✍ህይወትህ ብኩን የሚያደርጉ ነገሮች፦
• ምርጥ ሃሳቦች በአእምሮህ ዉስጥ እየመጡ በተግባር ካላዋልካቸዉ
• እራስህን ከሌሎች ጋር የምታነጻጽር ከሆነ
• የሚጠቅምህ ነገር ላይ ሳይሆን የማይጠቅምህ ላይ ጊዜህን ካቃተልክ
• ሰዎች ስለኔ ምን ያስቡ ይሆን ብለህ መጨነቅ ከጀመርክ
• ትላንት ስላሳለፍከዉ ህይወት ሁሌ የሚቆጭህ ከሆነ
• ነገ ምን እሆናለሁ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ
• እቅድህ በጣም ከበዛ
• ሰዉን ለመለወጥ ሁሌ የምትሞክር ከሆነ
• ምንም የማይጠቅም ክርክር ዉስጥ እራስህን ካገኘህ
• ለምትሰራዉ ነገር ደንታ ቢስ ከሆንክ ህይወትህን በጣም እያባከንከዉ ነዉ
✍️ህልመኛው
#በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት🙏
#ሰናይ ቀን ይሁንልን❤️
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
👇 SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@weygud18?si=u9zP5gLZfK-ndqi6
#Join us @Eyosc1
#አስተያየት ካሎት📩 @Eyos18
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄

❤20👍17
🤝ስብሃትና ቅንነት !
«የደሞዝ መምጫ ሰሞን ነው፤ ጋሽ ስብሃትና ጓደኞቹ መዋያ አጥተው ተፋጠዋል፡፡ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ አንድ ሰው መዋያ ቦታው ጭር ማለቱን አስተዋለና "እስኪ በዚች ነገር ሻይ ቡና ተባባሉበት" ብሎ 50 ብር አውጥቶ ሰጣቸው ፡፡ ይህቺን ብር ይዘው፤ ቅዳሜያቸውን ደማቅ ለማድረግ የሚረዱ አንዳንድ ግብዓቶችን ለማሟላት ጋሽ ስብሃትና አንድ ወጣት ተያይዘው ወጡ፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ፤ አንድ ጧሪ ቀባሪ ያጣሁ ነኝ ያሉ ሽማግሌ ድምጻቸውን አስተዛዝነው ምፅዋት ጠየቋቸው፡፡ ጋሽ ስብሃትም 50 ብሩን መዥረጥ አድርጎ አውጥቶ ለሽማግሌው ሰጣቸውና "ይዘው ይሂዱ" አላቸው፡፡ በዚህ መጠን ተመጽውተው የማያውቁ የሚመስሉት ሽማግሌም የምስጋና ቃል አጥሯቸው፤ ተፋጠጡ፡፡
ወጣቱም ---" ምን ሆንክ?" ምን ሆነህ ነው ለአንድ ለማኝ 50 ብር የምትሰጠው?" አለ በብስጭት፡፡
ስብሃት---"ስጓጓለት የቆየሁትን ነገር ነው፤ ዛሬ በተግባር ያዋልኩት"
ወጣቱም---"ምንድን ነው ስትጓጓለት የቆየኸው ነገር?"
ስብሃት---ብዙውን ጊዜ አንድ ለማኝ፤ 5፣ 10 ሣንቲም ግፋ ቢል 1 ብር ሲመፀወት ቆይቶ ድንገት50ብር ቢሰጠው ምን እንደሚሰማው ማወቅ እፈልግ ነበር፤ ዛሬ ሆነ - ቀኑ"
ወጣቱም---"እኛኮ ምንም የለንም፣ መዋያችንን ሙሉ በሙሉ እኮ ነው ያሻርካቸው " አለ በቁጣ!
ስብሃት---"ወዳጄ አሁን ስንመለስ፤ እግዜሩ ደግሞ እኛን የሚያሽር ልኮልን ይሆናል፤ ይልቅ ነቅተን እንጠብቀው፡፡"» አለው በደስታ!
