FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ የቀጠለ የአያሌ ዘመን ታሪክ ያላት ሃገር ናት
   ሌተናል ጀኔራል ሞሃን ሰብረማንያን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ኃይል አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሞሃን ሰበረማኒያን በዩናሚስ ሴክተር ኢስት ግዳጁን እየፈፀመ የሚገኘውን የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃን ጎብኝተዋል።

ሌተናል ጀኔራል ሞሃን ሰበረማኒያን በጉብኝታቸው ወቅትም ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ የቀጠለ የበርካታ አያሌ ዘመን ታሪክ ያላት ሃገር መሆኗን በመጥቀስ በተለይ በአለም ሰላም ማስከበር ሂደት ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ እንዳላት እና እሱን ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከአድዋ እስከ ካራ ማራ የዘለቀው የማይደበዝዘው አኩሪ ታሪክ የኢትዮጵያዊያን የጀግንነት ታሪክ ነው። ከዚህም ባለፈ በኮሪያ ምድር የተጀመረው የኢትዮጵያ ሰላም ማስከበር አስተዋፅኦ አሁን ያለው ሠራዊትም  በውጤታማነት እያስቀጠለው መገኘቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

አሁን ላይም በደቡብ ሱዳን የተሰማራችሁ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት የትላንቱን የአያቶቻችሁን የጀግንነት ታሪክ በመድገም ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ቀጠና ሆኖ እንዲቀጥል መስራት ይጠበቅባችኋል በማለት አሳስበዋል።

ሌተናል ጀኔራል ሞሃን ሰበረማኒያን በታምቡራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ካምፕ አድዋ በሚል ስያሜ መሰየማቸውን አስታውሰው  በደቡብ ሱዳን ሴክተር ኢስት የሚገኘውን የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃንም ካራማራ በሚል መጠሪያ ስያሜ ሰጥተዋል።

የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ የተሰጠው ስያሜ አባቶቻችን በጀግንነት ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለው ጠላትን ድል የነሱበት ታሪካዊ መሆኑን ጠቅሰው የነሱን ታሪክ በተጀመረው የአለም ሰላም ማስከበር ስኬታማ የግጃጅ አፈፃፀም አጠናክረን እንድናስቀጥል የሚያነሳሳ ስያሜ ነው ብለዋል።

በወቅቱ የሴክተር ኢስት አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ራዛቅ አህመድ ፣ የመስክ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ የፎርስ ኮማንደር እና የሴክተር ኢስት ስታፍ አባላት በቀጠናው የሚገኙ የተለያዩ ሃገራት ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዦች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ አንዋር ሁሴን
ፎቶ ግራፍ መብሪሂት ገብረ ሚካኢል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1918👏10🔥2
በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጤራ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ  የነበሩ የፅንፈኛው አባላት ለሠራዊቱ እጅ ሰጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጤራ ወረዳ አሳግርት ቀበሌ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጽንፈኛው አባላት ከአንድ ድሽቃ መሳሪያ እና ከነሙሉ ትጥቃቸው ጋር እጃቸውን  ሰጥተዋል።

በሰላማዊ መንገድ እጅ ለሠጡት ለእነዚህ የፅንፈኛ አባላትም የሰሜን ሸዋ ዞን አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ንጉሴ ሞገስ ፅንፈኛው ቡድን ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት ማድረሱን ገልፀው ቡድኑ ከሥህተቱ ሊማር ባለመቻሉ አስተማሪ እርምጃ ሥለተወሰደበት በርካታ የፅንፈኛ ቡድኑ አባላት እጃቸውን ለሠራዊቱ እየሠጡ ይገኛሉ ብለዋል።
  
በመሆኑም በጤራ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፅንፈኞች አንድ ዲሽቃ ፣አራት ብሬን ፣ስናይፐር ፣በርካታ ክላሽ፣ የእጅ ቦምብ እና ተተኳሽ በመያዝ ከ13 አባላት ጋር ለመከላከያ ሠራዊቱ እጅ ሰጥተዋል።

ዘጋቢ ፋሲል ጌትነት
ፎቶግራፍ ጌትነት አበባው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
33👍10👏6🔥2
የምስራቅ ዕዝ አመራሮች በባህርዳር ከተማ በኮሪደር ልማት የተሰሩ ስራዎችን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በኮሪደር ልማቱ የተሰሩ ስራዎችን በማሥመልከት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ለጎብኝዎች ገለፃ አድርገዋል። አመራሮቹ በጣና ሀይቅ ዳር የተሰሩ መዝናኛ ቦታዎችንና በከተማው የተሰሩ መንገዶችን እንዲሁም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመዘዋወር ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ መከላከያ ሠራዊት እንደመሆናችን መጠን በጠረፍም ይሁን መሃል ሀገር የተሰሩ ልማቶችን አይተናል፤ ዛሬ ደግሞ በባህርዳር  ከተማ በሚገርም ሁኔታ የለማውን ለባህርዳር ከተማ የሚመጥን የኮሪደር የልማት ሥራ ተመልክተናል ብለዋል።

