FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.5K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ኮሩ ከዞን አስተዳደሮች ከፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መከረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም

የደቡብ ዕዝ ኮር ከምስራቅ ቦረና እና ከምስራቅ ጉጂ ዞን አስተዳደር እንዲሁም ከተለያዩ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች ጋር ባከናወናቸው ስኬታማ ተልዕኮዎች ዙሪያ ተወያይቷል።

በበጀት አመቱ ጥምር የፀጥታ ሃይሉ በቀጠናዉ የሸኔ አሸባሪ ሃይሎች ላይ በወሰደዉ ስኬታማ እርምጃ ተጨባጭ ዉጤት መመዝገቡን የኮሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ግርማ አየለ ተናግረዋል።

ባለፉት በርካታ ዓመታት ቡድኑ የሀገራችንን እድገት፤ ሰላምና አንድነት መናድ ከሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመሰለፍ ህዝባችን ላይ ግፍ መፈፀሙን ያነሱት ዋና አዛዡ፤ የጋራ ጥምር ሃይሉ በወሰዳቸው እርምጃዎች ፀረ ሠላም ሃይሎች ማንሰራራት ወደ ማይችሉበት ደረጃ ደርሰዋል ብለዋል።

በቀጥታም ይሁን በስዉር ተልዕኳቸውን መፈፀም የሚፈልጉ ርዝራዥ የቡድኑ አባላት ቢኖሩም በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ የማፅዳት ስራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከፍተኛ መኮንኑ አስረድተዋል።

የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን በበኩላቸው፤ ፀረ ሰላም ሃይሎች ህዝቡ ላይ ሲያደርሱት የነበረዉ ዘርፈ ብዙ መከራ በሰራዊታችንና በፀጥታ ሃይሉ ብርታት ተገትቷል ብለዋል።

በቀጠናው በፀረ ሰላም ሃይሎች እጅ የሚገኝ አንድም ቀበሌ አለመኖሩን ያመላከቱት ዋና አስተዳዳሪዉ፤  ተቋማት ተገቢዉን ግልጋሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ  እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዘጋቢ ፈይሳ መልካሙ
ፎቶግራፍ ሰለሞን በዛብህ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39👍13🔥3
ብቁ ሠልጣኞችን በማፍራቱ ረገድ የአሰልጣኞች ሚና ከፍተኛ መሆን እንዳለበት ተገለፀ።
        
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም
      
የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮነን በሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመገኘት ከአሰልጣኞች ጋር ተወያይተዋል።
  
ውትድርና በሳይንሳዊ ጥበብ ስልታዊ ታክቲክ እና ቴክኒክ ተጠቅመውበት በዘመናዊ የአመራር ዘዴ የሚመራ የተከበረ ሙያ መሆኑን ገልፀዋል።
    
ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮነን የፕሮፌሽናል ሰራዊት ግንባታ ሂደት ለማስቀጠል የአሰልጣኞች ሚና በስልጠና ጊዜ በሚያስተምሩበት ካሪኩለም ውስጥ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም አመላክተዋል ።
           
ወታደራዊ ሰልጠና እጅግ አቅምን የሚፈትሽ በውጤት የሚመዘን መሆኑን ጠቅሰው፤ አሰልጣኞች ዕውቀታቸውን እና ልምዳቸውን ተጠቅመው ከዘመኑ ጋር እየዘመኑ ተልዕኳቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል ።
     
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የረቀቀ ወታደራዊ የልህቀት ማዕከል በመገንባት ሁለንተናዊ ዝግጅቶችን አጠናክራ በመሥራት ላይ እንደምትገኝ የመከላከያ ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ተስፋዬ ያረጋል
ፎቶግራፍ አማረች አሌና

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
63👍13🔥2
የሜካናይዝድ ዕዝ ለአባላቱ ማዕረግ አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 03 ቀን 2017 ዓ.ም

የሜካናይዝድ ዕዝ የመቆያ ጊዘያቸውን ሸፍነው በሥራ አፈፃፀማቸው ውጤታማ ለሆኑ የዕዙ አባላት ማዕረግ አልብሷል።

ለተሿሚዎች ማዕረግ ያለበሱት የሜካናይዝድ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሜጀር ጀነራል ሙሉአለም አድማሱ እኛ የሜካናይዝድ ዕዝ ሀገር እና ተቋም የሰጡንን ታላቅ ሀገራዊ ሃላፊነት በተገቢው መንገድ እየተወጣን እንገኛለን ብለዋል።

ተሿሚዎችም ያገኛችሁት ማዕረግ ትልቅ ሃላፊነት መሆኑን ተረድታችሁ በአስተሳሰብ ራሳችሁን በማጎልበት የሀገርን ሰላም ማረጋገጥ የሚሠጣችሁን ተልዕኮ በድል በጀግንነት መፈፀም ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
42👍15
በመርሀ-ቤቴ ፊጥራ ንዑስ ወረዳ የሰላም ጥሪ ለተቀበሉ የፅንፈኛው አባላት አቀባበል ተደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 03 ቀን 2017 ዓ.ም

