FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዕዙ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ከምንጊዜውም በላይ በውጤታማነት እየተወጣ ይገኛል።
     ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

የምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በዕዙ ጠቅላይ መምሪያ የበጀት ዓመቱን እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ማጠቃልያ ላይ የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት የውስጥም ሆነ የውጭ ፀረ-ሰላም ሃይሎችን በመደምሰስ አንፀባራቂ ድል ከማስመዝገብ የሚያግደን ሃይል አለመኖሩን በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን ብለዋል።

ሠራዊቱ እንደባለፉት ጊዜያቶች ሁሉ የተሰጠውን ትልቅ ሃገራዊ ግዳጅ ውጤታማ በሆነ መልኩ እየፈፀመ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው ለተልዕኮው ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራት የበለጠ ድል ማስመዝገብ የሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

ሠራዊታችን በተሰማራበት ቀጠና በሽብርተኝነት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሃገራችን የሰላም ማነቆ እየሆኑ ያሉ ፅንፈኛ ሃይሎችን ዳግም የህዝባችን ስጋት እንዳይሆኑ ለማድረግ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ጄኔራል መኮንኑ ተናግረዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሠረት በቀጠናው የፅንፈኛውን እና የአሸባሪውን የሸኔ ቡድን በመደምሰስ ያሳካናቸውን ድሎች አቅበን የህዝባችንን ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ መስራትና ከአካባቢው የመስተዳደር አካላት ፣ የፀጥታ ሃይሎች ፣ ከሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጋር በመቀናጀት ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥና ዋስትና ሆኖ መቀጠላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዕዙ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሰረተ ድንጋይ ከተቀመጠበት ዕለት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ዋዜማ ድረስ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን መደረጉ የሠራዊታችንን ጥንካሬ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከህዝባችን ጋር ያለንን የሰላም እና የልማት ትስስር ይበልጥ አጠናክረን በመቀጠል የኢትዮጵያን ሰላም እና አንድነት አስጠብቀን ማቆየት አለብንም ብለዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶ ግራፍ ሽመልስ እሸቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
46👍16🔥4
ምዕራብ ዕዝ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አሥጀመረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች በምስራቅ ወለጋ ዞን በነቀምት ከተማ በመከላከያ መሃንዲስ በመሰራት ላይ በሚገኘው በምዕራብ ግንባር  የሠራዊት ሆስፒታል " በመትከል ማንሰራራት" የሚለውን ሀገራዊ መሪ ሀሳብ መሰረት በማድረግ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ፤ ምክትል አዛዦች እንዲሁም የኮር እና ክፍለጦር አመራሮች የስታፍ የክፍል ሃላፊዎች በተገኙበት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

በመርሃ - ግብሩ ላይ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ፣ የተፈጥሮ ሥነ ምህዳር ችግሮችን ለመቅረፍ እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከፍተኛ ለውጥ እያስገኘ መሆኑን አመላክተው ችግኝ መትከል ህይወትን ማፅናት ነው ብለዋል።

‎ስለሆነም የችግኞች መኖር ለሰው ልጅ ህይወትና ስነ ምህዳር መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ተቋም በተሰራው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ስራ ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን ማምጣት የተቻለ ሲሆን በዚሁ ዕለት የተጀመረውን የችግኝ ተከላ ስራ ማስቀጠል፣ መንከባከብ፣ ማጠርና በሚገባ እንዲያድጉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ዛሬ  ለዕዛችን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኝ እንድንተክል በሁሉም የግዳጅ ቀጠናችን የተሰጠን በመሆኑ ዛሬ በይፋ ስንጀምር የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በኮሮችና በክፍለጦሮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶ ግራፍ አከለ አባተ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
45👍17🔥5
ጤና ይሥጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ የነርቭ ህመም  ዋና ዋና ምልክቶች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

መደንዘዝ  ፦ ነርቮች መጎዳታቸውን የምናውቅበት የመጀመሪያው ምልክት የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት በእጅ፣ በጣት፣ በእግር፣ እና በእግር ጣቶች ላይ ሲፈጠር ነው። ስሜታዊ ነርቮች ስራቸው የስሜት መልእክት መላክ ሲሆን ጉዳት ሲያጋጥማቸው ቆይቶ ወደ መደንዘዝ የሚቀየር የመውረር ስሜት ይሰማናል።

