FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ለተዋጊ ክፍሎች ያልተቋረጠ የጥገና አገልግሎት እየሰጠ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

በጎጃምና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ፅንፈኛውን በማፅዳት ዘመቻ ላይ ተልዕኮዉን እየፈፀመ የሚገኘው የዕዙ ሜንቴናንስ መምሪያ ለኮሮችና ድጋፍ ሰጭ ሀይሎች አስፈላጊውን ጥገና እየሠጠ ይገኛል፡፡

በምስራቅ ዕዝ የባህርዳር ሜንቴናንስ አስተባባሪ ሌተናል ኮሎኔል ጀምበሬ በቀለ፣ በክፍሉ ዘርፈ ብዙ ስራ እየተከናወን መሆኑን ገልፀዋል።

ተሽከርካሪዎች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የመከላከል ስራ፣ የነፍስ ወከፍ፣ የቡድን መሳሪያዎችንና ብልሽት ያጋጠማቸውን የመጠገን ስራ መሠራቱን ተናግረዋል።

ሁሉም ኮሮች ባሉበት የግዳጅ ቀጠና ሙያተኞችን በመላክ ግዳጁ ያለምንም እንከን ሳይቆራረጥ እንዲወጡና የተኩስ አቅማቸው ይበልጥ እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን እና ወደፊትም እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የፈጠራ አቅም በመጨመር የተለያዩ የመሳሪያ ክፍሎች ሞደፊክ በመስራት የተገኘውን መለዋወጫ በቁጠባ ለተገቢው ተሽከርካሪና መሳሪያ እየዋለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዘጋቢ ታደሰ ይሴ
ፎቶ ግራፍ  ማሩፍ ደስታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28👍13🔥3
የምዕራብ ዕዝ አመራሮች በነቀምት ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን ሆስፒታል ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

በምስራቅ ወለጋ ዞን በነቀምት ዙሪያ ጉቴ ከተማ በመከላከያ መሃንዲስ እየተገነባ የሚገኘውን የምዕራብ ግንባር የሠራዊት ሆስፒታልን የግንባታ ሂደት የምዕራብ ዕዝ አመራሮች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ እየተገነባ የሚገኘው የምዕራብ ግንባር ሠራዊት ሆስፒታል አሁን ያለበት ሁኔታ በጣም ጥሩ በሆነ ሁኔታ ላይ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ግንባታው ሲጠናቀቅ ለሰራዊቱና ለቤተሰቡ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ለአካባቢው ህብረተሰብም ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑን በጎብኝታቸው ተናግረዋል።

በ13.9 ሄክታር ላይ ያረፈውና ጥር ወር 2016 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ምዕራብ ግንባር የሠራዊት ሆስፒታል ጥር 2019 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ውል የተያዘ ሲሆን ከተባለው ጊዜ ቀድሞ ለመጨረስ በፍጥነትና በጥራት እየተሠራ ሰለመሆኑ ደግሞ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል ኢንጂነር ፍቃዱ ያዘው ተናግረዋል።

እየተገነባ የሚገኘው ምዕራብ ግምባር የሠራዊት ሆስፒታል ከ400 በላይ አልጋዎችን የሚይዝ የመሰብሰቢያ አዳራሽና የሎጂስቲክስ ስቶሮችን ያካተተ ክሊኒክን ጨምሮ ሁሉንም መሠረተ ልማቶች ያሟላና ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ የተናገሩት ሌተናል ኮሎኔል ኢንጂነር ፍቃዱ ያዘው የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በኮንስትራክሽን መምሪያ ሙያተኞች የቁፋሮ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ገልፀዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶ ግራፍ አከለ አባተ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍13🔥2🤔1
           አባይ የዘመን መብራት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

ብርቱ እጆች ውሃን ይገራሉ፣ አስፈሪ ማዕበልን ያስታግሳሉ፤ ተጓዡን ያሳርፋሉ፤ ብርቱ እጆች ነገን ይተነብያሉ፤ ዛሬ ላይ ሆነው ስለ ነገ ይሠራሉ፤ ዘመናቸውን ያሳምራሉ፤ የልጅ ልጆቻቸውን እጣ ፋንታ ብሩህ ያደርጋሉ።

ብርቱ እጆች ተፈጥሮን ያስጌጣሉ፤ በላባቸውና በደማቸው የከበረ ታሪክን ይፅፋሉ ፤ዘመናት አልፈው ዘመናት በተተኩ ቁጥር የማይናወጥ የታሪክ ሃውልት ያቆማሉ፤ ለታላቅነታቸው ህያው አሻራ ያኖራሉ።ብርቱ እጆች ተባብረው ይሰራሉ፤የሚገፋቸውን ይጥላሉ፣ የሚተናኮላቸውን ይቀጣሉ፤የስልጣኔን ጎዳና ያሳምራሉ፣

