FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.5K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የማይተካ ነፍሱን ለሚሰጥ ወታደር የሚተካ ደም መለገስ መታደል ነው
     የኢንዱስትሪ ግሩፑ ደም ለጋሾች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች ደም ለግሰዋል።
ኢንዱስትሪ ግሩፑ በሥሩ ባለው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አስተባባሪነት በግንባር ግዳጁን እየተወጣ ያለው ሠራዊት በሚያጋጥመው ጉዳት የደም ዕጦት እንዳያጋጥመው በማሰብ በርካታ በጎ ፈቃደኞች ደም ለግሰዋል።

ደምን መለገስ  ከጥቅሙ ውጭ አንዳች ጉዳት የለውም ያሉት የቤላ ደም ባንክ ሜዲካል ዳይሬክተር ኮሎኔል ዶክተር ጌታቸው አምባው በየሦስት ወር የሚተካውን በበጎነት ለዜጎች በመለገስ ሕይወትን ማዳን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በየዓመት የደም ልገሳን ጨምሮ የተለያዩ የክረምት በጎ አድራጎት ተግባራትን እንደሚያደርግ የገለፁት የኢንዱስትሪ ግሩፑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ሻምበል እመቤት ጌታቸው ከየክፍሎች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ለማበርከት መሰብሰቡን ተናግረዋል።

ለሠራዊታችን ደም መለገስ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ያነሱት የዕለቱ የደም ለጋሾችም የማይተካ ነፍሱን ለሚሰጥ ወታደር የሚተካ ደም በመለገስ ሕይወትን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ውብሸት አንበሴ
ፎቶግራፍ አብርሃም ዘርጋው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
10🔥7👍3
የሜካናይዝድ ዕዝ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በጋራ በመሆን ችግኝ ተከሉ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ የሜካናይዝድ ዕዝ አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ከፍያለው አምዴ የመከላከያ ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ምንጊዜም ካለው ዝግጁነት እና ቁርጠኝነት ባለፈ የተረጋጋ ሀገርና ትውልድ ለመገንባት በሚደረግ ማንኛውም ሀገራዊ ተልዕኮ ላይ በሙሉ ግንባር ቀደም ሚናውን ይወጣል ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ረጋሣ በበኩላቸው በአረንጓዴ ዐሻራ ልማት የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ ዩኒቨርሲቲው ቀዳሚ ድርሻውን እንደሚወጣ ገልፀዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ የዘንድሮው ሰባተኛው የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አንድ ሆነን በጋራ ስንሰራ ማንኛውንም ጉዳይ ማሳካት እንደምንችል እና አንድነታችን በየትኛውም ሀገራዊ ምዕራፎቻችን ወሳኝ ሚና እንዳለው ማሳያ ነው ብለዋል።
ዘገባው የዩኒቨርሲቲው የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ዳይሬክቶሬት ነው


የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
15👍7🔥2
ዕዙ ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ የለመለመች ኢትዮጵያን ለትውልድ እያሻገረ እንደሚገኝ ተገለፀ።
‎       
‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
      
እንደ ሀገር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ የሚገኘው የችግኝ መትከል መርሀ ግብር ላይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የተገኙት የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ በጋራ በመሆን የለመለመች ኢትዮጵያን ለማሻገር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

‎ማዕከላዊ ዕዝ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና እንደተቋም "ከካምፓችን ወደ ህዝባችን "በሚል መሪ ቃል የችግኝ መትከል መርሀ ግብር የተከናወነ ሲሆን ሀገራዊና ተቋማዊ ፍላጎት የሆነውን በአንድ ጀምበር ሁሉንም አሳታፊ በጎ ተግባር የዕዙ አዛዦች ጄኔራል መኮንኖችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተከናውኗል።

‎ዕዙ የተሰጠውን ህገ መንግስታዊ ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ አስተማማኝ ሰላም የማስፈን ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ሰራዊቱ በአረንጓደ አሻራ መርሀ ግብር ሲሳተፍ ይህ የመጀመሪያው ሳይሆን በሰፈረባቸው አካባቢዎች የማልማት ልምዱን ከካምፕ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በማስፋት አሻራውን እያኖረ መምጣቱን ገልፀዋል።

‎ችግኝ መትከል ለመጭው ትውልድ ህይወት እንደመስጠት ነው ያሉት ደግሞ የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጄኔራል አብድሮ ከድር ናቸው።

