ከትዕቢቴ ትገራኝ ዘንድ ሰብረህ ትጠግነኛለህ።እንደወርቅ አንጥረህ ልታወጣኝ በመከራ እቶን ውስጥ ታሳልፈኛለህ !
ምሪትህን ምጋቤህን ፣ ጥበቃህን ፣ በወዳጆቼ አጀብታ መረዳት ለተሳናት ነብሴ ትማር ዘንድ ነጥለህ ብቻዬን ታስቀረኛለህ!
በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ በየዕለት ድካሞቼ ያለፀጋህ ምን ያህል ድኩም እንደሆንኩ አስገንዝበህ ይበልጥ ወደ ውስጤ ሳይሆን ወደ ልጅህ እንዳይ ታደርገኛለህ !ኢምንት የማታክለው እውቀቴ እንደ ምታስታብየኝ ስለምታውቅ ሌሎችን ቁልቁል እንዳላይ ከማውቀው በላይ የማላውቀውን አበዛህ !የአንተን መልካምነት በፍጥነት የምትዘነጋው ነብሴን በነገር ሁሉ ውስጥ መልካምነትህን አስታወስካት !
ከኃጢአት ጋር እንዳልጫወት ገስፀህ ከቅድስህናህ እንድካፈል አደረከኝ !
ከህይወቴ ጨለማዎች ውስጥ ብርሃንን እያወጣህ በነገሮች ሁሉ ልጅህን እንድመስል በጎን እንድሰራ አደረክ!
እኔው ለራሴ ጠላት ነኝና ከጽዮን ጉዞዬ እኔነቴ እንዳይገታኝ በጉዞው መስቀልህን አሸክመህ እኔነቴን በመከራዎቼ ጎሰምከው!
አቤቱ አሁንም ስበረኝ እና ጠግነኝ!
በመከራው እቶን አሳልፈኝና አጥራኝ !
ከቅድስናህ እካፈል ዘንድ ገስጸኝ!
ኑዛዜ

🥰6
" ግብዝነት ማለት አንድ ነገር የሚጠይቀውን ዋጋ ላለመክፈል ሲባል እና የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በራስ ወዳድነት ተነሳሽነት የሚደረግ ትወና ነው። "
❝25 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ጽዋውንና ሳህኑን በውጭ ታነጻላችሁ፥ በውስጡ ግን በመዝረፍና በመብላት የተሞላ ነው።
26 አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ መጀመሪያ የጽዋውንና የሳህኑን ውስጥ አንጻ፥ ውጭውም ንጹሕ ይሆናል።❞
የማቴዎስ ወንጌል 23፥25-26

👍2
ፓስተር አገኘሁ ይደግ - በለሲቱን & ...
Agegnehu Yideg Wube
የዘማሪ አገኘሁ ይደግ ቆየት ያለ ዝማሬ
መሬት አበላሸች ሌላ አታፈራ
ቅጠልም ያወጣች በብዙ መከራ
ቢሆንም ታገሳት ታፈራ ይሆናል
ጌታዬ ምህረት ከህይወት ይሻላል
ኢየሱሴ ምህረት ከህይወት ይሻላል*2
በለሲቱን ታገሳት ×2
አትቁረጣት
አንድ አመት ታገሳት አትቁረጣት
ከሌሎች በለሶች ዘለላ አላገኘህ
ይቺ ግን መጣበት ቀረ እንደተመኘ
አንድ አመት ታገሳት ዕድል ጨምርላት
ታፈራ ይሆናል በፀጋህ ምን አልባት (እንደሆነ) በፀጋ ምናልባት ×2
አዝማች × 2
በለስን ጠብቀህ ፍሬዋን ካልበላህ
እንዳልቀናው አዳኝ...................
ፈጥነህ አትርገማት የደካሞች ታዛ
ቁጣህ የዘገየ ምህረት የበዛ
አዝማች ×2
ሁልጊዜ መፍገምገም ሁልጊዜ ንስሀ
ፍሬ አላደረገች እንደሆነች ደሀ
ቀኑን አይምሽባት አንተው እዘንላት
በጎደላት ሁሉ ሙላቷ ሁንላት
ደግፈህ ደጋግፈህ ቀኑን አሳልፍት
ታፈራ ይሆናል በፀጋህ ምናልባት
ታፈራ ይሆናል አንድ ቀን ምናልባት
ና ጎብኘኝ ×2 ይህን ክፋ ዘመን አሳልፈኝ
የጠራራው ፀሀይ ግለቱ
የምድረ በዳው ትኩሳቱ
ያላንተ ግን ጌታ አይዘለቅ
እሾህ አሜኬላው መንገዳችን ላይ
.....
