FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
33 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ክፍለጦር በህገወጥ ቡድኑ ላይ እርምጃ ወስዷል።  

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 04 ቀን 2017 ዓ.ም
                   
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ብርሃኑ በላይ እንዳሉት ፅንፈኛው ቡድን የተለመደ የዝርፊያና እገታ ተግባሩን ለማራመድ በደቡብ ወሎ ዞን በከለላ ወረዳ ላይ ሙከራ ቢያደርግም በህገወጥ ቡድኑ ላይ ሠራዊቱ በወሰደው እርምጃ በርካታ የቡድኑ አባላትን ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።
  
ክፍለጦሩ ባደረገው ዘመቻ የህገወጥ በድኑ ላይ እርምጃ በመውሰድና በማቁሰል፣ 06 አባላትን መማረክ ችሏል። በዚህም ብሬን ፣ክላሽ ፣የቃታ መሳሪያ መማረክ የተቻለ ሲሆን ሠራዊቱ በህገ-ወጥ ቡድኑ ላይ የሚያደርገውን ስምሪት አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። ዘገባው የክፍለጦሩ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
45👍32🔥4👎2
የኮማንዶ ሬጅመንት በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ የፅንፈኛውን ቡድን ደመሰሰ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮማንዶ ሬጅመንት በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ብርቂቱ ቀበሌ በወሰደው እርምጃ በርካታ የፅንፈኛ አባላትን በመደምሰስ አንድ የቡድኑ ሎጀስቲክስ አመራርን ጨምሮ ሰባት የቡድኑ አባላትን ከነትጥቃቸው መማራኩን የሬጅመንቱ ዋና አዛዥ ሻለቃ ግዛቸው ዘሪሁን ተናግረዋል፡፡

የሬጅመንቱ አባላት አስቸጋሪና ፈታኝ የመሬት ገፅታዎችን የአየር ሁኔታን በማለፍ ለሰላም አልገዛም አሻፈረን ብሎ በአካባቢው ተደብቆ ህዝብን ሲዘርፍና ሲያሰቃይ የነበረውን የፅንፈኛ ቡድን በመደምሰስ ለአካባቢው ህዝብ እፎይታን መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።

ሬጅመንቱ ፅንፈኛውን ቡድን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ፅንፈኛውን ጨምሮ ክላሽ ፣ የተለያዬ አይነት ጥይት እና ሌሎችንም በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ተናግረዋል። ዘገባው የክፍለጦሩ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
52👍25🔥6🖕3
የኮሩ አመራሮች ከዞንና ከፀጥታ ሀይል አመራሮች ጋር በአዳማ ከተማ ተወያዩ።
     
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 05 ቀን 2017 ዓ.ም

የደቡብ እዝ ኮር አመራሮች በምስራቅ ሸዋ ዞን ከዞን እና ከወረዳ ከተውጣጡ አመራርና የፀጥታ ሀይሎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በአዳማ ከተማ  ተወያይተዋል።
   
የኮሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋየ ሰላምን ለማረጋገጥ ሰራዊታችን ሌት ተቀን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መሰናክሎችን እየተጋፈጠ መምጣቱን ገልፀው ሰላምን ለማስፈን ሁሉም በየተሰማራበት የስራ ዘርፍ ስለ ሰላም ጠንክሮ ሊሰራ እንደሚገባው አመላክተዋል።

በዞኑ ሰላም እንዲሰፍን ሰራዊታችን ከፀጥታ ሀይሉና ከዞኑ አመራሮች እንዲሁም ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በቅንጅት በመስራቱ የዞኑን ሰላም ማረጋገጥ ችለናል ቀጣይም ለሰላምና ለልማት የምናደርገውን የጋራ ስራ አጠናክረን በመቀጠል ሰላምን ማሥፈን ይገባናል ብለዋል።
   
ሰራዊታችን የሀገርን ሰላም ለማረጋገጥ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የፀናች ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ሰራዊት ነው ያሉት  የምስራቅ ሸዋ ዞን ፓሊስ መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሽዋየ ደቻሳ የዞኑን ሰላም ለማረጋገጥ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ ከሠራዊቱ ጎን መቆም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
    
ዘጋቢ ሰለሞን አማረ
ፎቶግራፍ መለስ ውለታው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
57👍21🔥3👏3
ምስራቅ ዕዝ የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅና ሰላምን የማረጋገጥ ግዳጅን አጠናክሮ ቀጥሏል።
   ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ሞ

የምስራቅ ዕዝ 48ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሐረር ከተማ ኢማም አህመድ ስታድዬም በስፖርት ፌስቲቫል መከበር ጀምሯል።

