FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ
ውጤታማ ሥራ ማከናወኑን አሥታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የ2017 በጀት አመት የሥራ አፈፃፀም ከማዕከል እና ከዕዞች የሰው ሃብት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ የሰው ሃብት አመራር የሰው ሃይሉን በመመልመል በማሰልጠንና በማብቃት በማንኛውም ሁኔታ የሚሰጡ ግዳጆችን በሙሉ አቅም መወጣት የሚያስችል ቁመና የተላበሰ ሠራዊት መገንባት መቻሉን ገልፀዋል።

ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ የምንሰራቸውን ስራዎች ነጥበን በማስቀመጥ የሚጎድሉትን ክፍተቶች በመለየት እና በተጠያቂነት እዲሁም በታማኝነት መንፈስ በመስራት በበጀት አመቱ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ይህንን አቅማችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ በኩልም ለተገልጋዩ የተጣራ መረጃ በመስጠት እና የሰው ሃይል በመቆጣጠር ዳታን በማደራጀትና ሠራዊቱ በግዳጅ ላይ ደስተኛ እንዲሆን በማድረግ በኩል ሁሉም የሰው ሃይል ሙያተኛ በላቀ ደረጃ ስራውን በመስራት ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ  ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ገልፀዋል።                          

በመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የእድገትና ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል አምሳሉ ኩምሳ በበኩላቸው የሰው ሃብት አመራር ሙያተኞች የተሰጣቸውን ተግባራት በሚገባ ለመወጣት ሁሌም በጥረት እንደሚሠሩ እና ውጤት ማምጣት እንደቻሉ ገልፀው በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ በተቋሙ የተወሰኑ ክፍሎች ላይ የተሳካ ኢንስፔክሽን መደረጉን ተናግረዋል።

በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በመወያየት የሠራዊቱን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ተችሏል።

ዘጋቢ ትግስት ሙላት   
ፎቶ ግራፈር ዮዲት በዛወርቅ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👍5🔥2
ወለጋ በአስደማሚ የሠላም አየር ላይ ትገኛለች ሚስጥሩ ምን ይሆን ? ... የቀጠለ
   
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

አቶ ጉዲና ገመዳ የሻምቡ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ፤ የስራ እድል ፈጠራና ኢንቨስትመንት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ናቸው።  የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አስተዳደር መቀመጫ የሆነችው ሻምቡ ከተማ ከዛሬ  ሦስትና አራት ዓመታት በፊት የነበረችበትን የሠላም እጦትና በዚሁ ምክንያት በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ሠብዓዊ ፤ ኢኮኖሚያዊ ፤ ማህበራዊ እና ስነ - ልቦናዊ ቀውሶች ለአፍታ አስታውሠው ሲያበቁ ዛሬ ለተጎናፀፈችው ሠላም እና የመልማት ተስፋ የምዕራብ ዕዝን በተለይም ደግሞ የቴዎድሮስ ኮርን መስዋዕትነት ፤ ፅናት እና ቁርጠኝነት አብዝተው ያደንቃሉ።

ምክትል ከንቲባ አቶ  ጉዲና ገመዳ የቴዎድሮስ ኮር አመራርና የሠራዊት አባላትን የሚገልፁበት ቃል አጥሯቸው በብዙ ሲቸገሩ በመታዘባችን የሚስጥሩ ቋጠሮ ፍቺ እዚህ ጋር ስለ መኖሩ አልተጠራጠርንም።

የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አስተዳደር መቀመጫ የሆነችው ሻምቡ ከተማ ያንን ክፉ ዘመን እንድትሻገርና ዛሬ ለምትተነፍሰው የሠላም አየር ትበቃ ዘንድ ሁለንተናዊ መስዋዕትነትን ለከፈለው የቴዎድሮስ ኮር ከልብ የመነጨ ምስጋናን ቸረውታል።