በማለዳ ለፀሎት ቀስቅሰኝ
የመንፈስህን እሳት አልብሰኝ
https://t.me/eyesovwisdom

🥰4
የ 12ተኛ ክፍል ውጤት ለምትጠብቁ
ሰሞኑን የ 12ተኛ ክፍል ፈተና የተፈተነው ታናሽ ወንድሜ በብዙ ሲጨነቅ እና ሲያስብ ራሱንም ከዛ ሀሳብ distract ለማድረግ ሲል ብዙ ነገር ሲያደርግ አየሁት። አሳዘነኝ ። እኔም በጊዜው ተፈትኜ ውጤት የሚለቀቅበት ወቅት ላይ የነበረኝን ጭንቀት አስታወሰኝ።
ዛሬ ላይ እንዳለፈበትና እንደ አንድ ወጣት ነገሩን ስታዘበው የዚህ ጭንቀት መንስኤ ነገ የተሻለ ቦታ ላይ ለመድረስ ማሰብ ሊሆን ቢችልም ከምንም በላይ " ምን ይሉኝ ይሆን ? ባይሳካ ቤተሰቤ ፣ የሰፈር ሰው ፣ ጓደኞቼ ምን ይሉኝ ይሆን ? " የሚለው የይሉኝታ ስሜት የሚፈጥረው ጫና እንደሆነ ታዝቤያለሁ። የእኛ ማህበረሰብ በአንድ በኩል ልጁ በትምህርት የጎለበተ ሆኖና የተሻለ ቦታ ደርሶ ማየት መፈለጉ መልካም ቢሆንም ነገር ግን ሕይወት መንገዷ አንዳንዴ ጠመዝማዛ ነውና ባላሰብነውና ባላቀድነው ጎዳና ላይ የመጓዛችንን ሁኔታ ህብረተሰባችን ( በተለይም ቤተሰብ (አንዳንዴ) ) በፍፁም ከግምት ውስጥ ያላስገባ አካሄድን ሲሄድ እናያለን። ከዚህም የተነሳ ነገሮች ባላሰበው መንገድ መሄድ ሲጀምሩ ወጣቱ ለራሱ ያለው ገፅታ (ምልከታ) እየተበላሸ ይሄዳል። ከዚህም የተነሳ ተስፋ መቁረጥ ፣ Depression (ድባቴ) ፣ አንዳንዴም ሲከፋ ራስን መጉዳት ውስጥ ይገባል።
ወጣቶች ሆይ ከፊታችን ብዙ አስፈሪ እና አስጨናቂ ጎዳናዎች ሊኖሩ ይችላሉ ። ነገ የሚባለው ነገር ያስፈራናል ምክንያቱ ደግሞ ነገን ማወቅም ማየትም አንችልም ስለዚህ እንጨነቃለን። ነገር ግን ነገን የሚያውቅ ደግሞ ነጋችን በእጁ የሆነ አምላክ አለን። ወዳጆች ሆይ ነጋችን ሁኔታዎች ፣ ጭንቀቶቻችን ፣ አንዳንዴም ቤተሰብና ማህበረሰብ እንደሚሉት ሳይሆን እግዚአብሔር እንደሚለው ነውና እንዲመራንና እርሱ እንዲዘውረው (እንዲሾፍረው) እንተውለት። በየትኛውም ሁኔታ እግዚአብሔርን ታምነን ተስፋ ሳንቆርጥ ዛሬም አቅንተን ወደፊት እንመልከት እርሱ ያደርሰናል።
ውጤት እየጠበቃችሁ ያላችሁ ወንድም እህቶቼ ውጤት ሲመጣም ሳይመጣም እግዚአብሔር መልካም ነው። ባይመስልም ግን ነው! ሕይወት ደግሞ ሰፊ እንዲሁም የላቀ ትርጉም ያላት ናት። ትምህርት በሚባል መነፅር ብቻ አትታይም ከዛም ትሰፋለችና። እንዲህ ስል መማርንና ውጤት ማምጣትን ማጣጣሌ አይደለም ነገር ግን በተላያዩ ምክንያቶች ከሕይወታችን ቢጎድሉ የዓለም መጨረሻ ( End of the world ) አለመሆኑን ለመናገር ያህል ነው።
" ተደናቅፈሃል ማለት ሩጫውን አትጨርስም ማለት አይደለም። "
“Above all else, guard your heart, for everything you do flows from it.”
— Proverbs 4:23 (NIV)
ምሳሌ 4፥23
“ከሁሉ በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጮች ሁሉ ከእርሱ ይወጣሉና።”
ለወንድም ለእህቶቻችሁ አጋሩ ! ተባረኩ!
