FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
33 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ሠላም አሥከባሪ ሻለቃው ህዝባዊነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን ዌስት ኢኳቴርያ ቀጠና በያምቢዮ እና ፓዙ ካምፖች የሚገኙ የ21ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት በያምቢዮ ስቴት ሆስፒታል ለሚገኙ ታካሚዎች የመድሃኒት እና የምግብ ድጋፍ አድርገዋል።

በደቡብ ሡዳን የዌስተር ኢኳቴሪያ ስቴት ጥብቅ አስተዳዳሪ ሚስተር ዳንኤል ባግደቡ ሪምባሳ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ተልዕኮውን በብቃት እየፈፀመ እንደሆነ መስክረው ከፀጥታ አካላት እና ከማሕበረሰቡ ጋር በመናበብ የቀጠናው ሠላም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እንዲመጣ አበክረው እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል። ለተቸገሩ ወገኖች የሚያደርጉት ልዩ ልዩ ድጋፎቾም የሚደነቅ እንደሆነ አብራርተዋል።

የዩናሚስ የመሰክ ኦፊሠር  ወይዘሮ ጄይን ኮኒ በበኩላቸው ሠላም አስከባሪው የአከባቢው የፀጥታ ችግሮች በሚገባ በመረዳት በሠላም ግንባታ ሂደቶች ውጤታማ ተግባራት ከማከናወኑ በተጨማሪ በየወቅቱ መሠል ድጋፎች ማድረጋቸው መልካምነታቸውን ያመላከተ ተግባር መሆኑንም ገልፀዋል።

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሥከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል እንዳለ እሸቱ ሠላም አስከባሪ ሠራዊቱ የቀጠናውን ሠላም እና ፀጥታ ከማረጋገጥ ባሻገር ከራሱ የሚጠቀመውን መድሀኒት እና ምግብ ቀንሶ በህክምና ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች ድጋፍ ማድረጉ ህዝባዊነቱን ያሳያ እንደሆነ ገልፀው  በቀጣይም መሠል ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ደረጃ አንድ ሆስፒታል ሲኒየር ሜዲካል ኦፊሰር ሻለቃ ዶክተር ተክለወይኒ ተስፋይ ሰላም አስከባሪ አባላቱ ሀላፊነታቸውን በዲሲፕሊን ከመወጣት አልፈው በዌስት ኢኳቴርያ ስቴት ከሚገኙ የጤና ሙያተኞች ጋር በቅንጅት የሕብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል። 

በዌስተርን ኢኳቴሪያ የያምብዮ ስቴት ሆስፓታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሳሙኤል ኮንጅ ሰላም አስከባሪ ሻለቃው በየወቅቱ ከየአካባቢው የማሕበረሰብ ተወካዮች በጋራ ተቀራርቦ በመስራት ሕዝቡ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያከናውነት በጎ ተግባራት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው አሁን ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ተካ
ፎቶ ግራፍ ግርማቸው አብረሀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
38👍6🔥5
አባቶቻችን ያስረከቡንን ሀገር ለትውልድ ማስረከብ እንደሚጠበቅ ሌተናል ጀኔራል መሃመድ ተሰማ ተናገሩ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም

የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በዕዙ ማስልጠኛ ማዕከል ተገኝተው ከሁሉም ኮሮች ተውጣጥተዉ በስልጠና ላይ ከሚገኙ ሰልጥኖ አስልጣኞች፣ ከማሰልጠኛ ማዕከሉ አሰልጣኞችና አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጥንት አባቶቻችን ያስረከቡንን ሀገር የማቆየትና የማስጠበቅ እንዲሁም ለቀጣይ ትውልድ ማስረከብ ከኛ ይጠበቃል ያሉት ሌተናል ጀኔራል መሃመድ ተሰማ አገራችን እና ተቋማችን የሰጡንን ተልዕኮ ለመወጣት የሰራዊቱን ስነ-ልቦና በመገንባት ረገድ ስልጠና ትልቁን ድርሻ ይወጣል ብለዋል።

የአገራችንን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ የውጭም ሆነ የውስጥ ጠላቶችን እና የህዝቦችን አንድነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሃይሎችን በመመከት ተልዕኳችንን በውጤት እየተወጣን እንገኛለን ሰሉ ተናግረዋል፡፡

ሠራዊቱ ከተሰጠው ተልዕኮ አንፃር አገራዊ ግዳጁን በብቃት መፈፀም የሚያስችል የስነ-ልቦና ዝግጅትን በማጠናከርና የማድረግ አቅምን በማሳደግ እንዲሁም በብቃት፣ በእውቀትና በክህሎትን ብቁ ሆኖ መገኘት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። ዘጋቢ አበበ ያለዉ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31👍18🔥3
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች የሎጀስቲክስ ክፍሎችን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 07 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ትምህርታቸውን በኮሌጁ እየተከታተሉ የሚገኙ ከፍተኛ መኮንኖች በሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ቆሬ የሚገኘውን የጥገና መምሪያን፣ የገመኔ ትራንስፖርትን እና የመልካ ቃሊቲ የሎጅስቲክስ ክፍሎችን ጎብኝተዋል።

ጀግኖችን መፍጠር የማይታክታት ታላቅ ሀገር እንዲሁም የግዙፍና ጠንካራ ተቋም ፍሬዎች በመሆናችሁ ልትኮሩ ይገባል ሲሉ በዕለቱ የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል ተናግረዋል።

የዋና መምሪያ ሃላፊው ሎጀስቲክስ የተቋማችንን ሀብት አቅቦ በመንከባከብ እያሻሻለና እያዘመነ የሚያስታጥቅ፤ እንዲሁም በሳይንሳዊ መንገድ እያቀደ ስራውን የሚያሳካ ክፍል እንደሆነ ተናግረዋል።

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሙሉጌታ አምባቸው በበኩላቸው የማዕከላቱ ግንባታ የተቋሙን ዝግጁነት እንደሚያሳድግ ጠቅሰው፤ ሎጀስቲክስ በተቋም የሚገኝ የሃገር ሀብት ነው ብለዋል።

በምግብ ራስን የመቻል ተቋማዊ ዕቅዳችንን በሚያፋጥን መልኩ በአሳ፣ በማር፣ በዶሮ እንዲሁም ስንዴና በሚበሉ ፍራፍሬዎች በዋና መምሪያው አመርቂ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

የማዕከላቱን የቀድሞ ገፅታ ያሥታወሱት ኮሎኔል ድንበሩ ደጀኔ አሁን መከላከያን የሚመጥን የሎጀስቲክስ ማዕከል መገንባቱ ስራን ለማቀላጠፍ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብላዋል።

ሌተናል ኮሎኔል አብርሃም ቻሌ በበኩላቸው የኮሊደር ልማቱን አርአያ ተከትለው የተገነቡት ለትውልድ የሚተላለፉ ድንቅ ስራዎች መሆናችውን አንስተዋል።

ዘጋቢ ዳዊት ብርሃኑ
ፎቶግራፍ ወንድሙ መድህን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
35👍9🔥3👏2