FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
33 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዕዙ የመመልመያ መሥፈርቱን ላሟሉ አባላቱ ማዕረግ  አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ  የመቆያ ጊዜአቸዉን ሸፍነዉ ውጤታማ  የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ከፍተኛ እና መስመራዊ መኮንኖች እንዲሁም ባለሌላ ማዕረግተኞች ማዕረግ አልብሷል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዉ ተሿሚዎችን ማዕረግ ያለበሱት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል በርጋዲየር ጄኔራል አበባው ሰይድ የማዕረግ እድገት ማለት ከብዙ የስራ ድካም  እና ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ የሚገኝ ዉጤት መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕረግ ጊዜዉን ስለሸፈነ ብቻ የሚሰጥ አይደለም ስለዚህ ሁሉም አመራር ዘወትር በተመደበበት ሀለፊነት በመትጋት ውጤት ማስመዝገብና የሚመራዉን ተመሪ በሚገባ ማወቅ እና በስራዉ በመለካት ከአቻዎቹ የሚወዳደርበትን መንገድ መፍጠር አለበት ብለዋል።

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የሰዉ ሃብት እድገት እና ስምሪት ቡድን መሪ ኮሎኔል ሞላ አሻግሬ በበኩላቸዉ በማዕረግ ለማደግ ሁሉም ሰዉ ትርጉም ያለዉ ስራ መስራት እንዳለበት ጠቁመው መሥፈርቱን አሟልቶ መገኘት  እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ ምህረት ስመኝ
ፎቶ ግራፍ አብዱራህማን ሃሰን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
43👍6🔥1😁1
ዋና ዳይሬክቶሬቱ በበጀት ዓመቱ ስኬታማ የግንባታ ስራ አከናውኗል።
ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት
እንደ ተቋም በየወቅቱ እየታዩ ያሉ አካባቢያዊና ሀገራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት የግንባታ ሥራውን የመደገፍ ፣የሚሰጡትን ሥራዎች የበላይ አካልን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ አግባብ በመፈፀም ስኬታማ የግንባታ ስራ ማከናወኑን የዋና ዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን ገልፀዋል፡፡

በመከላከያ ሚዲያ የሠራዊቱን የዕለት ተዕለት የግዳጅ አፈፃፀምና ውጤቶች፣ የፀረ ሠላም ሀይሎችን እንቅስቃሴ፣ አጠቃላይ የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ተግባራት፣ የሀገራችንን የሠላም ማሥከበር ተልዕኮ ሚና፣ የሠራዊቱን እና የህብረተሠቡን አንድነት እንዲሁም ሌሎችንም ተቋማዊና ሀገራዊ ጉዳዮች በመዘገብ ለአድማጭ ተመልካች ብሎም ለንባብ ተደራሽ የሆኑ ሳቢ የሚዲያ ሥራዎች በበጀት ዓመቱ መሠራታቸውንም አሥረድተዋል፡፡

የሠራዊት ግንባታ ሰነዶች እንዲዘጋጁ እና ሠራዊቱ እንዲወያይበት በማድረግ በሠራዊቱ የሚታዩ ዝንባሌዎችን ለማስተካከል ጥረት ተደርጓል ያሉት ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ከሁነት ተኮር ፅሁፍ አኳያ የሚከበሩ በዓላትን በመንተራስ ፅሁፎችን በማዘጋጀትና ሠራዊቱን በማወያዬት የተዛቡ አመለካከቶችን ማሥተካከልና መቅረፍ መቻሉንም አንስተዋል፡፡

የመቻል ስፖርት ክለብ ምንም እንኳ በአዋቂ ወንዶች እግር ኳስ በፕሪሜርሊጉ የተፈለገውን ያህል ነጥብ መሠብሰብ ባይቻልም የመከላከያ ሠራዊትን የወከለ ተቋም በመሆኑ አንዱ የሠራዊታችን የግንባታ አካል አድርጎ በመውሰድ በሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች ሠራዊቱን እና ደጋፊውን የሚያሥደስት ውጤታማ ውድድሮችን ማከናወኑን ተናግረዋል።

የኪነ-ጥበብ ዘርፉን ለሰራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ለመጠቀም በተለያዩ ዝግጅቶችና በዓላት ሰራዊቱን በመቀስቀስ በማዝናናት፤ ታላላቅ እንግዶችን የውጪ ሀገር መሪዎችን ዲፕሎማቶችን በመቀበልና በመሸኘት በማርች ባንድና በክብር ዘብ በርከት ያሉ ስራዎች ተከናዉነዋል፡፡

የመከላከያ ኪነ ጥበባት ሥራዎች ከሁለት ዓመት በላይ ያሥተማራቸውን የሙዚቃ ሙያተኞች በዋና ዳይሬክቶሬቱ ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ማጠቃለያ ላይ ያሥመረቀ ሲሆን ከተለያዩ ማሠልጠኛ ማዕከላት፣ ከዕዞችና ከአየር ሀይል የመጡ ከ70 በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመማር ላይ ሥለመገኘታቸውም ተገልጿል።

ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን የተጀመሩ ሥራዎችን መጨረስ ፤የነበሩ ሥራዎችን ማዘመን አዳዲስ መፍጠር በቀጣይ ከሁሉም የመከላከያ ሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት አመራርና አባላት እንዲሁም ሲቪል ሠራተኞች የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ ይበልጥ ልንተጋ ይገባል ብለዋል።

በዕለቱ ሥልጠናቸውን ለሁለት ዓመት የተከታተሉ የኪነ ጥበባት ሙያተኞች የተመረቁ ሲሆን የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑ የዋና ዳይሬክቶሬቱ አመራርና አባላት ማዕረግ እንዲለብሱ ተደርጓል። ለበርካታ ዓመታት በኪነጥበባት ዘርፍ ሥልጠና ሲሰጡ የቆዩ ዕውቅ መምህራኖችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ
          
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👏21👍5🔥1
የመከላከያ ሠራዊት ለመቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረጉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት ከ1.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የሠራዊት አባላቱ ማዕከሉን በመጎብኘት ማዕድ አጋርተዋል። በየዓመቱ ሐምሌ 29 ቀን በመቄዶንያ የመከላከያ ቀን ተደርጎ የሚታሰብ ሲሆን ሠራዊቱም ልዩ ልዩ ድጋፎችን ያደርጋል።

በተለያዬ መልኩ ለሀገር ዋጋ የከፈሉ ጧሪ የሌላቸው እናቶችንና አባቶችን መደገፍ ከመላው ዜጋ የሚጠበቅ ነው ያሉት የመከላከያ ሴቶችና ማህበራዊ  ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ ሠራዊታችን ለሀገሩ መስዋዕትነት እየከፈለ ሰላምን እያረጋገጠ ህዝባዊነቱንም በተግባር እያስመሰከረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መቄዶንያ አሁን ላይ ከ8500 የሚበልጡ አረጋዊያንን  እየተንከባከበ እንደሚገኝ የገለፁት የመቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል መሥራችና ኃላፊ የክብር ዶክተር ቢንያም በለጠ ከሕዝብ አብራክ የተገኘው የመከላከያ ሠራዊት በማዕከሉ በየዓመቱ በጎ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ለሠራዊቱ ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡት ዶክተር ቢኒያም መከላከያ ይህን በጎ ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥልና የተለያዩ ሚኒስቴር ተቋማትም ተሞክሮ በመውሰድ መሰል በጎ ተግባር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ አስማረወርቅ አስታወሰኝ
ፎቶግራፍ ሠናይት ኃይለኢየሱስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👍11🔥2