ሰላም 👋☺️

Telegram
አዕይንተ-ጥበብ
#አዕይንተ_ጥበብ ፦ ማለት ሕይወትን በጥበብ የሚመለከቱ አይኖች ማለት ሲሆን ቃሉ የግዕዝ ቃል ነው። ሁላችን በእግዚአብሔር ቃል የጥበብ መነፅሮች (አይኖች) ሕይወትን እንመለከት ዘንድ ይህ page ይጋብዛል።
#ግላዊ ምለከታዎችንና ትዝብቶችንም የማጋራ ይሆናል።
For comment @solacristus
#ግላዊ ምለከታዎችንና ትዝብቶችንም የማጋራ ይሆናል።
For comment @solacristus
❤10
ንስሐ
በንስሐ ዙሪያ የተፃፈ ጥሩ መፅሀፍ ዙሪያ የሚያትት ርቱዕ ፅሁፍ...
"ቶማስ ዋትሰን Doctrine of Repentance በተሰኘው መጽሐፋቸው ከሁለት አደገኛ ዘመናዊ ስህተቶች ራሳችንን እንድንጠብቅ አስጠንቅቀዋል፦ አንደኛው ንስሐን ከጸጸት በላይ ምንም ነገር እንዳልሆነ መቁጠር [Treating repentance as cheap, shallow regret] እንደ ቁጭት ስሜት መመልከት፣ ሁለተኛው፤ ንስሐን ረዘም ላል ጊዜ የሚሆን የሀዘን ስሜት ወይም የስሜት ስቃይ [emotional misery] አድርጎ መቁጠር።
አንድ ልናስተውለው የሚገባ መሰረታዊ ሀቅ ንስሐ እውነተኛ ሐዘንን [Sorrow] ይፈልጋል። ኃጢአት ቅዱስ በሆነው እግዚአብሔር ላይ የሚፈጸም በደል ስለሆነ፣ ሐዘንን ዘለን ልናልፈው አንችልም።
እውነተኛ ሐዘን አስፈላጊ ነው፤ እውነተኛ ሐዘን የነፍስን ሕመም የሚያጸዳ መድኃኒት ነው። ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን በዚያው ለመኖር የተዘጋጀ መኖሪያ ቦታ አይደለም።
ዋትሰን እንደገለጹት ሐዘን መግቢያ በር እንጂ መድረሻው አይደለም። የሐዘን [Sorrow] ዓላማው ኃጢአተኛውን ወደ መስቀሉ መምራት ብቻ ነው። አንዴ መስቀሉ ጋር ደርሰን የሚያነጻውን የክርስቶስን ደም ከተቀበልን፣ ሐዘን ተግባሩን ፈጽሟል፤ ወዲያውኑም ለደስታ ቦታውን መልቀቅ አለበት።
ኃጢአታችንን ከተናዘዝን በኋላ በማያልቅ ሐዘን ውስጥ መቆየት፣ መግቢያ በሩን እንደ መዳረሻ አድርጎ የመቁጠር ስሕተት ነው። ዋትሰን እንደጻፉት፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን በመጨረሻ ከሁሉ የሚጣፍጥ የደስታ ፍሬን የሚያፈራ፣ የሚጠወልግ አበባ ነው።
ሐዘን ልብን ይሰብራል፤ ደስታ ደግሞ ይፈውሰዋል... ለቅሶ ዘር ነው፤ ደስታ ግን ፍሬው ነው። እውነተኛ ንስሐ በእግዚአብሔር ላይ በተፈጸመ ኃጢአት ላይ አጥብቆ ያዝናል።
ከዚያም፣ ሙሉ በሙሉ ይቅር የመባል ቃሉን በማመን፣ ከአመዱ ውስጥ ወጥቶ ወደ ደስታው ድግስ ይገባል። መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ ይህንን እውነት እንዲል ሲል ዘምሮታል
ደስ ፡ ይበልህ ፡ ወንድሜ ፡ ከሳሽህ ፡ ተጥሏል.
የኃጢአትህ ፡ ዋጋ ፡ በጌታ ፡ ተከፍሏል
ምህረቱን ፡ ተቀበል ፡ ኃዘንህን ፡ እርሳው..
ከንስሐ ፡ ወዲያ ፡ ልብህን ፡ ደስታ ፡ ይሙላው"
Pursuing Holiness

“ኢየሱስ መች ይተውሃል” በዘማሪ ተስፋ...
