FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዓለም-ዓቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ለሴት መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ስልጠና ሠጠ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ለመከላከያ ሴት መስመራዊ እና ከፍተኛ መኮንኖች በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ለ3 ቀናት ያሠለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመርቋል።

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ ከዓለም-አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በጋራ በመስራታችን ደስተኞች ነን ብለዋል። ዛሬም ከፆታዊ እና ከወሲባዊ ጥቃት አንፃር ራስን ለመከላከል ምን ማድረግ አለብን በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ጥሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሥጠታቸው አመሥግነዋል።

ከመከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች እና እዞች የተውጣጡት ሰልጣኞቹ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ በተለይም በጦርነት ጊዜ ሴቶች እና ህፃናት ራሳቸውን ከፆታዊ እና ወሲባዊ ጥቃት መከላከል በሚችሉባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና መውሰዳቸው ከሙያቸው ባህሪ አንፃር ጠቃሚ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከሰልጣኞች መካከል ሻምበል እመቤት ጌታቸው እንደ አንድ ሴት የመከላከያ አባል ይህን ስልጠና በመካፈሌ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለሌሎች ጓዶች ለማከፈልም ፈቃደኛ ነኝ ብለዋል።

ሰልጣኞቹ ከየዕዞች እና ከመከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊዎች ሲሆኑ ስልጠናውን የወሰዱት ሰልጣኞች ሰልጠናው የሚያሰልጥኑ አሰልጣኞች ናቸው። ሰራዊቱ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ ስልጠናው እንዲዳረስ ስልጠኞች አስተዋፅኦቸው የጎላ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ ዕፀገነት ዴቢሰ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
27👍7🔥2
ኢንዱስትሪው የከተማ አውቶብሶችን፣ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን በጥራት እያመረተ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ  የቢሾፍቱ ሞተር  ቬሄክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ያመረታቸውን የከተማ አውቶብሶች፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ለአዳማ ከተማ አስረክቧል።

የኢንዱስትሪው ምክትል ሥራ አሥኪያጂ ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ተሰማ ኢንዱስትሪው፣ አሁን ላይ ከውጭ ሃገር በሚያስመጣቸው እቃዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጅን የተላበሱ፣ ከከተማ አውቶብስ ጀምሮ፣ ቀላልና ከባድ፣ ለቤትና ለመስሪያ ቤት አገልገሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን በጥራት እና በብዛት እያመረተ መገኘቱን ገልፀዋል።

ኢንዱስትሪው ከመኪና በተጨማሪ የተለያዩ ጀልባዎችን  እያመረተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የመኪና ቁልፍ ርክክብ ያደረጉት የአዳማ ከተማ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ትራንስፖርት ዳይሬክተር አቶ ከበደ አዱኛ የከተማ አውቶብሶች የዘመኑን የጥራት ደረጃ የጠበቁ ፣በጥራታቸው ተመዝነው የተረጋገጡ፣ መሆናቸውን መሥክረዋል።

በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ  ቢሾፍቱ ሞተር  ቬሄክልስ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የተመረቱት  የከተማ አውቶብሶች፣የቤትና የመስሪያ ቤት ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ በሃገር ውስጥ መመረታቸው
ወጭን ከመቀነስ ባሻገር የትራንስፖርቱን ዘርፍ ይበልጥ ለማሳለጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ተጠቁሟል።

ዘጋቢ ቢያድግልኝ መሪ
ፎቶ ግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
21👍11👏3😁2🔥1