እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
8.68K subscribers
121 photos
16 videos
40 files
403 links
“እውነት ለሁሉ” በዓለም ዙርያ በሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ክርስቲያኖች የተመሠረተ ድረ-ገፅ ሲሆን እስልምናንና ክርስትናን የተመለከቱ መጣጥፎችን፣ መጻሕፍትን፣ ዜናዎችንና የመሳሰሉትን ያስነብባል፡፡ የኦዲዮና የቪድዮ መረጃዎችንም ያቀርባል፡፡ የበለጠ ለማወቅ http://www.ewnetlehulu.org ይጎብኙ።
Download Telegram
Forwarded from Isaiah 48 Apologetics
"እንዲህም አሉ። እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር #ሰማይንና #ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን #ሁሉ ወደ #ፈጠረ ወደ ሕያው #እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።"
(የሐዋርያት ሥራ 14:15)

" #ዓለሙንና በእርሱ ያለውን #ሁሉ #የፈጠረ #አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤"
(የሐዋርያት ሥራ 17:24)

"ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ። ጌታችንና #አምላካችን ሆይ፥ አንተ #ሁሉን #ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።"
(የዮሐንስ ራእይ 4:10-11)

" #ሁሉ ከእርሱና #በእርሱ ለእርሱም #ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 11:36)

▶️ መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ሁሉን ፍጥረት የፈጠረው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ያስተምራል። ፍጡር አብሮት ፈጠረ የሚል አስተምህሮ ለመጽሐፍ ቅዱስ ባዕድ ነው።

በመጀመሪያ የነበረውም ቃል "ሁሉ በእርሱ ሆነ" መባሉ፥ እውነተኛው አምላክ መሆኑን በማያሻማ መልኩ ያረጋግጣል። እውነተኛው አምላክ ባይሆን ኖሮ፥ ሁሉን መፍጠር ባልቻለ ነበር። ይህ፥ ቃል ፍጡር ሳይሆን እግዚአብሔር መሆኑን ከምንም በላይ ያረጋግጣል።

✍️ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ሁሉን የፈጠረው ፈጣሪ መሆኑ በዮሐ 1:1-3 ላይ ብቻ የተነገረ እውነት አይደለም። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም እንደሚያረጋግጡት፥ ልጁ/ቃል የሁሉ ፈጣሪ ነው

"13-14፤ እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ #ልጅ መንግሥት አፈለሰን። 15-16፤ እርሱም የማይታይ አምላክ #ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ #በሰማይና #በምድር ያሉት #ሁሉ በእርሱ #ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። #ሁሉ #በእርሱና ለእርሱ #ተፈጥሮአል። 17፤ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው #ሁሉም በእርሱ #ተጋጥሞአል።"
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕራፍ 1:13-17)

"2፤ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም #ዓለማትን #በፈጠረበት #በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ 3፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ #ምሳሌ ሆኖ፥ #ሁሉን በስልጣኑ #ቃል #እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤"
(ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 1:2-3)

"ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር #ሁሉም #በእርሱ በኩል #የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ #ኢየሱስ #ክርስቶስ አለን።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8:6)

"8፤ ይላል፤ ስለ #ልጁ ግን። #አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው። 9፤ ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ 10፤ ይላል። ደግሞ። #ጌታ #ሆይ፥ አንተ ከጥንት #ምድርን #መሠረትህ#ሰማዮችም #የእጆችህ #ሥራ #ናቸው፤ 11፤ እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ 12፤ እንደ #መጎናጸፊያም #ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም"
(ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 1:8-12)

▶️ ስለዚህ የይሖዋ ምስክር ወገኖቻችን ተሳስተዋል። በዮሐንስ 1:1-3 ላይ የተተረከው ቃል ፍጡር አይደለም። ፍጡር አለመሆኑን ከሚያረጋግጡት ብዙ ማስረጃዎች መካከል ከላይ የተመለከትናቸው ተጠቃሽ ናቸው። ሁሉም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች እንደሚያረጋግጡት፥ ቃል ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለም።

1) ሁሉ በቃል ከተፈጠረና፥ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ ቃል የተፈጠረ ከሌለ፥ እንዴት ቃል ራሱ ፍጡር ሊሆን ይችላል? ራሱን ፈጠረ ማለት ነው?