✍ከ እንዳለጌታ ከበደ [ማዕቀብ መጽሐፍ]

❤41👍9🥰2😢2
⏰የባከነ ጊዜ!
“በአንድ በሚፈስ ወንዝ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ማቋረጥ አትችልም” ይባላል፡፡ እውነት ነው!
ይህ አባባል ሲተነተን፣ አሁን በእግሮችህ ተራምደህ የገባህበት ወንዝ አልፏል፡፡ ስትገባበት የነበረው ውኃ ቀጥሎ ለሚፈስሰው ውኃ ስፍራውን ለቆ በመሄዱ ምክንያት ተመልሰህ ብታቋርጥ ሌላ ውኃ ነው የምታገኘው፡፡ ወንዙ አንድ ነው፣ ውኃው ግን የተለያ ነው፡፡ ፍሰቱ ተመሳሳይ ነው፣ ወንዙ ይዞት የሚመጣው ነገር ግን የተለያየ ነው፡፡ የአፈሳሰሱ ሂደት ያው ነው፣ የፈሰሰው የውኃው አካል ግን ሌላ ነው፡፡
የጊዜያችንም ጉዳይ እንደዚሁ ነው፡፡
⏱️ የሰዓታት፡- ነግቶ እስኪመሽ የሚመጡትና የሚሄዱት ሰዓታት በተመሳሳይ ስም ይጠራሉ፣ ይዘውት የሚመጡትና ይዘውት የሚሄዱት ምርጫ ግን የተለያየ ነው፡፡
⏱️ የቀናት፡- ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉን ቀናት በስም ተመሳሳይ ናቸው፣ ይዘው መጥተው የሚያሳልፉት እድል ግን ልዩ ልዩ ነው፡፡
⏱️ የወራት፡- በየሰላሳ ቀናት የሚቀያየሩት ወራቶች መምጣትና መሄድ አንድ አይነት ነው፣ እነሱም ቢሆኑ ደግሞ የማይገኝ እድልን ይዘው መጥተው ጥርግ ብለው ይሄሉ፡፡
ጊዜ እንዲህ ነው! ሲመጣና ሲሄድ ያለው “አንድ አይነትነት” ያታልላል፡፡ የምንባንነው በወቅቱ ማድረግ የምንችለውን ነገር ማድረግ የማንችልበት ቀን ከመጣና ኋላ ከቀረን በኋላ ነው፡፡
✍ዶ/ር እዮብ
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል🙏
#አስተማሪ ሆኖ ካገኙት👍
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!
Join us @Eyosc1 📩 @Eyos18

👍28❤15👏1
ወዳጄ ሆይ እራስህን ብዙም ግልፅ አታርግ ምክንያቱም ግልፀኝነትህን ተጠቅሞ ወዳጅህም ጠላትህ ይሆናልና!
ቀን ጠብቆ የወጋህን እሾክ ጊዜ ጠብቀህ እስክትነቅለው ድረስ ታገስ እንጂ አውጡልኝ ብለህ ቁስልህን ለሰው አሳልፈክ አትስጥ ምክንያቱም የባሰ ያቆስልሀልና
ውሻ ጭራውን ሚቆላው ላንተ ሳይሆን እጅህ ላይ ላለው ዳቦ ነው አስመሳይና ውሸታም ሰውም እንደዛው ነው!
አንድን ሰው ስትተዋወቀው በአለባበሱ ልትመዝነው ትችላለህ ስትለየው ግን በአስተሳቡ ትመዝነዋለህ!
እንደ እኔ አንዴ እንደምትኖር አውቀህ ጊዜህንና ጉልበትህን በማይጠቅም ቦታና ማንነት ውስጥ አታባክን።
#በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት🙏
#ሰናይ ቀን ይሁንልን❤️
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
👇 SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@weygud18?si=u9zP5gLZfK-ndqi6
#Join us @Eyosc1
#አስተያየት ካሎት📩 @Eyos18
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄
ቀን ጠብቆ የወጋህን እሾክ ጊዜ ጠብቀህ እስክትነቅለው ድረስ ታገስ እንጂ አውጡልኝ ብለህ ቁስልህን ለሰው አሳልፈክ አትስጥ ምክንያቱም የባሰ ያቆስልሀልና
ውሻ ጭራውን ሚቆላው ላንተ ሳይሆን እጅህ ላይ ላለው ዳቦ ነው አስመሳይና ውሸታም ሰውም እንደዛው ነው!