Paradise
#ፓሰተር_ተስፋዬ_ጋቢሶhttps://t.me/eyesovwisdom
የንስሐ መዝሙር
የተሸከመው ሀጢአት ከብዶት
ነፍሱ ተጨንቃ ሰላሙ ርቆት
የሕይወቱ ተስፋ ያለቀበትን
ቀኑ ጨለማ የሆነበትን
ኢየሱስ መች ይተዋል
ከቶስ እንደምን ይረሳዋል
የፍቅር አባት ይፈልገዋል
በምህረት ጠርቶ ይመልሰዋል
ከክፉ መንገድ ሀጥ ቢመለስ
በመስቀሉ ስር ወድቆ ቢያለቅስ
ይድናል እንጂ ያ ሰው አይሞትም
ይበዛለታል ሰላም ህይወት
ኢየሱስ መች ይተወዋል
ከቶስ እንደምን ይረሳዋል
የፍቅር አባት ይፈልገዋል
በምህረት ጠርቶ ይመልሰዋል2×
የመታደስን ዘመን አምጥቶ
በፀጋው ክብር ልጁን ጎብኝቶ
ያለፈውን በደል በደሙ ሽሮ
ይቀበለዋል በፍቅር ምሮ
እየሱስ መች ይተወዋል
ከቶስ እንደምን ይረሳዋል
የፍቅር አባት ይፈልገዋል
በምህረት ጠርቶ ይመልሰዋል2×
አንዱ ቢባዝን ወድቆ ከመንጋ
የማይሄድ ማነው ያንን ፍለጋ
የፍቅር ግዳጅ ስራ ላይ ውሎ
ብዙ ተጓዘ ጌታ አንተን ብሎ
ኢየሱስ መች ይተውሀል
ከቶስ እንደምን ይረሳሀል
የፍቅር አባት ይፈልግሀል
በምህረት ጠርቶ ይመልስሀል*2
❤5
መተው
ከኮዬ ወደ መገናኛ ለመሄድ ከጠዋቱ 3:30 አካባቢ መስቀለኛው ጋር ደረስኩኝ። ከአንድ ቀን በፊት ልንገናኝ ከተቀጣጠርነው ወዳጆቼ ጋር በጠዋት ለመገናኘት ተስማምተን ነበርና አርፍጄባቸው እየተበሳጩብኝ ነው። እንደምንም በጥድፊያ ባሶቹ ጋር ስደርስ ሁለት ሰልፍ አየሁኝ። የመጀመሪያው ሰልፍ ረዘም ያለ ሲሆን ሁለተኛው ሰልፍ አጭር እና ከመጀመሪያው ሰልፍ በተቃራኒ ያለ ሰልፍ ነው።
ሰልፎቹ ትይዩ ናቸው ማለትም ፊት ለፊት አንዱ ሰልፍ ከሌላው ሰለፍ ተፋጦ ነው ያለው። በሕይወቴ እንዲህ አይነት ሰልፍ አይቼ አላውቅም።( እንደ ማንኛውም ኢትዩጵያዊ ብዙ ሰልፎችን ተሰልፌ አውቃለሁና ግር ብሎኛል) አጠገባቸው ደርሼ ስጠይቅ ሁለቱም የ መገናኛ ሰልፎች ናቸው። ልዩነቱ አንዱ ቁሞ ለመሄድ የሚፈልግ የሚሰለፍበት ሲሆን ሌላው ተቀምጦ በምቾት ለመሄድ የሚፈልግ የሚሰለፍበት ነው።....ረፍዶብኝ ነበርና ቆሞ ከሚሰለፈው ወገን ተሰይሜ ብዙም ሳልቆይ እባሱ ላይ ተሳፈርኩኝ።
እንደ ሰው ሁላችንም ምቹ ነገር እንወዳለን። ምቾትንስ የሚጠላ አለ ?
ነገር ግን በሕይወት መንገድ ላይ ከምቾት የላቀ ቁም ነገር አለና አንዳንዴ ምቾታችንን ሰውተን (ትተን) ቁምነገሩን አስበልጠን እንመርጣለን። ታዲያ በሕይወት መንገድ ላይ ከየትኛው ወገን ራሳችንን አገኘነው ? ለምቾቱ ከተሰለፈው ወይንስ ለቁምነገሩ ከተሰለፈው ሰልፈኛ..?
ብቻ ቁም ነገሩ "ቁም" አለኝና ቆሜ ይህን ሳወጣ ሳወርድ ደረስኩ እላቹሃለሁ። 😄
ሰላም 👋😊

❤10😁4🔥1👏1
የዘመኔ ጸሐፍተ -ትእዛዛት
በንጉሳዊያን ዘመነ - ንግስና የንጉሱን ውሎ (ዜና መዋዕል) ጦማር አሰናጅ ጸሐፌ-ትዕዛዛት ነበራቸው። ታዲያም ቃላትን በማጎን በወገንተኝነት እንዝርት እየፈተሉ ጥሁፋቸውን ያቀርባሉ ከመንበረ ንግስና እስከ ጦር ሜዳ ጀብዱ ይተርካሉ። ንጉሱን ምን ቢፈራ የጀግንነት ውሀ ልክ፤ንፉግ ቢሆን የድሆች አባት፤ጭካኔው ፅንፍ ቢረግጥም የባልቴት ዳኛ እያለ ያሞካሻል። ለምን? ድርጎ ፣ምንዳ፣የዕለት ጉርሱን እንዳያጣ ነዋ!