2) መጽሐፍ ቅዱስ #ሁሉን የፈጠረው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን እየተናገረ፥ እንዴት ፍጡር ሁሉ ሊፈጥር ይችላል? ፍጡር ሁሉን ፈጠረ የሚል አስተምህሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ?

ትክክለኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ አውቃችሁ ወደ እውነት ትመጡ ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው

ጌታ ይርዳን!
ተለቀቀ 🙌

“The Deception of Allah” የተሰኘው የክርስቲያን ፕሪንስ መጽሐፍ ተለቋል።
አጣጥሙት

https://drive.google.com/file/d/1-0DxUJGiibd9Q5nKofbdCz7Ex2eubOVv/view
Forwarded from Isaiah 48 Apologetics
🚩 አል-ራህማን:- ሌላኛው እስላማዊ ኩረጃ

የሙስሊሞች አምላክ አላህ ዘጠና ዘጠኝ መጠሪያዎች ያሉት ሲሆን ከእነርሱ አንዱ "አል-ራህማን" የተሰኘው ነው። አል-ራህማን ማለት "መሐሪው" ወይንም "ይቅር ባዩ" እንደማለት ሲሆን በቁርአን እና በሃዲሳት ውስጥ በዚህ ስም ተጠርቷል።

✍️ በቁርአን ውስጥ በዚህ ስም የተጠራበትን ጥቂት ቦታዎች እንመልከት፦

#አልረሕማን (ሱራ 55:1)

"ምእምናንን የተከበሩ ጭፍሮች ኾነው ወደ #አልረሕማን የምንሰበስብበትን ቀን (አስታውስ)፡፡" (ሱራ 19:85)

" #አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡" (ሱራ 19:87)

"«አላህን ጥሩ፤ ወይም #አልረሕማንን ጥሩ፤ (ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ (መልካም ነው)፡፡ ለእርሱ መልካም ስሞች አሉትና» በላቸው፡፡ በስግደትህም (ስታነብ) አትጩህ፡፡ በእርሷም ድምጽህን ዝቅ አታድርግ በዚህም መካከል መንገድን ፈልግ፡፡" (ሱራ 17:110)

"በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) #ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡" (ሱራ 19:93)

✍️ በሀዲሳትም ላይ አላህ በዚህ ስም የተጠራባቸውን ቦታዎች እንመልከት፦

It was narrated that Jabir said:
"The Messenger of Allah said: 'The Throne of #The_Most_Merciful trembled upon the death of Sa'd bin Mu'adh.'"
(Sunan Ibn Majah 158)

It was narrated from Abdullah bin 'Amr that the Messenger of Allah(ﷺ) said: "Worship the #Most_Merciful and spread (the greeting of) peace.'"
(Sunan Ibn Majah 3694)

Abdullah bin 'Amr narrated that the Messenger of Allah said:
"The merciful are shown mercy by Ar-Rahman. Be merciful on the earth, and you will be shown mercy from Who is above the heavens. The womb is named after #Ar_Rahman, so whoever connects it, Allah connects him, and whoever severs it, Allah severs him."
(Jami` at-Tirmidhi 1924)

♦️ ነገር ግን ይህ መጠሪያ ከአይሁዳውያን ታልሙድ የተኮረጀ መሆኑን ያውቁ ኖሯል?