አንድን ሰው ስትተዋወቀው በአለባበሱ ልትመዝነው ትችላለህ ስትለየው ግን በአስተሳቡ ትመዝነዋለህ!
እንደ እኔ አንዴ እንደምትኖር አውቀህ ጊዜህንና ጉልበትህን በማይጠቅም ቦታና ማንነት ውስጥ አታባክን።
#በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት🙏
#ሰናይ ቀን ይሁንልን❤️
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!
በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
👇 SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@weygud18?si=u9zP5gLZfK-ndqi6
#Join us @Eyosc1
#አስተያየት ካሎት📩 @Eyos18
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄
❤39👍15
እያነቡ እስክስታ
የሕይወት ቀለሙ እየሳቁ ህመምን መሸፈን፣ እያነከሱ ማዝገም፣ እየለፉ ማመስገን፣ እየተወጉ መትከል እናም የደረቀ በሚመስል ልምላሜ ውስጥ መፍካት.....ውበቱ ዳገቱ አናት ላይ መገኘት ሳይሆን ካናቱ ላይ ብርሀን ሆኖ መፍካት ነውና....እንደ ባለዜማው
ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ
ከተራራው ጫፍ ናትና ሕይወቴ
.
.
.
ቀላል ይሆናል....
#በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት🙏
#ሰናይ ቀን ይሁንልን❤️
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!👍

❤23👍8
❤️ለውብ ቅዳሜያችን!!
አዳም የሚያስጎመጀውን የዛፍ ፍሬ በሚስቱ ወትዋችነት ለመብላትና ላለመብላት ከራሱ ጋር ከታገለበት ጊዜ ጀምሮ ዓለም እስከ አሁን ድረስ በትግል ውስጥ ናት ።
የአንዳንዶቹ ትግል የቃየል አይነት ከንቱ ትግል ነው ።
ቃየል ያለ ፍትሀዊ ምክንያት ታግሎ የገዛ ወንድሙን አቤልን በመግደል በምድር ላይ የመጀመሪያው ሰው
ሆነ።ምክንያቱ ከንቱ ነበርና ውጤቱም ከንቱ ሆነ።
ትግሉ ያተረፈለት መቅበዝበዝ ብቻ ነበር።በእኛ ዘመንም ከንቱ ታጋዮችን አይተናል ፣ሰምተናል፣እያዬንም ነው ።
ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ለፍትሐዊ ምክንያት የታገሉ እነሱ በመከራ ውሰጥ አልፈው ብዙዎችን እፎይ ያስባለ ውጤት ያስገኙ ምርጥ ታጋዮች ነበሩ፥አሁንም አሉ ፣ወደፊትም ይኖራሉ።
የደቡብ አፍሪካው ጀግና ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ ከዘረኛው የቅኝ ግዛት ስሪት አፓርታይድ ጋር ባካሄዱት የእኩል እንሁን ትግል 27 ዓመት በሮበን ደሴትና ሌሎች እስር ቤቶች የስቃይን ፅዋ ተጎንጭተዋል።
በዓላማ ፅናታቸው ግን ሁሉንም ነገር በማለፍ የመጀመርያው የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት
በመሆን ተመርጠዋል።
ማንዴላ ያሳለፉት ውጣ ውረድና ትግል ታሪካቸውን ለሚያነብ ሰው አስደናቂ ነው።
ያላነበባችሁ መፅሀፏ በ148 ገፅ የተዘጋጀ እጥር ምጥን ያለ ስለሆነ ብታነቡት ብዙ ነገር ታተርፉበታላችሁ።
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡
🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/Eb7GSEtReo0?si=xnW1Fqjr0ezyZ2xo
❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
❇️ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@piyasa188
🙏አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን

❤26👍8🔥1
✍ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር!
ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡
የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ?
የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡
የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡
“በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡
❤መልካም ግዜ🙏

👏31❤26🔥1
ካነበብኳቸውና ከሚረብሹኝ ነገሮች አንዱ💔
―ዶክተሩ፡-የስኳር በሽታው ጸንቶብሻል ሌላኛውን እጅሽን ለመቁረጥ እንገደዳለን..
እሷም እንዲህ አለችው፦“አንድ ሳምንት መጠበቅ እንችላለን። ልጄ ጉዞ ሊያደርግ ነው። እና በአውሮፕላኑ ውስጥ ሲገባ ለመጨረሻ ግዜ እጄን ማወዛወዝ እፈልጋለሁ!”
―ዊልሰን እንዲህ ይላል፡-
“ከለሊቱ 8 ሰአት ላይ የእግዚአብሄርን መኖር የካድኩበትን ፅሁፍ ጨረስኩ እና ስተኛ እግዚአብሔር ምን ያደርገኛል በሚል ፍርሃት መብራቱን ማጥፋት አልቻልኩም ነበር።
―በትምህርት ቤት ደካማ ተሳትፎ የነበረው አንድ ልጅ ወደ እናቱ መቃብር ሄዶ፡- መች ነው እኔ ጋር የምትመጪው? መምህሩ በተማሪዎቹ ፊት ሁሌ እየመታኝ እንዲህ ይለኛል፦ “እናትህ ግድ የለሽ ናት ስለ አንተ ደንታ የላትም!”
― “ባሌ ቸልተኛ ይለኛል ምክንያቱም ፀጉሬ ሁል ጊዜ የምሰራው ምግብ ላይ ስለሚረግፍ። እንዴት ብዬ ነው ካንሰር እንዳለብኝ የምነግረው!”
― “የእናቴን ሬሳ ከመጠቅለሌ በፊት አፍንጫዋ ውስጥ ጥጥ ማስገባት ነበረበኝ። እና ጥጡን ከጓዳ ለማምጣት ስላልተመቸኝ ሁሉንም ዘንግቼ ጮክ ብዬ ተጠራሁ “እማዬ ከጓዳ ጥጥ አምጪልኝ..”
|እነዚህ የእውነት ክስተቶች ናቸው የትኛው የበለጠ ያማል?|
✍ሞገስ ዘአምድ
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል🙏
#አስተማሪ ሆኖ ካገኙት👍
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!
Join us @Eyosc1 📩 @Eyos18
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
―ዶክተሩ፡-የስኳር በሽታው ጸንቶብሻል ሌላኛውን እጅሽን ለመቁረጥ እንገደዳለን..
እሷም እንዲህ አለችው፦“አንድ ሳምንት መጠበቅ እንችላለን። ልጄ ጉዞ ሊያደርግ ነው። እና በአውሮፕላኑ ውስጥ ሲገባ ለመጨረሻ ግዜ እጄን ማወዛወዝ እፈልጋለሁ!”
―ዊልሰን እንዲህ ይላል፡-
“ከለሊቱ 8 ሰአት ላይ የእግዚአብሄርን መኖር የካድኩበትን ፅሁፍ ጨረስኩ እና ስተኛ እግዚአብሔር ምን ያደርገኛል በሚል ፍርሃት መብራቱን ማጥፋት አልቻልኩም ነበር።
―በትምህርት ቤት ደካማ ተሳትፎ የነበረው አንድ ልጅ ወደ እናቱ መቃብር ሄዶ፡- መች ነው እኔ ጋር የምትመጪው? መምህሩ በተማሪዎቹ ፊት ሁሌ እየመታኝ እንዲህ ይለኛል፦ “እናትህ ግድ የለሽ ናት ስለ አንተ ደንታ የላትም!”
― “ባሌ ቸልተኛ ይለኛል ምክንያቱም ፀጉሬ ሁል ጊዜ የምሰራው ምግብ ላይ ስለሚረግፍ። እንዴት ብዬ ነው ካንሰር እንዳለብኝ የምነግረው!”
