FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
መቻል ሶስት ወሳኝ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የግብ ጠባቂውን ውል አራዝሟል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

መቻል እግር ኳስ ቡድን ሶስት ወሳኝ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ሲያሥፈርም የግብ ጠባቂውን ውል አራዝሟል።

የመጀመሪያ ፈራሚው በወላይታ ዲቻ በቅዱስጊዮርጊስ እና ያለፈውን ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ባህርዳር ከተማ ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው እና ለብሄራዊ ቡድን ግልጋሎት እየሠጠ የሚገኘው የመስመር አጥቂው ቸርነት ጉግሳ ለመቻል ፊርማውን አኑሯል።

ሁለተኛው በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በባህርዳር ከተማ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ለመቐለ 70 እንደርታ ሲጫወት ያሳለፈው የመሀል ሜዳ ተጫዋቹ የአብስራ ተስፋዬ ለመቻል ፈርሟል።

ላለፉት ሶስት አመታት በሀዲያ ሆሳዕና ቤት ምርጥ ብቃቱን በማሳየት ብሄራዊ ቡድን በተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበለት ሲጫወት የቆየው የተከላካይ አማካይ ብሩክ ማርቆስ ለማቻል ሶስተኛ ፈራሚ ሆኗል።

ያለፉትን ሁለት አመታት ለመቻል ግልጋሎቱን ሲሰጥ የቆየው ግብ ጠባቂው ውብሸት ጭላሎ በመቻል ለመቆየት ውሉን አራዝሟል። ዘጋቢ ገረመው ጨሬ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍4👎2🔥2
በተለያዬ አካባቢ የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ደም ለግሰዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

የሁርሶ እጩ መኮነን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አመራሮችና ዕጩ መኮነን ሠልጣኞቾ፣ የደቡብ ዕዝ ኮር የሠራዊት አባላት እና የ7ኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦር የሠራዊት አባላት በፈቃደኝነት ደም ለግሰዋል።

የሁርሶ እጩ መኮነን ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ምክትል አዛዥ ለውጊያና ድጋፍ አገልግሎት ኮሎኔል ሙዞ ሸሪፋ የሚተካ ደም በመስጠት የማይተካ ህይወት ማዳን የሠራዊቱ አንዱ ተግባር በመሆኑ አጠናክረን በማስቀጠል የሰብአዊነት በጎ ተግባራችንን መወጣት ይገባናል ብለዋል።

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የበሽታ መከላከል ሀላፊ  ሻለቃ አበራ ታደሰ በበኩላቸው  የደም ልገሳ በተለያየ ምክንያት የደም እጦት ለገጠማቸው ወገኖች በመድረስ ህይወትን ማስቀጠል በመሆኑ የሚያኮራ ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል። ዘጋቢ ሜሮን ጌታነህ ናት

በተመሳሳይ የደቡብ ዕዝ ኮር ሰራዊት በደም እጥረት ምክንያት የሚጠፋዉን የሰው ህይወት እንታደግ በሚል መሪ ሃሳብ ለኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ አገልግሎት የምስራቅ ቦረና ዞን ቅርንጫፍ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ማድረጋቸውን የኮሩ 3ኛ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሻለቃ ተረፈ ታደሰ ተናግረዋል።

የምስራቅ ቦረና ዞን ደም ባንክ ቅርንጫፍ ሃላፊ አቶ ዳርጌ ባርጩ በበኩላቸው፤ ሰራዊታችን ከግዳጁ ጎን ለጎን ደም በመለገስ የበርካታ ወገኖቻችንን ህይወት መታደግ እየቻለ መሆኑን አሥረድተዋል ዘጋቢ ፈይሳ መልካሙ ነው።

በተያያዘ የ7ኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦር የሠራዊት አባላት በመተከል ዞን ግልገል በለስ ሆስፒታል ደም መለገሳቸውን የክፍለጦሩ ጤና ማበልፀግና በሽታን መከላከል ሀላፊ ሻለቃ ጥላሁን ገዛሃኝ ሰማ ገልፀዋል።

ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር በሚለው እሴት መሠረት የክፍለጦሩ አባላት በተሠማሩበት የግዳጅ ቀጠና  ሠላምን ከማስፈን በተጓዳኝ በደም እጥረት ምክንያት  የሚሰቃዩ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ደም እየለገሱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዘገባው የተሾመ ወንደሰን ነው
‎    
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32👍8👏2🔥1😁1💔1
የጥበቃ ብርጌዱ ተልዕኮውን በውጤት መፈፀም በሚያሥችለው አግባብ መገንባቱ ተገለፀ። 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

‎የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል በውጊያና በተለያዩ ግዳጆች ደጀን በመሆን ከፍተኛ የሆነ ኮምቮይ 
‎እጀባና የዲፖዎችን ደህንነት የሚጠብቅ እንዲሁም ለተቋሙ ጋሻ የሆነ ጠንካራ የጥበቃ ብርጌድ መመሥረቱን ተናግረዋል።

‎የጥበቃ ብርጌድ አባላት አካባቢያችሁን ለስራ ውብና ማራኪ በማድረግ ላሳያችሁት ቁርጠኝነት እያመሠገንኩ በተመደባችሁት የስራ ዘርፈ ከመተግበርና ከማስተግበር ባሻገር በመስክ ስልታዊ እንቅስቃሴ ውጊያን መርቶ የመፈፀምና የማስፈፀም የላቀ ክህሎት መፍጠር መቻላችሁ የሚመሠገን ነው ብለዋል።

‎የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የጥበቃ ብርጌድ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሁሴን ሀሠን በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ ለመስራት የሚያስችል ሁለንተናዊ አቅም መፍጠር መቻሉን ገልፀው ተጣጣፊና ሁለገብ የሆነ ክፍል መገንባቱን አረጋግጠዋል።

‎በዕለቱ በሥራ አፈጻጸማቸው የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ  አባላት የምስጋና እና የዕውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

‎ዘጋቢ ወርቅነህ ተስፋው
‎ፎቶግራፍ በድሩ መሀመድ

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏2215👍10🔥2
ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እየተገነባ የሚገኘውን  የሠራዊት መኖሪያ ቤት ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስቴር  ሚኒስትር  ክብርት ኢንጂነር  አይሻ መሐመድ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን እየተገነባ የሚገኘውን ጋሻ የሰራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ሂደቱን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከጥቂት አመታት በፊት የአልሙኒየም ፍሬም ወርክ ቴክኖሎጂን መጠቀም የማይቻል እንደነበር አስታውሰው ዛሬ በአልሙኒየም ፍሬም ወርክ ቴክኖሎጂ የተሰራ የቤት ግንባታ ለማየት በቅተናል ብለዋል።

ሚኒስትሯ የአልሙኒየም ቴክኖሎጂ በዋጋ፣በጥራት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው አበርክቶ ላቅ ያለ መሆኑን ገልጸው በፕሮጀክቱ እየተሳተፋ ለሚገኙ ሙያተኞች እና አመራሮች እየሠሩ ላለው ፈጣን እና ጥራት ያለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱን አስመልክተው ገለፃ ያደረጉት የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጃ መገርሳ ጋሻ የሰራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት በ26ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ 16 ህንፃዎችን የሚያካትት መሆኑን ገልፀው ግንባታው የሠራዊት መኖሪያ ፍላጎትን ከማሟላት በተጨማሪ ለሠራዊት የግዳጅ አፈፃፀም የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ስለ ግንባታው ሂደት ገለፃ ያደረጉት የፕሮጀክቱ ስራ አስፈፃሚ አቶ ይርጉ አደራ የሰራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤት በውስጡ ባለ አንድ፣ባለ ሁለት እና ባለ ሶስት መኝታ ቤቶችን ያካተተ መሆኑን ገልፀው ግንባታውም በፍጥነት እና በጥራት እየተገነባ መሆኑን ገልፀዋል።
 
ዘጋቢ ደበላ ዲንሳ
ፎቶግራፍ እፀገነት ደቢሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
45👏5🔥3👍2