FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
33 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ለውድድር አመቱ በቂ ዝግጅት እያደረገ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሀሴ 09 ቀን 2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየርሊግ ውድድር ላይ የሚሳተፈው የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ለ2018 የውድድር አመት ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር መሠረት ማኔ ገልፀዋል።

የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ለ2018 የውድድር አመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ጀምሮ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ በመቀለቀል እንዲሁም የነባሮችን ውል በማደስ ዝግጅታቸውን በቢሾፍቱ ከተማ  ከሁለት ሳምንት ቢፊት በመጀመር በርካታ የጥንካሬና ቡድኑን የማቀናጀት ስራ በመሥራት ላይ ናቸው።

የቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር መሠረት ማኔ  መቻል አንጋፋ ክለብ ነው እድሉ ተሰጥቶኝ ያለኝን ልምድ እና አቅም ተጠቅሜ  ውጤታማ እንዳደርገው ሃላፊነት ለለሰጡኝ ለክለቡ አመራሮች እና ለተቋሙ ትልቅ ክብር አለኝ ብለዋል።

ኢንስትራክተር መሠረት እንዳሉት ቡድኑ በዝግጅት ስራቸው የጥንካሬ ስራን ከኳስ ጋር አጣምረን እየሰሩ መሆኑን አንስተው በቀጣይ የተለያዩ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ለማድረግ ማቀዳቸውን ተናግረው ከአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹ ጥንካሬ እና ድክመት በመለየት ነሀሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሚጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየርሊግ ውድድር ላይ የተሻለ ውጤት እንደምናመጣ እምነት አለኝ ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

   መቻል ለኔ ሁሉ ነገሬ ነው ያለችው የቡድኑ አምበል አምሳ አለቃ ዙሪያሽወርቅ መልኬ በ2018 የውድድር አመት የተሻለ ውጤት ለማሳካት ያለን አንድነት እና ተነሳሽነት ጥሩ ነው በመሆኑ በዚህ አመት የተሻለ ውጤት እናሳካለን ብላለች።

በመቻል ቤት ለሁለተኛ ተከታታይ አመት የቆየችው የተከላካይ መስመር  ተጫዋች የሆነችው ብርቄ አማረ ካለፉት የውድድር አመት በተሻለ መልኩ የዘንድሮው የቡድናችን ቅንጅትና አንድነት የተሻለ በመሆኑ ጥሩ ተፎካካሪ ሆነን እናጠናቅቃለን ስትል ተናግራለች።ዘጋቢ ገረመው ጨሬ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31👍7👎3🔥2
ኮሩ ሰላምን በማስፈን ላበረከተው አስተዋፅኦ እውቅና ተሰጠው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም
 
የደቡብ እዝ ተወርዋሪው ኮከብ ኮር ሰላምን በማስፈን ላበረከተው አስተዋፅኦ በአዳማ ከተማ ለፀጥታ ሀይሉ በተዘጋጀው የምስጋና ዝግጅት ላይ የዋንጫና የዕውቅና ሰርተ-ፊኬት ተበርክቶለታል። ሽልማቱንም የኮሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ደጀኔ ፀጋዬ ተቀብለዋል።

ሽልማቱን የሰጡት የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀይሉ ጀልዴ መሰረቷ የማይናጋ የተከበረች ሀገርን ለማስቀጠል ሰራዊታችን ከውጭና ከውስጥ ፀረ ሰላም ሀይሎች ጋር እየተጋፈጠ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ሀገርን ያቆየ ህዝባዊ ሠራዊት በመሆኑ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

አቶ ሀይሉ ጀልዴ ተወርዋሪው ኮኮብ ኮር በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ የሀገር ሰላምን የማይሹ ፀረ ሰላም ሀይሎችን በመፋለም  የሀገራችንን ሰላም በማረጋገጥ የህዝባችንን ደህንነት በመጠበቅ  በአዳማ ከተማ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜ ያለምንም እንቅፋት እንዲቀጥሉ በማድረግ ኮሩ የአንበሳውን ድርሻ ይዟል በማለት ገልፀዋል።

ሠራዊታችን ለራሱ  የተመቻቸ ኑሮ ሳይኖር  ለብርድና ሙቀት ሳይበገር ጫካ ውሎ የሚያድረው የማትደፈር ሀገርን ለማቆየትና ህዝባችን በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ስራውን በነፃነት እንዲያከናውን ፀረ ሰላም ሀይሎችን ከፀጥታ ሀይል ጋር በጥምረት በመፋለም ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ሰለሞን አማረ
ፎቶ ግራፍ መለስ ውለታው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍9🔥2
ጠንካራ ስነ-ልቦና ያለው ሠራዊት በማንኛውም ግዳጅ ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል እሸቱ አሥማማው በቡርቃ ማሠልጠኛ ማዕከል ለሚገኙት የሻለቃና የሻምበል አመራሮች አንዲሁም ድጋፍ ሠጭ ሙያተኞች የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ስራን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሠጥተዋል።