አንድነት ታሪክ ይሠራል፤አንድነት ሉአላዊነትን ያስከብራል፤ አንድነት ነፃነትን ያፀናል ፤ከነ ክብርና ከነ ኩራት ያስቀምጣል፤ ኢትዮጵያዊያን በአንድነታቸው እንደ አለት የጠጠረ ነፃነት አኑረዋል፤ በእሳት የታጠረች ሃገር አቆይተዋል፤ በታሪክ የከበረች ምድር ለልጅ ልጅ አስረክበዋል፤ ታሪክ በደማቅ ቀለም የፃፈው አሻራ ከትበዋል፤ በአንድነት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ደርሰዋል፤ የጭንቅ ቀን መሻገሪያዎች ሆነዋል።

በረጅሙ ዘመናት የሠሯቸው አኩሪ ታሪኮቻቸው ሁሉ የአንድነት ውጤቶች ናቸው፤ አንድ ሆነው የሰሯቸው፣ አንድ ሆነው ያበጇቸው፣አንድ ሆነው ያስጌጧቸው፣እነሆ በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የረቀቀ አሻራ አሳርፈዋል፤ የከበረ ታሪክ ፅፈዋል፤ ስለምን ቢባል አንድነት ጠፋ በተባለበት የኢትዮጵያዊያን የኖረ ብርታት ማሸሸ እየተባለ በሚታማበት ዘመን አንድነታቸውን አጠናክረው የቆየውን መንፈስ ተላብሰው ለዘመናት የፈሰሰን ውሃ ገድበዋልና ነው።

አንድ የሆኑ እጆች አስበው የሰሩት፣ዘመን የሚገለፅበት አድርገው ያረቀቁት፣ታላቁ አባይ ከጥቂት ወራት በኋላ ይመረቃል፤ አዎ አባይ የኢትዮጵያዊያን ተስፋ ነው፤አባይ የኢትዮጵያ ኩራት ነው፤አባይ የኢትዮጵያ ሌላኛው ጌጥ ነው፤ አባይ አንድነት የሚሰበክበት ሃውልት ነው፤አባይ መተሳሰብ የሚነገርበት የፍቅር ማዕድ ነው፤አባይ ለኢትዮጵያዊያን ከወንዝነት የተሻገረ ከግድብ ያለፈ ህያው ምልክት ነው።

ታዲያ ጀግናው ሠራዊታችንም ይህን የኢትዮጵያዊያንን ተስፋ የዚያን ተሰፋና የስራ ቦታ ሰላም ለማስጠበቅ ሳይታክት እየተጋ ይገኛል። የአካባቢው የሙቀት መጠን እንኳንስ አቀበትና ቁልቁለቱን ወጥተው ወርደውበት አይደለም ለአፍታ ቁጭ ሲሉ ላብ እንደ ጎርፍ ሲወርድ ጊዜ አይወስድም።

በተለይ ደግሞ ከግድቡ በጣም በራቀ መልኩ ረጃጅም የአሰሳና የቅኝት ስራዎችን ያለማቋረጥ ዘወትር ተግባሩ የሆነው ሠራዊታችን ታላቁ ግድቡን በአሻጋሪ እያየ የህዝቡ ተስፋ ሲደክሙ ብርታት ሆኖት ሳይሠንፍ በትጋት የሃገሩን ተስፋና ህዳሴ በፅናት እየጠበቀ ይገኛል።

ሠራዊታችን የህዝቡን አደራ በመጠበቁ በኩል ያሳደገው አሠራርና ህዝባዊነት ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል። ሠራዊቱ ሁሌም ለቃሉ ይኖራል። አባይ የሁላችንም የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ነው በመሆኑም ከጉባ ሰማይ ስር ከአባይ ጋር አብሮ ይኖራል።

በውብሊቀር ደስያለው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
43👍20🔥4🍌4
የሚሰጠውን ግዳጅ በድል መወጣት የሚችል አዋጊና ተዋጊ ሠራዊት ተገንብቷል።
   የኮር እና የክፍለጦር አመራሮች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

የሚሰጠውን ማንኛውንም ውስብስብና ፈተኝ ግዳጆች በድል መወጣት የሚችል ሠራዊት ተገንብቷል ሲሉ የስድስተኛ ዕዝ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ሃብታሙ ምህረቴ ተናገሩ።

