FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
31 videos
9 files
8.47K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የትራንስፖርት መምሪያ ዝግጁነታችንን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ክፍል ነው።
ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን ኢስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን ኢስማኤል የሠራዊታችንን ሁለንተናዊ ዝግጁነት ለማረጋገጥ በሎጀስቲክስ ስር ያሉ ሁሉም ክፍሎች በቅንጅት የሚሠሩ ቢሆንም ትራንስፖርት መምሪያ ለየት ባለ የተዘጋጀውን ሁሉንም አቅርቦት ለሠራዊታችን በተፈላጊው ጊዜና ቦታ ኃላፊነት ወስዶ ተደራሽ በማድረግ እየፈፀመ ያለው ግዳጅ የሚያኮራ ነው ብለዋል።

የትራንስፖርት መምሪያ የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ለሁሉም የሰራዊት ክፍሎች እንዲደርስ እንዲሁም ዝግጁነታችንን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ክፍል መሆኑንም አንስተዋል።

በተቋማችን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሎጀስቲክስ እየተተገበሩ ያሉት የልማት ስራዎች አካል የሆነውን የትራንስፖርት ማዕከል ጽዱ፣ ውብና ለስራ የተመቸ በማድረጋቸው ጀኔራል መኮንኑ ምስጋና አቅርበው፤ በመምሪያው ውስጥ ያለው አሃዳዊ ፍቅር እና አንድነት የሚያኮራ እንደሆነ ገልጸዋል።

የትራንስፖርት መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ፍቃዱ ታደሠ በበኩላቸዉ ተቋማችን አስተማማኝ የሞቢሊቲ  አቅም መገንባቱን ተናግረው፤ መምሪያው የትኛውንም ግዳጅ በብቃት መወጣት የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ባለፈው በጀት አመት በሎጀስቲክስ ማዕከላት ግቢ ውስጥ ወጪ ቆጣቢና ዘመናዊ አሰራርን በመከተል ትርጉም ያለው የልማት ስራ መስራት መቻሉንም አንስተዋል።

በዕለቱ በግዳጅ አፈጻጸማቸው የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ የመምሪያው አባላት የምስጋና እና የዕውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

ዘጋቢ ዳዊት ብርሃኑ
ፎቶ ግራፍ በድሩ መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
38🔥4👍2
የተቋሙን ውጤታማ የለውጥ ጉዞ  በሳይበር ዘርፉም ለመድገም ተዘጋጅተናል።
  የሳይበር  ዋና ዳይሬክቶሬት አመራሮች 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክትሬት በበጀት ዓመቱ ላከናወናቸው ውጤታማ ተግባራት የዕውቅናና የምስጋና ዝግጅት አካሄዷል።

በዕለቱም ዕውቅናና ሽልማት ከተሰጣቸው  መካከል    የሳይበር ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ኮሎኔል ሀገር አስቻለ ፣ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን የሀገርና የተቋሙን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ቁመና እየተገነባ  እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በቀጣይም ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን በማከል የተጀመሩ  ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅና በሳይበር ዘርፉ የተመዘገቡ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

የሳይበር ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ኮሎኔል እስማኤል አብደላ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ስራዎችን በውጤታማነት በማከናወናቸው ለዕውቅና መብቃታቸውን ጠቁመው፣  በተለይም በሰው ሀይል ግንባታ፣ በሳይበር የስጋት ትንተና፣ በሳይበር እሴትና በፈጠራ ላይ በማተኮር የተሰሩት ስራዎች አበረታች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

በ2018 የበጀት ዓመት የተሻለ የስራ ዕቅድ በማውጣትና ለመፈፀም የሚያስችል ሁለንተናዊ አቅም መገንባቱንም ገልፀዋል።

የሳይበር አካላዊ ደህንነት ቡድን መሪ ተወካይ ሻለቃ ሀብታሙ ደሳለኝ፣ በራስ ተነሳሽነት ሶፍትዌር በማበልፀግና የተቋሙን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ የደህንነት ሶፍትዌር በራስ አቅም መስራታቸውንና የተቋሙን የለውጥ ጉዞ ለማገዝ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