በበዓሉ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ ምስራቅ ዕዝ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለህዝቦች ደህንነት መከበር ከፍተኛ ተጋድሎ ካደረጉ ዕዞች መካከል አንዱ መሆኑን አውስተው ዕዙ የ48ኛ የምስረታ በዓሉን ለመዘከር ዋዜማው ላይ ይገኛል ብለዋል።

ምስራቅ ዕዝ ከሌሎች ዕዞች ጋር በመሆን ህዝባዊ ባህሪያቶቹንና እሴቶቹን በመጠበቅ ኢትዮጵያን ከውስጥም ሆነ ከውጪ ጥቃቶች በመከላከል አገርና ተቋሙ የሰጡትን ተልዕኮ በውጤት እየፈፀመ ይገኛል። በቀጣይም  የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅና ሰላምን የማፅናት ተግባራችንን እናጠናክራለን ብለዋል።

ሰራዊቱ የኢትዮጵያዊነት እሴቶችን ተላብሶ የፈፀማቸው ተልዕኮዎች በህዝባችን ዘንድ የክብር ካባ ያጎናፀፈውና ላስመዘገባቸው ውጤቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን ተናግረዋል።

የምስረታ በዓሉን "ህገ መንግስታዊ ተልዕኳችንን በድል እየተወጣን የሀገራችንን ሰላም እናፀናለን" በሚል መሪ በተለያዩ መረሃ ግብር እንደሚከበር ያበሰሩት  የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ በዓሉ ስፖርታዊ ፌስቲቫል፣ በወታደራዊ  ትርዒቶች፣ በፓናል ውይይት፣ በመጽሐፍ ምረቃና በሌሎች ፕሮግራሞች ይከበራል ብለዋል።

ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ የዕዙን የግዳጅ አፈፃፀም የሚያሳዩ ዘጋቢ ፊልምና የፎቶ ዐውደ ርዕይ ለእይታ እንደሚቀርብም የገለፁ ሲሆን ምስራቅ ዕዝ ከተልዕኮው ጎን ለጎን በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ሁሉ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር  ከህዝቡ ጋር  በመሆን ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ሰፋፊ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀረሪ ክልሉ የፖሊስ አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  ታድመዋል።

ዘጋቢ ሳምሶን ባህሩ
ፎቶ ግራፍ ኪሶ ኢቲቻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
47👍10🔥3
ዕዙ በየጊዜው የሚሰጡትን ግዳጆች በብቃት የተወጣና በመወጣት ላይ የሚገኝ ነው።
    ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሠፋ ቸኮል በቡርቃ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝተው በስልጠና ላይ ለሚገኙ ፣ለሻምበል እና ለሻለቃ አመራሮች እንዲሁም ለልዩ ልዩ የሙያ ሰልጣኞች የግንዛቤ ማሥጨበጫ ሰጥተዋል።

ዕዙ በየጊዜው የሚሰጡትን ግዳጆች በብቃት የተወጣ እና በመወጣት ላይ የሚገኝ አስተማማኝ ሀይል መሆኑን አሁን ላይም ማንኛውንም ሀይል በብቃትና በቁርጠኝነት መመከት በሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ እና ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

ዋና አዛዡ የዕዙ የሠራዊት አባላት ሀገርን ለማፍረስ ቀን ከሌሊት የሚኳትኑ ባንዳዎችን እና ፅንፈኞችን ህልም በማክሰምና እኩይ አላማቸውን በማክሸፍ እያደረጉት ያለው የጀግንነት ተግባር የሚመሰገን መሆኑን ገልፀው ይህ የሰራዊቱ በመስዋዕትነት የደመቀ የድል ተግባርም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የሰራዊቱን ሁለንተናዊ አቅምና ብቃት የማሳደግ ሂደትና ብቁ አመራሮችን ማፍራት የስልጠናው ዋና አላማ መሆኑን በማስገንዘብ ይህ ተግባር ዕንደ ዕዝ ብሎም እንደተቋም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የገለፁት ዋና አዛዡ በስልጠናው ሂደትም የሚሰጡ ስልጠናዎችን በትኩረት መከታተልና በግዳጅ አፈፃፀም ወቅት አኩሪ ድል ማስመዝገብ ከሰልጣኞች የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል።

የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ግርማ ስዩም በበኩላቸው በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ በሚሰጡ ስልጠናዎች የአመራሩን ብቃት የሚያሳድጉ ልዩ ልዩ ሰልጠናዎች እየተሰጡ የቆዩ መሆናቸውን ገልፀው በአሁኑ ሰአትም አመራሩን ማዕከል ያደረገ ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን ማዕከሉ ብቁና ተኪ አመራሮችን በማፍራት ረገድ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል። ዘገባው የንጉሴ ውብሊቀር ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
36👍12👏3🔥2🥰2