― “የእናቴን ሬሳ ከመጠቅለሌ በፊት አፍንጫዋ ውስጥ ጥጥ ማስገባት ነበረበኝ። እና ጥጡን ከጓዳ ለማምጣት ስላልተመቸኝ ሁሉንም ዘንግቼ ጮክ ብዬ ተጠራሁ “እማዬ ከጓዳ ጥጥ አምጪልኝ..”
|እነዚህ የእውነት ክስተቶች ናቸው የትኛው የበለጠ ያማል?|
✍ሞገስ ዘአምድ
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል🙏
#አስተማሪ ሆኖ ካገኙት👍
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!
Join us @Eyosc1 📩 @Eyos18
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😢25👍12❤11
ጥበበኛው
ዶሮይቱ አንዲት እንቁላል ለመጣል ሰፈር ምድሩን እያስካካች ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለች። አትዩኝ፣ አትንኩኝ፣ ይነጠፍልኝ....አሳዳሪዋ እንቁላል አለኝ ብሎ አይለፍፍም። ጎረቤቶቹ በዶሮይቱ ማስካካት እንቁላል ሊኖራቸው እንደሆነ ብስራቱን ሰምተዋል።
በባህር ያለችው አሳ በአንዴ ዝም ባለው ባህር ውስጥ የት እንደሆነ አጥማጆች ሳይሰሙ፣ የባህር ኗሪዎች ኮሽታዋን ሳይሰሙ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ትጥልና ባህሩን በዐሳ ትሞላዋለች። አጥማጆቹም ማጥመጃቸውን በባህሩ በጣሉ ጊዜ የአሳይቱን ፍሬ ያገኛሉ።
የመኖር ቅኔው በዝምታህ ውስጥ ስራህን ስራ፤ ሥራህን ያስተዋሉ በፍሬህ ይመሰክሩልሀል እንጂ የስሙልኝ ጉባኤ አትዘርጋ ነውና በዝምታ እደግ፣ በዝምታ ፍካ፣ በዝምታ አፍራ። ፍሬህ በያንዳንዱ ልብና ነፍስ ሲዘልቅ ሁሉም ጋ ትኖራለህና!
ህልምሽ

👍24❤11👏5👎2🔥1
ካህሊል_ጂብራን The Prophet
ትናንት ከመቅደሱ በራፍ ቆሜ መንገደኞቹን ስለ ፍቅር ተዓምራቶችና ጥቅሞች ያውቁ እንደሆነ በጥያቄ ሳደርቃቸው ዋልኩ፡፡
አንድ የደከመና የገረጣ ፊት ያላቸው በዕድሜ የገፉ አዛውንት በአጠገቤ እያለፉ እንዲህ አሉኝ፡-
"ፍቅር ከመጀመሪያው ሰው የተሽለምነው ተፈጥሯዊ ድክመት ነው፡፡"
ይሁን እንጂ አንድ ጎበዝ ወጣት በንዴት መልስ ሰጠ፡-
"ፍቅር ዛሬን ከትናንት እና ከነገ ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው።"
አንዲት ሃዘን የተላበሰ ፊት ያላት ሴት አቃስታ እንዲህ አለች፦
"ፍቅር በገሃነም የሚሄድ ጥቋቁር እፉኝቶች የሚወጉን ገዳይ መርዝ ነው መርዙ እንደ ጤዛ ትኩስ ስለሚመስል የተራበች ነፍስ ተስገብግባ ትጠጣዋለች ከመጀመሪያው ስካር በኋላ ግን ጠጪው ይታመምና ቀስ በቀስ ይሞታል፡፡"
ከዚያም አንዲት ውብ ጉንጮቿ እንደ ፀሃይ የሚያበሩ ልጃገረድ ፈገግ ብላ እንዲህ አለች፡
"ፍቅር በንጋት ሙሽሮች የሚቀርብ ጠንካራ ነፍሶችን የሚያጠነክርና ወደ ከዋክብት እንዲመጥቁ የሚያስችላቸው ወይን ነው፡፡"
