አንተዛዘብ‼
=========
✍ «'ካሁኑ የጮኸ ጂብ አያሳድረኝም» እንዲሉ አበው፤ የመጅሊስ ለውጥ ተደረገ ብለን ሳንጨርስ ገና ከአሁኑ ለአንድ ተራ ነገር በዚህ ደረጃ መፍረክረክ ተገቢ አይመስለኝም። ባለፈ ቅዳሜ የአዲስ አበባ መጅሊስ በአል-ዐንሲ መስጂድ ዙሪያ የምክር ቤት አባላቱን ሰብስቦ ስላደረገው ሹራ ጭብጥ የሚናገር የድምፅ ቅጅ ተልኮልኝ አዳመጥኩት። በጣም ነው ያፈርኩት። እስከ ዛሬ መስጂዶቻችንን የሚተናኮሱን የሌሎች እምነት ተከታዮች የሆኑ ጽንፈኞች ነበሩ። መጅሊሱ ለእንዲህ አይነቶቹ ትንኮሳ ከለላ ይሆነናል ብለን ስንጠብቅ ጭራሽ የመስጅድን ቦታ የሚያራቁት ከሆነ ጠቃሚያችን ሳይሆን ጎጂያችን ሊሆን ነው ማለት ነው። «ለዚህ ለዚህ'ማ ምን አለኝ ሃገሬ!» እንዲሉ፤ ለእንዲህ አይነቱ'ማ ከለውጡ በፊት የነበረው መጅሊስስ ከዚህ የባሰ ምን አደረገ?
የአዲስ አበባ መጅሊስ በዕለቱ ለግለሰቡ 500 ካሬ ገደማ እንስጠው ብለው እዛው ተወያይተው ከጨረሱ በኋላ ውሳኔውን አሳውቀው ለማስፈረም ነበር አባላቱን የሰበሰበው። ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ሐሰን ፈዽሉና የባዩሽ መስጂዱ ሸይኽ ዐብዱ-ስ'ሰላም አንዋር እንዲሁም ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ጉዳዩን መቃወማቸው ታውቋል። አላህ ይጠብቃቸው። ዓሊም ለማንም ሳይሸለጠለጥ ሐቅን ፊት ለፊት የሚናገርና ሐሰትን የሚጋፈጥ ነው።
√ ቦታው ወይ የግለሰቦቹ ነው ወይም ወቅፍ ነው። የግለሰቦቹ ነው ከተባለ ሐቃቸውን ካለፈቃዳቸው ለመስጂድ ማዋል ፈፅሞ አይቻልም። ወቅፍ ነው ከተባለ ደግሞ በየትኛውም መልኩ ለመስጅድ የተሰጠውን ወቅፍ ለግለሰቦቹ አይሰጥም። ዝም ብሎ ታላላቅ ዓሊም ነን በሚል ሽፋን ብቻ ለማስፈራራት «ኢጅቲሃድ» ብለው የመሃል ሰፋሪ ውሳኔ መወሰን አይችሉም። ይህን ለመናገር ታላቅ ዓሊም መሆን አይጠበቅም። ጉዳዩ ጥልቅ ሸሪዓዊ ግንዛቤን የሚጠይቅ ሳይሆን መሠረታዊ የዲን ዕውቀት ያለው ሰው ራሱ የሚፈርደው የማያሻማ ጉዳይ ነው።
♠
ለማንኛውም፦ «የት ይደርሳል የተባለውን ዛፍ ቀበሌ ቆረጠው!» እንዲሉ፤ ለብዙዎች ችግሮች መፍትሄ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው የመጅሊስ ለውጥ በአንድት ተራ ጉዳይ እንዳይመክንና እንዳንተዛዘብ፤ ጉዳዩ ከአዲስ አበባ መጅሊስ አቅም በላይ ከሆነ የፌዴራሉ መጅሊስ ጣልቃ ገብቶ ተገቢውን ማስተካከያ ሊሰጥ ይገባል። ምክንያቱም የአዲስ አበባ መጅሊስ ያልተገባ ውሳኔ ይፋ ከተደረገ አሉታዊ ተፅዕኖው ወደ ፌዴራልና ወደ ክልል መጅሊሶችም የሚዛመት ነው።
የአዲስ አበባ መጅሊስ ለግለሰቡ ካዘነለት፤ አቅሙ ከሌለው ህዝቡን እርዱኝ ብሎ ገንዘብ ያዋጣና ለግለሰቡ ሌላ ተለዋጭ ቦታ ይሰጠው እንጂ ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ላይ አንድትም ኢንች የመስጠት መብት የለውም። ከተወቀፈ በኋላ የአላህ ነው። ማንም አያገባውም። እንዳውም የአዲስ አበባ መጅሊስ እዛ አካባቢ ያለውን የመስጅድ እጥረት ታሳቢ አድርጎ ለግለሰቡ ምትክ ካስፈለገ ሰጥቶ መስጂዱን በተሻለ ጥራትና ስፋት በማስገንባት ሰፊና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እንዲሰጥ ተቋማዊ ሚናውን መወጣት ይጠበቅበታል። በፍጹም በዚህ ቀላል ነገር ትልቅ ነጥብ እንዳትጥሉ። አንዳንድ አቋመ ዥዋዥዌ የሆኑ አክቲቪስቶችን ተማምናችሁ ሐቁን በድምፅ ብልጫ እንቀብረዋለን ካላችሁ፤ በአንካፋ ብትቀብሩት በማንካ እንደምናወጣው ስነግራችሁ በሙሉ ልብ ነው። ያቺኑ የተለመደች «መድኸሊይ» የምትል ካርድ በመምዘዝም ይሁን በእስርና ዛቻ ማንም ከሐቁ ዘንበል አይልም። ይህ ስህተታችሁ መልካም ሥራችሁንም ይዞት እንዳይጠፋ በደንብ አስቡበት። በጉዳዩ ላይ አጂቲሃዳችሁን ወደ ጉድጓድ ክተቱትና ሐቁን ብቻ ተግብሩ። አላህን እንፍራ‼
መልካም ስትሠሩ ከጎናችሁ እንደምንቆመው ሁሉ ካጠፋችሁ ደግሞ የማንቃወምበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ለናንተም የሚጠቅማችሁ ስታጠፉ በሐሰትና በብዥታ ፈጠራ የሚከላከልላችሁና የሚወግንላችሁ ሳይሆን ስህተታችሁን የሚያርማችሁ ነው። ይልቅ በዚህ ተራ ነገር የመነቋቆሪያ አጀንዳ ተከፍቶ የመጅሊሱን ለውጥ ለማይፈልጉ አካላት በር ከመክፈት ይልቅ፤ ኡማው በውስጣዊ ንትርክ ሳይጠመድ ከፍ ባሉ አጀንዳዎች ላይ እንዲያወራና በጋራ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሳተፍ አድርጉ። ከወዲሁ አንተዛዘብ‼
♠
Cc:
====
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Murad tadess tellegram chanal

የሆነ ነገር ማድረግ ፈልገህ ሰዎች ምን ይሉኛል ወይ ደግሞ ፍርሀት ሲሰማህ እንዲህ ብለህ ለራስህ ንገረው "አንድ አይን ያለው በአይን አይቀልድም፤ አንድ ህይወት አለኝ ያመንኩበትን አደርጋለሁ!"