ታዲያ ይህን ያነሳሁት ለ አንድ ትምህርታዊ ለሆነ ኘሮግራም ወደ ሆነ ቦታ ባቀነሁበት መቅፅፈት ሀገረ-ምድሩ ወሬው አፈሳ ሆኖ ቆየኝ። እናም ከስልጠናው እንደወጣሁ የመረጃ ጥሜን ጋብ ቢያደርግልኝ ብዬ ከትዕይንተ መስኮት ፊት ተሰይሜ ዜና ፍለጋ ተቅለበለብኩ ምን ያደርጋል ጋዜጠኛው ሁላ ሀገር ውስጥ እንደሌለ ሰው ፤ ምንም እንዳልሰማ የሰላም ነጋሪት ይጎስማል። አንዱ" የሀገሪቷ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታው አመርቂ ውጤት አስገኘ ሲል "ሌላው "ለጥቆ ድህነትን በጋራ መዋጋት አለብን ሲሉ አንዳንድ የአዲስ-ሳባ ነዋሪዎች ተናገሩ" ይላል። እነሆ የዘመኔ ጸሐፍተ -ትዕዛዛት...
ኤርሚያስም በትንቢቱ በሀሰተኛ ነቢያት የሀሰት ዲስኩር የተነሳ እንዲህ ይላል
የሕዝቤን ቍስል እንደ ቀላል ቈጠሩ፣
እንዲፈወስም ተገቢውን እንክብካቤ አላደረጉለትም፤
ሰላምም ሳይኖር፣
‘ሰላም፣ ሰላም’ ይላሉ።
ኤርምያስ 6፥14

❤3👍3🔥1🥰1
እግዚአብሔር በሦስት ውርደቶች ውስጥ ዐልፏል። ከእነዚህም የመጀመሪያው ትሥጉት ነው፣ ቃል ሥጋ ሲሆን ፣እግዚአብሔር ሰው መሆንን መምረጡ። ሁለተኛው መስቀሉ ነው፣በህዝቡ ፊት ዕርቃኑን መሰቀሉ። ሥስተኛው ውርደት ቤተክርስቲያን ናት ፤የከበረውን ስሙን የማንመጥነውን ሰዎች በወኪልነት መምረጡ።
Philip yancey, just wondering (London: Monarch Books,1989),187-88
ትርጉም:-(ጳውሎስ ፍቃዱ በተሰቀለው መፅሀፍ እንደተጠቀመው።)
Join👇
https://t.me/eyesovwisdom
Philip yancey, just wondering (London: Monarch Books,1989),187-88
ትርጉም:-(ጳውሎስ ፍቃዱ በተሰቀለው መፅሀፍ እንደተጠቀመው።)
Join👇
https://t.me/eyesovwisdom
😢4❤3
አደረስከኝ
ዛሬም እንደ ትላንትናው አሳልፈህ አደረስከኝ ! የማያልፉ የመሰሉኝን ቀናት አሳልፈህ ፣ ያስጨነቁኝን ገለል አድርገህ ፣ ሁኔታዎቼን ከአንተ ይልቅ አምኜ ተስፋ ስቆርጥ እንደገና እያስቀጠልክ፣ ስለዋወጥ አንተ ግን ሳትለወጥ እየታገስክ ይኸው አደረስከኝ !
እንደኔማ ቢሆን ዛሬንም ባላየሁ ! እንደ ዕቅዶቼ ቢሆን ኖሮ ፣ እንደ ሄድኩባቸው ራስ ገዝ መንገዶች ቢሆን ኖሮ ፣ እንደኔ ውሳኔዎች ቢሆን ኖሮ.....ዛሬን ባላየሁ ነበር። አንተ ግን የእንደገና አምላክ ነህና ስወድቅ እንደገና እያነሳህ ፣ እግሮቼ ሲስቱ እንደገና እየመለስክ ፣ ሳጠፋ እንደገና እየማርክ ፣ በማወቅ ከገባሁበት ማጥ አውጣኝ ስልህ ሳትሰለች እያወጣህ እንደገና አጥበህ ቀድሰህ እያቆምከኝ.....አደረስከኝ ።
አሁን ምንም እንደማልችል ገብቶኛል። በራሴ አልተማመንም ነገም እንደ ትላንት ሲኳትን አገኘዋለሁና። ስለዚህ ቃልህ እንደሚል በፍፁም ልቤ በአንተ እታመናለሁ ነገዬንም በአንተ ላይ እጥላለሁ። አንተ ትላንት እንዳሳለፍከኝ ነገንም ታሳልፈኛለህ አቤቱ ታምኜህ እንድጓዝ እርዳኝ። ከራሴ ማስተዋል ይልቅ ባንተ ሁሉን አዋቂነት እደገፍ ዘንድ ሀይልን ስጠኝ። ዛሬን ስላደረስከኝ ስላበቃኸኝ አመሰግንሃለሁ።
እንኳን ለ 2019 ዓ.ም በሰላም "አደረሳችሁ"!!!

