FBC (Fana Broadcasting Corporate)
206K subscribers
69.9K photos
1.38K videos
23 files
58.5K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

‹‹ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለአካላዊ ጥንካሬ፣ ለአዕምሯዊ ንቃትና ለጤንነት ጉልህ ፋይዳ አለው።

ዛሬ ማለዳ "ልህቀት በሰው ተኮር አገልግሎት" በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠና እየወሰዱ ከሚገኙ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ጋር የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ኳስ ጨዋታ አድርገናል።

እንደዚህ ያሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በአማራሩ መካከል ያለውን ግንኙነትን በማጠናከር የተሻለ አንድነትን ይፈጥራሉ፡፡››
በአማራ ክልል ትናንት የተጀመረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬም ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ያስጀመረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው። በዚህም ከዛሬ ጀምሮ በሦስት ክላስተሮች ከ4 ሺህ 500 በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች በቡድን ተከፋፍለው በአጀንዳዎቻቸው ላይ እየተወያዩ ነው። ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው በባሕርዳር ከተማ በሚገኘው በአማራ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ነው። የሕብረተሰብ…

https://www.fanamc.com/archives/288861
የትግራይ ክልል ተወላጆች ሕዝባዊ የምክክር መድረክ እያካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ተወላጆች አስተባባሪ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሕዝባዊ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የምክክር መድረክ የትግራይ ክልል ተወላጆች አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳዘጋጀው ተገልጿል። የክልሉ ሕዝብ የዴሞክራሲና የልማት ጥያቄዎች የሚፈቱበትን ሁኔታ እውን ለማድረግ ከየትኛውም የፖለቲካ…

https://www.fanamc.com/archives/288864
የሹዋሊድ በዓል ዓለም አቀፍ ቅርስነቱን በሚመጥን መልኩ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሹዋሊድ በዓል ዓለም አቀፍ ቅርስነቱን በሚመጥንና ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ባንፀባረቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ አስታወቁ፡፡ ርዕሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሹዋሊድ በዓል ባህላዊ ሥርዓቱንና እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሯል ብለዋል፡፡ በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የክልሉ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣…

https://www.fanamc.com/archives/288869
ኢትዮጵያ ገና አውቃ ያልጨረሰቻቸው የማዕድን ፀጋዎች አሏት – ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ያላትን ሀብት አውቃ እንዳልጨረች እና የማዕድን ሀብቷ ከፍተኛ እንደሆነ የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) ገለፁ፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት በማዕድን ዘርፍ ያላቸውን ሀብት አውቀው እንዳልጨረሱ ጠቅሰው፤ በዘርፉ ብዙ ያልተሰሩ ብዙ ቀሪ ሥራዎች እንዳሉ ጠቁመዋል። የማዕድን ሃብቱን ለመጠቀም እና ያለውን ሃብት ለይቶ…

https://www.fanamc.com/archives/288872
የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሰልጣኞችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 10ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች እና የ27ኛ የባለሌላ ማዕረግተኛ ሰልጣኞችን አስመረቀ፡፡

የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ተመራቂዎች ለኢትዮጵያ ዘብ ለመቆም በመብቃታችሁ ክብር ሊሰማችሁ ይገባል።

https://www.fanamc.com/archives/288877
ማስታወቂያ

12 ብር ደምሩበት!
*****
እስከ ሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም
ከባህር ማዶ በኢትዮ ዳይሬክት (#EthioDirect)፣
ካሽ ጎ (#CashGo) እና ፋስት ፔይ (#FastPay) የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያዎች፣ እንዲሁም
በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ሲላክልዎ
ከእለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን በተጨማሪ
በተላከልዎት በእያንዳንዱ ዶላር ላይ
የ12 ብር ተጨማሪ ጉርሻ ያገኛሉ!
********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #eidmubarak #gift #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #EthioDirect #CashGo #mto #fastpay
************
- የ EthioDirect መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• IOS፡ https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491

- የ CashGo መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US
• IOS: https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306
የጦላይ ከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 10ኛ ዙር ምልምል ወታደሮች እና የ27ኛ የባለሌላ ማዕረግተኛ ሰልጣኞች የምረቃ መርሐ-ግብር በምስል
አቢሲንያ ባንክ ከ349 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር በላይ ብድር አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አቢሲንያ ባንክ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመፍታትና የገቢ ንግድን ለመደገፍ በበጀት ዓመቱ 349 ሚሊየን 943 ሺህ 588 የአሜሪካ ዶላር ብድር ማቅረቡን አስታወቀ፡፡ ባንኩ ለደንበኞች ካቀረበው የምንዛሪ ድልድል ውስጥ በ3ኛው ሩብ ዓመት ከ1 ሺህ በላይ ደንበኞች ወደ ሀገር ውስጥ የገበያ ዕቃዎችን እንዲያስገቡ 189 ሚሊየን 82 ሺህ 861…

https://www.fanamc.com/archives/288893