ሁሉም የሚኖረው አንተ ስትኖር ነው፤ ታዲያ አንተ የምትፈልገውን ካላደረክ፣ አንተ ራስህን ካልሆንክ ሌላ ማን እንዲሆንልህ ትፈልጋለህ? ወዳጄ እንዲ የሚያስቡ ሁሉ የተሻለ የአይምሮ ሰላም አላቸው፤ ውስጥህ እየወቀሰህ እስከመቼ ትኖራለህ? አንተም እኮ ይሄ የአይምሮ ሰላም ይገባሀል!
https://t.me/faruk126g

Telegram
Faruk media_ ፋሩቅ ሚድያ
የቻናሉ አላማዎች
1, ቁርአን እና ሀድስ በሰለፎች አረዳድ
2, የተላያዩ የሱና ኡስታዞች ደርሶች
3, ዳዓዋዎች
4, ፈተዋዎች
1, ቁርአን እና ሀድስ በሰለፎች አረዳድ
2, የተላያዩ የሱና ኡስታዞች ደርሶች
3, ዳዓዋዎች
4, ፈተዋዎች
ጠንከር በል!
አንዳንዴ የዋንጫ ቡድን ይሸነፋል፤ ጀግና ተደብቆ ያለቅሳል፤ ብርቱ ሰው ይዝላል፤ ጎበዝ ሰው ይሰንፋል፤ አንዳንዴ የማይሆነው ሁሉ ይሆናል።
የመሸነፍ ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርጉ ከባድ ጊዜያት ይመጣሉ ግን ለዘላለም አይዘልቁም፤ የመጡት ሊያፉ ነው። ወዳጄ ብቻህን አይደለህም ሁሌም ሲስቅ የምታየው ሰው አንዳንዴ እንዳንተ ይደክማል። ሁሉም ያልፋል፤ ጠንከር በል!
ታላቀ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏

መቀጠል ብቻ ነው ምርጫህ!
በየቀኑ የምትለፋቸው ትናንሽ ልፋቶች ትልቁ ምኞትህን እውነት ያደርጉታል፤ አሁን የማይመስሉህ ነገሮች የሚሳኩት ጥረትህን ካላቆምክ ነው።
ለምን እንደጀመርክ አስታውስ፣ በአንተ ስኬት የሚወዱህ ሁሉ ምን ያህል እንደሚረኩ አትርሳ! ወዳጄ ጠንክረህ መቀጠል ብቻ ነው ምርጫህ!

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አብረሃና ወታደሩ የእሳት ድንጋይ የወረደባቸው በካእባ ፋንታ በየመን ሌላ ቤት እናዘጋጃለን በማለታቸው ነው።
ይድረስ ለዶክተር አብይ አህመድ
ይድረስ ለዶክተር አብይ አህመድ
ኢስላማዊ ድንጋጌዎች 9️⃣
የኒካሕ መስፈርቶች /ሸርጦች/
1. የተጋቢዎቹን ስም ለይቶ መግለፅ፡- ከአንድ በላይ ልጆች ባሉበት ሁኔታ “ልጄን አጋብቼሃለሁ” ወይም ለልጅህ አጋብቼያለሁ” ቢል በቂ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ስም ተጠቅሶ ለምሳሌ “ልጄን ፋጢማን ለዐብደላህ አጋብቻለሁ” ሊል ነው፡፡
2. የሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት፡- የግዴታ ጋብቻ ተቀባይነት የለውም፡፡ [ቡኻሪ ፡ 5136 ፣ ሙስሊም ፡ 1419]
3. ለሴቷ ወልይ መኖር፡፡ ነብዩ ﷺ “ያለ ወልይ ኒካሕ የለም” ብለዋልና፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ማጃህ ፡ 1537]
4. ኒካሑ ሲታሰር ሁለት ብቁ ምስክሮች መኖራቸው፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ሒባን ፡ 4075]
5. ተጋቢዎቹን እንዳይጋቡ የሚከለክል ነገር (ቅርብ ዝምድና ፣ አማችቻ ፣ ጥቢ ፣ የእምነት ልዩነት ፣ …) አለመኖር፡፡
የኒካሕ ማእዘናት፡-
1. ጋብቻን ከሚከለክሉ ነገሮች ነፃ የሆኑ ተጋቢዎች
2. ከሴቷ ወልይ በኩል “አጋብቻለሁ” ወይም መሰል የይሁንታ ቃል
3. የአግቢው ወይም ወኪሉ “ተቀብያለሁ” ወይም መሰል የመስማማት ቃል
(ከአልፊቅሁል ሙየሠር ኪታብ የተወሰደ ገፅ ፡ 404-406)
https://t.me/faruk126g
የኒካሕ መስፈርቶች /ሸርጦች/
1. የተጋቢዎቹን ስም ለይቶ መግለፅ፡- ከአንድ በላይ ልጆች ባሉበት ሁኔታ “ልጄን አጋብቼሃለሁ” ወይም ለልጅህ አጋብቼያለሁ” ቢል በቂ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ስም ተጠቅሶ ለምሳሌ “ልጄን ፋጢማን ለዐብደላህ አጋብቻለሁ” ሊል ነው፡፡
2. የሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት፡- የግዴታ ጋብቻ ተቀባይነት የለውም፡፡ [ቡኻሪ ፡ 5136 ፣ ሙስሊም ፡ 1419]
3. ለሴቷ ወልይ መኖር፡፡ ነብዩ ﷺ “ያለ ወልይ ኒካሕ የለም” ብለዋልና፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ማጃህ ፡ 1537]
