FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዋና መምሪያው በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ስራዎችን በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን አሥታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የዋና መምሪያው የሠራዊት አመራሮች እና አባላት እንዲሁም ሲቪል ሠራተኞች በአመቱ በመናበብ አሠራር እና መመሪያን በመከተል የተሳካ ውጤታማ ተግባር መከናወናቸውን የመከላከያ ሠው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ተናግረዋል።

እንደ ዋና መምሪያ በመደጋገፍና በመረዳዳት የጋራ ሥራ መሥራት ውጤታማ እንደሚያደርግ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎች ማሳያ መሆናቸውን የገለፁት ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ መምሪያዎች እና ቡድኖች የተሠጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ ተወጥተዋል ብለዋል።

አሥቀድሞ በመዘጋጀት በሠራዊት ምልመላ ላይ በሁለት ዙር የተደረገው ሥራ እጅግ የተሳካና ውጤት ያለው መሆኑን ብሎም በተፈለገው ልክ መከናወኑን የመምሪያ ሃላፊዎች ገልፀዋል።

የካዴት ሥልጠናን ጨምሮ አመራሩን በትምህርት ዕድል በየደረጃው የማብቃት ስራ ከሀገር ውስጥ ባለፈ ተቋሙ በከፍተኛ ወጪ ወደውጭ ሃገር በመላክ እያሥተማረና እያበቃ እንደሚገኝ የገለፁት ኃላፊዎቹ የትምህርትም ሆኑ ሌሎች ምልመላዎች አሠራር እና ሥርዓትን የተከተሉ ሥለመሆናቸውም አንስተዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ በኩልም ለተገልጋዩ የተጣራ መረጃ በመስጠትና የሰው ሃይል በመቆጣጠር ዳታን በማደራጀትና ሠራዊቱ በግዳጅ ላይ ደስተኛ እንዲሆን በማድረግ በኩል ሁሉም የሰው ሃይል ሙያተኛ በላቀ ደረጃ ስራውን በመስራት ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ሌላዉ የአገልግሎት አሰጣጡ ተደራሽ መሆኑን ለማረጋገጥ ሰራዊቱ ባለበት ቦታ ድረስ በአካል በመገኘት በኢንስፔክሽን በዳታዎች ምልከታና በውይይት የማረጋገጥ ስራ ተሰርቷል።

ከጡረታና  ከስንብት አንፃር ለተቋሙ አገልግሎት ሰጥተው የሚሠናበቱ የሠራዊት አባላትን በመመሪያና በአሰራሩ መሠረት በመተግበር የተቀመጠለትን በወቅቱ እንዲያገኝ እና በደስታ ሲያገለግል እንደነበር ሲሰናበትም ደስተኛ ሆኖ እንዲወጣ በማድረግ በኩል የተሻለ ስራ መሠራቱን የመምሪያ ሃላፊዎች ገልፀዋል።

ዘጋቢ መልካሙ ያደታ
ፎቶግራፍ ትግስት ሙላት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39🔥3👍2
ዘመኑን የሚመጥን የኢንፎርሜሽን ሲስተም የመዘርጋት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

ዋና መምሪያው በበጀት አመቱ  በርካታ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን የገለፁት የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ሲስተም ዋና መምሪያ ሀላፊ ብርጋዲየር ጀነራል አዱኛ ዴሬሳ ፣ ተቋሙ የያዘውን የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ለማጠናከር በወታደራዊ ግንኙነት መስኩ ብቁ የሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ እየገነባ መሆኑን ገልፀዋል።

መምሪያው የሰው ሃይልን የማብቃት ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን የገለፁት ሀላፊው ፣ዘመኑን የሚመጥን የኢንፎርሜሽን ሲስተም በመታጠቅ ፣ በመዘርጋትና በመጠቀም ተቋሙን ወደላቀ ደረጃ  የማሳደግ ጥረቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የውጊያ አቅምን ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉና ከፍተኛ ወጪ ያወጡ የነበሩ ሶፍትዌሮችን በራስ አቅም በመጠቀም በመስራት ለተቋሙ የሚጠቅሙ ቀላልና ዘመናዊ ሶፍትዌሮችን በማበልፀግ ወደ ስራ የተገባ መሆኑንም ብርጋዲየር ጀነራል አዱኛ ዴሬሳ ገልፀዋል።

በእለቱ በስራ አፈፃፀማቸው ብልጫ ላመጡ አባላት የእውቅና ሰርተ-ፊኬት እና ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ከሰራዊቱ በክብር ለተሰናበቱ አባላትም የክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

ዘጋቢ ራሔል ዮሐንስ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍10🔥3
ግዳጅ እና ተልዕኳችንን በላቀ ብቃት ለመፈፀም የሚያሰችል አቅም ፈጥረናል።
       ተመራቂ አመራሮች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

በስልጠና ግዳጅና ተልዕኳችንን በላቀ ብቃት መፈፀም የሚያስችለንን አቅም ፈጥረናል ሲሉ የ6ኛ ዕዝ ተመራቂ አመራር እና ሙያተኞች ተናገሩ።

የ6ኛ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለሁለት ወራት በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ፣በሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ፣በመደበኛ እና ኢ-መደበኛ ውጊያዎች ግዳጅን  በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ መወጣት የሚያስችል አቅም በሥልጠና እንድንፈጥር አድርጎናል ሲሉ የሬጅመንት እና የሻምበል አመራሮቹ ተናግረዋል።

ማሰልጠኛ ማዕከሉ ሁለንተናዊ ብቃት ተላብሰን እንድንወጣ አድርጎናል ያሉት አመራሮቹ መደበኛም ሆነ ኢ-መደበኛ ውጊያዎችን በዕቅድ መምራት፣በመሬት አጠቃቀም፣ በውጊያ ስልት እንዲሁም ተኩስን መምራት በሚያስችሉ ፕሮግራሞች ዙሪያ የተሰጡ ስልጠናዎች ለቀጣይ ግዳጅና ተልዕኮ የበለጠ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው ናቸውም ብለዋል።

ስልጠናው ከማዕከሉ አሰልጣኞች ባሻገር የተለያየ ልምድና ዕውቀት ባካበቱ ተጋባዥ መምህራን መሰጠቱ አገራዊ፣ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ግንዛቤ እንዲኖረን አስችሎናል ሲሉም ተናግረዋል።

አመራሮቹ ከዕዝ ኮሮች እና ክፍለጦሮች የተውጣጣን ከመሆኑም ባሻገር ከተጨባጭ ግዳጅና ተልዕኮ ላይ ወደ ማዕከሉ መምጣታችን ስልጠናው በተሞክሮ ልውውጥ እንዲዳብር አድርጎታል ፤የዚህ አይነት ስልጠና ወደፊትም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። 

ተመራቂ አመራሮች የወሰዱት ወቅታዊ ተልዕኮን እና  ሀገራዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀው ይህም በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተሰጠ በመሆኑ ተደማሪ አቅም ፈጥሮልናል ነው ያሉት።

ዘጋቢ አዲሱ አራጋው
ፎቶግራፍ ሌሊሴ አራራሜ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3420🔥4