በዓመቱ ብቁና ዲሲፒሊን ወጣት የሳይበር ባለሙያዎችን ለማብቃት በርካታ ስልጠናዎች ሲሰጡ መቆየታቸውን የገለፁት በዋና ዳይሬክትሬቱ የሳይበር ደህንነት ስልጠና ክትትል ኤክስፐርት ሻምበል ሲሳይ ዴሬሳ ፣ ስራዎችን በዕውቀትና በዲሲፕሊን የሚሰሩ ባለሙያዎችን የማፍራትና የራስን አቅም የማሳደግ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍12🔥3
የምዕራብ ዕዝ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አመራርና አባላቱ ማዕረግ አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

ለተሿሚዎች ማዕረግ ያለበሱት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት የማዕረግ ሹመቱ አመራሩን ለተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም የሚያነሳሳና ተጨማሪ ሃላፊነት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

ዕዙ በአመቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎች ማከናወኑን ገልፀው በዚህ ሂደትም የሃምሌ ወር ማዕረግ ተሿሚዎች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰዋል።

የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አመራርና አባላት ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ጊዜ ፈተናዋን በድል እንድትወጣ ያደረገ ጀግና ሠራዊት በመሆኑ ይህን አኩሪ ድል ለመድገም ተሿሚዎች ከፍተኛ ሃላፊነት አለባችሁ ብለዋል።

ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ግዳጃችን ሰፊና ውስብስብ ቢሆንም ሀገራችን የኛን ጥንካሬ የምትፈልግበት ጊዜ በመሆኑ ህዝባዊ አለኝታነታችንን በተግባር በማሳየት የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ማዕረግ ተሿሚዎች ድርብ ሀላፊነት እንደተሰጣቸው በማሰብ በቀጣይ ለተሻለ ውጤት ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶ ግራፍ  ሽመልስ እሸቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
40🔥6👍3🥰1
የዉጊያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸውን የከባድ መሳሪያ ምድብተኞች አስመረቀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የትምህርት ቤቱ  አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ታየ አለማየሁ፣ ተመራቂዎች የህዝብ ኩራትና የሃገር መከታ መሆናቸውን ገልፀው ፣    በሰለጠኑበት ሙያ ጠንክረው ተቋሙንና ሀገራቸውን በማገልገል የሃገርን ክብርና ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ እንደሚኖርባቸው አመላክተዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ምክትል አዛዥ ለሥልጠና ሃላፊ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ዳዊት ዳኛቸዉ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ ብቁና አስተማማኝ የሆኑ የሜካናይዝድ ሙያተኞችን እያፈራ በመሆኑ ተመራቂ ምድብተኞች የዚሁ አንድ ማሳያ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በዕለቱ በስራ አፈፃፀማቸው የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አባላት
ማዕረግ የማልበስ ስነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ ዘጋቢ ሃይሉ ምንአየ ነው።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የመቆያ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ እና በስራ አፈፃፀማቸው ብልጫ ላስመዘገቡ የአካዳሚው አባላት የመዓረግ ማልበስ እና የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ አሰልጣኝ መኮንኖች የዕውቅና ስነ-ስርዓት አከናውኗል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ለተሿሚዎች ማዕረግ ያለበሱት እና ሰርተ-ፊኬት የሠጡት የአካዳሚው አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተመስገን አቦሴ ተሿሚዎች የማዕረግ ዕድገት ተጨማሪ ግዳጅና ሃላፊነት መቀበል በመሆኑ በቀጣይ ስራችሁ ህዝብና መንግስት የሰጧችሁን አደራ ከምንጊዜውም በላይ በመጠበቅ በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል። ዘጋቢ ፍቃዱ ጆቴ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2919👏12🔥5🥰1