❤3🥰1
የምትመለከቱት ሰው በኦሮምኛ ቋንቋ መፅሐፍ ቅዱስን ለመጀመሪያ ጊዜ የተረጎሙ የወንጌል አርበኛ ሲሆኑ ባለቤታቸውን እና አራት ልጃቸውን በሞት ያጡ ሲሆን ሀዘናቸው ወንጌልን ከመመስከርና ከአገልግሎት አላገዳቸውም ነበር። እስከ ዕለተ ሞታቸውም ለተላኩበት አካባቢ ወንጌልን እየሰበኩና እያስተማሩ የቆዩና ለእግዚአብሔር መንግስት ስራ ዋጋቸውን ተምነው የቆረጡ አባት ነበሩ። ዛሬስ እኔ፣ አንተ፣ አንቺ....እኛ ለእግዚአብሔር መንግስት ምን አይነት አሻራ እያሳረፍን ይሆን..?
👍3❤1🔥1
Addisu Worku //ኑሮ ያለ ጌታ ታክቶኝ//
🎵 ኢየሱስ
👤 አዲሱ ወርቁ
💿 የመስቀሉ ፍቅርVol. 1
ኑሮ ያለ ጌታ ታክቶኝ ኀጢአቴ አስመርሮኝ
ወደ ኢየሱሴ ብመለስ የእርሱ ደግነት ማርኮኝ
በድል ጐዳና ብገባ ፍቅሩ ነፍሴን ብትፈታ
ጉልበቴን ለጠላት ላልሰጥ ቃል ገባሁኝ ለጌታ
በመከራና በጭንቀትም ሁሉ ጌታን አመልከዋለሁ
ኑሮ ያለእርሱ ጉዳት ነው ከእርሱ ጋር ግን ደስታ
የመልካም ሁሉ መሰረት ይመስገን የእኛ ጌታ
ስንጨነቅ የሚራራ ስንደክም ደጋፊያችን
በበረሃ ዓለም እያለን ስንጠማ እርካታችን
ዞሮ መግቢያችን ኢየሱስ ማረፊያችን አንተ ነህ
ብንከዳህ አያዋጣንም የድሃ ጐጇችን ነህ
ጌታ ጌታችን ጌታችን አስታውሰን (2x)
ብለን ተጣርተን ሳናፍር እስካሁን ተጉዘናል
በነገር ሁሉ መጽናትን ከጌታ ተምረናል
የሚያሳፍር ስም አይደለም የሰጠኸን ጌታችን
ክርስቲያን ጀግንነት እንደው ይረዳልን ልባችን
ክፉውን ሁሉ ተቃውመን ከኀጢአት ጋራ ታግለን
ጉዟችን በድል ያከትማል የጌታን መስቀል ይዘን
ክብር ክብር ሃሌ ሉያ (2x)
የነፍሳት ሁሉ ምሥጋና ዙፋንህን ይክበበው
በቸርነትህ ተገርሟል በልጅህ የዋጀኸው (2x)
👇የዝማሬዎችን lyrics በዚህ link ማግኘት ትችላላችሁ🙏
🔗 https://mezmurlyrics.et/#/singer/addisu-worku/eyesus
Via Mezmur Lyrics (mezmurlyrics.et)

🥰3👏1
ሰላም ወገኖች በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ 🙏
ከዛሬ ጀምሮ ተከታታይ ፅሁፍ "በዕፍኝ ዱቄት ማፏጨት " በሚል ርዕስ ስለመስጠት ከዱባ ጥጋብ መፅሀፍ እንቋደሳለን🙏
እስከዛ ይህን ግጥም ተጋበዙልን🙏
እኔ አንዳንዴ ስ'ሰጥ
ኑሮ ለገረፈው በችግር አለንጋ
በረኃብ ጠውልጎ እጁን ለዘረጋ
በመከራ ስለት ጐኑን ለተወጋ
ለዚህ ብሶተኛ፥ ለዚህ ጉዳተኛ
ጥቂት ልመጸውት ፥ከኪሴ እገባለሁ
ከብሮች መካከል፥ ብሮች አወጣለሁ
ዐምስት ብር አውጥቼ ፥ልሰጠው እልና
እነዚህ አምስት ብሮች፥ ይበዙብኝና
አራቱን ለመስጠት ፥ጥቂት ሳሰላስል
"ለእኔ አይበዛብኝም ለእሱ ይበዛል"ስል
ሦስት ብር ለመስጠት ፥ውሳኔ ደርሼ
"ጐደሎ አይሰጥም" እልና መልሼ
በኹለት ብሮች ላይ ፥ፍርዴን እሰጣለሁ
ፍርዴን ግን መልሼ ፥እከልሰዋለሁ
ኹለት ብር ከምሰጥ ፥በመንገድ ልመና
አንዳንድ እንካፈል ፥ ብዬ እወስንና
"አንድ ብር ብሰጠው ለዚህ ብሶተኛ
