FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
33 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ጠንካራ ስነ-ልቦና ያለው ሠራዊት በማንኛውም ግዳጅ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል እሸቱ አሥማማው በቡርቃ ማሠልጠኛ ማዕከል ለሚገኙት የሻለቃና የሻምበል አመራሮች አንዲሁም ድጋፍ ሠጭ ሙያተኞች የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ስራን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሠጥተዋል።

ጠንካራ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ያለው አመራር ጠንካራ አሃዱ ከመፍጠርም በላይ በማንኛውም ግዳጅ የድል ባለቤት እንደሚሆን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ሠራዊት ከምንም በላይ በውስጡ ጥልቅ የሃገር ፍቅር ስሜት እና የድል አድራጊነት አመለካከትን መላበስ እንዲችል በየደረጃው ያለ አመራር ቀጣይነት ያለው የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ስራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

አመራሩ የጠላትን አፍራሽና ፅንፍ የወጣ አመላካከት
መመከት የሚችል ሠራዊት ለመገንባት የትኩረት አቅጣጫ መንደፍ እና መከተል እንዳለበትም አመላክተዋል።

በመከላከያ ሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት የግንባታ ሥራዎች ዝግጅት እና ሥልጠና ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ተወካይ ኮሎኔል መንግሥቱ ጌታንጋ  በበኩላቸው ተከታታይነት ያለው ለወጥ ለማምጣት ሁሌም ሠራዊቱ መገንባት በሚችልባቸው መሠረታው የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከአመራሩ ጋር በመናበብ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የስነ-ልቦና ዝግጁነትና የድል አድራጊነት ስሜት የሚገነባው ቆራጥና ሃገር ወዳድ መሪዎችን ማፍራት ሲቻል መሆኑን ገልፀው የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ስራ ብቻ ስላልሆነ ሁሉም የሠራዊት አመራሮች ትኩረት ሠጥተው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ ጌትነት ሊበን
ፎቶግራፍ ልዑል ዘውዴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
21👍5🔥2
ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ በጌጃ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን ፕሮጀክት ተመለከቱ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.,ም

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ በጌጃ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን የስትራቴጂክ መሳሪያዎች ኮር የክፍለጦር  መኖሪያ ካምፕ እና የጠጠር መንገድ የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ የስትራቴጂክ መሳሪያዎች ኮር ለመከላከያ ዋነኛ ድጋፍ ሰጪ እንደመሆኑ ፕሮጀክቱ ሳይጓተት በፍጥነት ተገንብቶ ማስረከብ እንደሚገባ ገልፀው ግንባታው የደረሰበት ደረጃ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

የሜሮብ ኮንስትራክሽን ድርጅት አምራችና ባለቤት ኢንጂነር ተስፋዬ ዲንሳ ሳይቱ ሁለት ፕሮጀክቶችን ያካተተ መሆኑን ገልፀው አንደኛው የክፍለ-ጦር ካምፕ አሁን ላይ 87% መድረሱንና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ፕሮጀክት ደግሞ 2.8 ኪሎ ሜትር አንደኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ አየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ከመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ጋር በመስራታቸው ደስተኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ ሻለቃ መጋቢ ባሻ ኢንጂነር ሲሳይ አበጋዝ እና ዳታ ኮሌክተር ምክትል አስር አለቃ መንፈሱ ገዴቻ የበላይ አካል ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ሰራተኞች ለሃያ አራት ሰዓት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ዲዛይኑን ጠብቆ በተቀመጠለት ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት እንዲያልቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ሃያ ብሎኮች፣ጂ+3 እና ጂ+1 ፎቆች ያሉት ነው፡፡

ዘጋቢ አዳም ወንድማገኝ
ፎግራፍ ታሪኳ ብረሃኑ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍13🔥3
የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት የሚወጡ የፈጠራ ባለቤት ጀግኖችን አፍርተናል።                   
  ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የኦርዲናንስ መምሪያ፣ የአቅርቦት መምሪያና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት፤ እንዲሁም ልዩ ልዩ ስታፍ ቡድኖች ስኬታማ እንቅስቃሴን አስመልክተው ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥተዋል።

የተቀበሉትን ግዳጅ በብቃት ከመተግበር ባለፈ ስራን የሚያቀሉ ፈጠራዎችን የሚሰሩ የሰራዊት አባላት  ማፍራታችን፤ ዕቅዶቻችን ስኬታማ እንዲሆኑ ጉልህ ድርሻ አላቸው ሲሉ በመርሃ- ግብሩ በእንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል ገልፀዋል።

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ሙስጠፋ መሀመድ የሁሉም ክፍሎች የላቀ ትብብርና ዘመናዊ አሰራር፤ ዘርፈ ብዙ እምርታ እንዳስገኘ ተናግረዋል።

በዕለቱ ሃገራቸውን ለረጅም አመታት አገልግለው በክብር ለተሰናበቱ አባላት እንዲሁም በአመቱ በስራ አፈጻጸማቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አባላት ዕውቅና እና ሽልማት ተበርክቷል።

ዘጋቢ ዳዊት ብርሃኑ
ፎቶግራፍ በድሩ መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
23👍8👏2🔥1🥰1😭1
የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር የጋራ ሥልጠና ሰጡ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሀሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም 

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ያዘጋጀው ስልጠና ሰራዊቱ ተላላፊ በሽታዎችን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚረዳ እና ሰራዊቱን ከተለያየ በሽታ ለመከላከል እንደሚያስችል በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የደቡብ ዕዝ ጤና መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ግርማይ ከበደ ገልፀዋል።

ሙያተኞችን በስልጠና ለማብቃት የተቋሙና የሲቪል ተቋማት ርብርብ ማድረጋቸው የሚበረታታ መሆኑን
የሀገር አቀፍ የናሙና ቅብብሎሽ አስተባባሪ ሬድዋን መሀመድ ገልፀዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ የሰራዊት አባላትም ስልጠናውን በመውሰዳቸው ጥሩ እውቀት መጨበጣቸውን እና ወደ ክፍላቸውም ሲመለሱ ባገኙት እውቀት ሰራዊቱን ለማገልገል ዝግጁ መሆናችውን አረጋግጠዋል::

ስልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ ዕዞች፣ ማሰልጠኛዎች እና ከልዩ ልዩ ከፍሎች ለተውጣጡ የሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኒሺያን ሙያተኞች ነው።

ዘጋቢ እዮብ ሰለሞን
ፎቶግራፍ አብረሃም ወርቁ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32🥰2🔥1