4. ኒካሑ ሲታሰር ሁለት ብቁ ምስክሮች መኖራቸው፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ሒባን ፡ 4075]
5. ተጋቢዎቹን እንዳይጋቡ የሚከለክል ነገር (ቅርብ ዝምድና ፣ አማችቻ ፣ ጥቢ ፣ የእምነት ልዩነት ፣ …) አለመኖር፡፡
የኒካሕ ማእዘናት፡-
1. ጋብቻን ከሚከለክሉ ነገሮች ነፃ የሆኑ ተጋቢዎች
2. ከሴቷ ወልይ በኩል “አጋብቻለሁ” ወይም መሰል የይሁንታ ቃል
3. የአግቢው ወይም ወኪሉ “ተቀብያለሁ” ወይም መሰል የመስማማት ቃል
(ከአልፊቅሁል ሙየሠር ኪታብ የተወሰደ ገፅ ፡ 404-406)
https://t.me/faruk126g
Telegram
Faruk media_ ፋሩቅ ሚድያ
የቻናሉ አላማዎች
1, ቁርአን እና ሀድስ በሰለፎች አረዳድ
2, የተላያዩ የሱና ኡስታዞች ደርሶች
3, ዳዓዋዎች
4, ፈተዋዎች
1, ቁርአን እና ሀድስ በሰለፎች አረዳድ
2, የተላያዩ የሱና ኡስታዞች ደርሶች
3, ዳዓዋዎች
4, ፈተዋዎች
ውስን የደዕዋ ስልቶችን ስትመለከት አንዱ የግል አለመስማማትን ወደ ዲን ያስጠጋና ''ባብ'' ይሰጠዋል። በመቀጠል ከታች ትችትና ዘለፋን ሰካክቶ ያቀርባል። በውስጡ የግል ፍላጎቱን ባስጠበቀበት ቦታ የዲን ዘብ እንደሆነ ለራሱ ይነግራል። በመጨረሻ ሲሰክን የሚረዳውን በወኔ መንፈስ ሳይረዳው አልፎ ይቀጥላል።
አልሆን ያለህ ጊዜ ማደግና መግዘፍ
ከትልቆች መሀል አንዱን መርጠህ ዝለፍ
በልቡ «ተቃረንና ግነን» የሚለው የተዛባ ብሒል ቁራጭ የሌለበት በርሱ ኢስላም መለያው ሰላም ነው።
ሸይኽ ሷሊህ አስ ሲንዲ حفظه الله
«ሱንይነቱ የታወቀን ግለሰብ ስህተት በሙብተዲዖች ስህተት ልክ አካብዶ መውሰድና በእኩል መነጸር መመልከት በዘመናችን ያሉ በወኔ የሚነዱ አንዳንድ ተማሪዎች መገለጫ ሆኗል።»
አሏህ ትክክለኛ የዲን ግንዛቤን ለሁላችንም ይስጠን
https://t.me/faruk126g
አልሆን ያለህ ጊዜ ማደግና መግዘፍ
ከትልቆች መሀል አንዱን መርጠህ ዝለፍ
በልቡ «ተቃረንና ግነን» የሚለው የተዛባ ብሒል ቁራጭ የሌለበት በርሱ ኢስላም መለያው ሰላም ነው።
ሸይኽ ሷሊህ አስ ሲንዲ حفظه الله
«ሱንይነቱ የታወቀን ግለሰብ ስህተት በሙብተዲዖች ስህተት ልክ አካብዶ መውሰድና በእኩል መነጸር መመልከት በዘመናችን ያሉ በወኔ የሚነዱ አንዳንድ ተማሪዎች መገለጫ ሆኗል።»
አሏህ ትክክለኛ የዲን ግንዛቤን ለሁላችንም ይስጠን
https://t.me/faruk126g
Telegram
Faruk media_ ፋሩቅ ሚድያ
የቻናሉ አላማዎች
1, ቁርአን እና ሀድስ በሰለፎች አረዳድ
2, የተላያዩ የሱና ኡስታዞች ደርሶች
3, ዳዓዋዎች
4, ፈተዋዎች
1, ቁርአን እና ሀድስ በሰለፎች አረዳድ
2, የተላያዩ የሱና ኡስታዞች ደርሶች
3, ዳዓዋዎች
4, ፈተዋዎች
ትንሽ ፈገግ በሉ‼
=============
✍ ባልና ሚስት ተጣሉና አሉ ሊመታት ሲሞክር «እረፍ!» ብላ አስጠነቀቀችው።
ጨከነና እጁን ሰንዝሮ ሲመታት ያዘችውና መሬት ላይ ጥላው ከላይ ሁና የሌለ ገረፈችው። «ኧረ! ተጋደልን!» እያለ እየጮኸ ለጎረቢቱ የድረሱልኝ ጥሪ አሰማ።
«ለይ!» አለችው። "ለይ" ማለቷ «ገደለችኝ!» በል እንጅ አንተም አቅም ኖሮህ እኔን እየተመታኸኝ አስመስለህ «ተጋደልን!» አትበል ማለቷ ነው። በአጭሩ Bargaining power የለህም ማለቷ ነው።
ከዚያ እንዳለችው «ገደለችኝ!» እያለ ሲጮኽ ጎረቤት ሰምቶ የመጣ ጊዜ፤ እርሷ ከላይ ሆና ደበደበችው እንዳትባል ያው ሁሉ በእጇ ስለሆነ (አቅሙ ስላላት) አውቃ ከላይ አደረገችውና ሰው ሲገባ እርሱ እየደበደባት እንዲመስል ማለት ነው።
ከዚያ ጎረቤቶቹ ሲገቡ እርሱ ከላይ ሆኖ ያዩት ጊዜ «እንደት ትገላታለህ?» አሉና ሊለያዯቸው ሲሉ፤ ባል ምን ቢል ጥሩ ነው፦
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
«ኧረ! ትንሽ ተውኝ! አዲስ ግልብጥ ነኝ!» አለ።
«አዲስ ግልብጥ ነኝ!» ማለቱ "እስካሁን ከታች ተደርጌ ስቀጠቀጥ ነበር፤ ገና አሁን ነው ቀን ወጥቶልኝ ከላይ የዞርኩት!" ማለቱ ነው።
ይሄኑንም እኮ እርሱው ሳይሆን እርሷው በፈቃዷ አዙራው ነው!