በጊዜው ተገቢ ህክምና ካላገኘ ይህ ስሜት ወደ ሌሎች የሰውነት አካሎች ሊዛመት ይችላል። እጅ እና እግር ላይ ለሚፈጠር የመደንዘዝ ስሜት ሌሎች መንስኤዎች፡- እግር እና እጅ ላይ የተፈጠረ ከፍተኛ ጫና፣ ለብርድ መጋለጥ፣ እንቅስቃሴ የሌለበት የአኗኗር ዘይቤ እና የቫይታሚን ቢ12 እና ማግኒዢየም እጥረት ናቸው።

ህመም
ሌላዉ የነርቭ ህመም ምልክት የሚሰነጥቅ ወይም የሚያቃጥል የህመም ስሜት ነው። የዚህ አይነት ስሜት እጅ እና እግር ላይ የሚፈጠር ሲሆን ከሌላ የህመም ስሜት ይለያል። ህመሙ የሚፈጠረው ስሜታዊ ነርቮች ላይ በተፈጠረ ጉዳት ነው። ስሜት በአግባቡ ከአእምሮ ወደ ቆዳ መተላለፍ ካልቻለ የተጎዳው ቦታ ላይ ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። ህመሙ በተጎዳው ቦታ ዙሪያ ብቻ ወይም ሰፊ የሰውነት ክልል ላይ ሊፈጠር ይችላል። ህመሙ ብዙ ጊዜ በምሽት ይባባሳል። ከነርቭ ጉዳት ውጪ የስኳር በሽታ፣ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ወይም የጀርባ አጥንት ሰረሰር ላይ የተፈጠረ ጉዳት ለከባድ ህመም ያጋልጠናል።

የጡንቻ ድካም
ጡንቻ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርገውን መልእክት በሚያስተላልፉ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ ድካም ይፈጥራል። አልፎም ጡንቻን የመቆጣጠር ችሎታ ሊያሳጣ ይችላል። ለጡንቻችን የሚላከው መልእክት በአግባቡ ካልተላለፈ መራመድ እንቸገራለን። በእጃችን እቃዎች ለማንሳት እና ጭብጥ አድርጎ መያዝ ይከብደናል። በነርቭ ጉዳት ምክንያት ጡንቻ ጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜ ሲቀንስ እራሱ እየደከመ ይመጣል። ጡንቻ መዳከም ከነርቭ ጉዳት ውጪ እንደ ፓርኪንሰን በሽታ፣ የዲስክ መንሸራተት፣ ስትሮክ የመሳሰሉ ህመሞች መንስኤ ይሆናሉ።

የጡንቻ መሸማቀቅ
የእንቅስቅሴ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ ሊያመጣ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ በራሱ የተጎዱት ነርቮች ላይ በሚፈጥረው እንቅስቃሴ ጉዳቱን ሊያባብስ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ የሚፈጠረው የእንቅስቃሴ ነርቮች በብዛት ሲሰሩ ነው። የመሸማቀቅ ስሜት ክብደቱ ቀላል፣ መካከለኛ ወይም በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል።

የላብ ችግር
አውቶኖሚክ ነርቮች ሲጎዱ የላብ ችግር ሊፈጥር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ላብ ሲፈጠር ሌሎች ላይ ደግሞ የላብ መቀነስ ይታያል። ላብ በአግባቡ ካልመነጨ ሰውነታችን ሙቀቱን በአግባቡ መቆጣጠር አይችልም። በከፍተኛ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ችግሩ ይገዝፋል።

ከባድ ራስ ምታት
የኤሌክትሪክ ንዝረት የሚመስል አጭር ጊዜ የሚቆይ ከባድ ራስ ምታት የነርቭ ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል።

የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር
የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር ወይም መንገዳገድ ሌላ የነርቭ ጉዳት ምልክት ነው። ወድቀው ሊጎዱ ስለሚችሉ ይህን ምልክት ችላ ማለት የለብዎትም። የነርቭ ጉዳት አእምሮ የሰውነትን እንቅስቃሴ በአግባቡ እንዳይቆጣጠር ያደርጋል። ይህ ሁኔታ ወድቀው እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል። የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር የፓርኪንሰን ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
41👍8🔥3
በመስዋዕትነታችን ለመጪው ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን እናወርሳለን።
     ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

