FBC (Fana Broadcasting Corporate)
201K subscribers
61.2K photos
759 videos
23 files
54.2K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለውጡ ሂደት በሁሉም መስክ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማስቀጠል መንግስት በላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት እንደሚሰራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ ገለጹ፡፡

አቶ ተስፋዬ በለውጡ ሂደት ባለፉት አምስት ዓመታት በፖለቲካው መስክ የተከናወኑ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/186918
ትራምፕ የወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው የመጀመሪያው የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀድሞዋን የወሲብ ፊልም ተዋናይ ስቶርሚ ዳንኤልስን ዝም ለማሰኘት 130 ሺህ ዶላር ከፍለዋል በሚል ክስ ሊመሰረትባቸው መሆኑ ተሰማ።

ትራምፕ በፈረንጆቹ 2016 በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ከመሆናቸው ቀደም ብሎ ለግለሰቧ የከፈሉት ገንዘብ አለ በሚል በኒውዮርክ ጠበቆች ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል።

ምርመራው ትራምፕ ከቀድሞዋ የወሲብ ፊልም ተዋናይ ጋር የፈጸሙት ጾታዊ ግንኙነት ይፋ እንዳይሆን ገንዘብ ከፍለዋል በሚል ነው ሲካሄድ የቆየው።https://www.fanabc.com/archives/186931
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፕሬዚዳንቱን በቢሯቸው ተቀብለው እንዳነጋገሩ አስፍረዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ፣ በክልላዊ እና በባለ ብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከኮሞሮስ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ እና በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ለማጠናከርም እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።
ለግድቡ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ፈጠራ በታከለበት ሁኔታ ሊጠናከር ይገባል - አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረተሰቡ ለታላቁ ሕዳሴ ግድቡ ያለውን ጽኑ ድጋፍ በሚመጥን ደረጃ የማስተባበር ስራን ፈጠራ በታከለበት ሁኔታ ሊጠናከር ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
በ12ኛው ዓመት ዋዜማ የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሳባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩም የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ የስድስት ወራት አፈፃፀም ተገምግሞ አስተያየት እና የቀጣይ ስራ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል፡፡
አቶ ደመቀ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በታላቅ ንቅናቄያችን "እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን" በሚል ወኔ የተረባረብንበት ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ከተጀመረ እነሆ 12 አመታት ሆነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
12 የጥረት እና የስኬት ብሎም የፈተና ጉዞ የታየባቸውን አመታት አሳልፈን በስተመጨረሻ የድል ዘመናት ላይ ደርሰናል ነው ያሉት።
በዚህ ጉዞ ከሁሉ በላይ ህዝባችን በእውቀቱ፣ በችሎታው፣ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ ሳይሰሰት ለታላቁ የባንዴራ ፕሮጀክት አስተዋጽኦ አድርጓል ያሉት አቶ ደመቀ÷ በየደረጃው ያለው አመራርም ወደር የለሽ ርብርብ ማድረጉን አውስተዋል።
በህዝባዊ ተሳትፎም ሆነ በመሬት ላይ ያለው የፕሮጀክቱ አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ እየተጓዘ መሆኑ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው፥ ይሁንና ኅብረተሰቡ ለግድቡ ያለውን ፅኑ ድጋፍ በሚመጥን ደረጃ የማስተባበር ስራን ፈጠራ በታከለበት ሁኔታ ሊጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል።
ከአረንጓዴ አሻራ ስራ ጋር በማያያዝ የተፋሰስ ልማቱን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ትኩረት ልንሰጠው ይገባልም ነው ያሉት።
አቶ ደመቀ መኮንን ለዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ማህበረሰብ የአፍጥር ፕሮግራም አካሄዱ


አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ማህበረሰብ የአፍጥር ፕሮግራም አካሄዱ።

ፕሮግራሙ በስካይላይት ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፥ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፋሲለደስ ጥንታዊ ቤተ-መንግስትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጎንደር ከተማ የሚገኘውን የፋሲለደስ ጥንታዊ ቤተ-መንግስትን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷"በዚህ ስፍራ አባቶቻችን የሰሩት እጅግ አስደናቂ ጥበብና የእጅ ስራ ይታያል" ብለዋል፡፡

"ፋሲለደስ፣ አክሱም፣ ላሊበላን እና ሌሎች ጥንታዊ ቅርሶችን ስናይ በእጦት እሳቤ ያልተያዙ፣ አቅም ፣ ዕውቀትና ጥበብን ካለበት ማምጣት፤ ማሰናሰን፣ መደመር የሚችሉ አባቶች እንደነበሩን ያሳያል" ብለዋል፡፡

"ፋሲለደስ ሁሉም ዲዛይኖቹ የሚያሳየው የተገለጠላቸው፣ የማይታየውን ማየት የሚችሉ ሰዎች እንደነበሩም ነው ብለዋል፡፡

በቤተ መንግስቱ ሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የነበሩ ሙያዎች እና ስራዎች ተንፀባርቀዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ "ሊቃውንቶች ወደዚህ ስፍራ መጥተው ስራው ላይ ተሳትፈዋል፤ ድሮ በጋራ የሌለው ካለው አምጥቶ ያማረ የላቀ ስራ መስራት ነበረም ነው ያሉት፡፡

እዚህ ቦታ ላይ ያየነው የተደመረ ጭንቅላት ውጤት ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ያን በቅጡ መገንዘብ እና ጠቀሜታውን አውቆና አጉልቶ መጠቀም ላይ ውስንነት መኖሩንም ጠቁመዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/187101
ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በኦሮሚያ ክልል ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ኦሮሚያ ክልል ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከለውጡ በኋላ ባለፉት 5 ዓመታት በክልሉ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊና በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ለውጦችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ ድልና ስኬቶችን ለማስቀጠል ቁርጠኝነቱን በተለያዩ መፈክሮች አረጋግጧል፡፡

ሰልፈኞቹ የለውጡን ውጤቶች አጠናከረን እናስቀጥላለን፣ፀንፈኝነትን እንቃወማለን ፣ የህዳሴ ግድቡንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸውን የለውጡን ቱሩፋቶች ከጎናቸው ሆነን ከዳር እናደርሳለን፣ መጋቢት 24 የነጻነትነ የእኩልነት ሃውልት የተቀመጠበት ቀን ነው የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችን አሰምተዋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል፡፡
በጅማ ከተማ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማና አካባቢው ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ ፡፡

በድጋፍ ሰልፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ መንግስት በለውጡ የተገኙ ድሎች በማስቀጠል ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያረገውን ጥረት እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሀገር የመበታተን አደጋ በገጠማት አስቸጋሪ ጊዜ ወደ ስልጣን መምጣታቸውንና ፈታኝ ሒደቶችን በፅናት በማለፍ ሃገርን በመታደጋቸው እውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ነዋሪዎች አንስተዋል።

https://www.fanabc.com/archives/187122