♠
በሉ ይመቻችሁ! ወሬውን የሰማሁት ሸይኽ ሙሐመድ ኢድሪስ ዛሬ የአል-አጀሩሚያህ ደርሳቸው ላይ ስለ መዕሪፋና ነኪራህ ሲያስተምሩን፤ "አል" በሚገባበት ጊዜ ሁልጊዜ "አጠቃላይ" የሚለውን ላይተካ እንደሚችል ሲናገሩ "الرجال اقوى من النساء" የሚል ምሳሌ ስለነበር ሁሉም ወንድ ከሴት ይበልጣል ማለት አይደለም የሚለውን ሲያስረዱን ይህን ተረት ነግረውን ነው።
ደህና እደሩልኝ! አላህ ከእንዲህ አይነት ሴት ይጠብቀን በሉ¡
(ቀልድ አይመቸኝም 'am serious የሚል ሰው ባላዬ ይለፍ!)
ከሙራድ ታደሰ

❤1👍1
ሳዑዲና ሃሎዊን
~
ሰሞኑን በሳዑዲ ሪያድ ውስጥ ሃሎዊን የሚያከብሩ ሰዎች መታየታቸውን ተከትሎ ጫጫታ እያየን ነው። የሳዑዲ መንግስት ላይ፣ ከዚያም በሱ በኩል አቆራርጦ ዑለማዎቹ ላይ፣ አሁን ካሉትም አልፎ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ላይ የሚዘምቱ ሰዎችን በተደጋጋሚ አይቻለሁ። የሆነ ነገር በለጠፍኩ ቁጥር ደጋግመው እየመጡ 'ኮሜንት' ላይ ብዙ ነገር የሚለቀልቁም ገጥመውኛል። "ስለዚህ ግን ትንፍሽ አትሉም" ይላሉ። ብዙዎቹ ከሁኔታቸው መውሊድን በማውገዛችን ቂም ያረገዙ እንደሆኑ ያስታውቃሉ።
ሃሎዊን ምንድነው?
-
የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ስመለከት ያገኘሁት እንዲህ የሚል ነው፦
Halloween "የሁሉም ቅዱሳን ቀን" ማለት ሲሆን በአብዛኛው እንግሊዝኛ ተናጋሪ በሆኑ ሃገራት የሚከበር በዓል ነው፡፡ የሚከበረውም በፈረንጆች October 31 ነው። ህፃናት የተለዩ አስፈሪ ልብሶችን በመልበስ በየቤቱ እየዞሩ ከረሜላና መሰል ነገሮችን ይጠይቃሉ።
ምንጭ፦ http://en.wiktionary.org/wiki/Halloween
መነሻው ኬልቲክ አካባቢ ቢሆንም አሜሪካ ከገባ በኋላ ወደሌሎች ሃገራት ተሰራጭቷል። ከህፃናት አልሮ በ"አዋቂዎችም" ይከበራል። የሰይጣን አምልኮ ነው እያሉ የፃፉ አይቻለሁ። ሊሆን ይችላል። እኔ ግን ማረጋገጥ አልቻልኩም። በዓሉ መነሻው የጣዖታውያን ልማድ እንደሆነ፣ ከዚያም ከፊል ክርስቲያኖችና የሁዶች እንደሚያከብሩት፣ ከክርስቲያኖችና የሁዶች ውስጥ እራሱ አጥብቀው የሚያወግዙት እንዳሉ አንብቤያለሁ።
ሃሎዊን በኢስላም
~
በኢስላም የትኛውንም የጃሂሊያ (ኢስላማዊ ያልሆነ) ስርአት በዓል ማክበር አይፈቀድም። ነብያችን ﷺ የመዲና ሰዎች ሲያከብሯቸው የነበሩ የፋርስ ዞራስቲያኒዝም ሃይማኖት በዓላትን መከልከላቸው የሚታወቅ ነው። በተጨማሪም "በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው" ብለዋል። [አቡ ዳውድ፡ 4031] ይሄ እጅግ አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ነው።
ሃሎዊን በሳዑዲ
~
ሳዑዲ ውስጥ እስከ ቅርብ አመታት ድረስ የሃሎዊን በዓል አልነበረም። የሚፈልግ ስለሌለ ሳይሆን በመንግስት ስለተከለከለ ነበር። የክልከላውን መላላት ወይም መነሳትን ተከትሎ ግን - በአንድ ዌብሳይት ላይ እንዳየሁት - ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እየተከበረ ነው። ይሄ በጣም ዘግናኝ ጥፋት ነው። ጥፋቱ በሳዑዲ ስለተፈፀመ የሚቀየር ብይን የለም። ማንም ለዚህ ወግኖ የሚከራከርም የለም። ከኖረም ባይፈፅመው እንኳ የጥፋቱ አካል ነው።
ለኢኽዋኖ - አሕባሽ መን-ጋዎች!