በመስዋዕትነታችን ለመጪው ትውልድ የበለፀገች ኢትዮጵያን እናወርሳለን ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ከጠቅላይ መምሪያው ስታፍ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ብዙ ተስፋዎች ያሏትና በፈተና ውስጥ ሆና የዕድገትና የልማት ግስጋሴዋን ማስቀጠል የቻለች ጠንከራ ሃገር ናት ብለዋል።

ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ ህልውና የምንከፍለው መስዋዕትነት  ለመጪው ትውልድ የበለፀገች ሀገር የማውረስ መሠረት ነው ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ የጠላቶቻችን ፍላጎት በሠራዊታችን ብርቱ ክንድና በሠላም ወዳዱ ህዝባችን ድጋፍ ከሽፏልም በማለት ተናግረዋል።

ከሃገራዊ ለውጡ በኋላ በተቋማችን የተካሄደው ሪፎርም ለምንምና ለማንም የማይበገር ጠንካራ፣ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆነ፣ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊሰነዘር የሚችል ጥቃትን መመከት የሚችልና ከዘመኑ ጋር እየዘመነ የሚሄድ ፕሮፌሽናል ሠራዊት እየተገነባ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

እኛ የህገ -መንግስቱ አስተማማኝ ዘብ ነን ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ መንግስታችን የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት ማንኛውንም መስዋዕትነት ሁሉ ከፍለን ለማሳካት ዝግጁነታችን ከመቼውም ጊዜ የላቀ ነው ብለዋል።

ህዝብ ጠል የሆኑት ዘራፊው ቡድንና ኦነግ ሸኔ እንዲሁም ፅንፍ የያዘው የህወሃት ቡድን የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፈው የሰጡ ከሃዲያን ናቸው ያሉት አዛዡ ድብቅ አጀንዳቸው መቼም ቢሆን እንደማይሳካ አስረድተዋል።

ሰሜን ምዕራብ ዕዝ የፅንፈኛው ህልውና እንዲያከትም ግዳጁን በድል አድራጊነት እየተወጣ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ለተልዕኮው መሳካት የጠቅላይ መምሪያው ድጋፍ ሰጪ ስታፍ ሚና የሚያኮራ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

ዕዙ በጠንካራና አስተማማኝ ድጋፍ ሰጪ ስታፍ  መገንባቱን ገልፀው ክፍተቶቻችሁን በመሙላት ለሠራዊቱ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠት ተግባራችሁን በቀጣይም አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል ። ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👍13🔥2
የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ለተዋጊ ክፍሎች ያልተቋረጠ የጥገና አገልግሎት እየሰጠ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

በጎጃምና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ፅንፈኛውን በማፅዳት ዘመቻ ላይ ተልዕኮዉን እየፈፀመ የሚገኘው የዕዙ ሜንቴናንስ መምሪያ ለኮሮችና ድጋፍ ሰጭ ሀይሎች አስፈላጊውን ጥገና እየሠጠ ይገኛል፡፡

በምስራቅ ዕዝ የባህርዳር ሜንቴናንስ አስተባባሪ ሌተናል ኮሎኔል ጀምበሬ በቀለ፣ በክፍሉ ዘርፈ ብዙ ስራ እየተከናወን መሆኑን ገልፀዋል።

ተሽከርካሪዎች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የመከላከል ስራ፣ የነፍስ ወከፍ፣ የቡድን መሳሪያዎችንና ብልሽት ያጋጠማቸውን የመጠገን ስራ መሠራቱን ተናግረዋል።

ሁሉም ኮሮች ባሉበት የግዳጅ ቀጠና ሙያተኞችን በመላክ ግዳጁ ያለምንም እንከን ሳይቆራረጥ እንዲወጡና የተኩስ አቅማቸው ይበልጥ እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን እና ወደፊትም እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የፈጠራ አቅም በመጨመር የተለያዩ የመሳሪያ ክፍሎች ሞደፊክ በመስራት የተገኘውን መለዋወጫ በቁጠባ ለተገቢው ተሽከርካሪና መሳሪያ እየዋለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዘጋቢ ታደሰ ይሴ
ፎቶ ግራፍ  ማሩፍ ደስታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28👍13🔥3