Fana Media Corporation S.C (FMC)
205K subscribers
71.1K photos
1.45K videos
23 files
59.2K links
This is FMC's official Telegram channel.

For more updates please visit
https://fanamc.com
Download Telegram
የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ምረቃ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ምረቃ እየተካሄደ ነው። በፋብሪካው ምርቃ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ሸገር ዳቦ በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርት ሲሆን፥ በቀን በሶስት ፈረቃ እስከ 2 ሚሊየን…

https://www.fanabc.com/የሸገር-ዳቦ-ፋብሪካ-ምረቃ-ስነ-ስርዓት-እየ/
በ2013 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በ2013 በጀት ዓመት የበጀት ዝግጅት ላይ ተወያይቷል። በውይይቱም የበጀት ዝግጅቱን አስመልክቶ በገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ አጭር መግለጫ ተሰጥቷል። ዶክትር እዮብ  በዘህ ወቅት እንደገለጹት የ2013 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ሲዘጋጅ…

https://www.fanabc.com/በ2013-በጀት-ዓመት-የፌደራል-መንግስት-በጀት-ዝ/
የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ራሳቸውን አገለሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማክኪ ሳል በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ሰው ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን አግልለዋል። ፕሬዝዳንቱ በተደረገላቸው ምርመራ የኮሮና ቫይረስ ባይገኝባቸውም ለጥንቃቄ ሲባል ለሁለት ሳምንታት ያህል ራሳቸውን አግልለው እንደሚቀመጡ ከፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት በተሰጠው መግለጫ ተገልጿል፡፡ የሴኔጋል የሕግ ባለሙያ የያ ዲያሎ በትናንትናው ዕለት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አስታውቀዋል ፡፡ ባለሙያዋ ሰዎች…

https://www.fanabc.com/የሴኔጋሉ-ፕሬዚዳንት-ከኮሮናቫይረስ-ጋር/
በማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ የኮሮናቫይረስ ስርጭት አሁን ካለው እየከፋ እንደሚመጣ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ ሀገራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ገና ጣራውን እንዳልነካ እና ከዚህ በባሰ ሀገራቱ ሊጠቁ እንደሚችሉ ተነገረ ። የዓለም የጤና ድርጅት ድንገተኛ ህክምና ዳይሬክተር ሚካኤል ሪያን ኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰው ቀውስ በአብዛኞቹ የማዕከላዊና ደቡባዊ አሜሪካ ሀገራት ስርጭቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ በሀገራቱ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ሊመዘገብ እንደሚችል ነው ዳይሬክተሩ…

https://www.fanabc.com/በማዕከላዊና-ደቡባዊ-አሜሪካ-የኮሮናቫይ/
ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባውና በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርተው ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ። በፋብሪካው ምርቃ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ፋብሪካው የዳቦ…

https://www.fanabc.com/የሸገር-ዳቦ-ፋብሪካ-ምረቃ-ስነ-ስርዓት-እየ/
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሱዳን አቀኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ሱዳን ማቅናታቸው ተነገረ። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝቱን የሚያደርጉት በሱዳን የሽግግር መንግስት ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በቀረበላቸው ግብዣ ነው። በካርቱም ቆይታቸውም የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት የሚያደርጉ መሆኑን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው…

https://www.fanabc.com/የኤርትራ-ፕሬዚዳንት-ኢሳያስ-አፈወርቂ-ለ/
በደቡብ ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት ግምገማ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል የአስፈጻሚ ተቋማት የ2012 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የስራ ክንውን ግምገማ ተጀመረ ። የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ ተቋማት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት እንደሚገመግሙ ተገልጿል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ÷በክልሉ ለውጡን ተከትሎ የተፈጠሩ ችግሮችን በመፍታት የህዝብን ደህንነትና ሠላም ለማረጋገጥ መንግሥት የወሰዳቸው እርምጃዎች…

