FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
33 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
150 የሸኔ አባላት በተደረገላቸው የሠላም ጥሪ መሰረት በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጡ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

የደቡብ ዕዝ ኮር ግዳጅ እየተወጣበት በሚገኘው ምዕራብ ጉጅ ዞን 150 የሸኔ አባላት የተደረገላቸውን የሠላም ጥሪ በመቀበል በሰላማዊ መንገድን እጅ ሰጥተዋል፡፡

የደቡብ ዕዝ ኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል አባዲ ልዑል፣ የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አዶላ ሂርጳዬ ፣የዞንና የወረዳ አመራሮች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እጅ ለሰጡ የሸኔ አባላት አቀባበል አድርገዋል።

የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል አባዲ ልዑል፣ እና የምዕራብ ጉጂ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አዶላ ሂርጳዬ፣
በሠላማዊ መንገድ እጅ የሠጡ የሸኔ አባላት ሠላም መርጠው እና የሠላም ጥሪውን ተቀብለው መግባታችው ትክክለኛ አማራጭ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ለሠላም መሥራት እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

በሰላማዊ መንገድ የገቡት የሸኔ አባላትም እስካሁን ድረስ በሀገር እና በህዝብ ላይ ለፈፀሙት ያልተገባ ድርጊት መፀፀታቸውን ገልፀው ከእንግዲህ ሠላምን የማሥቀደም ሥራ እንደሚሠሩና ለሠላም እንደሚቆሙ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ የዞንና የወረዳ እንዲሁም የሠራዊቱ አመራሮች አባገዳዎች የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። ዘገባው የኮሩ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
52👏12👍8🕊6🔥2🫡1
ዝግጁነቱን ያረጋገጠና በጠንካራ ስነ-ልቦና የተገነባ  ሠራዊት ተልዕኮዉን ለመፈጸም አስተማማኝ ነው።
‎     ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

‎የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት በቴዎድሮስ ኮር አንድ ክፍለጦር በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ተገኝተዉ  አጠቃላይ የወትሮ ዝግጁነት እና የግዳጅ አፈፃፀም የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ዝግጁነቱን ያረጋገጠና በጠንካራ ስነ-ልቦና የተገነባ  ሠራዊት ሀገራዊ ተልዕኮዉን ለመፈጸም አስተማማኝ  መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዋና አዛዡ ሠራዊታችን ከህዝብ የወጣ ለህዝብ የሚኖር እና ለህዝብ የሚሞት፣ አላማውን የማይሸጥ፣ ሃላፊነቱን የማይዘነጋ፣ ለህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ የታመነ በተቋማዊ እሴቶች ብቻ የሚመራ የሰላም እና የልማት ሃይል ነው ብለዋል።

‎አገርን መውደድ መዳረሻው ለሀገር ሰላም መስዋዕትነት መክፈል በመሆኑ በሰራዊታችን ዘንድ ሁሌም የሚፈፀም ሃቅና ተግባር ነው ያሉት ሌተናል ጀኔራል መሰለ መሰረት፤ የነፃነት ተምሳሌት የሆነችውን አገራችን ኢትዮጵያን ለተተኪው ትውልድ ማሻገር በሚችል በደማቅ መስዋዕትነት የህዝቦችን ዘላቂ ሰላም በማፅናት የአገሩን ሉዓላዊነትና ደህንነት እያስከበረ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

‎የክፍለጦሩ የሠራዊት አባላት የኢትዮጵያን ሠላም ለማናጋት ሌት ተቀን በሚያሴሩ ፀረ ሰላም ሃይሎች ላይ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የሚታወቅ ድል አድራጊ የህዝብ ልጅ መሆኑን የገለፁት ጀኔራል መኮንኑ፤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንቅፋት የሆነው አሸባሪው ሸኔ ላይ እርምጃ በመውሰድ ዞኖችን፣ ወረዳዎችን እና ቀበሌዎችን ከሸኔ በማፅዳት ህዝቡ በነፃነት ተንቀሳቅሶ ሰርቶ መግባት እንዲችል ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ክፍለጦር መሆኑን ገልፀዋል።  

ዝግጁነቱን ያረጋገጠና በጠንካራ ስነ-ልቦና የተገነባ  ሠራዊት ሀገራዊ ተልዕኮዉን ለመፈጸም አስተማማኝ በመሆኑ በየትኛዉም ሁኔታ ዉስጥ እየተዋጋና እየሰለጠነ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ ጠንካራ አሃድን በስልጠና በማብቃት የማድረግ አቅሙን በየጊዜው በተግባር እያረጋገጠ የሚሰጠውን ማንኛውም ግዳጅ በጀግንነት በመፈፀም ዘላቂ ሰላም በማምጣት ኢትዮጵያን ማፅናት ከሁሉም የሠራዊታችን አመራርና አባላት ይጠበቃል ብለዋል።

‎ዘጋቢ ጋብዘው ዳና
‎ፎቶ ግራፍ ጋብዘው ዳና

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
19👏10👍6🔥2🏆1
መቻል ሶስት ወሳኝ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የግብ ጠባቂውን ውል አራዝሟል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

መቻል እግር ኳስ ቡድን ሶስት ወሳኝ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ሲያሥፈርም የግብ ጠባቂውን ውል አራዝሟል።

የመጀመሪያ ፈራሚው በወላይታ ዲቻ በቅዱስጊዮርጊስ እና ያለፈውን ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ባህርዳር ከተማ ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው እና ለብሄራዊ ቡድን ግልጋሎት እየሠጠ የሚገኘው የመስመር አጥቂው ቸርነት ጉግሳ ለመቻል ፊርማውን አኑሯል።

ሁለተኛው በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በባህርዳር ከተማ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ለመቐለ 70 እንደርታ ሲጫወት ያሳለፈው የመሀል ሜዳ ተጫዋቹ የአብስራ ተስፋዬ ለመቻል ፈርሟል።

ላለፉት ሶስት አመታት በሀዲያ ሆሳዕና ቤት ምርጥ ብቃቱን በማሳየት ብሄራዊ ቡድን በተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበለት ሲጫወት የቆየው የተከላካይ አማካይ ብሩክ ማርቆስ ለማቻል ሶስተኛ ፈራሚ ሆኗል።

ያለፉትን ሁለት አመታት ለመቻል ግልጋሎቱን ሲሰጥ የቆየው ግብ ጠባቂው ውብሸት ጭላሎ በመቻል ለመቆየት ውሉን አራዝሟል። ዘጋቢ ገረመው ጨሬ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍4👎2🔥2