አዎ፥ ልክ ከዚህ በፊት እንዳየናቸው ኩረጃዎች ሁሉ ይህኛውም መጠሪያ ከአይሁዳውያን ታልሙድ የተኮረጀ መጠሪያ ነው። የአይሁድ ረበናት በታልሙዳቸውና በሌሎች ምንጮቻቸው ውስጥ አምላክን ለመጥራት ከሚጠቀሟቸው መጠሪያዎች አንዱ "ሃ-ራኽማን" ወይንም "መሐሪው" የሚለው ስም ነው። መሐመድም እነርሱ አምላክን በዚህ ስያሜ ሲጠሩ ሰምቶ የእስልምና አካል ያደረገው ኩረጃ ነው። ማስረጃው እነሆ፦

"Rabbi Shimon said to all the friends, I beg of you all not to utter any words of the Torah which you did not hear from a great tree and did not learn properly. So that you may not be the cause of that wife of harlotry slaying multitudes of human beings without reason! They all answered: May #the_Merciful_One save us all!"

👉 [https://www.sefaria.org/Zohar%2C_Introduction.11.71?vhe=Hebrew_Translation&lang=bi&with=all&lang2=en]

" #The_All_merciful shall reign over us for ever and ever. #The_All_merciful shall be blessed in heaven and on earth. #The #All_merciful shall be praised throughout all generations, glorified amongst us to all eternity, and honored amongst us for everlasting"

👉 [https://www.sefaria.org/Birkat_Hamazon%2C_Birkat_Hamazon%2C_Hatov_Vehametiv.2?vhe=Birkat_Hamazon_--_Edot_HaMizrach&lang=bi]

"May #the_All_merciful grant us an honorable livelihood. May #the_All_merciful break the yoke from off our neck, and lead us upright to our land. May #the_All_merciful send a plentiful blessing upon this house, and upon this table at which we have eaten. May #the_All_merciful send us Elijah the prophet (let him be remembered for good), who shall give us good tidings, salvation and consolation"

👉 [https://www.sefaria.org/Birkat_Hamazon%2C_Birkat_Hamazon%2C_Hatov_Vehametiv?vhe=Birkat_Hamazon_--_Edot_HaMizrach&lang=bi]

"May #the_All_merciful let us inherit the day which shall be wholly a Sabbath and rest in the life everlasting."

👉 [https://www.sefaria.org/Birkat_Hamazon%2C_Birkat_Hamazon%2C_Hatov_Vehametiv.7?vhe=Birkat_Hamazon_--_Edot_HaMizrach&lang=bi]

✏️ ይህ መጠሪያ አይሁዳውያን በታልሙድ አምላክን የሚጠሩበት መጠሪያ እንደሆነ ከዚህም በላይ ማስረጃ ማምጣት እንችላለን። ይህ ስም የአይሁድ ረበናት በታልሙድ ውስጥ ለአምላክ የሰጡት ስያሜ ነው። መሐመድም ይህን ስያሜ ለአምላክ ሲሰጡ ሰምቶ በመኮረጅ እስልምና ውስጥ አካተተው

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለማለት እንደሞከርነው፥ ኮራጆቹ አይሁዳውያኑ ናቸው ሊባል አይችልም። ምክንያቱም የአይሁድ ረቢዎቹም ሆነ፥ ታልሙዱ ከመሐመድና ከቁርአን በፊት ነበሩ። ስለዚህ የኩረጃ ክስ ቢነሳ ተጠያቂ የሚሆነው ማን እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህ እስልምና ከተለያዩ ምንጮች የተኮረጀ የውሸት ሃይማኖት መሆኑን በግልፅ ያሳያል።
"ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።" (ራዕይ 1:17-18)
Forwarded from Isaiah 48 Apologetics
🚩 ኦሪትና ወንጌል መች ይሆን የተበረዙት?

