FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ንብ የእግር ኳስ ክለብን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማሣደግ እንደሚሠራ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

የአየር ሃይል ንብ እግር ኳስ ክለብ አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን የቦርዱ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አካሂዷል፡፡

የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአቪየሽን ከበድ ጥገና ማዕከል ሃላፊ እና የንብ እግር ኳስ ክለብ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መሰረት ጌታቸው የንብ እግር ኳስ ክለብ ከፕሪሚየር ሊግ እስከ ብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ  ተጫዋቾችን ያፈራ መሆኑን ተናግረዋል።

ክለቡ ለውድድር በተጓዘበት ቦታ ሁሉ የሠራዊታችን መለያ የሆነውን ህዝባዊነት እና ስፖርታዊ ጨዋነትን በመላበስ በዲሲፕሊን ከተመልካች ጋር መልካም ግንኙነት በመፍጠር በከፍተኛ ሊጉ ስኬታማ የውድድር አመት ማሳለፍ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በጉባኤው በበጀት አመቱ የንብ እግር ኳስ ቡድን የነበሩ እንቅስቃሴዎች እና የስራ አፈፃፀም ዝርዝር ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ሪፖርት በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ በቀጣይ በ2018 በጀት አመት ንብ እግር ኳስ ክለብን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለማሳደግ እንዲሁም ተተኪ ተጫዋቾችን በመለየት እና በማብቃት ቡድኑ የተሳካ የውድድር ዘመን እንዲያሳልፍ እቅድ አስቀምጧል፡፡ 
  
የአየር ኃይል ንብ እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በሜዳና ከሜዳ ውጭ ባደረጋቸው ግጥሚያዎች በአመቱ በ40 ነጥብ እና 11 ንፁህ ጎል በመሰብሰብ በምድቡ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

በእለቱም ለንብ እግር ኳስ ክለብ ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት የትጥቅ ስጦታ በምክትል ፕሬዘዳንቱ ተበርክቷል፡፡

ዘጋቢ እሱያውቃል ሙሉየ
ፎቶ ግራፍ ባጫ ለገሰ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
49👍14🔥4
የኢትዮ-ጂቡቲ የጋራ መከላከያ ኮሚቴ 11ኛ ስብሰባውን ማካሔድ ጀመረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እና የጂቡቲ የጋራ መከላከያ ኮሚቴ 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እያካሔደ ነው።

ስብሰባው እየተካሔደ ያለው የመከላከያ ውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹና የጂቡቲ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ ኮሎኔል ማጆር (ሜጄር ጄነራል) አብዱረህማን አብዲ በተመራ ወታደራዊ ልዑካን መካከል ነው።

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያላቸው ሀገሮች መሆናቸውን የገለፁት ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹ ለልዑካን ቡድኑ ሁለተኛ ሀገራችሁ ወደሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጣችሁ ብለዋል። 

የጂቡቲ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ ኮሎኔል ማጆር (ሜጄር ጄነራል) አብዱረህማን አብዲ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል።

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አታሼ ሜጄር ጄነራል ተስፋዬ ወልደማርያም በተገኙበት መድረክ ዛሬ መካሔድ የጀመረው ውይይት ሀገራቱ በ10ኛው የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ በተስማሙባቸው አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ነው።

ስብሰባው የሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡት የሰላምና ደህንነት ስራዎች አፈፃፀም መሠረት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ለወደፊት  በሚሰሩ ስራዎች ላይም አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል።

ይህ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ በየጊዜው የሚካሄድ ሲሆን፣ በሁለቱ ወንድማማች አገሮች መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት እና ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ዘጋቢ አብዮት ዋሚ 
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28👍10🔥2👏2
ዕዙ የሻለቃ፣ የሻምበል እና ልዩ ልዩ የስታፍ ክፍሎችን አሰልጥኖ አስመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ ለወራት በዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን የሻለቃ፣ የሻምበል፣ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ እና የፋይናንስ ዘርፍ ሙያተኞችን አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው የስራ መመሪያ የሰጡት የዕዙ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን በየጊዜው የሚያጋጥሙ ፈተናዎች በአሸናፊነትና ድል አድራጊነት በመሻገር ሃገርን ከነ ሙሉ ክብሯ ለማስቀጠል በሁለንተናዊ አቅምና ችሎታ ልቆ መገኘት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ሜጀር ጄኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ዕዙ ከዚህም ከዚያም  ብቅ ብቅ እያሉ የሃገራችንን ሰላምና ልማት ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ፣ከትናንት የማይማሩ ተላላኪ ባንዳዎችና ታሪካዊ ጠላቶቻችን አደብ እንዲገዙ ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