‎በጅማ ከተማ ከዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል ሰልጣኝ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች የተሳተፉበት የችግኝ መትከል መርሀ ግብር የተከናወነ ሲሆን የአካባቢን ስነ ምህዳር ለመጠበቅ አሻራን ከማሳረፍ ባለፈ በየጊዜው መከታተልና መንከባከብ እንደሚገባ ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ ሰራዊቱ ከተሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በአንድ እጁ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት እየጠበቀ በሌላ በኩል ሀገሩን እያለመለመ አጋርነቱን በተለያዩ ህዝባዊነቱን በሚገልፁ ተግባራት ከማስመስከሩ ባለፈ ላስመዘገባቸው ድሎች ምስጋና አቅርበዋል።

‎የጅማ ዞን ምክትል አስተዳዴር አቶ የሱፍ ሻሮ በበኩላቸው ሰራዊቱ ፀጥታውን ከማረጋገጥ አልፎ አርዓያ የሆነ በጎ ምግባሩን ለህብረተሰቡ እያወረሰና ሀገሩን እየገነባ የሚገኝ የሰላምና የልማት ሀይል መሆኑን አረጋግጧል ብለዋል።

‎ዘጋቢ መሀመድ አህመድ
‎ፎቶግራፍ ሚኪያስ እስክንድር


የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
16👍15👏3
የመከላከያ አይሲቲ ማዕከል በዘርፋ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ አይሲቲ ማዕከል ስራ ከጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሃገር የዲጅታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እየተሰራ ባለው ስራ ማዕከሉ በተቋማችን ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በሃላፊነት ተረክቦ በመስራት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

መከላከያ እንደ ሃገር ከፍተኛውን የቴክኖለጂ ተጠቃሚ መሆኑን የገለፁት የአይሲቲ ማዕከል ኋላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል ጥላሁን አሸናፊ በተቋሙ ውስጥ እስካሁን የነበሩ የወረቀት ስራዎችን ወደ ዲጅታል መቀየር፣ በራስ አቅም ልዩ ልዩ ሶፍትዌሮችን አበልፅጎ ወደ ስራ ማስገባት፣ አሁን በዕቅድ በመሰራት ላይ ነው ብለዋል።

መከላከያ የራሱ ፕራይቬት ኔትወርክ እንዲኖረው ትልቅ ፕሮጀክት ይዘው በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝ እና ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ተቋሙ ደህንነቱ የተጠበቀ ኔትዎትክ እንዲኖር የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቴክኖለጂ ጋር ለመራመድ ክፍሎችን በስልጠና ማሳደግና ሙያዊ ድጋፍ ጭምር እየሰጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ዘጋቢ ደጀኔ አሳይቶ
ፎቶግራፍ ሳሙኤል መንገሻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍8🔥1
ሠራዊታችንን የሚደግፍ በራሱ ተነሳሽነት የሚሠራ ሙያተኛ ተፈጥሯል፡፡
ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የጥገና ሙያተኞችን አሠልጥኖ አሥመርቋል። በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል ግዳጅን ተቀብሎ የሚወጣ ብቻ ሳይሆን በሚሰጠው ስልጠና መሰረት ጨምሮና ፈጥሮ ጥራት ባለው መንገድ የሚሠራ ጀግና ሙያተኛ እንደተፈጠረ ገልፀዋል።

ሙያተኞች የሠለጠናችሁትን ሙያ በመጨመር ወደ አሃዳችሁ ስትመለሱ ዘርፈ ብዙ ችግር ፈቺ ስራዎችን በተሻለ በመስራት የሠራዊታችንን ሁለንተናዊ ዝግጁነት ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የሜንተናንስ መምሪያ የታንክና ጦር መሳሪያ ሜንተናንስ ቡድን መሪ ኮሎኔል መስፉን ሐይሉ ሰልጣኞቹ ከእዞችና ክፉለ ጦሮች የተውጣጡ የሠራዊት አባላት ሲሆኑ በከባድ የጦር መሳሪያ፣ በታንኮች እና በሮኬቶች የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና ለአስር ወራት ሲሠለጥኑ የቆዩ ሙያተኞች መሆናቸውን ገልፀዋል ። ዘጋቢ ወርቅነህ ተስፉዉ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍6👏2🔥1