እንደሚታወቀው ሙስሊሞች የቀደሙት የአይሁዳውያንና የክርስቲያኖች ቅዱሳት መጻሕፍት ተበርዘዋል ብለው ያምናሉ። ለዚህም መንስኤው ቁርዓናቸው የአይሁዳውያንና የክርስቲያኖችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ አምላክ ቃል እያጸደቀ፤ በመሰረታዊ አስተምህሮ ግን ስለሚቃወማቸው ነው። ይህ ማለት የክርስቲያኖችና የአይሁዳውያን ቅዱሳት መጻሕፍት እውነትም ሆኑ ሀሰት እስልምና የውሸት ሀይማኖት ነው ማለት ነው። በዚህም ምክንያት ሙስሊሞች የቀደሙት መጻሕፍት ተበርዘዋል ብለው ያምናሉ

ይህ እጅግ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነገር ነው። የአምላክ ቃል እንዴት ሊበረዝ ይችላል? ቁርአን በእርግጥ እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ተበርዘዋል ብሎ ያስተምራል ወይ? እነዚህና ሌሎች እጅግ ብዙ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ

ዛሬም ይህ መረዳት ከሚያስከትላቸው ችግሮች አንዱን ለመዳሰስ እንሞክራለን። ይኸውም፦

እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት (scriptures) ተበርዘዋል ከተባለ፥ መቼ ነው የተበረዙት? ከመሐመድ ዘመን በፊት? ወይስ ከመሐመድ በዘመን በኋላ?

ቀጥለን እንምንመለከተው፥ ሁለቱም አማራጮች እስልምና የውሸት ሀይማኖት መሆኑንና መሐመድም ኃሳዊ ነብይ መሆኑን ከማረጋገጥ ያለፈ ፋይዳ አይኖራቸውም።

♦️ 1. ከመሐመድ ዘመን በፊት ተበርዘዋል

ወገኖቻችን የአይሁዳውያንና የክርስቲያኖች ቅዱሳት የተበረዙት መሐመድ ከመወለዱ በፊት በነበሩት ዘመናት ወይንም መሐመድ ነብይ ሆኖ ከመነሳቱ በፊት ነው ካሉ፥ ቁርአን የተበረዙ መጻሕፍትን እንደ አምላክ ቃል የሚያረጋግጥ ሀሳዊ መጽሐፍ ይሆናል ማለት ነው።

35፥31 ያም ከመጽሐፉ ወደ አንተ ያወረድንልህ #ከበፊቱ ላለው #አረጋጋጭ ሲኾን እርሱ እውነት ነው፡፡ አላህ በርግጥ በባሮቹ ውስጥ ዐዋቂ ተመልካች ነው፡፡

3፥3 ከእርሱ #በፊት ያሉትን #የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን በአንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡

6፥92 አላህ (አወረደው)» በላቸው፡፡ ከዚያም በውሸታቸው ውስጥ የሚጫወቱ ሲኾኑ ተዋቸው፡፡ ይህም ያወረድነው የኾነ ብሩክ ያንንም #በፊቱ የነበረውን (መጽሐፍ) #አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው

10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ (ከሆነ ፍጡር) የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን ከእርሱ #በፊት ያለውን (መጽሐፍ) #የሚያረጋግጥና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ (የተወረደ) ነው፡፡

12፥111 በታሪካቸው ውስጥ ለአእምሮ ባለ ቤቶች በእርግጥ መገሰጫ ነበረ፡፡ (ይህ ቁርኣን) የሚቀጣጠፍ ወሬ አይደለም፡፡ ግን ያንን #በስተፊቱ ያለውን #አረጋጋጭ ለነገርም ሁሉ ገላጭ ለሚያምኑ ሕዝቦችም መሪና ችሮታ ነው፡፡

46፥30 አሉም «ሕዝቦቻችን ሆይ! እኛ ከሙሳ በኋላ የተወረደን መጽሐፍ #በፊቱ ያለውን (መጽሐፍ) #የሚያረጋግጥ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛ መንገድ የሚመራ የኾነን ሰማን፡፡