ዕዙ ውስብስብ እና አስቸጋሪ ግዳጆችን በፅናት ተወጥቷል ያሉት ዋና አዛዡ አሁን ላይም ህገ መንግስታዊ እምነቱ የፀና ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ ክብር የሚዋደቅ አመራርና አባላት መገንባት እንደተቻለም አስረድተዋል።

ስልጠናው የሠራዊቱን አመራሮች ሙያዊ ብቃት ከፍ ለማድረግና ተልዕኮና ግዳጆችን በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ
ሁሉም አመራር በየደረጃው በቀጣይ በክፍሉ በሚመራው ሠራዊት አርዓያ በመሆን አስከ ታችኛው ክፍል ድረስ ስልጠናዎችን በመስጠት ማብቃት እና ማስተማር ለፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታ ሂደት አጋዥ ሆኖ መገኘት የእለት ተእለት ስራችሁ ልታደርጉ ይገባል ብለዋል።

ዋና አዛዡ የስታፍ ከፍሎችም ለዕዙ ስኬታማ የግዳጅ አፈፃፀም ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ያገኛችሁትን ሙያዊ አቅም ተጠቅማችሁ ሃላፊነታችሁን በቅንነትና በታታሪነት ልትወጡ ይገባል ነው ያሉት።

የስልጠናውን ሪፓርት ያቀረቡት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌተናል ኮሎኔል ታምራት ሌንጅሶ ማሠልጠኛ ማዕከሉ የዕዙን የሠራዊት አመራሮችና አባላት በመሪነት ሚና እንዲሁም ልዩ ልዩ ሙያዎች አሰልጥኖ በማብቃት የዕዙን የግዳጅ አፈፃፀም የተሳካና ሁሌም በድል የሚቋጭ እንዲሆን በማድረግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶግራፍ ይህዓለም አታላይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2916🔥2🥰1👏1
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በመሆን ችግኝ ተከሉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የሠራዊት አባላት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል ነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ያከናወኑት።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ዉበት ቢሮ ሃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ እንዳሉት ሰራዊቱ  የአገርን አንድነት እና ሰላም ከማረጋገጥ ባሻገር በሃገራዊ ልማቱ የሚያደርገዉ ተሳትፎ ህዝባዊነቱን አጉልቶ የሚያሳይ ነዉ።

ኃላፊው ሠራዊቱ ህይወትን ሰጥቶ ህይወትን ያሚያኖር ከመሆኑም በላይ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያደረገው ልማታዊ ተሳትፎ የሚያኮራ ነው ለዚህም የላቀ ክብርና ምስጋና ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ ግርማ ሰይፉ የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ እና ለታለመለት ደረጃ እንዲበቃ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡ 

ዘጋቢ ምህረት ስመኝ
ፎቶ ግራፍ አብዱራህማን ሃሰን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👍12🔥3
ክፍለጦሩ በሽብር ቡድኑ ላይ በወሰደው ጠንካራ እርምጃ በርካቶች ተደምስሰዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ ጋሻ ክፍለጦር በሰሜን ሽዋ ዞን አቦቴ ወረዳ በአለቆች ቀሬ እና በያያ ማርያም ቀበሌዎች ሲንቀሳቀስ በነበረው አሸባሪ የሸኔ ቡድን ላይ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ የጦር መሳሪያና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክፍለጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ጌትነት ተድላ ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ ራሱን የህዝብ ነፃ አውጭ ነኝ በማለት እየነገደና አሉባልታ እየነዛ ህዝቡን ለአመታት እረፍት በመንሳት ሃብትና ንብረቱን ሲዘርፍ የቆየ መሆኑን አንስተው አሁን ላይ በተወሰደበት እርምጃ ተደምስሷል ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምበት የቆየው መሳሪያ እና ተተኳሽ እንዲሁም የወገብ ትጥቅ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልፀዋል።  ዘጋቢ ውበቴ አማረ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39👍12🔥3