ኋላ ቢጠጣበት"እያልኩ ዐስብና
ያቺን አንድ ብርም ፥ኪሴ እከታታለሁ
"እግዚአብሔር ይስጥልኝ!" ብዬው እኼዳለሁ።
ሰለሞን ሞገስ (እውነትን ስቀሏት)ገፅ4

😁4❤1
ንዑስ ርዕስ :- "ጉድለት እንደ ሰንደቅ ዘንግ"
ሰዎች ስንባል ሌሎች ስለ እኛ ጥሩ ጥሩውን እንዲያስቡልን በተተፈጥሯዊ ደመ-ነፍስ የምንነዳ ሳንኾን አንቀርም። በመኾኑም እዚህ ግባ የማይባሉ ዕለታዊ ድርጊቶቻችንም ኾነ የተጋነኑ ስራዎች በሌሎች ሰዎች ላይ ጥሩ ስሜት ለመፍጠርያንት ስንጠቀምበት እንገኛለን። ሰዎችን ለማስደነቅ ወይም ስለ እኛ ትልቅ ስሜት እንዲያድርባቸው በማሰብ ከምናደርጋቸው ነገሮች መካከል ልግስናም ተጃምሎ መገኘቱ አሳማሚ ሥላቅ ነው።
ለበአል ጦማቸውን እንዳይውሉ በሚል ሰበብ ከያሉበት የሰበሰብናቸውን ድሆች በዝርግ ምንጣፍ ከተደረደሩ የሥጋ ቅንጣብጣቢ ጎን ሰድረን ፎቶ እናነሳቸዋለን። እኛ ስናጐርስ እነሱ የተሰነጣጠቀ ከንፍሮቻቸው ሲወጥሩ ካሜራችንን አስተካክለን ታሪከ እናስቀራልን። ችግር እና ችጋር ያገረጣውን የቆዳቸውን ሽብሽብ ለአይን ትዝብት እንጋለጣለን። ገመናቸውን በገሀድ እንገልጣለን። ታመው ከተኙበት ታዛ ገብተንና መጋረጃቸው ዐልፈን ያየነውን የሕመማቸውን ዝርዝር እንተርካለን። የማንሰፍረውን እንባቸውን እናጅባለን። በችግር ተኰራምተው ከተኰለኰሉበት መካከል ተጀንነን እየተመላለስን ማዘንና መደንገጣችንን እንተውናለን።ደግነታችን ለዓለም እንዲነግር የየራሳችን ጻሐፍት ቀጥረን እናሰማራለን።
የወረወርንላቸው ዳረጎት ከተሸከሙበት ከረጢት ጋር በምስል ቀርጸን ስናበቃ አበላናቸው፥ አጠጣናቸው ፥አለበስናቸው እያሉ ማስታወቅ ምን ከሚሉት መንፈሳዊነት ጋር ሊዛመድ ይችላል? ድኩማኑን የምናነሣቸውና ሕሙማንም የምንጐበኛቸው ዜናው በብዙኃን መገናኛ መሰራጨቱን አስበን አስልተን አረጋግጠን መምሰሉ በራሱ ያሳምማል። በማን ገመና ነው ገጽታ ምን ገነባው? ስማችን የሚወደስበትና ገድላችን የሚተረክበትን ሰሌዳ ከፍ አድርገን ለመስቀል የጐሥቋሎች ጉድልት የሰንደቃችን ዘንግ መደረጉ ያስተክዛል።በሰማይ መዝገብ የማናከማችበትና የአስመሳይነት ድር ለተበተበው የሽንገላ ስጦታ መሽቀዳደም በእግዚሃብሄር ፊት ከብር የማያስገኝ ተግባር መኾኙ እንዴት ይጠፋናል?
ይቀጥላል...
JOIN👇

ስለ ምጽዋት አሰጣጥማቴ 6፥6
“ሰዎች እንዲያዩላችሁ፣ መልካም ሥራችሁን በፊታቸው ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ እንዲህ ካደረጋችሁ ከሰማዩ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም።
“ግብዞች በሰዎች ዘንድ ለመከበር ብለው በየጐዳናውና በየምኵራቡ እንደሚያደርጉት፣ አንተም ለድኾች ምጽዋት በምትሰጥበት ጊዜ ይታይልኝ ብለህ ጥሩንባ አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል።
JOIN👇
https://t.me/eyesovwisdom
👏2🔥1
#የቀጠለ....