2፥97 ለጂብሪል (ለገብርኤል) ጠላት የኾነ ሰው (በቁጭት ይሙት) በላቸው፡፡ እርሱ (ቁርኣኑን) #ከበፊቱ ለነበሩት (መጻሕፍት) #አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡

እነዚህ አንቀጾች በሙሉ ቁርአን ከእርሱ በፊት የነበሩትን የአይሁዶችና የክርስቲያኖችን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ መጽሐፍ መሆኑን የሚናገሩ ጥቅሶች ናቸው። ይህንን ከአስባባቸው (የወረዱበት ምክንያት) እና ከሙፈሲሮች (የቁርአን ተንታኞች) ማረጋገጥ ይቻላል።

እነዚህ ቁርአን አረጋግጣቸዋለሁ ያላቸው የክርስቲያኖችና የአይሁዶች ቅዱሳት መጻሕፍት መሐመድ ከመወለዱ በፊት ወይንም ወሕይ መቀበል ከመጀመሩ በፊት የተበረዙ ከሆነ፥ ቁርአን የተበረዙ፥ ዋጋቸውን ያጡና ከአምላክ ቃልነት ውጪ የሆኑ መጻሕፍትን የሚያረጋግጥ የውሸት መጽሐፍ ይሆናል። ማለትም የአምላክ ቃል አይደለም ማለት ነው።

➣ ይህንን የተረዱ አንዳንድ ሙስሊሞች እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት የተበረዙት ለመሐመድ ቁርአን እየወረደለት በነበረበት ሰዓት ወይንም simultaneously ነው ይላሉ።

ይህ ሀሰትን ለመሸፈን የተቃጣ ከንቱ ሙከራ ነው። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች አይደለም መሐመድ ቁርአንን እየተቀበለ በነበረበት ሰአት ኦሪትና ወንጌል እየተበረዙ ነበር ሊሉ ቀርቶ፥ ጨርሶውኑ ተበርዘዋል ብለው አያምኑም ነበር። ሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት አላህ ባወረዳቸው ቁመና እንደሚገኙ ነው የመሰከሩት

♦️ ሲቀጥል፥ ቁርአን የሚያረጋግጠው ከእርሱ መውረድ በፊት የነበሩትን ኦሪትና ወንጌል ብቻ ሳይሆን፥ በመሐመድ ዘመን በነበሩ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ጋር የነበሩትንም ነው

2፥41 #ከናንተ #ጋር ያለውን (መጽሐፍ) #የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም (ቁርኣን) እመኑ፡፡ በርሱም የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ፡፡ በአንቀጾቼም ጥቂትን ዋጋ አትለውጡ፡፡ እኔንም ብቻ ተጠንቀቁ፡

2፥89 #ከነሱም #ጋር ያለውን (መጽሐፍ) #አረጋጋጭ የኾነ መጽሐፍ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ (ከመምጣቱ) በፊት በነዚያ በካዱት ላይ ይረዱበት የነበሩ ሲኾኑ ያወቁት ነገር በመጣላቸው ጊዜ በርሱ ካዱ፡፡ የአላህም ርግማን በከሓዲዎች ላይ ይኹን፡፡

2፥91 አላህም ባወረደው (ሁሉ) ለእነርሱ «እመኑ» በተባሉ ጊዜ «በኛ ላይ በተወረደው (መጽሐፍ ብቻ) እናምናለን» ይላሉ፡፡ ከርሱ ኋላ ባለው (ቁርአን) እርሱ #ከነሱ #ጋር ላለው (መጽሐፍ) #አረጋጋጭ እውተኛ ሲኾን ይክዳሉ፡፡ «አማኞች ከኾናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነቢያት ለምን ገደላችሁ?» በላቸው፡፡

2፥101 #እነርሱ #ጋርም ላለው (መጽሐፍ) #አረጋጋጭ የኾነ መልክተኛ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ከነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ከፊሉ እነርሱ እንደማያውቁ ኾነው የአላህን መጽሐፍ ከጀርባዎቻቸው ኋላ ጣሉ፡፡