https://www.fanabc.com/በደቡብ-ክልል-የአስፈጻሚ-ተቋማት-ግምገማ/
የአለም ኢኮኖሚ ክፉኛ እየባሰ እንደሚመጣ የዓለም ምጣኔ ሀብት (IMF) ትንበያ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)ዓለም አሁን ካለው የኢኮኖሚ ችግር በባሰ ሁኔታ እንደሚቀጥል የዓለም ምጣኔ ሃብት ግምቱን አስታውቋል፡፡ ዓለም አቀፉ የዓለም ምጣኔ ሃብት ተቋም በዚህ ዓመት የአለም ኢኮኖሚ 4ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅሶ በዚህም ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ካስከተለው ችግር ለመውጣት እየታገለ መሆኑን አሰታውቋል፡፡ አነስተኛ እና ትላልቅ የንግድ ድርጅቶችና ኢኮኖሚያቸው በዚህ ወቅት ክፉኛ…

https://www.fanabc.com/የአለም-ኢኮኖሚ-ክፉኛ-እየባሰ-እንደሚመጣ/
የዓለም ምግብ ፕሮግራምና ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍ ጥምረት ፈጠሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመቅረፍ በጋራ ለመስራት ጥምረት መፍጠራቸው ተገለፀ። ለ3 ዓመታት የሚቆየው ጥምረቱ መንግስትን በማገዝ በኢትዮጵያ በህፃናትና በእናቶች ላይ የሚያጋጥመውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመቅረፍ እና የትምህርት ቤት ምገባን ለማገዝ እንደሆነም ተነግሯል። በያዝነው ዓመት በኢትዮጵያ 2 ነጥብ 7…

https://www.fanabc.com/የዓለም-ምግብ-ፕሮግራምና-ዩኒሴፍ-በኢትዮ/
ጠ/ሚ ዐቢይ “እንሥራ” የሸክላ ስራ ማዕከልን ጉበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ “እንሥራ” የሸክላ ስራ ማዕከልን በዛሬው እለት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ጉብኝቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “እንሥራ በተሰኘው አዲስ የሸክላ…

https://www.fanabc.com/ጠ-ሚ-ዐቢይ-እንሥራ-የሸክላ-ስራ-ማዕከል/
ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ ከጅቡቲና ሩዋንዳ ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት አዋጅን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል። ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባውም የተለያዩ አጀንዳዎችን ተመልክቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመትን የተመለከተ ሲሆን፥ በዚህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ…

https://www.fanabc.com/ምክር-ቤቱ-ኢትዮጵያ-ከጅቡቲና-ሩዋንዳ-ጋር/
ጠ/ሚ ዐቢይ ከሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዲኤታዎች ጋር በእንጦጦ አረንጓዴ ዐሻራን አሳረፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዲኤታዎች ጋር  ዛሬ በእንጦጦ አረንጓዴ ዐሻራን አሳርፈዋል። ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ÷በአካል ተራርቀን፤ ንጽሕና ጠብቀን፣ እርስ በርስ ተረዳድተን- ኢትዮጵያን ከኮሮና እንታደግ  ብለዋል። አገር አቀፉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ጠቅላይ…

https://www.fanabc.com/ጠ-ሚ-ዐቢይ-ከሚኒስትሮች-እና-ሚኒስትር-ዲኤ/
በአሜሪካ በአንድ ቀን ከ35 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት 35 ሺህ 900 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ማስመዝገቧን ጆንስ ሆፒኪንስ ዩኒቨርስቲ አስታውቋል። ከዚያም ባለፈ በሀገሪቱ ባለፉት 24 ሰዓታት 756 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል። በምጣኔ ሀብት ዓለምን በምትመራው አሜሪካ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ካሏት 50 ግዛቶች ግማሽ በሚሆኑት በየቀኑ የበሽታው ስርጭት በመጨመር ላይ መሆኑ…

https://www.fanabc.com/በአሜሪካ-በአንድ-ቀን-ከ35-ሺህ-በላይ-ሰዎች-በ/
የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓትን ከጥምረቱ አባልነት ሰረዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት (ኢዴሕ)ን ከጥምረቱ መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ሆነው ተገኝተዋል በሚል ከአባልነት መሰረዙን አስታወቀ። ጥምረቱ አራተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ አካሄዷል። በዚሁ ጊዜ ጥምረቱ በአደረጃጀቱ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና የጥምረቱ ቀጣይ አቅጣጫ ላይም…