የዕዙ የሠራዊት አባላት በውስብስብ ሁኔታዎች ሳይበገር ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮዎች በጀግንነት፣ በውጤታማነትና በድል እየተወጣ የህብረተሰቡን ሰላም እያረጋገጠ ይገኛል ያሉት አመራሮቹ በተደረጉ የስምሪት ስራዎች የላቀ ውጤት ማስመዝገቡንና አስደናቂ ገድሎች መፈፀማቸውን አውስተዋል።

ሠራዊቱ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በተደረጉ ሰፋፊና ተከታታይ ህዝባዊ መድረኮች አሸባሪው የሸኔ ቡድን እና ፅንፈኛው  ፈጥረውት የነበረውን ችግር ማጥራት የተቻለ መሆኑን ተናግረዋል።

የዕዙ አባላት ሞራላዊና ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነት የመገንባት ፣ የአሃዱዎችን ግዳጅ የመፈፀም እና የማድረግ አቅሞች  የማሳደግ ፣በየደረጃዉ የሚገኙ አመራሮችን ዙሪያ-መለስ የመምራት አቅም የማጎልበት እንዲሁም የተለያዩ ሙያተኞችን በየተመደቡበት ዘርፍ ሙያዊ ብቃታቸዉን የማሳደግ ስራ በስፋት መሠራቱን ገልፀዋል።

ስልጠናዎችም የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደቱን መነሻ በማድረግ ከውጊያ ፅንሰ-ሃሳብ ጀምሮ እስከ አሃድ መምራትና ለዉጊያ ማዘጋጀት እንዲሁም ግዳጅ ተኮር የስልጠና ስምሪት በማከናዎን ተደማሪ የማድረግ አቅሞችን ለመፍጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።


ዘጋቢ አዲሱ አራጋው
ፎቶግራፍ ሌሊሴ አራራሜ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍4129🔥5👏3
ዕዙ ተስፋ ሰጪ ውጤት የተገኘባቸውን የግብርና ልማቶች እንደሚያዘምን ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም

ተስፋ ሰጪ ውጤት የተገኘባቸውን የግብርና ልማት ስራዎች ማስፋትና ማዘመን ይገባል ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ከዕዙ ስታፍ መምሪያ ኃላፊዎች ጋር የግብርና ልማት እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ ያደረጉት አዛዡ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ለ2017/18 የምርት ዘመን ከ30 ሄክታር በላይ መሬት በበቆሎ ሰብል የተሸፈነውን ማሳ ተመልክተዋል። አንደተቋም የተጀመረው የግብርና ልማት ግብን ለማሳካት ዘርፉ የሚፈልገውን ክትትል ማድረግና ለውጤት ማብቃት እንደሚገባም አመላክተዋል።

የዕዙ ግብርና ልማት በአጭር ጊዜ ውጤታማ ከሆነባቸው የግብርና ልማት ስራዎች አንዱ የሆነውን የዶሮ እርባታ ጣቢያንም አዛዡ  ጎብኝተዋል። በአሁኑ ጊዜ  አንድ ሺህ ዘጠና አራት በሚሆኑ የእንቁላል ዶሮዎች አማካኝነት በሳምንት ከ6 ሺህ በላይ እንቁላል እንደሚገኝና  በተመጣጣኝ ዋጋም ለሠራዊቱ ፣ለሠራዊቱ ቤተሰብ፣ ለመዝናኛ ክበብና ለደረጃ ሶስት ሆስፒታል በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ በግብርና ባላሟያዎች ገለፃና ማብራሪያ ተደርጓል።

የዶሮ እርባታ ፕሮጀክቱን በሁለት እጥፍ ለማሳደግ የተሰጠውን አቅጣጫ ተግባራዊ በማድረጉ ረገድ የግብርና ልማት ጥረት አበረታች መሆኑን የተናገሩት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ  ግንባታው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባና የሌማት ትሩፋት ዕቅዱን ማሳካት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በዕዙ የግብርና ልማት እንቅስቃሴ ዙሪያ የመስክ ምልከታ ያደረጉት አዛዡ  ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ እንደተቋም የተጀመረውን የግብርና ልማት ስኬታማ ለማድረግ በሁሉም አቅጣጫ ያሉ የግብርና ልማት ስራዎችን ክትትል ማድረግ ይገባልም ብለዋል።

በሌላም በኩል ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል ተገኝቸው ታካሚዎችን ጎብኝተዋል አበረታትተዋልም።

በህክምና ላይ ለሚገኙ ታካሚዎችም መልካም ጤንነትን ተመኝተው አገግመው ወደ እናት ክፍላቸው እንደሚመለሱም ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል።
ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2523🔥3