~
ለብዙኛ ጊዜ ደጋግሜ የምናገረው ነገር ቢኖር ሳዑዲ ውስጥ ከዚህም ውጭ ብዙ ጥፋቶች እንዳሉ እናውቃለን። አንዳንድ ቂላቂሎች እንደሚያስቡት ሳዑዲን ፍፁም አድርገን የምንስል አይደለንም።
ግን እናንተ የመጮሁንም የማስጨሁንም ሞራል ከየት አገኛችሁት? ምዬ እናገራለሁ ከአብዛኛቻችሁ ጩኸት ጀርባ ያለው ለኢስላም መቆርቆር አይደለም። የጩኸታችሁ ቀዳሚ መንስኤ ቡድናዊ ልዩነት ነው። ይሄ በዓል'ኮ ዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ቀደም ብሎ ጀምሮ ቱርክ ውስጥ ይከበራል? በዚህ መልኩ አስጩሃችሁት ታውቃላችሁ? ለምን? አንዱ ሳዑዲን በዚህ ሰበብ እያብጠለጠለ በለቀለቀበት ረዥም ፅሑፍ ውስጥ ኳታርን ሲያወድስ አይቻለሁ። እስኪ Halloween in Qatar ብለህ ጉግል ላይ ፈልግ። የእውነት ለዲን መቆርቆር ከሆነ ምክንያታችሁ ምነው ስለ ኳታር እስከዛሬ አልጮሃችሁም?! እነዚህ አካላት በተመሳሳይ ጊዜ ብዙ ፊት የሚያሳዩ፣ በተመሳሳይ ጉዳይ የተለያየ ስፍር የሚሰፍሩ፣ ሃይማኖትን ለፖለቲካዊ ንግድ የሚጠቀሙ ቆሻ - ሻ ፍጥረቶች ናቸው።
ሲጀመር የኢኽዋን አንጃ በምን መለኪያ ነው ከሳዑዲ መንግስት የሚሻለው? የቡድኑ መሪ ዑመር ቲልሚሳኒይ ገንዘብ እየከፈልኩ የፈረንጅ ዳንስ ተምሬያለሁ፣ ሲኒማ ለማየት ብዬ ሁለት ሶላቶችን በአንድ ላይ ጀምዕ እያደረግኩ እሰግድ ነበር አላለም? ቀርዷዊ ነፃነትን መተግበር ከሸሪዐ ይቀድማል አላለም? የቡድኑ መስራች ሐሰነል በናና ዩሱፍ አልቀረዳዊ በተጨባጭ ሐዲሥ የተረጋገጠውን የመህዲን መምጣት አላስተባበሉም? መውዱዲ የደጃልን መምጣት አላስተባበለም? ቱራቢ በርካታ መረጃዎችን ረግጦ የቀብር ቅጣት የሚባል የለም፣ ነኪርና ሙንከር የሚባል የለም አላለም? ነብያት መዕሱም አይደሉም አላለም? የዒሳን ዳግም መምጣት አላስተባበለም? ቀረዳዊና ሙርሲ የክህደት ቁንጮ ለሆኑ ጳጳሶች አላህ እንዲምራቸው ዱዓ አላደረጉም? ሰይድ ቁጥብ ከሶሐቦች አልፎ ነቢያትን አልጎነተለም? ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ከኢስላም እያስወጣ አልፃፈም? ሰዕድ አልከታቲኒ በግብፅ ምርጫ ብናሸንፍ አስካሪ መጠጥ አንከለክልም፣ የብልግና ድረ ገፆችን አንዘጋም አላለም? እስኪ ምናችሁ ተሽሎ ነው ምላሳችሁን የምታሾሉት?
የእውነት ለኢስላምና ለሙስሊሞች ተቆርቁራችሁ ከሆነ ይሄንን እያንሸዋረረ የሚያሳያችሁን ቡድናዊ መነፅር አሸቀንጥራችሁ ጣሉና በስርአት አስተምሩ። ኢስላም በሚያስተምረው መልኩ ከሃሎዊንም፣ ከቫሌንታይኑም፣ ከሳዑዲ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሃገራት ብሄራዊ በአላትም፣ ከኢሬቻም፣ ከገናም፣ ከመስቀልም ፣ ከመውሊድም፣ ወዘተ አስጠንቅቁ። ከፊሎቻችሁ'ኮ ለመስቀል ስታፀዱ እናውቃችኋለን! ከፊሎቻችሁኮ ኢሬቻን ለማውገዝ የምትሽኮረመሙ ናችሁ። ከሌሎቻችሁ'ኮ ሉሲን ተከትላችሁ ከሃገር ሃገር ስትዞሩ ነበር። የምን ማስመሰል ነው? እምቢ ብላችሁ ስለ ሳዑዲ ብቻ ከሆነ ማውራት የምትፈልጉት ቢያንስ በሌላ ሃገር የሌለ ጥፋት እየጠበቃችሁ ብትጮሁ ይሻላችኋል! ያለበለዚያ ግን ጧት ማታ ሙገሳ በምትሰፈሩላቸው ሃገራት ውስጥ ያለው ሲወጣ አስመሳይነታችሁ ይጋለጣል።
በርግጥ ለኛም ቢሆን የሳዑዲ ጥፋት ይለያል! ምክንያታችን ግን እንደናንተ የገነፈለ ጥላቻ አይደለም። አዎ ከሌሎቹ በበለጠ ሳዑዲ ላይ ይሄ መሆኑ ያመናል። ተሽለው መገኘት እንዳለባቸው ስለምናምን። ለሃገሪቱ ካለን መቆርቆር። የኢስላምና የሙስሊሞች ምልክት (symbol) በመሆኗ።
የአሕባሸና የኢኽዋን ጩኸት ግን "ከፍየሏ በላይ ነው።" የተጠራቀመ ቂም ስላላቸው አጋጣሚ እየጠበቁ ከሳዑዲ መንግስት አልፈው ዑለማዎች ላይ ዘመቻ ለመክፈት ነው አድብተው የሚጠብቁት። የሙዚቃ ኮንሰርት ሲካሄድ ልክ ዑለማዎቹ የፈቀዱ ይመስል እነሱም ላይ ጭምር ይዘምታሉ። ልክ በግልፅ ሙዚቃ የሚፈቅደውን ቀረዷዊን ሲያንቆለጳጵሱ እንደማናውቃቸው። ልክ ቱርክና ኳታር የሙዚቃ ድግስ፣ ከዚህም አልፎ ብዙ ነገር እንደሌለ። ይሄው በቅርቡ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ኳታር ውስጥ የሙዚቃ ድግስ እየተዘጋጀ እንደሆነ አልጀዚራ እየዘገበ ነው። ሪያድ ሲሆን እንደምታወግዙት ደውሐ ሲሆን ታወግዙታላችሁ? አታደርጉትም። ምክንያቱም መስፈሪያችሁ የሚታወቅ ነው። حصانة إخوانية
.