https://www.fanabc.com/የኢትዮጵያ-ፌዴራሊስት-ኃይሎች-ጥምረት-ህ/
የመን በቂ የፋይናንስ ድጋፍ ባለማግኘቷ የከፋ ችግር ገጥሟታል – ተመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳይ ሀላፊ የመን በቂ የሆነ የፋይናንስ ድጋፍ ባለማግኘቷ ሳቢያ የከፋ ችግር ተጋርጦባታል ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡ ሃላፊው ማርክ ሎውኮክ በርካታ የየመን ዜጎች በረሃብ ሳቢያ ፤ አሁን ላይ በየጊዜው ስጋቱ እየጨመረ ባለው የኮሮና ቫይረስ እንዲሁም በኮሌራ ይሞታሉ ብለዋል። ህጻናቱም ክትባት ስላልወሰዱ በገዳይ በሽታዎች ሳቢያ እንደሚሞቱ ትናነት በዝግ…

https://www.fanabc.com/የመን-በቂ-የፋይናንስ-ድጋፍ-ባለማግኘቷ-የ/
ወርልድ ቪዥን-ኢትዮጵያ ለሚኒስቴሩ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ወርልድ ቪዥን-ኢትዮጵያ ለጤና ሚኒስቴር 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መሳሪያዎች ድጋፍ አድርጓል። በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ፍቃዱ ያደታ ÷ ወርልድ ቪዥን -ኢትዮጵያ ለኮቪድ-19 መከላከያ እና መቆጣጠሪያ የሚውሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል። ድጋፎቹ ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ሀገር አቀፍ ርብርብ ያግዛልም ነው ያሉት…

https://www.fanabc.com/ወርልድ-ቪዥን-ኢትዮጵያ-ለሚኒስቴሩ-1-ነጥብ-7/
በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት 141 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 675 የላብራቶሪ ምርመራ 141 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 175 መድረሱንም የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል። ከዚህ ባለፈ 3 በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት…

https://www.fanabc.com/በኢትዮጵያ-በ24-ሰዓታት-141-ሰዎች-የኮሮና-ቫይረ/
የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየሰጠ ነው በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን እየሰጠ ነው በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን ገለፀ። የከተማ አስተዳደሩ እያስገነባቸው የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው ለሚገኙ ነዋሪዎች እንጂ ለተለያዩ ክልል ሰራተኞችም ይሁን ግለሰቦች የሚሰጥበት አሰራር የለውም ብሏል የከንቲባ ጽህፈት ቤት…

https://www.fanabc.com/የከተማ-አስተዳደሩ-በተለያዩ-ክልሎች-ለሚ/
ጠ/ሚ ዐቢይ በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው የሱዳን የአጋርነት ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው የሱዳን የአጋርነት ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ። ተባበሩት መንግስታት ድርጅ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ጀርመን ከሱዳን መንግስት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የሱዳን አጋርነት ዓለም አቀፍ ስብሰባ በዛሬው እለት ተካሂዷል። በኢንተርኔት በመታገዝ በተካሄደው ስብሰባው ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት…

https://www.fanabc.com/ጠ-ሚ-ዐቢይ-በኢንተርኔት-በመታገዝ-በተካሄ-2/
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ተከስቶ የነበረው አስከፊው የኢቦላ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ከሁለት ዓመት በፊት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል ። በርካታ የታጠቁ ቡድኖች በሚንቀሳቀሱበት ሰሜናዊ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል በፈረንጆቹ ከሚያዝያ 27 ወዲህ በበሽታው የተያዘ አዲስ ሰው አለመመዝገቡም ነው የተነገረው። ወረርሽኙን በቁጥጥር ስር ለማዋል የኢቦላ ክትባት ዘመቻ መስፋፋቱን ቁልፍ ሚና መጫወቱ ተገልጿል። በአገሪቱ የኢቦላ…

https://www.fanabc.com/በዲሞክራቲክ-ሪፐብሊክ-ኮንጎ-ተከስቶ-የነ/