በመስዋዕትነታችን ለመጪው ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን እናወርሳለን።
ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
በመስዋዕትነታችን ለመጪው ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን እናወርሳለን ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።
ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ከጠቅላይ መምሪያው ስታፍ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ብዙ ተስፋዎች ያሏትና በፈተና ውስጥ ሆና የዕድገትና የልማት ግስጋሴዋን ማስቀጠል የቻለች ጠንከራ ሃገር ናት ብለዋል።
ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ህልውና የምንከፍለው መስዋዕትነት ለመጪው ትውልድ የበለፀገች ሀገር የማውረስ መሠረት ነው ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ የጠላቶቻችን ፍላጎት በሠራዊታችን ብርቱ ክንድና በሠላም ወዳዱ ህዝባችን ድጋፍ ከሽፏልም በማለት ተናግረዋል።
ከሃገራዊ ለውጡ በኋላ በተቋማችን የተካሄደው ሪፎርም ለምንምና ለማንም የማይበገር ጠንካራ፣ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነ፣ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊሰነዘር የሚችል ጥቃትን መመከት የሚችልና ከዘመኑ ጋር እየዘመነ የሚሄድ ፕሮፌሽናል ሠራዊት እየተገነባ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
እኛ የህገ -መንግስቱ አስተማማኝ ዘብ ነን ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ መንግስታችን የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት ማንኛውንም መስዋዕትነት ሁሉ ከፍለን ለማሳካት ዝግጁነታችን ከመቼውም ጊዜ የላቀ ነው ብለዋል።
ህዝብ ጠል የሆኑት ዘራፊው ቡድንና ኦነግ ሸኔ እንዲሁም ፅንፍ የያዘው የህወሃት ቡድን የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፈው የሰጡ ከሃዲያን ናቸው ያሉት አዛዡ ድብቅ አጀንዳቸው መቼም ቢሆን እንደማይሳካ አስረድተዋል።
ሰሜን ምዕራብ ዕዝ የፅንፈኛው ህልውና እንዲያከትም ግዳጁን በድል አድራጊነት እየተወጣ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ለተልዕኮው መሳካት የጠቅላይ መምሪያው ድጋፍ ሰጪ ስታፍ ሚና የሚያኮራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
ዕዙ በጠንካራና አስተማማኝ ድጋፍ ሰጪ ስታፍ መገንባቱን ገልፀው ክፍተቶቻችሁን በመሙላት ለሠራዊቱ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠት ተግባራችሁን በቀጣይም አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል ። ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤34👍13🔥2
የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ለተዋጊ ክፍሎች ያልተቋረጠ የጥገና አገልግሎት እየሰጠ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
በጎጃምና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ፅንፈኛውን በማፅዳት ዘመቻ ላይ ተልዕኮዉን እየፈፀመ የሚገኘው የዕዙ ሜንቴናንስ መምሪያ ለኮሮችና ድጋፍ ሰጭ ሀይሎች አስፈላጊውን ጥገና እየሠጠ ይገኛል፡፡
በምስራቅ ዕዝ የባህርዳር ሜንቴናንስ አስተባባሪ ሌተናል ኮሎኔል ጀምበሬ በቀለ፣ በክፍሉ ዘርፈ ብዙ ስራ እየተከናወን መሆኑን ገልፀዋል።
ተሽከርካሪዎች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የመከላከል ስራ፣ የነፍስ ወከፍ፣ የቡድን መሳሪያዎችንና ብልሽት ያጋጠማቸውን የመጠገን ስራ መሠራቱን ተናግረዋል።
ሁሉም ኮሮች ባሉበት የግዳጅ ቀጠና ሙያተኞችን በመላክ ግዳጁ ያለምንም እንከን ሳይቆራረጥ እንዲወጡና የተኩስ አቅማቸው ይበልጥ እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን እና ወደፊትም እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የፈጠራ አቅም በመጨመር የተለያዩ የመሳሪያ ክፍሎች ሞደፊክ በመስራት የተገኘውን መለዋወጫ በቁጠባ ለተገቢው ተሽከርካሪና መሳሪያ እየዋለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ ታደሰ ይሴ
ፎቶ ግራፍ ማሩፍ ደስታ

❤28👍13🔥3
የምዕራብ ዕዝ አመራሮች በነቀምት ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን ሆስፒታል ጎበኙ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
በምስራቅ ወለጋ ዞን በነቀምት ዙሪያ ጉቴ ከተማ በመከላከያ መሃንዲስ እየተገነባ የሚገኘውን የምዕራብ ግንባር የሠራዊት ሆስፒታልን የግንባታ ሂደት የምዕራብ ዕዝ አመራሮች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ እየተገነባ የሚገኘው የምዕራብ ግንባር ሠራዊት ሆስፒታል አሁን ያለበት ሁኔታ በጣም ጥሩ በሆነ ሁኔታ ላይ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ግንባታው ሲጠናቀቅ ለሰራዊቱና ለቤተሰቡ ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ለአካባቢው ህብረተሰብም ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑን በጎብኝታቸው ተናግረዋል።
በ13.9 ሄክታር ላይ ያረፈውና ጥር ወር 2016 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ምዕራብ ግንባር የሠራዊት ሆስፒታል ጥር 2019 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ውል የተያዘ ሲሆን ከተባለው ጊዜ ቀድሞ ለመጨረስ በፍጥነትና በጥራት እየተሠራ ሰለመሆኑ ደግሞ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል ኢንጂነር ፍቃዱ ያዘው ተናግረዋል።
እየተገነባ የሚገኘው ምዕራብ ግምባር የሠራዊት ሆስፒታል ከ400 በላይ አልጋዎችን የሚይዝ የመሰብሰቢያ አዳራሽና የሎጂስቲክስ ስቶሮችን ያካተተ ክሊኒክን ጨምሮ ሁሉንም መሠረተ ልማቶች ያሟላና ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ የተናገሩት ሌተናል ኮሎኔል ኢንጂነር ፍቃዱ ያዘው የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በኮንስትራክሽን መምሪያ ሙያተኞች የቁፋሮ ስራው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ገልፀዋል።
ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶ ግራፍ አከለ አባተ