3፥81 አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ ከዚያም « #ከእናንተ #ጋር ላለው (መጽሐፍ) #የሚያረጋግጥ መልክተኛ ቢመጣላችሁ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ (አስታውስ)፡፡

4፥47 እናንተ መጽሐፉን የተሰጣችሁ ሆይ! ፊቶችን ሳናብስና በጀርባዎች ላይ ሳንመልሳቸው ወይም የሰንበትን ባለቤቶች እንደረገምን ሳንረግማቸው በፊት #ከእናንተ #ጋር ያለውን #የሚያረጋግጥ ኾኖ ባወረድነው እመኑ፡፡ የአላህም ትዕዛዝ ተፈጻሚ ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሱት አንቀጾች በሙሉ በመሐመድ ዘመን በነበሩ አይሁዳውያን እና ክርስቲያኖች ዘንድ ስለነበሩት ቅዱሳት መጻሕፍት (ኦሪትና ወንጌል) የሚናገሩ ናቸው። ይህንንም ከአስባባቸውና ከሙፈሲሮች ምስክርነት መረዳት ይቻላል

ታዲያ እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ቁርአን እየወረደ በነበረበት ሰአት እየተበረዙ ከሆነ አረጋግጣቸዋለሁ ማለት ምን ማለት ነው? እየተበረዙ ያሉትን መጻሕፍት ነው ቁርአን የሚያረጋግጠው? ይህ ማለት ቁርአን ሀሰትን የሚያረጋግጥ የውሸት መጽሐፍ ይሆናል ማለት ነው

➣ ከዚህም ባሻገር፥ ቁርአን በመሐመድ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖችና አይሁዶች በኦሪትና በወንጌል ይቁሙ ወይንም ይስሩ ይላል

5፥68 «እናንተ #የመጽሐፉ_ባለቤቶች ሆይ! #ተውራትንና_ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደእናንተ የተወረደውን #እስከምትቆሙ (እስከምትሠሩባቸው) ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም» በላቸው፡፡

የመውረድ ምክኒያቱም ሆነ ተንታኞቹ እንደሚያረጋግጡት፥ ይህ አንቀጽ በመሐመድ ዘመን የነበሩን ክርስቲያኖችና አይሁዶች የሚመለከት ትዕዛዝ ነው።
Forwarded from Isaiah 48 Apologetics
ኦሪትና ወንጌል መሐመድ መገለጥን እየተቀበለ በነበረበት ግዜ ብረዛ እየተካሄደባቸው ቢሆን ኖሮ፥ ለምን አላህ በእነርሱ ቁሙ ብሎ ያዛል? ተበርዘው ዋጋቸውን ባጡ መጻሕፍት ነው እመኑና ስሩ የሚለው?

ነገሩን በይበልጥ አስፈላጊ የሚያደርገው፥ በዚህ በምዕራፍ አምስት ያለ ማንኛውም ሀሳብ ተሻሪ አለመሆኑ ነው። የመሐመድ ሚስት የነበረችው አይሻ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያለ ማንኛውም አንቀጽ በሙሉ እንደማይሻር ተናግራለች

"Al-Hakim narrated that Jubayr bin Nufayr said, "I performed Hajj once and visited Aishah and she said to me ,O Jubayr! Do you read (or memorize) Al-Ma'idah ' I answered Yes. She said It was the last Surah to be revealed. Therefore, whatever #permissible matters you find in it, then consider (treat) them #permissible. And whatever #impermissible matters you find in it, then consider (treat) them #impermissible.'''

