FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለ ጤናዎ ሲጋራ ማጨስ ጤናን የሚፈታተን ስውር ጠላት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

ሲጋራ ማጨስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከ8 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የሚዳርግ ሲሆን፣ ይህም በአማካይ በየ4 ሰከንዱ አንድ ሰው በትንባሆ ምክንያት ህይወቱን ያጣል ማለት ነው። ከዚህ ውስጥ ከ80% እስከ 90% የሚሆነው የሳንባ ካንሰር ሞት ከማጨስ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። አጫሾች በልብ ሕመም (stroke) የመያዝ እድላቸው ከማያጨሱት ከ2 እስከ 4 እጥፍ ይበልጣል፤ እንዲሁም ሥር በሰደደ የሳንባ ምች በሽታ (COPD) ከሚሰቃዩ 10 ሰዎች ውስጥ 8ቱ አጫሾች ናቸው።

በአማካይ፣ ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱት ቢያንስ 10 ዓመት ቀድመው እንደሚሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ (WHO FCTC 2023)። ይህ ከባድ የህብረተሰብ ጤና ቀውስ በተለይ ከፍተኛ አካላዊ ጥንካሬ፣ አእምሮአዊ ቅልጥፍና እና የስነ-ልቦና ጽናትን በሚጠይቀው የውትድርና ማህበረሰብ ውስጥ ሲታይ የሚያስከትለው መዘዝ የበለጠ ጥልቅ እና አሳሳቢ ይሆናል። በመሆኑም ሲጋራ ማጨስ የወታደሩን ግላዊ ጤና ከመጉዳት ባለፈ የመላው ሰራዊቱን የውጊያ ዝግጁነት እና ውጤታማነት አደጋ ላይ የሚጥል ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው።

የዚህ አውዳሚ ተጽዕኖ ሥር መሰረት ያለው በሲጋራ ጭስ ውስጥ በሚገኙ ከ7,000 በላይ ኬሚካሎች ውህድ ውስጥ ነው። ከእነዚህም መካከል እንደ ኒኮቲን፣ ካርቦን ሞኖክሳይድ እና ታር (ቅጥራን) ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች በወታደሩ አካል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ይሰነዝራሉ። ለምሳሌ፣ ካርቦን ሞኖክሳይድ በቀይ የደም ሴሎች ውስጥ ኦክስጅንን በመተካት በሰውነት ውስጥ ያለውን የኦክስጅን መጠን በእጅጉ ይቀንሳል።

ይህ የልብ ምትንና የአተነፋፈስን ፍጥነት እንዲጨምር በማድረግ ልብና ሳንባ ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል። በዚህም ምክንያት የሚያጨሱ ወታደሮች በከፍተኛ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ወቅት ቶሎ የመድከም እና የትንፋሽ ማጠር ችግር ያጋጥማቸዋል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሲጋራ የሚያጨሱ የሰራዊት አባላት ከማያጨሱት ጋር ሲነፃፀሩ በሩጫ እና በሌሎች የአካል ብቃት መመዘኛዎች ላይ ያላቸው ብቃት ከ5-10% የቀነሰ ነው። ጉዳቱ በልብና በሳንባ ብቻ አያበቃም።

ሲጋራ ማጨስ ወደ ጡንቻዎች የሚደርሰውን የደም እና የኦክስጅን ፍሰት ስለሚቀንስ የጡንቻን ጥንካሬና ጽናት ያዳክማል። ከዚህም ባሻገር ኒኮቲን የአጥንትን እድገት እና ጥንካሬ የሚቆጣጠሩትን ህዋሳት ተግባር በማስተጓጎል የአጥንት ጥግግት እንዲቀንስ ያደርጋል። በዚህም ምክንያት የሚያጨሱ ወታደሮች በተለይም በስልጠና እና ከባድ እንቅስቃሰ ወቅት ለሚከሰቱ የአጥንት ስብራቶች (stress fractures) እና ሌሎች ጉዳቶች ያላቸው ተጋላጭነት ከማያጨሱት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው።

ከእነዚህ ቀጥተኛ አካላዊ ጉዳቶች ባሻገር፣ ሲጋራ ማጨስ የወታደራዊ ዝግጁነትን መሰረቶች በስርዓት ይሸረሽራል። የአንድ ወታደር አካል ዋነኛ መሣሪያው ሲሆን፣ ሲጋራ ማጨስ ግን የዚህን መሣሪያ ዋነኛ መከላከያ የሆነውን የበሽታ መከላከል አቅምን ያዳክማል። ይህም ወታደሮችን እንደ ብሮንካይተስ እና የሳንባ ምች ላሉ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች በስፋት ከማጋለጡም በላይ፣ የሰውነትን የመፈወስ ሂደት ስለሚያዘገይ ከጉዳት በኋላ የማገገሚያ ጊዜን ያራዝማል። አንድ ጥናት እንዳመለከተው የሚያጨሱ ወታደሮች ከማያጨሱት ጋር ሲነጻጸር በበሽታ ምክንያት ሆስፒታል የመታከም እድላቸው በ30% ይበልጣል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👏16👍8🔥2😁1
አባላቱና አመራሩ ተናበው በመስራታቸው የሽብር ቡድኑን ማጥፋት እየተቻለ ነው።  