ከእሷ በኋላ አንድ ጥቁር ካባ የደረበ ፂማም ሰው አይኖቹን አፍጥጦ ተናገረ፡
"ፍቅር ወጣትነት የሚጀምርበትና የሚያበቃበት የታወረ ድንቁርና ነው፡፡"
ሌላኛው ፈገግ ብሎ ቀጠለ፡
"ፍቅር ሰው የአምላካቱን ያህል እንዲያይ የሚያስችል ሰማያዊ ዕውቀት ነው፡፡"
አንድ አይነ-ስውር መንገዱን በበትር እየፈለገ እንዲህ አለ፡
"ፍቅር ነፍስ የህያውነትን ሚስጥር እንዳታሳይ የሚከልላት፣ በዚህም ልብ ከኮረብቶች መሃል የሚንቀጠቀጡትን ጣዕረ -ሞቶች ፍላጎት ብቻ እንዲያይ እና የድምፅ አልባዎቹን ሸለቆዎች የመስተጋባት ጩኸት ብቻ እንዲሰማ የሚያደርግ የጉም መጋረጃ ነው፡፡"

❤21👍7
ይህን ያውቃሉ⁉️ፓራስታሞል
አንድ ፓራስታሞል መዋጥ 3 ጠርሙስ ድራፍት ጋር ከመጠጣት እኩል መሆኑን ያውቃሉ?
ፓራስታሞል በጉበት ላይ ጉዳት ያስከትላል። ፓራስታሞል በተደጋጋሚ መዋጥ የጉበትን የመስራት አቅም ይቀንሳል። በጉበት ላይ ስብ እንዲከማች ያደርጋል። ብዙ ሰዎች በትንሽ በትልቁ የሚያዘወትሩት ፓራስታሞል ውጦ አልኮል መጠጣት በፍፁም ሊደረግ የማይገባው ነገር ነው።
ሲጀመር ፓራስታሞል ማስታገሻ እንጂ መድሃኒት አይደለም። መዋጥ ያለባችሁ በጣም አስፈላጊ ከሆነ እና ሌሎች አማራጭች ከሌሉ መሆን አለበት ።
✅Paracetamol
✅panadol
✅Tyloric
✅Acetaminophen እኚ ሁሉ የአንድ መድሃኒት የተለያዩ ስሞች ናቸው።
𝗗𝗿. 𝗔𝗯𝗶𝘆 - 𝗝𝗶𝗺𝗺𝗮
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል🙏
#አስተማሪ ሆኖ ካገኙት👍 ❤

❤26👍7
(ፈጣሪ)..
ፈጣሪ አይበላ፣ አይጠጣ፣ አይለብስ፣ ትራንስፖርት አይጠቀም፣ ቤት አይከራይ፣ አይታከም፣ አይማር፣ አይነግድ፣ አይከስር፣ የስራ ማስኬጃ አይፈልግ ....ግን በምድራችን ላይ እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ የሚሰበሰበው በፈጣሪ ስም ነው። ከደሀዋ መሃረም እስከባለፀጋው ካዝና የሚበዘበዘው በነዚሁ ተቋማት ነው። የዓለማችን ሐብታም ተቋማት የሐይማኖት ድርጅቶች ናቸው። ግን ነን አይሉም። የዓለም ከፍተኛው ሐብት የተከማቸው አሁንም በሐይማኖት ድርጅቶች ላይ ነው። በመረጃ እናስደግፈው ።
ለምሳሌ ይላል የ 2025 ጥናት ነው። የአለማችን የሀይማኖት ድርጅቶች አጠቃላይ ሐብት (ያውም በጣም ድብቆች ስለሆኑ ከዚህ ብዙ እጥፍ እንደሚበልጥ ታሳቢ ሆኖ)
190 ትሪሊየን ዶላር ይሆናል ። (ትሪሊየን) ይሄ ያላቸውን ድብቅ ሐብት ( dark assets) እንዲሁም በዋጋ የማይተመን ቅርሳቸውን ፣ህንፃና መሬታቸውን ሳይጨምር ነው። ይሄ ማለት የአለማችን ቁጥር አንድ ባለፀጋ ኤሎን መስክ አይነት 253 ሰወች ተደምረው ያላቸው ሐብት ማለት ነው። 253 ኤሎን መስክ!
