FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነትና ስጋት ለመቀነስ ንቃተ ህሊናን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨባጫ ሥልጠና የሰጡት የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬተር ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ ደመቀ ሳይበር ለሠራዊቱ ግዳጅና ለኦፕሬሽን ስራ ወሳኝ ከመሆኑም በላይ በተቃራኒው ደግሞ ጉዳት እንዳለውም አሥረድተዋል።

የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነትና ስጋት ለመቀነስና ጥቃቶችን ለመከላከል የሠራዊቱን ንቃተ ህሊና ማሳደግና ተቋማዊ የሳይበር ደህንነት አቅምን ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በአሁን ወቅት ውጊያው በቀጥታ ግንባር ለግንባር በመገናኘት ብቻ ሳይሆን በግንኙነት መረቦች በተለያየ መንገድ እንደሚካሄድ ያብራሩት ዳይሬክተሩ በሶሻል ሚዲያ ስነ-ልቦናን ለመጉዳት የሚሰራው የፕሮፖጋንዳ ስራ አንዱ የጠላት ሴራ በመሆኑ ሠራዊቱ በሳይበር ደህንነት ላይ ባቂ ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባም አመላክተዋል።

የተቋሙን የመረጃ መሰረተ ልማቶችንና ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን ከሳይበር ጥቃት መከላከል የሚያስችል አቅም መገንባቱን እና ይህ ተግባርም ተጠናሮ እንደሚቀጥል የገለፁት ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጀ ደመቀ ከየትኛውም አቅጣጫ በሠራዊቱ ላይ የሚካሄድ የዋልፌር ጦርነትን በተገቢው መንገድ ለመመከት  የሠራዊቱን አቅም ላማሳደግም ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቀዋል፡፡ ዘገባው የአብዱራህማን ሀሰን ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32👍12🔥3
ዘላቂ ሰላም ለማፅናት ታሳቢ ያደረገ ውይይት ተካሄደ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ አንድ ኮር ዘላቂ ሰላም ለማፅናት በጋራ እንተጋለን በሚል መሪ ሃሳብ ከሰሜን ሽዋ ዞን ከአቦቴ  ወረዳ አባ ገዳዎች የሃገር ሽማግሌዋች እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ህዝባዊ ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱን የመሩት የኮሩ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጋዲሳ ዲሮ ለሃገር ሰላምና ደህንነት የህዝቦች ተሳትፎ የጎላ በመሆኑ ሃገራችንና ህዝቦቿን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪና ፅንፈኛ ሀይሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት የአባ ገዳዎች የሃገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ምክትል አዛዡ በወረዳው የተገኘውን ሰላም ለማስጠበቅ በቁርጠኝነት መታገል የእያንዳንዱ ሰው ሃላፊነት መሆኑን ማወቅ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የአቦቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አሸብር ሂደቡ በበኩላቸው ሠራዊቱ የህይወት መሰዋዕትነት እየከፈለ ለሃገር ሰላምና ለህዝቦች ነፃነት እያደረገ ያለው ቁርጠኝነት የሚመሰገን መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ከሠራዊቱ ጎን ተሠልፈው አሥፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ዘጋቢ ውበቴ አማረ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍6🔥2
ንብ የእግር ኳስ ክለብን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ለማሣደግ እንደሚሠራ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

የአየር ሃይል ንብ እግር ኳስ ክለብ አመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን የቦርዱ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አካሂዷል፡፡

የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአቪየሽን ከበድ ጥገና ማዕከል ሃላፊ እና የንብ እግር ኳስ ክለብ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መሰረት ጌታቸው የንብ እግር ኳስ ክለብ ከፕሪሚየር ሊግ እስከ ብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ  ተጫዋቾችን ያፈራ መሆኑን ተናግረዋል።

ክለቡ ለውድድር በተጓዘበት ቦታ ሁሉ የሠራዊታችን መለያ የሆነውን ህዝባዊነት እና ስፖርታዊ ጨዋነትን በመላበስ በዲሲፕሊን ከተመልካች ጋር መልካም ግንኙነት በመፍጠር በከፍተኛ ሊጉ ስኬታማ የውድድር አመት ማሳለፍ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በጉባኤው በበጀት አመቱ የንብ እግር ኳስ ቡድን የነበሩ እንቅስቃሴዎች እና የስራ አፈፃፀም ዝርዝር ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ሪፖርት በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ በቀጣይ በ2018 በጀት አመት ንብ እግር ኳስ ክለብን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለማሳደግ እንዲሁም ተተኪ ተጫዋቾችን በመለየት እና በማብቃት ቡድኑ የተሳካ የውድድር ዘመን እንዲያሳልፍ እቅድ አስቀምጧል፡፡ 
  
የአየር ኃይል ንብ እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በሜዳና ከሜዳ ውጭ ባደረጋቸው ግጥሚያዎች በአመቱ በ40 ነጥብ እና 11 ንፁህ ጎል በመሰብሰብ በምድቡ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው፡፡

በእለቱም ለንብ እግር ኳስ ክለብ ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት የትጥቅ ስጦታ በምክትል ፕሬዘዳንቱ ተበርክቷል፡፡

ዘጋቢ እሱያውቃል ሙሉየ
ፎቶ ግራፍ ባጫ ለገሰ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
49👍14🔥4
የኢትዮ-ጂቡቲ የጋራ መከላከያ ኮሚቴ 11ኛ ስብሰባውን ማካሔድ ጀመረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እና የጂቡቲ የጋራ መከላከያ ኮሚቴ 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እያካሔደ ነው።

ስብሰባው እየተካሔደ ያለው የመከላከያ ውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹና የጂቡቲ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ ኮሎኔል ማጆር (ሜጄር ጄነራል) አብዱረህማን አብዲ በተመራ ወታደራዊ ልዑካን መካከል ነው።

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያላቸው ሀገሮች መሆናቸውን የገለፁት ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹ ለልዑካን ቡድኑ ሁለተኛ ሀገራችሁ ወደሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጣችሁ ብለዋል። 

የጂቡቲ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ ኮሎኔል ማጆር (ሜጄር ጄነራል) አብዱረህማን አብዲ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል።

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አታሼ ሜጄር ጄነራል ተስፋዬ ወልደማርያም በተገኙበት መድረክ ዛሬ መካሔድ የጀመረው ውይይት ሀገራቱ በ10ኛው የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ በተስማሙባቸው አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ነው።

ስብሰባው የሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡት የሰላምና ደህንነት ስራዎች አፈፃፀም መሠረት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ለወደፊት  በሚሰሩ ስራዎች ላይም አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል።

ይህ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ በየጊዜው የሚካሄድ ሲሆን፣ በሁለቱ ወንድማማች አገሮች መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት እና ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ዘጋቢ አብዮት ዋሚ 
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28👍10🔥2👏2