ሁኔታችሁን እያየሁ ልመለስ እችላለሁ፣ ኢን ሻአ'ላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/faruk126g
ከኢብኑ መነወር

አንድት በቀደምት መሪወች የተከሰተች ታሪክ
አንድ መሪ ነበር አና ያው እንደሚታወቀው የሙስሊም መሪዎች ሳልሞቱ በስተቀር ስልጣን በእጃቸው ነው እና አንድ መሪ ንጉስ በጣም ትልቅና ማስተዋል የተሳነው ነገር ግን ንጉስ ነው ከእለታት አንድ ቀን አስተዋይና አሳቢ ልጅን ጠራው ከዛም ልጁም መልክተኛው ሳይነጋው በፈጅር ነበር የመጣውና በመደናገጥ ጦሩን (ስራዊቱን) ሰብስቦ ወደ አባቱ ሲሄድ ምንም ነገር የለም እሱኮ የሆነ ጥላት መቶ ነው እጅ በለሊት አያስጠራኝም ነበር ብሎ ተዛጋጅቶ ሲሄድ ምንም የለም ከዛም ምን ሁነህ ነው አባ ሲለው አባትም እንቅልፍ አጥቸ አደሩኩ ምን መሠለህ :
ጀነት ገብቸ ይመስለኛል ፆታየን ቀይሬ ሁርላይን ሁኘ ነብዩሏህ ዩሱፉን ያገባሁ መስሎኝ ስጨናነቅ አደርኩ እንቅልፍ አላየሁም አለው ልጅም በጣም ተገርሞ ለምን ፆታህን ተቀየርክ አይቀር ሙሀመድ ሱ ዐ ወ ምን አታገባም ነበር ሲለው አይ ሳላስበው ቀርቸ አይደለም እኔ የአንተ አባት የነ አኢሻን ጭቅጭቅ ሳስብ አስጠልቶኝ ነው አለው ።
ተመልከቱ ይሄ መሪ ጭራሽ ጀነት ገብቶም ፆተ መቀየር ከዛም ጭቅጭቅ ምን አይነት የወረደ አስተሳሰብ ነው የዘመናችን መሪዎች ጋር ምን አመሳሰለው ትላለህ ።
የቴሌግራም ቻናል

#ትዳር....
~~~
ኢብን ኡሰይሚን ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ
ሪዚቅ(ሲሳይ) በሰበቦች የተፃፈና የተወሰነ እንደሆነው ሁሉ
ትዳርም ልክ እንደዚሁ የተፃፈና የተወሰነ ነው ።
በእርግጥም ለሁሉም ጥንዶች(ባለትዳሮች) ተፅፏል አንደኛው ለሌላኛው የትዳር አጋር(ጥንድ) እንደሚሆን።
#ምንጭ [ ፈታዋ ኑሩን አላደርብ]https://t.me/faruk126g

የሚያቆመን ሀሳባችን ነው!
የምንጎዳው የምንሰበረው የምንፈራው የምናጣው መጥፎ የሚባሉት ስሜቶች በአጠቃላይ የሚፈጠሩት በሀሳባችን ነው ፤ ገና በተግባር ያላየናቸው በእውኑ አለም ያላወቅናቸው ነገሮች በሙሉ ቀድመው በሀሳችን ይፈጠሩ እና ከመንገዳችን ያስቆሙናል መሰናክል ይሆኑብናል መሄድ ከምንፈልግበት መጓዝ ካሰብነው ቦታ ያርቁናል ስለዚህ እናስተውል እየተረበሽኩ ያለውት በምንድን ነው እውነት በተፈጠሩ ነገሮች ነው? ለምንድነው የቆምኩት ? ገብቼ አይቼው ነው ወይንስ በሀሳብ የሳልኩት መጥፎ ስዕል እየረበሸኝ ነው? ብለን እንነሳ ከመቆማችን በፊት ለምንድነው የቆምኩት ብለን እንመርምር !
መልካም ቀን ተመኘን 🙏https://t.me/faruk126g

የሴቶችን ድንግልና የሚወስደው ማን ነው?
ይህን ፅሁፍ ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ አብዛኛውን ጊዜ አንዳንድ ወደ እስልምና እንጣራለን የሚሉ ሰዎች ህግጋቱን ሁሉ ሴቶች ላይ ጫን አድርገው ወንዶችን ብዙም ሲሉ አይሰማም፡፡
ሰሞኑን አላዋቂዎች ብዙ ሲሳለቁ እና እራሳቸውንም መግለጫ ሰጪ አድርገው ሲያዩ ተመልክተናል፡፡ የሴት ልጅ ድንግልና በብዙ መንገድ ይሄዳል፡፡ ለምሳሌ ሴት ልጆችን በገዛ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እና ዘመዶቻቸው በመደፈር ሁሉ ያጡታል፡፡ ሴት ልጆች ሲደፈሩ ያውም ደፋሪያቸው እየታወቀ “በቃ ዝም በይ” አይነት ማስጠንቀቂያዎች ይሰጧታል፡፡ ድንግልና ያለ ግንኙነትም ሊጠፋ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ዑለማዎችም ሀኪሞችም ይገልፃሉ። ስለዚህ ድንግልና የሌላት ሁሉ ብልግና ፈፅማለች ማለት ዝቅ ሲል አላዋቂነት ከፍ ሲል ብልግና ነው። በሌሎችም መንገዶች ድንግልና ይሄዳል፡፡
አብዛኛዎቹ ሴቶች ልጅ በነበሩበት ሰኣት በጣም አይን አፋር እና ድንጉጥ ናቸው፡፡ ወንድን መቅረብ አይፈልጉም፡፡ ሴቶቹን ወደ መጥፎ ነገር የሚመሩዋቸው መጥፎ ሴት ጓደኞች እና ምላሳም ወንዶች ናቸው፡፡
መቼም ወንድ ከሌለ ሴቶች በራሳቸው ድንግልናቸውን አጠፉት አይባልም፡፡ አንድ ሴት ልጅ ድንግልናዋን ስታጣ እሷን ብቻ ከመውቀስ በምላሱ አታሎ፣ አጭበርብሮ ድንግልናዋን የወሰደባትን ለምን በደንብ አይኮንኑትም?
አስገራሚው ሴት ልጅ ስትሰራ ከነበረችው መጥፎ ነገር ቶብታለች ሲባል “እሷ እኮ…. ነበረች…. መጠንቀቅ ነው …. ምን ይታወቃል” እና የመሳሰለውን ትንኮሳዎች ይተበተባሉ፡፡
ወንድ ልጅ ግን ለምሳሌ አንዴ በድፍረት 21 ወይንም 22 አመት የሚጠጋው ወንድ ለጓደኞቹ “ከ180 እስከ 200 ሴቶች ጋር ግንኙነት ፈፅሚያለሁ” እንዳላቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ (የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የእኔ ኡመቶች ወንጀል ይማራል ግልፅ የሚያወጣው ሲቀር ብለዋል፡፡ ወንጀልን እንደቁም ነገር እና ጀብዱ የምታወሩ ሰዎች አላህን ፍሩ)፡፡ ለምሳሌ ይህን ሁሉ ሴት የነካካ ወንድ ቶብቷል ቢባል “አቤት እሱ እኮ ሷሊህ ነው፡፡ አቤት አኽላቁ፡፡ አቤት እሱን ያገኘች” ተብሎ ይለፈፋል፡፡
ለምን?
