FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.5K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ በሥራ አፈፃፀማቸው ውጤታማ ለሆኑ አባላቱ ማዕረግ አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
   
በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ውጤታማ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸውና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ የሠራዊት አባላት ከተቋሙ የተፈቀደላቸውን ማዕረግ አልብሷል።

ለተሿሚዎች ማዕረግ ያለበሱት የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ ለተሿሚዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማሥቀደም የማዕረግ ዕድገት ማለት የሃላፊነትና የተጠያቂነት እድገት መሆኑን ተገንዝባችሁ በቀጣይነት የተሻለ እና የተቋሙን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ተግባር በማከናወን የበኩላችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል።

መንግስትና ህዝብ የሰጠንን ተልዕኮ በመመሪያው መሠረት በመተግበር ለሀገራችን ሰላም መስፈን እና ለተቋሙ እደገት ተደጋግፎ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይ እውቀታችሁንና ችሎታችሁን የበለጠ በማሳደግ ሰራዊቱ ውጤታማና ቀጣይነት ያለው የተልዕኮ አፈፃፀም እንዲኖረው ድርብ ወታደራዊና መሃንዲሳዊ ሃላፊነታችሁን መወጣት ይኖባችኋል ብለዋል።
  
የተሿሚዎችን ሪፖርት ያቀረቡት በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሰው ሃብት ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል አንተነህ ብርሃኑ ለማዕረግ እድገት የበቁት አባላት በተቀመጠው የማዕረግ እድገት መመዘኛ መስፈርት መሰረት የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑ፤የተሻለ የስራ አፈፃፀም ያላቸው፤ በአካዳሚ በአካል ብቃት መመዘኛውን ያሟሉ መሆናቸውን ገልፀዋል። ዘጋቢ አዳም ወንድማገኝ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32👍13🔥1
ህብረተሰቡ ወደ ሠላማዊ ህይወት እንዲመለስ ኮሩ ግዳጁን በሚገባ እየተወጣ ነው፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017  ዓ.ም

የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጀኔራል ግዛዉ ኡማ ኮሩ በተሰማራበት ደቡብ ጎንደር ዞን ተግኝተው ከኮሩ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ፅንፈኛዉን ቡድን በመደምሰስ ህብረተሰቡ ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ በማድረግ ረገድ የተሻለ ዉጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ጎንደር ተሰማርቶ አስተማማኝ በሆነ መልኩ ግዳጁን ከመወጣቱ ባሻገር ተከታታይ ስልጠናዎችን እስከ ስታፍ ድጋፍ ሰጭ ሙያተኞች ድረስ በመሥጠት   የሰራዊቱን የማድረግ አቅም በማሳደግ ለቀጣይ ተልዕኮ መዘጋጀት ላይ ውጤታማ ሥራ መሠራቱን ገልፀዋል፡፡  

ሜጄር ጀኔራል ግዛዉ ኡማ ከግዳጃችን ጎን ለጎን ያደረግነውን ስልጠና እንደ ትልቅ አቅም ተጠቅመን ከዉስጥም ይሁን ከዉጪ የሚነሱ ጠላቶቻችንን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሀገራችን የሰጠችንን ህዝባዊ አደራ በሚገባ እንዋጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሀገራችን ኢኮኖሚ በተለየ ሁኔታ እያደገ በመሆኑ ከመቼዉም ጊዜ በላይ የሠራዊታችን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል ከእኛ የሚጠበቀዉን ሃላፊነት በሚገባ መወጣት አለብን በማለት አስገንዝበዋል፡፡

የምስራቅ ዕዝ አንድ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተሾመ ይመር በበኩላቸው በአጭር ጊዜ በተደረጉ ኦፕሬሽኖች ጠላትን በመደምሰስ ዞኑ ቀድሞ ወደ ነበረበት ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለስ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

ዘጋቢ ልዑል መኮንን
ፎቶግራፍ ኤልያስ ታምሩ
 
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
41👍9🔥2😁2
ዕዙ በተሟላ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገለፁ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
    
የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ በደቡብ ዕዝ ማሠልጠኛ ተገኝተው ለአመራሮች የግንዛቤ ማሥጨበጫ ሥልጠና ሰጥተዋል።

የዕዙን የሠራዊት አባላት በስልጠና በማብቃት በቡድንና በተናጠል ድልን የሚያስመዘግብ ከዘመኑ ጋር የሚራመድ አሰራርን እና መመሪያን የሚከተል ማድረግ መቻሉንም አሥረድተዋል።

ተልዕኮውን ለማሳካት የሰው ሃይሉን በየወቅቱ በማብቃት የአመራሩን እና የአባሉን ቅንጅታዊ አሰራር በማዘመን አስተሳሰብና አመለካከት መገንባት እንደሚገባም አንስተዋል። የተሻለ ነገን ለትውልድ ለማስረከብ በራሱ የሚተማመን መሪ በመፍጠር ከቃል በላይ በተግባር ጠንክሮ የመስራት ባህልን ማዳበር እንደሚገባም አረጋግጠዋል።

ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ዕዙ ወታደራዊ ዝግጁነቱን በማረጋገጥ የማድረግ አቅሙን እያሳደገ መምጣቱን ገልፀዋል።  ለተልዕኮው የሚተጋ በመርህና በእሴት የሚመራ የሃገራችን ሉአላዊነት ለመጠበቅ ሃገራዊ ተልዕኮውን በፅናት መወጣት የሚችል በዓላማው የፀና በአካል ብቃት የጠነከረ በስነ-ልቦና የተገነባ ሞራል ያለው ሠራዊት መፍጠር እንደሚያሥፈልግም አመላክተዋል።

