FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዕዙ ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ የለመለመች ኢትዮጵያን ለትውልድ እያሻገረ እንደሚገኝ ተገለፀ።
‎       
‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
      
እንደ ሀገር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ የሚገኘው የችግኝ መትከል መርሀ ግብር ላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የተገኙት የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ በጋራ በመሆን የለመለመች ኢትዮጵያን ለማሻገር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

‎ማዕከላዊ ዕዝ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና እንደተቋም "ከካምፓችን ወደ ህዝባችን "በሚል መሪ ቃል የችግኝ መትከል መርሀ ግብር የተከናወነ ሲሆን ሀገራዊና ተቋማዊ ፍላጎት የሆነውን በአንድ ጀምበር ሁሉንም አሳታፊ በጎ ተግባር የዕዙ አዛዦች ጄኔራል መኮንኖችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተከናውኗል።

‎ዕዙ የተሰጠውን ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ አስተማማኝ ሰላም የማስፈን ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ሰራዊቱ በአረንጓደ አሻራ መርሀ ግብር ሲሳተፍ ይህ የመጀመሪያው ሳይሆን በሰፈረባቸው አካባቢዎች የማልማት ልምዱን ከካምፕ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በማስፋት አሻራውን እያኖረ መምጣቱን ገልፀዋል።

‎ችግኝ መትከል ለመጭው ትውልድ ህይወት እንደመስጠት ነው ያሉት ደግሞ የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጄኔራል አብድሮ ከድር ናቸው።

‎በጅማ ከተማ ከዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል ሰልጣኝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች የተሳተፉበት የችግኝ መትከል መርሀ ግብር የተከናወነ ሲሆን የአካባቢን ስነ ምህዳር ለመጠበቅ አሻራን ከማሳረፍ ባለፈ በየጊዜው መከታተልና መንከባከብ እንደሚገባ ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ሰራዊቱ ከተሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በአንድ እጁ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት እየጠበቀ በሌላ በኩል ሀገሩን እያለመለመ አጋርነቱን በተለያዩ ህዝባዊነቱን በሚገልፁ ተግባራት ከማስመስከሩ ባለፈ ላስመዘገባቸው ድሎች ምስጋና አቅርበዋል።

‎የጅማ ዞን ምክትል አስተዳዴር አቶ የሱፍ ሻሮ በበኩላቸው ሰራዊቱ ፀጥታውን ከማረጋገጥ አልፎ አርዓያ የሆነ በጎ ምግባሩን ለህብረተሰቡ እያወረሰና ሀገሩን እየገነባ የሚገኝ የሰላምና የልማት ሀይል መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል።

‎ዘጋቢ መሀመድ አህመድ
‎ፎቶግራፍ ሚኪያስ እስክንድር


የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
16👍15👏3
የመከላከያ አይሲቲ ማዕከል በዘርፋ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ አይሲቲ ማዕከል ስራ ከጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሃገር የዲጅታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እየተሰራ ባለው ስራ ማዕከሉ በተቋማችን ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በሃላፊነት ተረክቦ በመስራት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

መከላከያ እንደ ሃገር ከፍተኛውን የቴክኖለጂ ተጠቃሚ መሆኑን የገለፁት የአይሲቲ ማዕከል ኋላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል ጥላሁን አሸናፊ በተቋሙ ውስጥ እስካሁን የነበሩ የወረቀት ስራዎችን ወደ ዲጅታል መቀየር፣ በራስ አቅም ልዩ ልዩ ሶፍትዌሮችን አበልፅጎ ወደ ስራ ማስገባት፣ አሁን በዕቅድ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል።