ከትርፍ ሳይሆን በልግስና መስጠት
ቸርነት ማለት ከትርፍችን ላይ ቀንሰን የምናደርገው ብቻ አይደለም።አሮጌውን ቁስ በዐዲስ ስንተካ ያረጀውን የምናስወግድበት መንገድ አድርጎ መጠቀምም የደግ ሰው ልኬት ሊኾን አይችልም። ከምጥለው ብሰጠው" ይሉት ዐይነት ልግስና ከክልከላ አይተናነስም። ጃክ ለንደን "ሥጋውን ግጠን የጨረሰነውን ባዶ ዐጥንት ለውሻ መወርወር ደግነት አይደለም" የሚል አባባል አለው፣እውነት ነው። ያማ ቆሻሻ ማስወገድ ነው። እውነተኛና ልባዊ ፍቅር ያልተለየው ደግነት ማለት፥ረኃባችንን ሳናስታግሥ በእጃችን ካለው " ዐጥንት አካፍለን ለተራበው ውሻ ከበላን ነው።" ልግስና ዳረጎት አይደለም። ፍቅርም ልግስናው አያልቅም።
ሊከፍሉን ለማይችሉ...
ልግስና ዉለታ ለማስመሰል የምናስመዘግበው በይደር የምናቈየው ቅርስ አይደለም።መልካም የምናደርገው ውሎ ዐድሮ እንዲከፍሉን ዐስበን ከኾነ ያ ብድር እንጂ ልግስና አይባልም። ስለዚህ ያደረግንለት ዐስቦና አስልቶ ሊከፍለን ለማይችል ማድረግ ቸር ሥራ ይባላል።" እንድትወስዱባቸው ተስፍ ከምታደርጉአቸው ብታበድሩ ምን ምስጋና አላችሁ? ኃጢአተኞች ደግሞ በትክክል እንዲቀበሉ ለኃጢአተኞች ያበድራሉ"(ሉቃስ 6፥34)

ማንም የዚህ ዓለም ሀብት እያለው፣ ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ልቡ ባይራራለት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በርሱ ይኖራል? ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።
1 ዮሐንስ 3፥17-18
JOIN👇
https://t.me/eyesovwisdom
❤1🥰1
Eyerusalem Negiya 03 10 የሩቅ አላሚ
Visit የዜማ Tube Telegram Channel
🎵 የእሩቅ አላሚ
👤 ኢየሩሳሌም ነጊያ
💿 የፀጋውን ቁርበትVol. 3
የሩቅ አላሚ ነኝ ግን የቅርብ አዳሪ
የሩቅ አሳቢ ነኝ ግን የቅርብ ተጓዥ ነዋሪ ሰፋሪ
የፈቃድን ሚስጥር እሻና በብርቱ
ግን ልቤ ሊኖረው አወይ ማመንታቱ
በውስጥ ማንነቴ በራለሁ ከሰማይ
ስጋዬ ጎትቶ ያወርደኛል ከላይ
ፍቅርህ ትዝ ሲለኝ ውስጤ ይነካና
አይኔ እንባ ያፈሳል ትናፍቀኝና
ነፍሴ ተነቃቅታ አንተኑን ስታስብ
መንፈሴ ወዲያውኑ ይጋልባል ሽቅብ
መንፈሳዊነቴ ያኔ ሲበረታ
ሀሌሉያ እያልኩ ከምድር ስፋታ
ያልማል ይመኛል ሰማዩን ምናቤ
ከደመናው በላይ ይሄዳል ሀሳቤ
ያን ግዜ እንዳልደክም ምዬ ተገዝቼ
ፈለግህን ልከተል ለራስ ቃል ገብቼ
በአለም ማዕበል ሲመታ ግለቴ
መች ይታወቀኛል ሲደክም ህይወቴ
በኑሮ ገጠመኝ ከፍና ዝቅ ስል
በወጣሁበት ልክ እየኝ ሳሽቆለቁል
በረታሁኝ እያልኩ ዝዬ እገኛለሁ
በሁለቱ ክበብ ላይ እሽከረከራለሁ
ከዚህ ሟች ስጋዬ የሚለየኝ ማነው?
ጥማቴም ረሀቤም አንተን ለመምሰል ነው
እንደማትጥለኝ በእርግጥ አውቃለሁ
ግን አንዳንዴ ራሴ ማመን እፈራለሁ
ድሮም ፀጋህ እንጂ እኔ የቻልኩት ምንድነው?
ሀይልን በምትሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ
ድሮም ፀጋህ እንጂ እኔ የቻልኩት ምንድነው
ሀይልን በምትሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ
ቢዝል ቢደክም ስጋዬ ዳግም ሊበረታ
በድካሜ ምትራራ ደጉ የኔ ጌታ
እጄን በእጅህ እንደያዝክ እስከ መጨረሻው
እያገዝከኝ በፀጋህ ዘልቄ እሄዳለሁ
ፀጋህ እየረዳኝ እያገዝከኝ
ባንተ ሁሉን እችላለሁ እችላለሁኝ
🔗 https://mezmurlyrics.et/singer/eyerusalem-negiya/yeruk-alami

🥰1😢1