እንደ ዕዝ በሚፈለገው ልክ ግዳጅን ተቀብሎ በእጥፍ መፈፀም የሚችል ሃይል በመፍጠር የሃገራችንን ሠላምና ልማት ለማሳለጥ የእድገት እንቅፋት ሆነው በስተጀርባ የሚሰሩ ፀረ ሰላም ሃይሎችን በንቃት መከታተልና መደምሰስ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የዕዙን የማያቋርጥ የጀግንነት ታሪክ አጠናክረን በማስቀጠል አመራሩ በሃላፊነትና የተጠያቂነት መንፈስ አይተኬ ሚናውን በአግባቡ መወጣት አለበት ሲሉም ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ጠቁመዋል፡፡  

ዘጋቢ በላይ ታደለ
ፎቶ ግራፍ ቦጋለ አዲሴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👍11🔥2
በኢትዮጵያ የህንድ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ሳሚር ማህዋል የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

ጉብኝቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት እና የሁለትዮሽ ትብብር በማጠናከር በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ተመስገን አቦሴ ተናግረዋል።

አካዳሚው ላለፉት 90 ዓመታት በነበረው የመማር ማስተማር ሒደት የህንድ መንግስት ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ያወሱት አዛዡ  አሁን የተደረገው ጉብኝት ይህንኑ የሁለቱን ሃገራት ወታደራዊ ግንኙነት ከፍ ወደአለ ደረጃ የሚያሸጋግረው መሆኑን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ የህንድ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ሳሚር ማህዋል አካዳሚውን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት ህንድና ኢትዮጵያ የቆየ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ገልፀው ፣ በአካዳሚው ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎችን የትምህርት እድል በመስጠት በሃገራቸው እንዲማሩ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል ያለው ወታደራዊ ትብብርም በማጠናከር ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ዘጋቢ ፍቃዱ ጆቴ
ፎቶግራፍ ነጋሽ ደጀኔ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍4🔥2
የወታደራዊ ግንኙነት መሳሪያዎችን የማዘመንና ሙያተኞችን የማብቃቱ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

የሬዲዮ ግንኙነት ትስስርን በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሰራር የመተካት ስራና የሰው ሀይሉን የማብቃት ጥረቱ  በታቀደለት መስኩ መከናወኑን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሲስተም ዋና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ ብርጋዲየር ጄኔራል አዱኛ ዴሬሳ ገልፀዋል።

ተቋሙን ከከፍተኛ ወጪ በማዳን በብልሽት ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ የግንኙነት መሳሪያዎችን በመጠገን የሞዴፌኬሽን እና የፈጠራ ስራዎችን በመጠቀም ወደ ሀይል የመመለስ እና የማባዛት አመርቂ ስራዎች በውስጥ አቅም መሠራታቸውንም ጠቅሰዋል።

በቀጣይም የመምሪያው አባላት ለሚሠጡ ሀገራዊና ተቋማዊ ተልዕኮዎች በማቴሪያልም ሆነ የሰው ሀይልን የማብቃትና ዝግጁ የማድረግ ስራዎችና የመስራት ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ዘጋቢ ራሔል ገዛኸኝ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
29🔥4👍2
ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ክቡር መስዋዕትነት ተከብራና ፀንታ ትቀጥላለች።
       ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ክብር መስዋዕትነት ተከብራና ፀንታ ትቀጥላለች ሲሉ  የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ከጠቅላይ መምሪያው ስታፍ መኮንኖች ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክና ታላቅ ህዝብ ያላት ሀገር ናት፤ ብሔራዊ ጥቅሟንና ህልውናዋን የሚፈታተኑ ሃይሎች  በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሉዓላዊነቷን ለመዳፈር ሞክረዋል ሆኖም ግን በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት የሃፍረት ካባን ተከናንበው ተመልሰዋል ብለዋል።

በውስጥ ባንዳና ተላላኪዎች ኢትዮጵያን የማዳከም ተደጋጋሚ ትንኮሳዎች በታሪካዊ ጠላቶቻችን ተሞክረዋል ያሉት ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት አሁን የገጠመን የፅንፈኛው እና የአሸባሪው ሸኔ ሴራም የነዚሁ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ድብቅ አጀንዳ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

እኛ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በጀግንነት ጠብቀን ያቆየን የዚህ ዘመን ባለ ታሪኮችና በተደራራቢ ግዳጅና ተልዕኮ ያልተበገርን የፅናት ተምሳሌቶች ነን ሲሉም ተናግረዋል።

የተዋጊ ክፍሉ ግዳጅ ስኬታማ እንዲሆን የጠቅላይ መምሪያው ድጋፍ ሰጪ ስታፍ ሚና የላቀ ነበር ያሉት አዛዡ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ከቀዳሚ መምሪያው ጋር ተናቦ ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ የሚችል ጠንካራ ስታፍ ነው ፤ወደፊትም የድጋፍ ሰጪነቱን ሚና ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ እንዲያከናውን የአቅም ግንባታ ሰራዎች ትኩረት ተደርጎባቸው እንደሚሰሩም ተናግረዋል። ዘጋቢ ፍፁም ከተማ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39🔥7👍2