FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ማዕከሉ የዕውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል ለተሿሚዎችም ማዕረግ አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ግሩፕ እና የመከላከያ ዲያግኖስቲክስ ማዕከል ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ሽዋዬ ሃይሌ ለላቀ የስራ አፈጻጸም ሽልማትና እውቅና መስጠቱ በሰራዊቱና በሲቪል ሰራተኞች መካከል የላቀ የስራ ተነሳሽነት ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ብርጋዲየር ጀኔራል ሸዋዬ ሃይሌ የእውቅና ፕሮግራሙ ለሁሉም  የላቀ ተነሳሽነት እንዲፈጥር እና ሆስፒታሉ ካለበት ደረጃ ከፍ በማለት የላቀ አገልግሎት እንዲሰጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ እምነቴ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

እውቅና መስጠት ሰራተኞች ለስራቸው ልዩ ትኩረት እንዲሰጡና የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ የሚያበረታታ መሆኑንም ገልፀዋል።

በሐምሌ ወር የመቆያ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ እና በላቀ የሥራ አፈፃፀም የተመዘኑ የሰራዊት አባላትን ማዕረግ የማልበስ መርሃ ግብርም ተከናውኗል።

ተሿሚዎች ማዕረግ ያገኙት ጊዜያቸው ስለደረሰ ብቻ ሳይሆን ካሳለፉት የአገልግሎት ዘመን ባሳዩት መልካም ስነ-ምግባርና በግዳጅ አፈፃፀማቸው የተሻሉ በመሆናቸው መሆኑን የገለፁት ብርጋዲየር ጄኔራል ሽዋዬ ሃይሌ ቀጣይ የበለጠ መሥራት እና የተሻለ ውጤት ማሥመዝገብ እንደሚጠበቅባቸውም አሥገንዝበዋል። ዘገባው የማዕከሉ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው
 
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31🥰15👍12🔥1
ዕዙ የመመልመያ መሥፈርቱን ላሟሉ አባላቱ ማዕረግ  አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ  የመቆያ ጊዜአቸዉን ሸፍነዉ ውጤታማ  የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ከፍተኛ እና መስመራዊ መኮንኖች እንዲሁም ባለሌላ ማዕረግተኞች ማዕረግ አልብሷል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዉ ተሿሚዎችን ማዕረግ ያለበሱት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል በርጋዲየር ጄኔራል አበባው ሰይድ የማዕረግ እድገት ማለት ከብዙ የስራ ድካም  እና ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ የሚገኝ ዉጤት መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕረግ ጊዜዉን ስለሸፈነ ብቻ የሚሰጥ አይደለም ስለዚህ ሁሉም አመራር ዘወትር በተመደበበት ሀለፊነት በመትጋት ውጤት ማስመዝገብና የሚመራዉን ተመሪ በሚገባ ማወቅ እና በስራዉ በመለካት ከአቻዎቹ የሚወዳደርበትን መንገድ መፍጠር አለበት ብለዋል።

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የሰዉ ሃብት እድገት እና ስምሪት ቡድን መሪ ኮሎኔል ሞላ አሻግሬ በበኩላቸዉ በማዕረግ ለማደግ ሁሉም ሰዉ ትርጉም ያለዉ ስራ መስራት እንዳለበት ጠቁመው መሥፈርቱን አሟልቶ መገኘት  እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ ምህረት ስመኝ
ፎቶ ግራፍ አብዱራህማን ሃሰን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
43👍6🔥1😁1
ዋና ዳይሬክቶሬቱ በበጀት ዓመቱ ስኬታማ የግንባታ ስራ አከናውኗል።
ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት
እንደ ተቋም በየወቅቱ እየታዩ ያሉ አካባቢያዊና ሀገራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት የግንባታ ሥራውን የመደገፍ ፣የሚሰጡትን ሥራዎች የበላይ አካልን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ አግባብ በመፈፀም ስኬታማ የግንባታ ስራ ማከናወኑን የዋና ዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን ገልፀዋል፡፡