❤30👍13🔥2🤔1
አባይ የዘመን መብራት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
ብርቱ እጆች ውሃን ይገራሉ፣ አስፈሪ ማዕበልን ያስታግሳሉ፤ ተጓዡን ያሳርፋሉ፤ ብርቱ እጆች ነገን ይተነብያሉ፤ ዛሬ ላይ ሆነው ስለ ነገ ይሠራሉ፤ ዘመናቸውን ያሳምራሉ፤ የልጅ ልጆቻቸውን እጣ ፋንታ ብሩህ ያደርጋሉ።
ብርቱ እጆች ተፈጥሮን ያስጌጣሉ፤ በላባቸውና በደማቸው የከበረ ታሪክን ይፅፋሉ ፤ዘመናት አልፈው ዘመናት በተተኩ ቁጥር የማይናወጥ የታሪክ ሃውልት ያቆማሉ፤ ለታላቅነታቸው ህያው አሻራ ያኖራሉ።ብርቱ እጆች ተባብረው ይሰራሉ፤የሚገፋቸውን ይጥላሉ፣ የሚተናኮላቸውን ይቀጣሉ፤የስልጣኔን ጎዳና ያሳምራሉ፣
አንድነት ታሪክ ይሠራል፤አንድነት ሉአላዊነትን ያስከብራል፤ አንድነት ነፃነትን ያፀናል ፤ከነ ክብርና ከነ ኩራት ያስቀምጣል፤ ኢትዮጵያዊያን በአንድነታቸው እንደ አለት የጠጠረ ነፃነት አኑረዋል፤ በእሳት የታጠረች ሃገር አቆይተዋል፤ በታሪክ የከበረች ምድር ለልጅ ልጅ አስረክበዋል፤ ታሪክ በደማቅ ቀለም የፃፈው አሻራ ከትበዋል፤ በአንድነት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ደርሰዋል፤ የጭንቅ ቀን መሻገሪያዎች ሆነዋል።
በረጅሙ ዘመናት የሠሯቸው አኩሪ ታሪኮቻቸው ሁሉ የአንድነት ውጤቶች ናቸው፤ አንድ ሆነው የሰሯቸው፣ አንድ ሆነው ያበጇቸው፣አንድ ሆነው ያስጌጧቸው፣እነሆ በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የረቀቀ አሻራ አሳርፈዋል፤ የከበረ ታሪክ ፅፈዋል፤ ስለምን ቢባል አንድነት ጠፋ በተባለበት የኢትዮጵያዊያን የኖረ ብርታት ማሸሸ እየተባለ በሚታማበት ዘመን አንድነታቸውን አጠናክረው የቆየውን መንፈስ ተላብሰው ለዘመናት የፈሰሰን ውሃ ገድበዋልና ነው።
አንድ የሆኑ እጆች አስበው የሰሩት፣ዘመን የሚገለፅበት አድርገው ያረቀቁት፣ታላቁ አባይ ከጥቂት ወራት በኋላ ይመረቃል፤ አዎ አባይ የኢትዮጵያዊያን ተስፋ ነው፤አባይ የኢትዮጵያ ኩራት ነው፤አባይ የኢትዮጵያ ሌላኛው ጌጥ ነው፤ አባይ አንድነት የሚሰበክበት ሃውልት ነው፤አባይ መተሳሰብ የሚነገርበት የፍቅር ማዕድ ነው፤አባይ ለኢትዮጵያዊያን ከወንዝነት የተሻገረ ከግድብ ያለፈ ህያው ምልክት ነው።
ታዲያ ጀግናው ሠራዊታችንም ይህን የኢትዮጵያዊያንን ተስፋ የዚያን ተሰፋና የስራ ቦታ ሰላም ለማስጠበቅ ሳይታክት እየተጋ ይገኛል። የአካባቢው የሙቀት መጠን እንኳንስ አቀበትና ቁልቁለቱን ወጥተው ወርደውበት አይደለም ለአፍታ ቁጭ ሲሉ ላብ እንደ ጎርፍ ሲወርድ ጊዜ አይወስድም።
በተለይ ደግሞ ከግድቡ በጣም በራቀ መልኩ ረጃጅም የአሰሳና የቅኝት ስራዎችን ያለማቋረጥ ዘወትር ተግባሩ የሆነው ሠራዊታችን ታላቁ ግድቡን በአሻጋሪ እያየ የህዝቡ ተስፋ ሲደክሙ ብርታት ሆኖት ሳይሠንፍ በትጋት የሃገሩን ተስፋና ህዳሴ በፅናት እየጠበቀ ይገኛል።
ሠራዊታችን የህዝቡን አደራ በመጠበቁ በኩል ያሳደገው አሠራርና ህዝባዊነት ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል። ሠራዊቱ ሁሌም ለቃሉ ይኖራል። አባይ የሁላችንም የጋራ መግባቢያ ቋንቋ ነው በመሆኑም ከጉባ ሰማይ ስር ከአባይ ጋር አብሮ ይኖራል።
በውብሊቀር ደስያለው

❤43👍20🔥4🍌4