ጠንካራ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ያለው አመራር ጠንካራ አሃዱ ከመፍጠርም በላይ በማንኛውም ግዳጅ የድል ባለቤት እንደሚሆን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ሠራዊት ከምንም በላይ በውስጡ ጥልቅ የሃገር ፍቅር ስሜት እና የድል አድራጊነት አመለካከትን መላበስ እንዲችል በየደረጃው ያለ አመራር ቀጣይነት ያለው የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ስራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

አመራሩ የጠላትን አፍራሽና ፅንፍ የወጣ አመላካከት
መመከት የሚችል ሠራዊት ለመገንባት የትኩረት አቅጣጫ መንደፍ እና መከተል እንዳለበትም አመላክተዋል።

በመከላከያ ሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት የግንባታ ሥራዎች ዝግጅት እና ሥልጠና ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ተወካይ ኮሎኔል መንግሥቱ ጌታንጋ  በበኩላቸው ተከታታይነት ያለው ለወጥ ለማምጣት ሁሌም ሠራዊቱ መገንባት በሚችልባቸው መሠረታው የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከአመራሩ ጋር በመናበብ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የስነ-ልቦና ዝግጁነትና የድል አድራጊነት ስሜት የሚገነባው ቆራጥና ሃገር ወዳድ መሪዎችን ማፍራት ሲቻል መሆኑን ገልፀው የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ስራ ብቻ ስላልሆነ ሁሉም የሠራዊት አመራሮች ትኩረት ሠጥተው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ ጌትነት ሊበን
ፎቶግራፍ ልዑል ዘውዴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
21👍5🔥2
ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ በጌጃ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን ፕሮጀክት ተመለከቱ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.,ም

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ በጌጃ ወረዳ እየተገነባ የሚገኘውን የስትራቴጂክ መሳሪያዎች ኮር የክፍለጦር  መኖሪያ ካምፕ እና የጠጠር መንገድ የግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼ የስትራቴጂክ መሳሪያዎች ኮር ለመከላከያ ዋነኛ ድጋፍ ሰጪ እንደመሆኑ ፕሮጀክቱ ሳይጓተት በፍጥነት ተገንብቶ ማስረከብ እንደሚገባ ገልፀው ግንባታው የደረሰበት ደረጃ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

የሜሮብ ኮንስትራክሽን ድርጅት አምራችና ባለቤት ኢንጂነር ተስፋዬ ዲንሳ ሳይቱ ሁለት ፕሮጀክቶችን ያካተተ መሆኑን ገልፀው አንደኛው የክፍለ-ጦር ካምፕ አሁን ላይ 87% መድረሱንና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ፕሮጀክት ደግሞ 2.8 ኪሎ ሜትር አንደኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ አየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ከመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ጋር በመስራታቸው ደስተኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሃንዲስ ሻለቃ መጋቢ ባሻ ኢንጂነር ሲሳይ አበጋዝ እና ዳታ ኮሌክተር ምክትል አስር አለቃ መንፈሱ ገዴቻ የበላይ አካል ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ሰራተኞች ለሃያ አራት ሰዓት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ዲዛይኑን ጠብቆ በተቀመጠለት ጊዜ በፍጥነት እና በጥራት እንዲያልቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ሃያ ብሎኮች፣ጂ+3 እና ጂ+1 ፎቆች ያሉት ነው፡፡

ዘጋቢ አዳም ወንድማገኝ
ፎግራፍ ታሪኳ ብረሃኑ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍13🔥3
የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት የሚወጡ የፈጠራ ባለቤት ጀግኖችን አፍርተናል።                   
  ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የኦርዲናንስ መምሪያ፣ የአቅርቦት መምሪያና የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት፤ እንዲሁም ልዩ ልዩ ስታፍ ቡድኖች ስኬታማ እንቅስቃሴን አስመልክተው ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥተዋል።

የተቀበሉትን ግዳጅ በብቃት ከመተግበር ባለፈ ስራን የሚያቀሉ ፈጠራዎችን የሚሰሩ የሰራዊት አባላት  ማፍራታችን፤ ዕቅዶቻችን ስኬታማ እንዲሆኑ ጉልህ ድርሻ አላቸው ሲሉ በመርሃ- ግብሩ በእንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል ገልፀዋል።

በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ሙስጠፋ መሀመድ የሁሉም ክፍሎች የላቀ ትብብርና ዘመናዊ አሰራር፤ ዘርፈ ብዙ እምርታ እንዳስገኘ ተናግረዋል።

በዕለቱ ሃገራቸውን ለረጅም አመታት አገልግለው በክብር ለተሰናበቱ አባላት እንዲሁም በአመቱ በስራ አፈጻጸማቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አባላት ዕውቅና እና ሽልማት ተበርክቷል።

ዘጋቢ ዳዊት ብርሃኑ
ፎቶግራፍ በድሩ መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
23👍8👏2🔥1🥰1😭1