FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.5K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መረጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ ተደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት  በየደረጃው የሚገኙ የተቋሙን ክፍሎች በማስተባበር በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። በዛሬው ዕለትም ከ240 በላይ ለሚሆኑ የጌርጌሴኖን ሴት የአእምሮ ህሙማን ከዋና መምሪያዎች እና ሌሎች ክፍሎች ጋር በመተባበር ድጋፍ ተደርጓል። 

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ ሠራዊቱ አቅሙ በፈቀደ መጠን ከኪሱ በማዋጣት ከ348 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የአልባሳት እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ለሀገር ዋጋ የከፈሉ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ራሳቸውን መርዳት የተሳናቸውን ወገኖቻችንን መርዳት እና ማገዝ የሁላችንም ሀላፊነት ሊሆን ይገባል ያሉት ብርጋዲየር ጄኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ ሌላው የማህበረሰብ ክፍልም መጥቶ ሊጎበኛቸው እና ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

እኛ በውትድርና ሙያችን ለሀገርና ለህዝብ ከምንከፍለው እንዲሁም ከምንሰራው የሙያ መስክ እና ከምንሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ካለን ላይ ቀንሰን ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጋችን ለሌላውም አርአያ መሆን አለብን ያሉት የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልና ዲያግኖስቲክ ማዕከል ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ሽዋዬ ሃይሌ ናቸው።

የማዕከሉ መስራች ሊቀ-ህሩያን መለሰ አየለ ለተደረገው ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበው ለሀገር መስዋዕትነት የምትከፍሉ የሀገር ምሰሶዎች መጥታችሁ ስለጎበኛችሁን እጅግ ደስ ብሎናል እናመሠግናለን ብለዋል።

ማዕከሉ በ1998 ዓ.ም በበጎ ፈቃደኞች መመስረቱን ገልፀው ጎዳና ላይ የወደቁትን በማንሳት ወደ ቀደመ ጤንነታቸው ለመመለስ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ብዙዎቹ ከጎዳና ላይ የተነሱት ህሙማን በአሁኑ ሰዓት ከህመማቸው አገግመው ለሌሎቹ አገልግሎት እየሰጡ በማየታቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶ ግራፍ ዕፀገነት ዴቢሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👍21🔥2
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሲቲሳምቪኤም (CTSAMVM) ተወካዮች ጋር ተወያዩ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሲቲሳምቪኤም (CTSAMVM) ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

የሲቲሳምቪኤም ተወካይ ልዑካን ቡድን አባላት ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ለምታደርገው ያልተቋረጠ ድጋፍ ያላቸውን አድናቆት በመግለፅ ፤ በደቡብ ሱዳን እንዲሁም የቀጠናውን ሠላም ለማጠናከር እና ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በቁርጠኝነት ለመወጣት እንዲችል ከኢትዮጵያና ከሌሎች አባል ሀገሮች ጋር በጋራ እየሰሩ ያሉትን ሥራ አጠናክረው ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ እና ክትትል እንደማይለያቸው ያላቸውን ፅኑ ዕምነትም ገልፀዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሲቲሳምቪኤም (CTSAMVM) እያደረገው ያለውን ሥራ በማድነቅ ለደቡብ ሱዳን ህዝብና መንግሥት እንዲሁም ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ኢትዮጵያ የበኩሏን አስተዎጽኦ ማበርከቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። መረጃውን ያደረሠን የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
43👍14🔥4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ማርችንግ ባንድ ቡድን በሩሲያ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም

ወደ ሩሲያ ያቀናው የኢትዮጵያ ማርችንግ ባንድ ቡድን ከሌሎች ሀገራት የማርችንግ ባንድ ቡድኖች ጋር በመሆን ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
35👍14🔥1
የክፍለጦሩ የሠራዊት አባላት ከኢትዮ-ቴሌኮም ሠራተኞች ጋር በመሆን ችግኝ ተከሉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
   
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የ6ኛ ሠርዶ ሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ኮሎኔል አስራት ዋና ሠራዊቱና የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች በራሳችሁ ሃሳብ ችግኝ በማዘጋጀት ሠራዊቱ በሚኖርበት አካባቢ መጥታችሁ የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጣችሁ ለሠራዊቱ ሞራል እና ተነሳሽነትን ፈጥሯልና ይህ በጎ ተግባር በሁሉም መስክ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አመላክተዋል።    

የአፋር ሪጅን የኢቲዮ ቴሌኮም ኢንፎርሜሺን ሴኩሪቲ ሃላፊ አቶ አብዱ ሙሃመድ በበኩላቸው ሠራዊቱና የኢቲዮ ቴሌኮም ሰራተኞች የትኛውንም የአየር ፀባይ ተቋቁመው ሀገራዊ ግዳጃቸውን እየተወጡ ያሉ ተቋማት መሆናቸውን ገልፀው የዛሬው የችግኝ ተከላ ዋና ዓላማም በአፋር ክልል በረሃማነትን ለመቀነስ የታሰበ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መሆኑን ተናግረዋል። ዘጋቢ አታክልት በላይ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
37👍12🔥1