በመከላከያ ሚዲያ የሠራዊቱን የዕለት ተዕለት የግዳጅ አፈፃፀምና ውጤቶች፣ የፀረ ሠላም ሀይሎችን እንቅስቃሴ፣ አጠቃላይ የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ተግባራት፣ የሀገራችንን የሠላም ማሥከበር ተልዕኮ ሚና፣ የሠራዊቱን እና የህብረተሠቡን አንድነት እንዲሁም ሌሎችንም ተቋማዊና ሀገራዊ ጉዳዮች በመዘገብ ለአድማጭ ተመልካች ብሎም ለንባብ ተደራሽ የሆኑ ሳቢ የሚዲያ ሥራዎች በበጀት ዓመቱ መሠራታቸውንም አሥረድተዋል፡፡

የሠራዊት ግንባታ ሰነዶች እንዲዘጋጁ እና ሠራዊቱ እንዲወያይበት በማድረግ በሠራዊቱ የሚታዩ ዝንባሌዎችን ለማስተካከል ጥረት ተደርጓል ያሉት ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ከሁነት ተኮር ፅሁፍ አኳያ የሚከበሩ በዓላትን በመንተራስ ፅሁፎችን በማዘጋጀትና ሠራዊቱን በማወያዬት የተዛቡ አመለካከቶችን ማሥተካከልና መቅረፍ መቻሉንም አንስተዋል፡፡

የመቻል ስፖርት ክለብ ምንም እንኳ በአዋቂ ወንዶች እግር ኳስ በፕሪሜርሊጉ የተፈለገውን ያህል ነጥብ መሠብሰብ ባይቻልም የመከላከያ ሠራዊትን የወከለ ተቋም በመሆኑ አንዱ የሠራዊታችን የግንባታ አካል አድርጎ በመውሰድ በሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች ሠራዊቱን እና ደጋፊውን የሚያሥደስት ውጤታማ ውድድሮችን ማከናወኑን ተናግረዋል።

የኪነ-ጥበብ ዘርፉን ለሰራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ለመጠቀም በተለያዩ ዝግጅቶችና በዓላት ሰራዊቱን በመቀስቀስ በማዝናናት፤ ታላላቅ እንግዶችን የውጪ ሀገር መሪዎችን ዲፕሎማቶችን በመቀበልና በመሸኘት በማርች ባንድና በክብር ዘብ በርከት ያሉ ስራዎች ተከናዉነዋል፡፡

የመከላከያ ኪነ ጥበባት ሥራዎች ከሁለት ዓመት በላይ ያሥተማራቸውን የሙዚቃ ሙያተኞች በዋና ዳይሬክቶሬቱ ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ማጠቃለያ ላይ ያሥመረቀ ሲሆን ከተለያዩ ማሠልጠኛ ማዕከላት፣ ከዕዞችና ከአየር ሀይል የመጡ ከ70 በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመማር ላይ ሥለመገኘታቸውም ተገልጿል።

ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን የተጀመሩ ሥራዎችን መጨረስ ፤የነበሩ ሥራዎችን ማዘመን አዳዲስ መፍጠር በቀጣይ ከሁሉም የመከላከያ ሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት አመራርና አባላት እንዲሁም ሲቪል ሠራተኞች የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ ይበልጥ ልንተጋ ይገባል ብለዋል።

በዕለቱ ሥልጠናቸውን ለሁለት ዓመት የተከታተሉ የኪነ ጥበባት ሙያተኞች የተመረቁ ሲሆን የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑ የዋና ዳይሬክቶሬቱ አመራርና አባላት ማዕረግ እንዲለብሱ ተደርጓል። ለበርካታ ዓመታት በኪነጥበባት ዘርፍ ሥልጠና ሲሰጡ የቆዩ ዕውቅ መምህራኖችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ
          
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24👏21👍5🔥1