ባህርዳር ከተማ በሀገሪቱ ካሉ ምቹና ለእይታ ማራኪ ከሆኑ ከተሞች አንዷ መሆኗን ገልፀው ሁላችንም የስራችንን ዉጤት ያየንበት እና ሀገራችን የበለጠ ሰላም ሆና ብትለማ ይበልጥ ማደግ እንደምንችል ያረጋገጥንበት ሥለሆነ ይህ የልማት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስተያዬት ሰጥተዋል።

ዕዙም ህግ የማስከበር ግዳጁን ከመወጣት ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ አረጋግጠዋል፡፡

ከጎብኝዎች መካከል ብርጋዲየር ጄኔራል መለስ መንግስቴ እና ኮሎኔል ፈይሳ አየለ በተመለከቷቸው የልማት ሥራዎች እና ውጤቶች ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ ተስፋ የሚሰጡ ስራዎች ማሳያ ስለሆኑ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ዘጋቢ ታደሰ ይሴ
ፎቶ ግራፍ ማሩፍ ደስታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
17👍6👏5🔥1
የሚሰጠውን ግዳጅ በድል መወጣት የሚችል ሠራዊት ተገንብቷል።
        የክፍለ ጦር አመራሮች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

የሚሰጠውን ማንኛውም ውስብስብና ፈተኝ ግዳጆችን በድል መወጣት የሚችል ሠራዊት ተገንብቷል ሲሉ የምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር አመራሮች ተናገሩ።

የዕዙ የሠራዊት አባላት በውስብስብ ሁኔታዎች ሳይበገር ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮዎች በጀግንነት፣ በውጤታማነትና በድል እየተወጣ የህብረተሰቡን ሰላም እያረጋገጠ ይገኛል ያሉት አመራሮቹ በተደረጉ የስምሪት ስራዎች የላቀ ውጤት ማስመዝገቡንና አስደናቂ ገድሎች መፈፀማቸውን አውስተዋል።

ሠራዊቱ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በተደረጉ ሰፋፊና ተከታታይ ህዝባዊ መድረኮች ፅንፈኛው ቡድን እና አሸባሪው የሸኔ ቡድን  ፈጥረውት የነበረውን ችግር ማጥራት የተቻለ መሆኑን ተናግረዋል።

የዕዙ አባላት ሞራላዊና ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነት የመገንባት ፣ የአሃዱዎችን ግዳጅ የመፈፀም እና የማድረግ አቅሞች  የማሳደግ ፣በየደረጃዉ የሚገኙ አመራሮችን ዙሪያ-መለስ የመምራት አቅም የማጎልበት እንዲሁም የተለያዩ ሙያተኞችን በየተመደቡበት ዘርፍ ሙያዊ ብቃታቸዉን የማሳደግ ስራ በስፋት መሠራቱን ገልፀዋል።

ስልጠናዎችም የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደቱን መነሻ በማድረግ ከውጊያ ፅንሰ-ሃሳብ ጀምሮ እስከ አሃድ መምራትና ለዉጊያ ማዘጋጀት እንዲሁም ግዳጅ ተኮር የስልጠና ስምሪት በማከናዎን ተደማሪ የማድረግ አቅሞችን ለመፍጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶ ግራፍ ሽመልስ እሸቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31👍10🔥3
ለደቡብ ሱዳን ሠላም የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ ሠራዊት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።
        ሚስተር ዳንኤል ሪምፖሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን የዌስት ኢኳቶሪያ ስቴት አስተዳዳሪ ሚስተር ዳንኤል ሪምፖሳ የሴክተር ሳውዝ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ዴቫድ ሲንግ እና የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል እንዳለ እሸቱ እና ሌሎችም አመራሮች በቀጠናው አሁናዊ የሠላም ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

የዌስት ኢኳቶሪያ ስቴት አስተዳዳሪ ሚስተር ዳንኤል ሪምፖሳ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ዜጎቻችን የሠላም አየር እንዲተነፍሱ ሌት ተቀን ከግዳጅ ቀጠናቸው ሳይለዩ እያከናወኑት ያለው የሠላም እና የፀጥታ ስራ ውጤታማ እንደሆነ ገልፀዋል። 

ሚስተር ዳንኤል ሪምፖሳ ስለ ሠራዊቱ ከእኔ በለይ ተጠቃሚ የሆነው ሕዝባችን አሳምሮ ያውቃል ያሉ ሲሆን ይህን የተገነዘብኩ የአካባቢው ነዋሪዎች ችግር እንዳይደርስባቸው አሥፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እና የፀጥታ ከለላ ማድረጋቸውን ተመልክቸ ነው ብለዋል።

የዩናሚስ ሴክተር ሳውዝ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ዲነሽ ሲንግ በበኩላቸው አንድም የቀጠናውን የሠላም ሁኔታ ለማወቅ ብሎም በቀጠናው የተሠማራው የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ ሠራዊት የግዳጅ ዝግጁነት አፈፃፀም ምን እንደሚመስል ለመመልከት ያለመ ግንኙነት መሆኑን ገልፀዋል። ዘጋቢ ፍፁም ተካ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31👍15🔥3