Exodus የወንጌል አገልግሎት
172 subscribers
157 photos
3 videos
15 files
41 links
Download Telegram
‎ማለዳ ብዙ ምሕረትህን በቀትርም ምስጋናህን
‎በሌሊት እውነትህን ብዘምር ብናገር ብተርክ ባወራ
‎በምድር ዙርያ ሁሉ አዋጅ ብል የማዳንን ስራ
‎በሕይወቴ ዘመን የበዛው ምሕረት
‎ልተመን ማይቻል የማዳንህ ጉልበት
‎ዝም ብዬ እንዲቀመጥ እንዴት ያስችለኛል
‎እንዳመሰግንህ ይጎተጉተኛል

‎ኃጢአትን ታቅፌ በልቦናዬ ክጄ
‎ቅድዱሱን ቃልህን ተላልፌ ሄጄ
‎ሥርዓትህን ጥሼ ብጓዝ በዐመጽ መንገድ
‎ያ የዋሁ ልብህ አይሰለቸው መውደድ
ከቶ አልጨርስም ብተርክ የአንተን ፍቅር
‎ስምህ ከፍ ከፍ ይበል ግነን ጌታ እግዚአብሔር 
  2*

‎በብርቱ ደክሜ ኮብልዬ ከቤትህ
‎ፈቃዴን ስከተል ሪቄ ከሐልዎትህ
‎ብቻዬን ሳዘግም በጥፈት ጎዳና
‎የምሕረትህ ክንድ ልያቅፈኝ ተዘረጋ
ከቶ አልጨርስም ብተርክ የአንተን ፍቅር
‎ስምህ ከፍ ከፍ ይበል ግነን ጌታ እግዚአብሔር
   2*

‎በበደሌ ምክንያት ሞች ሆኜ ሳለሁኝ
‎ፍቅር ግድ አለህና መጣህ ልታድነኝ
‎ምሕረትህ አይሎ ገኗል በእኔ ለይ
‎ሌላ ምን እልሃለሁ ከፍ በል በሰማይ
ከቶ አልጨርስም ብተርክ የአንተን ፍቅር
‎ስምህ ከፍ ከፍ ይበል ግነን ጌታ እግዚአብሔር
  2*

‎ደስታዬን ስፈልግ በኃጢአት ባህር ውስጥ
‎ያየህልኝን ትቼ ወዳየሁት ስሮጥ
‎አሳዝኜ ስሄድ መቼ ችላ አልከኝ
‎ፈቀቅ ባልኩኝ ሰዓት አብዝትህ ፈለከኝ
ከቶ አልጨርስም ብተርክ የአንተን ፍቅር
‎ስምህ ከፍ ከፍ ይበል ግነን ጌታ እግዚአብሔር
 
   2*

https://t.me/ExodusSDA
3
Dagim Eyasu:
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ቤተ-ክርስቲያናችን እየተዘውወሩ ካሉ የስህተት መልዕክቶች አንዱ "ኢየሱስን መልአክ ብለው ያስተምራሉ" የሚል ነው።

ይሄንን የተሳሳተ መረጃ ለማረም የተሰራ ቪዲዮ link ከታች ተያይዟል። ለብዙዎች እንዲደርስ share እና repost አድርጉ።

ተባረኩ!

https://vt.tiktok.com/ZSyUCkHqA/
አንድ የቤተ-ክርስቲያን አባል እና ጥሩ አገልጋይ የነበረ ወጣት ለስራ ከነበረበት አካባቢ ራቅ ብሎ 
ይሄድና የተወሰኑ ዓመታት ቆይቶ ቤተሰብ ጥየቃ ወደ ነበረበት ይመለሳል፡፡ “የእገሌ ልጅ መጣ” 
የሚል ዜና በአካባቢው ስለተሰማ ብዙዎች እየሄዱ ይህን ወጣት “እንኳን ደህና መጣህ! ቆይታ 
እንዴት ነበር?” እያሉ ይጠይቁት ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያናቸው መጋቢም ይህንኑ ሰምቶ 
ሊጠይቀው ሄደና “እንዴት ቆየህ…?” እየተባሉ ቆዩ። ወጣቱም ደጋግሞ ቆይታው መልካም 
እንደነበር፤ እግዚአብሔርም በብዙ እንደረዳው ለፓስተሩ ይነግራቸዋል፡፡ 
ፓስተሩም ለየት ያለ ምስክርነት ጠብቀው ስላላገኙ ኋላ ላይ በግልፅ “ይኸውልህ ወዳጄ 
የሄድክበት አካባቢ ራቅ ያለ፣ እንደሰማሁት ከሆነም ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ክርስቲያኖች ብዙም 
የሌሉበት ለእምነት ቀላል ያልሆነ አካባቢ ነበር፡፡ እና በእርግጥ በዚያ ቦታ እንዴት እንደቆየህ 
እንዴት ደግሞ ጌታ በዚያ ሁሉ እንደረዳህ ዘርዘር አድርገህ ብትነግረኝ?” ይለዋል፡፡ ወጣቱም 
በደስታ ሲመልስ “ፓስተርዬ ጌታ ይባረክ! ምንም ችግር አልገጠመኝም፡፡ ይገርምሃል ክርስቲያን 
መሆኔን እንኳን ያወቀብኝ አልነበረም!” አለው፡፡ 
“መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ 
በሰው ፊት ይብራ።”
ማቴ. 5፡16 (2 ቆሮ. 5፡20 ፣ 6፡14) 
አዎን እውነት ለመናገር ክርስቲያን መሆናችን ካልታወቀ፣ ጨው እና ብርሃን መሆናችን
ካልተገለጠ ዓለም አቅፋ ትቀበለን ‘ምንም ችግር አይደርስብን’ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የተጠራነው 
ብርሃንን ልናበራ፣ ልዩነትን ልንፈጥር ከሁሉ በላይ ወደ ሞት እያዘገመች ላለች ዓለም የህይወት 
ሽታ ልንሆን እና ከአዳኟ ከክርስቶስ ጋር ልናስተዋውቃት እንደሆነ ስናስብ (ስንረዳ) ይህ ወጣት 
ያለፈበት ልምምድ “ጌታ ይባረክ!” የሚያሰኝ ሳይሆን “ጌታ ሆይ ማረኝ!” የሚያሰኝ አንደሆነ 
እንረዳለን! ክርስቲያን የሚለው ስያሜ ሳይቀር ደቀ መዛሙርት ለራሳቸው የሰጡት ሳይሆን 
“እኚህስ ክርስቶስን ይመስላሉ” ያሏቸው ሌሎች የሰጧቸው ስም እንደሆነ እናያለን (ሐዋ. 11፡26)፡
ዛሬስ እኛ ስለ ራሳችን የምንለው እንዳለ ሆኖ ሌሎች ምን ይሉን፡ ማንን ይመስላሉ ይሉን ይሆን? 
ክርስትያንነታችንንስ የሚያዩን ሁሉ ያውቁ ይሆን?

https://t.me/ExodusSDA
👍1