እና ይሄ ሐብት ለሰው ልጆች ይከፋፈል ቢባል በአለም ላይ ያለውን እያንዳንዱን ሰው (ቤተሰብ አይደለም፣ ሰው ዛሬ የተወለደውን ጨምሮ) የቤት ባለቤት ማድረግ ይችላል። ለዓመታት ያለምንም ስራ አንድም ሰው ሳይራብ ያኖራል። እያንዳንዱ ሰው ንፁህ ውሃ ፣ በቂ ህክምና፣ ትምህርት ማግኘት ይችላል። የሚገርመው በየአመቱ 5 ትሪሊየን ዶላር ከምዕመኑ ይሰበሰባል። ይታያችሁ የዓለማችን ባለግዙፍ ኢኮኖሚ አገር አሜሪካ የአመት ገቢዋ ነግዳ ጉሮሯችሁን አንቃ ታክስ አስከፍላ ሁሉ 5.5 ትሪሊየን ዶላር ነው።
እንቀጥል...ለምሳሌ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የያዘችው መሬት ቢገጣጠም ቫቲካንን ጨምሮ ድፍን ፈረንሳይን ያክላል። የሌሎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተማከለ አሰራር ስለሌላቸው ባይታወቅም ቀላል አይደለም። የሆነ ሁኖ የእምነት ተቋማት ለበጎ አድራጎት እና መሰል ተግባራት በየአመቱ 1.3 ትሪሊየን ዶላር ቆንጠር አድርገው ይሰጣሉ። ገበያው ውስጥ (የዓለም ኢኮኖሚ ላይ) ካላቸው 5 በመቶ የሚሆነውን ኢንጀክት በማድረግ ገበያውን ይቆጣጠሩታል። እንግዲህ ታዘቡ። የአስር ያደጉ አገራት የሐይማኖት ተቋማት ተደምረው አንድ ግዙፍ ፋብሪካ ወይም አምራች ድርጅት የሚፈጥረውን ያህል የስራ እድል አይፈጥሩም። ሲጠቃለል አለማችን በድህነት አረንቋ ለመዘፈቋ ለሰው ልጆች አሰቃቂ ድህነት ከፖለቲከኞች በላይ የእምነት ተቋማት ስግብግብነት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ለዚያውም በሚጭሩት መለያየትና ግጭት የሚገበረውን ሕይወት ሳትቆጥሩት ነው።
ከመጮሀችን በፊት ጉዳዮን በጥልቀት ብታነቡና የራሳችሁን ሪሰርች ብትሰሩ ቢያንስ ወደየአምላካችሁ ኧረ ምን ጉድ ነው በስምህ የሚደረገው ብላችሁ ለመፀለይ ይረዳችኋል።
Alex አብርሃም ✍

❤7👍5🤔1
Forwarded from ONLY BETTING
ሃናንን በጣም እወዳት ነበር እሷም እንደዛው ለዛ ነው ትምህርት ላይ እያለን ኒካህ ያሰርነው።ከኔ ይበልጥ የሷ ፍቅር ከፍ ይል ስለነበር ነፃነቴን አሳጣቺኝ በ ቀን ከ 10ጊዜ በላይ ትደውላለች ምሳ ፣ ቁርስ ፣ እራት ፣ መክሰስ ጭምር መብላቴን ታረጋግጣለች። ሰለቸኝ!!
አንድ ቀን እንቅልፌን ልተኛ እየተዘጋጀው እያለ ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ሃናን ነበረች ቀን ስላወራን መልዕክቱን ሳልከፍተው ተኛው።
ጠዋት ስነሳ እናቴ እያለቀሰች ትቀሰቅሰኛለች ምን እንደሆነች ስጠይቃት የ ሃናን እናት ደውላ እንደነበር እና ማታ . ...read more 📍ሙሉ ለማንበብ 📥 ይጫኑ