አላህ በተከበረው ቁርኣን ላይ
- ዝሙትን በተመለከት ተከልከሉ ሲል ለወንዱም ለሴቱም ነው፡፡
- ዝሙት ከፈፀሙ ያላገቡ ከሆኑ 100 ጅራፉ ይገረፉ ሲል ወንዱንም ሴቷንም ነው፡፡
- ዝሙትን የፈፀሙት ያገቡ ከሆነ በድንጋይ ተቀጥቅጠው ይገደሉ ሲል ወንድንም ሴትንም ነው፡፡
ታድያ ለምን ይሄን ያህል ሁለቱንም የሚመለከተውን ህግ ሴቶች ላይ ብቻ ጫን ማለት አስፈለገ፡፡ እንጨት ለምሳሌ በራሱ አይቀጣጠልም እሳት ሲቀላቀልበት ቢሆን እንጂ፡፡ ስለዚህ ወንድ እና ሴት በፈፀሙት ወንጀል አንዱን ብቻ ጠንከር አድርጎ መውቀሱ በተለይ ከኢስላም ውጭ ያሉ ሰዎች “ኢስላም ሴትን ይበድላል” እንዲሉ የሚያደርጋቸው ይህ ነው፡፡
ፍትሀዊ የሆነ ሀይማኖት ይዘን ፍትህ የሌለ አስመስለን አናቅርበው፡፡ ያለ እውቀት መናገር ሁሌም ጣጣው ከሚታሰበው በላይ ነው፡፡
የቶበቱ ሰዎችን አስመልክቶ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ወደ አላህ የተመለሰ ወንጀል እንደሌለበት ነው፡፡” ብለው ሲያበቁ ወደ አላህ የተመለሱ ሰዎችን እያጣጣሉ መናገር መሀይምነትን በይፋ የሚያሳይ ነው፡፡
አስገራሚው ግልፅ ቢድኣና ሺርክን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ የሌላቸውን ጥንካሪ እና ድፍረት ወንጀል ላይ የወደቁት ላይ ሲያደርጉት እንመለከታለን፡፡
ወንጀል በድብቅ የሰራ ሰው አይቡ ይደበቅለታል፡፡ ቢድኣን እና ሺርክን በአደባባይ የሚፈፅም ደግሞ በአደባባይ ሙስሊሞች እንዲጠነቀቁት መልስ ይሰጥበታል ይህ ነው ፍትህ እና ሚዛናዊነት፡፡
ዛሬ የቢድኣ ካዝና ለሆኖ ሰዎች ጥብቅና ቆመው እነሱን አናስነካም፡፡ እነሱን የነካ “አይባቸውን እንዳወጣ ነው” ሲሉ ይቆዩና ተደብቀው ወንጀል የሚሰሩ ሰዎችን “ተከታትለን በካሜራ እናጋልጣለን” ብለው ስሜት አምላኪነታቸውን ያሳዩናል፡፡
እንዲህ አይነት መሀይማን ጉዳታቸው እጅጉን የከፋ ነው፡፡
ፅሁፌን ስጨርስ ሴቶችን እንደነ መርየም ድንግልናችሁን ጠብቁ ስንል፣ ወንዶችንም ልክ እንደነ ኡስማን ኢብን አፋን ሁኑ ከዝሙት ራቁ፡፡ ወንድ እና ሴቶች ሆይ! አላህን ፈርታችሁ ቶሎ ተጋቡ፡፡ በኢስላም ትዳር ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ከትዳር ያለ አስገዳጅ ሀጃ በመዘግየታችሁ ምንም የምትጨምሩት ነገር የለም፡፡ የምታጡት ነገር ቢብስ እንጂ፡፡
ስለ ትዳር የበሰሉ ሃያእ ያላቸውን ታላቆችን አማክሩ፡፡ ፀሀፊ ሳዳት ከማል

❤1
በጫማ መስገድና ተያያዥ ነጥቦች
~
[ሀ] በጫማ መስገድ ይቻላል?
አንዳንድ ሰዎች በጫማ መስገድ የማይፈቀድ ይመስላቸዋል። ለዚህ ያደረሳቸው ጉዳዩ በዑለማእ ሲፈፀም ወይም ሲነገር ስላላጋጠማቸው ይሆናል። ነገር ግን በጫማ ከመስገድ የሚከለክል አንድም ማስረጃ የለም። ይልቁንም በተቃራኒው በጫማ መስገድ የማያሻማ ሸሪዐዊ መሰረት ያለው ሱና ነው። ይህንን ከሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ውስጥ ከፊሉን ብናይ፡-
1. አቡ መስለማ ሰዒድ ብኑ የዚድ አልአዝዲ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ: أَكَانَ النَّبِيُّ ﷺ يُصَلِّي فِي نَعْلَيْهِ؟ قَالَ: «نَعَمْ»
“አነስ ኢብኑ ማሊክን ‘ነብዩ ﷺ በጫማዎቻቸው ይሰግዱ ነበርን?’ ብዬ ጠየቅኩት። ‘አዎ’ አለኝ።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. ዐብዱላህ ብኑ አቢ ሐቢባ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
جاءنا رسول الله ﷺ في مسجدنا ب(قباء فجئت وأنا غلام (حدث) حتى جلست عن يمينه (وجلس أبو بكر عن يساره) ثم دعا بشراب فشرب منه ثم أعطانيه وأنا عن يمينه فشربت منه ثم قام يصلي فرأيته يصلي في نعليه
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቁባእ ወዳለው መስጂዳችን መጡ - እኔ ለጋ ልጅ ነኝ በጊዜው መጣሁና በቀኛቸው በኩል ተቀመጥኩ። አቡበክር በግራቸው ተቀመጡ። ከዚያም የሚጠጣ ነገር ጠየቁና ከሱ ጠጡ። ከዚያም በቀኛቸው ላለሁት ለኔ ሰጡኝና ከሱ ጠጣሁ። ከዚያም ሊሰግዱ ተነሱ። በጫማዎቻቸው ሲሰግዱ አየኋቸው።” [አሶሒሐህ፡ 2941]
3. ከዐምር ብኑ ሹዐይብ ከአባታቸው፣ ከአያታቸው ተይዞ እንዲህ ብለዋል፡-
رأيت رسول الله ﷺ يصلي حافيا ومنتعلا.
