FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ሰላምን በሰላማዊ መንገድ መገንባት ዋነኛ የሠላም አስከባሪው ሚና ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ሱዳን የዮናሚስ ሴክተር ሳውዝ አዛዥ በዌስት ኢኳቶሪያ ቀጠና ታምቡራ ከሚገኙ የደቡብ ሱዳን የሠራዊት አመራሮች ጋር መክረዋል።

በደቡብ ሱዳን የዮናሚስ ሴክተር ሳውዝ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ዴኒሽ ሲንግ ሰላምን በሰላማዊ መንገድ መገንባት ዋነኛ የሠላም አስከባሪ ሀይል ቀዳሚ ተግባር  እንደሆነ ተናግረው በቀጠናው የተሠማሩ የ21ኛ  ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት አሰቀድመው ግጭት እንዳይፈጠር በመከላከል ረገድ አመርቂ ስራ አከናውነዋል ብለዋል።

በአካባቢው የተገነባው ሰላም ዘላቂነት እንዲኖረው ከደቡብ ሡዳን ሠራዊት አመራሮች እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት እንዲሁም ከማሕበረሰቡ ጋር በቅንጅት መስራታቸው ለውጤት እንዳበቃቸውም ጀኔራል መኮንኑ መስክረዋል።

በታምቡራ የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሠራዊት አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጀምስ ናንዱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ምን ጊዜም ግዳጁን በብቃት እንደሚወጣ ተናግረው ሠራዊቱ በታምቡራ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖችን ለመጠበቅ ዘወትር ያለ እረፍት በሚፈፅሙት ግዳጅ ሕብረተሰቡ የሠለም ዋስትና እያገኘ በመሆኑ አሁንም ሠራዊቱ ተልዕኮውን አጠናክሮ  እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ተካ
ፎቶ ግራፍ ግርማቸው አብረሀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
29👍7🔥1
የመቻል ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ቡድን የውድድር አመቱን በድል አጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር መቻል ኦሊማይንድን 5ለ3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የውድድር አመቱን በድል አጠናቋል።

መቻል ባለድል የሆነበትን አምስት ጎሎች ማርሲላስ ወንድማገኝ ዛኪር ኑረዲን ፣ በእሱፍቃድ ገረመው ፣ ያፌት መኮነን እና ኪሮቤል ከመረብ አሳርፈዋል።

የዛሬውን ድል ተከትሎ የመቻል ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ቡድን 39 ነጥብ እና 37 ተጨማሪ ጎል በመያዝ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።

በውድድሩ ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስ አንደኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛ ፣ መቻል ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

የመቻል ከ17 ዓመት በታች እግር ኳስ ቡድን የኳስ ክህሎት ያላቸውን ተጫዋቾች አቅማቸውን አውጥተው እንዲጫወቱ በማድረግ እና የአሸናፊነት መንፈስ እንዲይዙ በማድረግ በቀጣይ ከ20 ዓመት በታች እግር ኳስ ቡድን ተተኪ የሚሆኑ ተጫዋቾችን መፍጠር ችሏል።

በጨዋታው ላይ የመቻል ስፖርት ክለብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን እና ሌሎች የክለቡ ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተው ቡድኑን አበረታትተዋል። ዘጋቢ ገረመው ጨሬ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
36👍6👏4🔥3👎1
የኢትዮ- ጂቡቲ መከላከያ የጋራ ኮሚቴ ለቀጣይ ዓመት  የሚያከናውኗቸውን የሠላምና ደህንነት ስራዎች የተመለከተ  ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እና የጅቡቲ መከላከያ የጋራ ኮሚቴ የጋራ ተጠቃሚነት መከባበርና መተማመን ላይ በተመሠረተ መርህ አብረው በሚሰሯቸው የሠላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ነው በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል  ስምምነቱን የተፈራረሙት።

የጅቡቲና የኢትዮጵያ የጋራ  መከላከያ ኮሚቴ በፀጥታና ደህንነት በመረጃ ልውውጥ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርንና  ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚያስችሏቸው ተግባራት ላይ ውይይት በማድረግ ነው ስምምነት ላይ የደረሱት።

የመከላከያ ውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹና የጂቡቲ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ ኮሎኔል ማጆር  አብዱረህማን  አብዲ   ስምምነቱን ፈርመዋል።

የመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹ
በዚህ ቀጠና አብሮ እንደሚኖር ወዳጅ ሀገር የጋራ ተጠቃሚነታችንን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራታችን በቀጠናው ያለውን ተግዳሮት አሸንፎ ለመውጣት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።

የሁለቱ ሀገራት የጋራ መከላከያ ኮሜቴ  ባለፈው ዓመት ሊተገብሯቸው  ተስማምተውባቸው የነበሩትን ጉዳዮች የገመገሙ ሲሆን  ሁለቱም ሀገራት  ጥሩ አፈፃፀም እንደነበራቸውም ገልፀዋል።

የጋራ ጥቅማችን ላይ በተመሠረተው ግንኙነታችን መሠረት የተደረገውን ስምምነት የሁለቱ ሀገራት የፀጥታ ተቋመት ተግባራዊነቱን በጋራ እንደሚከታተሉም ሜጄር
ጄነራል ተሾመ ገመቹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የጅቡቲ መከላከያ ሰራዊት ግንኙነት በጅቡቲ እና በኢትዮጵያ መካከል ካለው ሰፊ ግንኙነት ጋር የተያያዘ ነው ያሉት ደግሞ 
የጅቡቲ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ ኮሎኔል ማጆር  አብዱረህማን  አብዲ ናቸው።

ሁለቱ ሀገራት ያደረጉት ስምምነት ለቀጠናው የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑንም ኮሎኔል ማጆር  አብዱረህማን ገልፀዋል።

ዘጋቢ አብዮት ዋሚ
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2719👏2🔥1
የምዕራብ እና የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አመራርና አባላት  የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም 

"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ  እየተተገበረ በሚገኘው  የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ላይ ከፍተኛ የክልል አመራሮች የምዕራብ እና የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አመራርና አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።

‎በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአፋር ክልሉ ፕሬዘዳንት  ሀጂ አወል አርባ   እስካሁን የተተከሉ ችግኞች ፍሬ አፍርተው  የፍራፍሬ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው ፣ የአረንጓዴ አሻራው ትግበራ የክልሉ ነዋሪዎችና የአርብቶ አደሮቹ  ልምድ እንዲያረጉት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዘንድሮው መርሀ ግብር የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት  ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ከአረንጓዴ አሻራ በሻገር የምግብ ሉዓላዊነት ለማስከበር እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በምዕራብ ዕዝ ችግኝ ተካላ መርሀ ግብር የተገኙት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት የዕዙ ጠቅላይ መምሪያ አባላት እና አመራሮች ከቀደመ ጊዜ ጀምሮ አረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ መምጣታቸውን በመግለፅ የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ ማለት የአካባቢ ስነ-ምህዳርን ማስጠበቅ በመሆኑ ሠራዊት የሀገሩን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በአካባቢያዊ ጥበቃ ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ምዕራብ  ዕዝ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ሁሉም የዕዙ አመራሮች እና አባላት በየግዳጅ ቀጠናቸው እየተከሉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። 

የነቀምት ከተማ ከንቲባ አቶ ምስጋናው ቱሉ በበኩላቸው   የፀጥታ ኃይሉ ለሀገር እና ለህዝብ ከሚከፍለው መስዋትነት ባሻገር በልማቱ መሳተፍ እጅግ ሊመሰገን እንደሚገባው ገልፀዋል። ዘገባው የቀረአለም አዱኛ እና የፍፁም ከተማ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2216👏2🔥1