መከላከያ የራሱ ፕራይቬት ኔትወርክ እንዲኖረው ትልቅ ፕሮጀክት ይዘው በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝ እና ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ተቋሙ ደህንነቱ የተጠበቀ ኔትዎትክ እንዲኖር የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቴክኖለጂ ጋር ለመራመድ ክፍሎችን በስልጠና ማሳደግና ሙያዊ ድጋፍ ጭምር እየሰጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ዘጋቢ ደጀኔ አሳይቶ
ፎቶግራፍ ሳሙኤል መንገሻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍8🔥1
ሠራዊታችንን የሚደግፍ በራሱ ተነሳሽነት የሚሠራ ሙያተኛ ተፈጥሯል፡፡
ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የጥገና ሙያተኞችን አሠልጥኖ አሥመርቋል። በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል ግዳጅን ተቀብሎ የሚወጣ ብቻ ሳይሆን በሚሰጠው ስልጠና መሰረት ጨምሮና ፈጥሮ ጥራት ባለው መንገድ የሚሠራ ጀግና ሙያተኛ እንደተፈጠረ ገልፀዋል።

ሙያተኞች የሠለጠናችሁትን ሙያ በመጨመር ወደ አሃዳችሁ ስትመለሱ ዘርፈ ብዙ ችግር ፈቺ ስራዎችን በተሻለ በመስራት የሠራዊታችንን ሁለንተናዊ ዝግጁነት ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የሜንተናንስ መምሪያ የታንክና ጦር መሳሪያ ሜንተናንስ ቡድን መሪ ኮሎኔል መስፉን ሐይሉ ሰልጣኞቹ ከእዞችና ክፉለ ጦሮች የተውጣጡ የሠራዊት አባላት ሲሆኑ በከባድ የጦር መሳሪያ፣ በታንኮች እና በሮኬቶች የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና ለአስር ወራት ሲሠለጥኑ የቆዩ ሙያተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል ። ዘጋቢ ወርቅነህ ተስፉዉ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍6👏2🔥1
የመከላከያ ክፍሎች የመቆያ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ አባላቱ ማዕረግ አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ የመቆያ ጊዜያቸውን አጠናቅቀው የላቀ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸው የዋና መምሪያው አባላት የማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓት አከናውኗል።

የዋና መምሪያው ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል በላይ ስዩም በማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ለተሿሚዎች የማዕረግ ማልበስ ስነ-ስርዓት በማከናወን የስራ መመሪያም ሰጥተዋል።

ተሿሚዎች የማዕረግ ዕድገት ማግኘት ተጨማሪ ግዳጅና ኃላፊነትን መቀበል መሆኑን አውቃችሁ ህዝብና መንግስት የሰጣችሁን አደራ ከዚህ በፊት ከነበረው በላይ ስራዎችን መፈፀም ይጠበቅባችኃል ብለዋል።

በተያያዘ የመከላከያ ሠላም ማሥከበር ማዕከል የተሻለ የስራ አፈፃፀም ለነበራችውና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የማዕከሉ የሠራዊት አባላት የተፈቀደላቸውን ማዕረግ አልብሷል።

የሠላም ማስከበር ማዕከሉ አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ ተሿሚዎች ዛሬ የምታገኙት የማዕረግ ሹመት ለቀጣይ ስራ መነሳሳት የሚፈጥር እና ለከፍተኛ ሃላፊነት የሚያዘጋጃችሁ የዕድገት መሰላል በመሆኑ በታታሪነት ልትሠሩ ይገባል ብለዋል።

ለረጅም ዓመት ተቋሙን ስያገለግሉ የቆዩ እና በክብር በጡረታ ለተሰናበቱ የሠራዊት አባላት ምሰጋና በማቅረብ ቀሪው ዘመን ጥሩ እንዲሆንላቸውም ለተሰናባች የሠራዊት አባላት መልካም ምኞታቸውን አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ የስትራቴጂክ መሳሪያዎች ኮር በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራር እና አባላት ማዕረግ አልብሷል።

በዕለቱ ማዕረግ ያለበሱት የኮሩ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ግርማ ከበበው የእለቱ ተሿሚዎች ከአሁን ቀደም ባሳዩት መልካም ስነ-ምግባርና በግዳጅ አፈፃፀማቸው የተሻሉ በመሆናቸው ለሹመት እንዲበቁ ተደርጓል ብለዋል።

ተሿሚዎች የተሰጣቸው ሹመት ጊዜያቸው ስለደረሰ ብቻ ሳይሆን ባሳለፉት የአገልግሎት ዘመን በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑና በተቀመጠው መመዘኛ ተመዝነው ያለፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
50👍20🔥1