በሰሜን ሸዋ ዞን መርሀ-ቤቴ ፊጥራ ከተማ ላይ የሰላም ጥሪ ለተቀበሉ ከጫካ ለተመለሱ የፅንፈኛው አባላት አቀባበል በማድረግ ከህብረተሰቡ ጋር የጋራ ህዝባዊ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱም የአየር ወለድ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ማቲዎስ ማዴቦን ጨምሮ የሰሜን ሸዋ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ እና ሌሎችም የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።  አመራሮቹ የእርስ በእርስ ጦርነቱን አስወግደን የጋራ ዓለማ እና ልማታችንን በማፋጠን ህዝባችንን የመታደግ አደራና ግዴታ አለብን ብለዋል።

የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የፅንፈኛው ቡድን አባላት መንግስት የሰጠውን የሰላም ጥሪ በማድነቅ ፣ ጫካ የነበርን ለህዝባችን ሠላምን መርጠናል ከእንግዲህ ለሠላም ጠንክረን እንሠራለን ሲሉ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ፈለቀ ዋሲሁን
ፎቶ ግራፍ ኤፍሬም ታምራት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3126🥰8👎1
ዕዙ ተተኪ አመራሮችን የማፍራትና የማብቃት ሃላፊነቱን እየተወጣ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 03 ቀን 2017 ዓ.ም

ዕዙ ተተኪ አመራሮችን የማፍራትና የማብቃት ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ግዛው ኡማ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በግዳጅ ላይ ለሚገኙ ጥሩ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ  ለምስራቅ ዕዝ ስታፍ መስመራዊ መኮንኖች እና ባለሌላ ማዕረግተኞች ማዕረግ የማልበስ ስነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

በዕለቱ ለማዕረግ ተሿሚዎች ማዕረግ አልብሰው ንግግር ያደረጉት የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጄኔራል ግዛው ኡማ የዕዙ የሠራዊት አባላት በተሰማራበት ቀጠና ግዳጁን በላቀ ውጤት እየፈፀመ መሆኑን በመጥቀስ ተቋማችንና ዕዛችን ትግል የትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን በመገንዘብ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሞክሮ በመውሰድ ተተኪ አመራሮችን  የማፍራትና የማብቃት ሃላፊነታችንን እየተወጣን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሀገራችን ብሄራዊ ጥቅምና ሀገራዊ ፍላጎትን ለማሟላት እንደ ሠራዊት ቀጣይ ለሚሰጠን ግዳጅ ዝግጁ ለመሆን ከእናንተ ከአመራሮች ብዙ ይጠበቃል ያሉት ምክትል አዛዡ ማዕረግ መልበስ ማለት ለሚቀጥለዉ ሃላፊነት መዘጋጀት ስለሆነ ራስን በዲሲፕሊን በማነፅ  ወደፊት ትልቅ ሃላፊነት እንዳለባቸሁ አዉቃችዉ ስራችሁን መስራት ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ ታደሰ ይሴ
ፎቶ ግራፍ ማሩፍ ደስታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
39👍8
ለማዕከላዊ ዕዝ ስታፍ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 03 ቀን 2017 ዓ.ም

ስልጠናው በወታደራዊ የአመራርነት ክህሎት ላይ ትኩረቱን በማድረግ አካላዊና ስነ-አዕምሯዊ ግንባታዎችን አክሎ ተሰጥቷል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የስታፍ አመራሩን ያነጋገሩት የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ስልጠናው የስታፉ አመራር በተመደበበት የስራ ዘርፍ የቢሮ ስራዎችን ከመተግበርና ከማስተግበር ባሻገር በመስክ ስልታዊ እንቅስቃሴ ውጊያን መርቶ የመፈፀምና የማስፈፀም የላቀ ክህሎት ለመፍጠር አስችሎታል ብለዋል።

ዘመኑ የደረሰበትን የውትድርና ሳይንስ መረዳት ፣ ጊዜው የፈጠረውን የሳይኮሎጅ ጦርነት መገንዘብ ፣ ከሃሰት የፕሮፖጋንዳ ትርክት መጠበቅና በአንፃሩ ቴክኖሎጅውን ተጠቅሞ አስፈላጊ መረጃዎችን በማግኘት ፈጣን የኢንፎርሜሽን ልውውጥ በማከናወን ስታፉ ምን ጊዜም ከዘመን ጋር አብሮ መዘመን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የተዋጊው ሃይል ድል አድራጊነት በተግባር የሚረጋገጠው የስታፍ ክፍሉ በሚሰጠው ጠንካራ የድጋፍ አገልግሎት መሆኑን የጠቀሱት ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ተመራቂ አመራሮች ከስልጠና የተገኘውን አቅም ወደ ተግባር በመለወጥ የተሰለፋችሁለትን ሃገርና ህዝብ የመጠበቅ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ በቁርጠኝነት መፈፀም አለባችሁ ሲሉም አሳስበዋል።

የስልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የጊቤ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አርዓያ ገብረ በበኩላቸው የዕዙ ስታፍ አመራር በወሰደው ስልጠና በየትኛውም ቦታ ላይ ተመድቦ ለመስራት የሚያስችለውን ሁለንተናዊ አቅም መፍጠሩን ገልፀው ተጣጣፊና ሁለ ገብ ሆኖ  ተገንብቷል ሲሉ አረጋግጠዋል። ዘገባው የዕዙ ሚዲያ ቡድን ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
42👍18