“የአላህ መልእክተኛን ﷺ በባዶ እግራቸውም ተጫምተውም ሲሰግዱ አይቻቸዋለሁ።” [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 660]
4. አቡ ሰዒድ አልኹድሪ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
“አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ﷺ አሰገዱን። በከፊል ሶላታቸው ላይ ሳሉ ጫማዎቻቸውን አወለቁና በግራቸው በኩል አስቀመጧቸው። ሰዎች ይህንን ሲያዩ ጫማዎቻቸውን አወለቁ። ሶላታቸውን ሲያጠናቅቁ ‘ምን ሆናችሁ ነው ጫማዎቻችሁን ያወለቃችሁት?’ አሉ። እነሱም ‘ጫማዎችህን ስታወልቅ ስናይህ ጫማዎቻችንን አወለቅን’ አሉ። በዚህን ጊዜ እሳቸው ﷺ እንዲህ አሉ፡-
"إن جبريل أتاني، فأخبرني أن فيها قذراً؛ فألقيتهما، فإذا جاء أحدكم إلى المسجد؛ فلينظر في نعليه: فإن رأى فيهما قذراً؛ فليمسحهما، ولْيصلِّ فيهما"
‘ጂብሪል ከኔ ዘንድ መጥቶ በነሱ (በጫማዎቼ) ላይ ቆሻሻ እንዳለባቸው ሲነገረኝ አወለቅኳቸው። አንዳችሁ መስጂድ ሲመጣ ጫማዎቹን ይመልከት። ቆሻሻ ካየባቸው ይጥረጋቸውና ይስገድባቸው።’” [ሲፈቱ ሶላት፡ 80]
5. ከሸዳድ ብኑ አውስ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«خالفوا اليهود فإنهم لا يصلون في نعالهم ولا خفافهم»
“አይሁዶችን ተፃረሩ። እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3210]
ማሳሰቢያ፡-
ባሳለፍናቸው አምስት ሐዲሦች በጫማ መስገድ እንደሚቻል አይተናል። ስላሳጠርኩት እንጂ ማስረጃዎቹ ከዚህም በላይ ናቸው። ትንሽ ሰፋ ያለ ነገር የፈለገ የሸይኽ ሙቅቢልን ረሒመሁላህ “ሸርዒየቱ ሶላቲ ፊኒዓል” ኪታብ ይመልከት። ነገር ግን:-
1ኛ፡- የሚሰገድበት ጫማ ንፁሕ መሆን አለበት።
2ኛ፡- በጫማ የሚሰገደው ለመታወቅ ወይም ተለይቶ ለመታየት አይነት ኒያ እንዳይሆን
3ኛ፡- ዛሬ ሰዎች ለሱናው ባይተዋር ሆነዋል። ስለሆነም በጫማ በመስገድ የሚነሳ ፈተና ካለ መታቀብ ያስፈልጋል። ጉዳትን ማስወገድ የሚወደድን/ የሚፈቀድን ነገር ከመፀም ይቀድማልና። በዚህን ጊዜ ወደ ተግባር ከመግባት በፊት ማስተማር ይቀድማል ማለት ነው።
4ኛ፡- በሶላትም ውስጥ ይሁን ከሶላት ውጭ ከአውሬዎች ቆዳ የተዘጋጀ ጫማ መልበስ አይቻልም።
[ለ] በጫማ መስገድ የተፈቀደ ወይስ የተወደደ?
በጫማ መስገድ እንደሚቻል ካለፉት ማስረጃዎች አይተናል። ግን ከነጫማ መስገድ የሚፈቀድ ብቻ ነው ወይ የሚወደድም ጭምር ነው? ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ በዚህ ጉዳይ ላይ ከጥንት ጀምሮ ውዝግብ እንደተከሰተ ከጠቀሱ በኋላ “የሚያደላው ይሄ ከሸሪዐዊ ድንጋጌዎች መሆኑ ነው፤ ስለሆነም የተወደደ ነው” ብለዋል። ለዚህም “አይሁዶችን ተፃረሩ። እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና” የሚለውን ሐዲሥና ሌላም ማስረጃ ጠቅሰዋለል። [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብን ዑሠይሚን]
[ሐ] በዘመናችን ባሉ መስጂዶች ውስጥ በጫማ መስገድ
በአሁ ሰዓት መስጂዶች ውድ ውድ ምንጣፎች ተነጥፎባቸዋል። ሰው ሁሉ ከነጫማው ቢገባ ምንጣፎቹ በቆሻሻ ይሞላሉ። ይሄ ደግሞ ሰጋጆችን ያስቸግራል። በዚህም የተነሳ ምንጣፍ በተነጠፉ መስጂዶች ውስጥ ከነጫማ መግባት አይገባም። ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ ውጭ ከሆኑ (በቤታቸው ወይም ምንጣፍ በሌለባቸው ቦታዎች) ፍላጎታቸው ከሆነ ከነጫማቸው መስገድ ይችላሉ።
[መ] ሶላት ሊሰግድ ሲል ጫማውን ማውለቅ ከፈለገ የት ያድርግ?
በቀኙ በኩል ማስቀመጥ የለበትም። ስለዚህ በግራው በኩል ማድረግ ይችላል። በግራው በኩል ሌላ ሰጋጅ ከኖረ በግራ በኩል ማድረግ የለበትም። ምክንያቱም ለሱ በቀኝ በኩል ይሆንበታልና። በዚህን ጊዜ በእግሮቹ መሀል ያድርግ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “አንዳችሁ መስገድ ካሰበ ጫማዎቹን በቀኙ በኩል አያድርግ። በግራውም አያድርግ፣ በሌላ ሰው ቀኝ በኩል ይሆናልና - በግራው በኩል ማንም ከሌለ ነው እንጂ። (በግራ ሰው ከኖረ ግን) በእግሮቹ መሀል ያድርጋቸው።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 645]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 17/2010)