዚህ አመት የተሻለ ውጤት እናሳካለን ብላለች።

በመቻል ቤት ለሁለተኛ ተከታታይ አመት የቆየችው የተከላካይ መስመር  ተጫዋች የሆነችው ብርቄ አማረ ካለፉት የውድድር አመት በተሻለ መልኩ የዘንድሮው የቡድናችን ቅንጅትና አንድነት የተሻለ በመሆኑ ጥሩ ተፎካካሪ ሆነን እናጠናቅቃለን ስትል ተናግራለች።ዘጋቢ ገረመው ጨሬ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31👍7👎3🔥2
ኮሩ ሰላምን በማስፈን ላበረከተው አስተዋፅኦ እውቅና ተሰጠው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም
 
የደቡብ እዝ ተወርዋሪው ኮከብ ኮር ሰላምን በማስፈን ላበረከተው አስተዋፅኦ በአዳማ ከተማ ለፀጥታ ሀይሉ በተዘጋጀው የምስጋና ዝግጅት ላይ የዋንጫና የዕውቅና ሰርተ-ፊኬት ተበርክቶለታል። ሽልማቱንም የኮሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ተቀብለዋል።

ሽልማቱን የሰጡት የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀይሉ ጀልዴ መሰረቷ የማይናጋ የተከበረች ሀገርን ለማስቀጠል ሰራዊታችን ከውጭና ከውስጥ ፀረ ሰላም ሀይሎች ጋር እየተጋፈጠ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ሀገርን ያቆየ ህዝባዊ ሠራዊት በመሆኑ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

አቶ ሀይሉ ጀልዴ ተወርዋሪው ኮኮብ ኮር በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ የሀገር ሰላምን የማይሹ ፀረ ሰላም ሀይሎችን በመፋለም  የሀገራችንን ሰላም በማረጋገጥ የህዝባችንን ደህንነት በመጠበቅ  በአዳማ ከተማ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜ ያለምንም እንቅፋት እንዲቀጥሉ በማድረግ ኮሩ የአንበሳውን ድርሻ ይዟል በማለት ገልፀዋል።

ሠራዊታችን ለራሱ  የተመቻቸ ኑሮ ሳይኖር  ለብርድና ሙቀት ሳይበገር ጫካ ውሎ የሚያድረው የማትደፈር ሀገርን ለማቆየትና ህዝባችን በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ስራውን በነፃነት እንዲያከናውን ፀረ ሰላም ሀይሎችን ከፀጥታ ሀይል ጋር በጥምረት በመፋለም ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ሰለሞን አማረ
ፎቶ ግራፍ መለስ ውለታው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍9🔥2
ጠንካራ ስነ-ልቦና ያለው ሠራዊት በማንኛውም ግዳጅ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል እሸቱ አሥማማው በቡርቃ ማሠልጠኛ ማዕከል ለሚገኙት የሻለቃና የሻምበል አመራሮች አንዲሁም ድጋፍ ሠጭ ሙያተኞች የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ስራን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሠጥተዋል።

ጠንካራ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ያለው አመራር ጠንካራ አሃዱ ከመፍጠርም በላይ በማንኛውም ግዳጅ የድል ባለቤት እንደሚሆን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ሠራዊት ከምንም በላይ በውስጡ ጥልቅ የሃገር ፍቅር ስሜት እና የድል አድራጊነት አመለካከትን መላበስ እንዲችል በየደረጃው ያለ አመራር ቀጣይነት ያለው የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ስራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

አመራሩ የጠላትን አፍራሽና ፅንፍ የወጣ አመላካከት
መመከት የሚችል ሠራዊት ለመገንባት የትኩረት አቅጣጫ መንደፍ እና መከተል እንዳለበትም አመላክተዋል።

በመከላከያ ሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት የግንባታ ሥራዎች ዝግጅት እና ሥልጠና ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ተወካይ ኮሎኔል መንግሥቱ ጌታንጋ  በበኩላቸው ተከታታይነት ያለው ለወጥ ለማምጣት ሁሌም ሠራዊቱ መገንባት በሚችልባቸው መሠረታው የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከአመራሩ ጋር በመናበብ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የስነ-ልቦና ዝግጁነትና የድል አድራጊነት ስሜት የሚገነባው ቆራጥና ሃገር ወዳድ መሪዎችን ማፍራት ሲቻል መሆኑን ገልፀው የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ስራ ብቻ ስላልሆነ ሁሉም የሠራዊት አመራሮች ትኩረት ሠጥተው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ ጌትነት ሊበን
ፎቶግራፍ ልዑል ዘውዴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
21👍5🔥2