University of Ethiopia Exit Exam 2017
33 subscribers
1 photo
10 files
1 link
Exit Exam 2017
Download Telegram
Channel name was changed to ÂŤUniversity of Ethiopia Exit Exam 2017Âť
በመውጫ ፈተና ውጤት ምክንያት 90 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ ባወጣው መመሪያ መሠረት፣ 90 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚያስፈትኗቸው ተማሪዎች 75 በመቶ ያህሉን ማሳለፍ ባለመቻላቸው መዘጋታቸው ተሰምቷል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ደኤታ ኮራ ቱሹኔ ይህን ያሉት፥ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ ባዘጋጀው የአፍሪካ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዓለም አቀፍ ጉባዔ መድረክ ላይ ነው።

"መመሪያው ከተላለፈ በኋላ ራሳቸው ላይ ዕርምጃ የወሰዱ ተቋማት አሉ፡፡ በተለይ ከግሎቹ 90 ያህል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተዘግተዋል፡፡ አብዛኞቹ መመሪያውን ካዩ በኋላ ራሳቸውም እየዘጉ ናቸው" ብለዋል፡፡

ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እስካሁን የተዘጋ ባይኖርም ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት እንዳሉም ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል፡፡ ተዘግተዋል የተባሉት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሲያስተምሩ የነበሩ ቢሆኑም ስማቸው አልተጠቀሰም፡፡

"የእኛ ሥራ ሔዶዶ መዝጋት ሳይሆን፥ ተቋማቱ ያሉበትን ሁኔታ መግለፅና መማር ለሚፈልጉ ዜጎች ለውሳኔ እንዲረዳቸው ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ነው" ያሉት ሚኒስትር ደኤታው፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የወጡ መመሪያዎችን በማየት ብቻ በራሳቸው ከገበያ የወጡ ተቋማት መኖራቸውንም ገልፀዋል፡፡ #ሪፖርተር
👇🏽👇🏽💪🏽🥰
https://t.me/exitexam124