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

ጀግና አመራር ጀግና ተዋጊን ይፈጥራል ይህም አመራሩና አባሉ ተናበዉ በመስራት የሚፈጥሩት ጥምረት የድል አድራጊነት አንዱ አካል መሆኑን የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጄኔራል አብድሮ ከድር ተናግረዋል።

ምክትል አዛዡ በራስ ዳሽን ኮር ተገኝተዋል የሰራዊቱን የግዳጅ አፈፃፀም ዉሎ ተመልክተዋል። የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ መሰናክሎችን በማቋቋም እና ከምንም በላይ ህዝባዊ ወገንተኝነትን በማስቀደም የሰላም ፀር የሆነዉን አሸባሪ ቡድን በገባበት ገብቶ እስከመጨረሻው በመደምሰስ ለህዝብ እፎይታን መስጠት እንደሚጠበቅ አሥገንዝበዋል።

ሜጄር ጄኔራል አብድሮ ከድር ህዝብና መንግስት የሰጣችሁን አደራ በመጠበቅ ጠላትን አምርሮ በመጥላት ሀገርን በንቃት መጠበቅ እና ራስን ካልሆነ አመለካከት በማዉጣት ከሀሰት ፕሮፖጋንዳ በመውጣት እስካሁን ካስመዘገባችሁት ድል በላይ ለማሥመዝገብ የበለጠ ራሳችሁን ማዘጋጄት ይገባችኋል ብለዋል።

የኮሩ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል አበባው መንግስቱ በበኩላቸዉ አንደ ሀገር ብሎም እንደ ክፍል የተሰጠንን ግዳጅ በብቃት በመወጣትና የአሸባሪዉ ኦነግ ሸኔን በገባበት ገብተን በመደምሰስ የተሠጠንን ተልዕኮ እየፈፀምን ነው እንፈፅማለንም ብለዋል።

ጠላት ጫካ ለጫካ ቢሹለከለክም ሰራዊቱ እግር በእግር እየተከታተለ እየደመሰሰዉ ይገኛል ሲሉ ብርጋዲየር ጄኔራል አበባዉ መንግስቴ ተናግረዋል ። ዘጋቢ ብሩክ ታደሰ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏2119👍6🔥2
በሁርሶ የ10ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም
    
የሁርሶ ኮንቲንጀትንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል ሰልጣኞች ከስልጠና ጎን ለጎን ለአራት ወራት በእግር እና በመረብ ኳስ እንዲሁም በገመድ ጉተታ ስፖርታዊ ውድድሮችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል።
   
በሰፖርታዊ ውድድር ፋፃሜ ላይ ተገኝተው ለአሸናፊ ቡድኖች ዋንጫ በመስጠት ንግግር ያደረጉት የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ስፖርት ለወታደር ተልዕኮ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ የጥንካሬው መገለጫ መለያ ባህሪው ነው ብለዋል።
   
የስፖርታዊ ውድድሩ ዋና አላማ ሰልጣኞች ከስልጠና ጎን ለጎን እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ እንዲግባቡ የሚረዳ ከመሆኑም ባለፈ አሃዳዊ ፍቅር እንዲኖራቸው አንድነታዊ መተሳሰብ እንዲያጠናክሩ በሰነ -ልቦና ዝግጁነት ውስጣዊ ሞራል መነቃቃት እንዲፈጠሩ የሚያሥችል መሆኑንም ገልፀዋል።
  
የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ስፖርት አስተባባሪ ሻለቃ ባሻ ደገፉ ማሞ በበኩላቸው በስፖርታዊ ውድድሩ ለተቋሙ ስፖርት ክለብ ተተኪ መሆን የሚችሉ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች የመመልመል የመለየት ስራ መሠራቱን ተናግረዋል።
   
ውድድሩ ውስጣዊ ፍክክር ኖሮት በውጤት እንዲጠናቀቅ የሻለቃ አመራሮች እና አሰልጣኞች ሚና ከፍተኛ ሲሆን ተወዳዳሪዎች በወታደራዊ ዲስፕሊን  ታንፀው ጨዋታውን ለፍፃሜ አድርሰዋል።

በውድድሩም በእግር ኳስ አምሰተኛ ሻለቃ አንደኛ ሻለቃን 1ለ0 ፤ መረብ ኳስ ስድስተኛ ሻለቃ ሁለተኛ ሻለቃን 3ለ1፤ ገመድ ጉተታ ሁለተኛ ሻለቃ አንደኛ ሻለቃን 2ለ1 ያሸነፉ ሲሆን የተዘጋጀላቸውን ዋንጫ ከዕለቱ የክብር እንግዳ እጅ ተቀብለዋል።

ዘጋቢ ተስፋዬ ያረጋል
ፎቶግራፍ አበበ እያሱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
48👍18🔥10🥰1