ዛሬ ይላሉ ምክትል ከንቲባ ጉዲና ገመዳ በጀግናው ቴዎድሮስ ኮር አባላት ክቡር መስዋዕትነት ብሎም ጀግንነትና ፅናት ህዝባችን ሠቅዞ ከያዘው መከራ እና ስቃይ  እፎይ ብሏል። ቴዎድሮስ ኮር በቀጠናው ከተሠማራ ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው እንደፈለገ ሲፈነጭና ንፁሃንን የግፍ ፅዋ ሲግት የነበረውን የአሸባሪውን ሸኔ ቡድን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል።

የሽብር ቡድኑን አከርካሪ ሠብሮ እንዲበታተንና በየጥሻው የሚሽሎከሎክ ተራ ሽፍታነት ደረጃ እንዲወርድ አድርጎታል። ለዚህም ቴዎድሮስ ኮር ቀን ከሌት ተልዕኮውን በአስገራሚ ፅናትና ቁርጠኝነት እየተወጣ ሃገራዊና ህዝባዊ ፍቅሩን በመስዋዕትነቱ ስለማስመስከሩ ምክትል ከንቲባ ጉዲና ገመዳ ነግረውናል።

የሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው በአሸባሪው ሸኔ የጥፋት ተግባራት ምክንያት የደበዘዘ የትላንት ትዝታቸውን በቁጭትና በሀዘን አስታውሠው ዛሬያቸው ብሩህ ይሆን ዘንድ ውድ ህይወቱን ሳይሰስት ለሠጣቸው ጀግናው ሠራዊት ምርቃትና ምስጋናን ሲያሽጎደጉዱለት መመልከት በመንፈሳዊ ቅናት ያቃጥላል። ምነው እኔም የዚህ ጀግና ሠራዊት አባል በሆንኩ እና እንዲህ ያለ የህዝብ ፍቅርና አክብሮትን በተጎናፀፍኩ ያሠኛል።
      
ከቅርብ ዓመታት በፊት ይላሉ የአካባቢው ተወላጅ የሀገር ሽማግሌዎች " ሆሮጉድሩ ወለጋን ጨምሮ አራቱም የወለጋ ዞኖች ለሠው ልጆች አደገኛ የሆኑ ምድራዊ ሲኦሎች ነበሩ። ንፁሃን በዘፈቀደና በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገደሉበት፤ እድሜልክ ያፈሩት ሃብት ንብረት በማንአለብኝነት የሚዘረፍበትና የሚወድምበት፤ ተወልደው ካደጉበት ቀዬ የሚፈናቀሉበትና የሚሠደዱበት ብቻ በጥቅሉ ሠዎች መፈጠራቸውን እንዲጠሉ የሚያደርግ ነውር የሚፈፀምበት በጣም አስቸጋሪ ስፍራ ነበር " ሲሉ ይገልፁታል።
  
ዛሬ ግን ታሪክ ተቀይሮ ያ ፀረ-ህዝብና አረመኔ ቡድን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ እና አከርካሪው ተሠብሮ ትርጉም የለሽ ቡድን ሆኖ ማየት ለእኛ ወደር የማይገኝለት ድል ነው ሲሉ ይገልፃሉ። ለዚህ ድል እና ትልቅ እፎይታ እንድንበቃ አንድ ህይወቱን ለሸለመን ጀግናው ሠራዊታችንም ልባዊ ክብርና ምስጋናችን ዘለዓለማዊ ነው ባዮች ናቸው የሀገር ሽማግሌዎቹ።

በቀጠናው የተሠማራው ቴዎድሮስ ኮር ለሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አንፃራዊ ሠላም መስፈን ሁለንተናውን ሳይሰስት የለገሠ ጀግና አሃድ ነው። በወለጋ ምድር ላይ እየነፈሠ ለሚገኘው አስደማሚ የሠላም አየር ሚስጥርም የቴዎድሮስ ኮር እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭን ጀግንነትና ተጋድሎ ውጤት ሆኖ አግኝተነዋል።
  
ለመሆኑ የቴዎድሮስ ኮር ማነው የት? ፤ እንዴት? መቼና በማን ተመሠረተ?  በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ከመሠማራቱ በፊትስ ምን ምን ግዳጆችን ፈፅሟል? እነዚህን እና ሌሎች ጉዳዮችን ይዘን እንመለሳለን...

በሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍25🥰2👎1🔥1