ስለዚህ ተሽሯል በሚል ሰበብ ቁርአን ስለ ቀደሙት መጻሕፍት የተናገረውን ነገር መሸፋፈን ሆነ መካድ አይቻልም። ለናሙና ያህል ቁ.68ን ጠቀስን እንጂ፥ ምዕራፍ አምስት ስለ ኦሪትና ወንጌል እውነተኝነት እና ባለስልጣንነት ብዙ ይናገራል

( ሱራ 5:43 ሱራ 5:44)

➣ ስለዚህ ኦሪትና ወንጌል የተበረዙት ከመሐመድ ዘመን በፊት ወይንም መሐመድ መገለጥን እየተበቀበለ በነበረበት ዘመን ነው ማለት እስልምና የውሸት ሀይማኖት መሐመድም ሀሳዊ ነብይ መሆኑን ከማሳየት ያለፈ ፋይዳ የለውም

♦️ 2. ከመሐመድ ዘመን በኋላ ተበርዟል

የመጀመሪያው ምርጫ አላዋጣ ሲል፥ በደመነፍስ "እርሱ ከሞተ በኋላ ተበርዟል" የሚል ሙስሊም አይጠፋም። ይህ መልስ አልሞት ባይ ተጋዳይነት ሲሆን፥ አሁንም እስልምና የሀሰት ሀይማኖት መሆኑንና መሐመድም ሀሰተኛ ነብይ መሆኑን ከማረጋገጥ ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም

በመጀመሪያ፥ እስላማዊ ምንጮች እንደመሰከሩት በመሐመድ ዘመን በነበሩ አይሁዳውያንና ክርስቲያኖች ዘንድ የነበሩት ኦሪትና ወንጌል፥ አሁን ከእኛ ጋር ያሉት ኦሪትና ወንጌል ናቸው።

ስለዚህ አሁን ያሉት ኦሪትና ወንጌል ከመሐመድ ዘመን በፊት የነበሩት ያልተበረዙ ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው እስካልተባለ ድረስ፥ ኦሪትና ወንጌል ከመሐመድ ዘመን በኋላ ተበርዘዋል ማለት አይቻልም።

➣ ሲቀጥል ከመሐመድ ዘመን በፊት የነበሩ የኦሪትና የወንጌል ቅጅዎች አሉ። ከክርስቶስ ልደት መቶ አመት በፊት የነበሩት የሙት ባህር የኦሪት ጥቅሎች አሁን በእጃችን ይገኛሉ። በወንጌልም ስንሄድ፥ በሁለተኛውና በሶስተኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ የወንጌል ዕደ ክታባት አሉን

ስለዚህ ኦሪትና ወንጌል የተበረዙት ከመሐመድ ዘመን በኋላ ነው ከተባለ፥ ከመሐመድ ዘመን በፊት የነበሩትን ኦሪትና ወንጌል ቁርአንን ለመመርመርና ለመዳኘት መጠቀም እንችላለን ማለት ነው። ተበርዘዋል የተባሉት እነርሱ ስላልሆኑ

🚩ነገር ግን ይህን ካደረግን እስልምና የውሸት ሀይማኖት፥ መሐመድም ሀሰተኛ ነብይ መሆኑን እናረጋግጣለን።

ምክንያቱም በመሐመድ ዘመን የነበሩትም ሆነ ከእርሱ ዘመን በፊት የነበሩት ኦሪትና ወንጌል፥ አምላክ ሥላሴ መሆኑን፤ ከመለኮት አካላት አንዱ የሆነው ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሰገዉን፥ ሀጢአት አልባ ኑሮ ኖሮ ስለ ሀጢአታችን መስዋዕት በመሆን ተሰቅሎ መሞቱን፥ በሶስተኛውም ቀን ከሙታን መነሳቱን፥ በስጋ ወደ ሰማይ ማረጉን፥ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ አሁን ፍጥረትን ሁሉ እንደ ሉዓላዊው አምላክ እንደሚገዛና ለፍርድም ተመልሶ እንደሚመጣ ያስተምራሉ።

እነዚህን እና ሌሎች መሰረታዊ ትምህርቶቻቸውን ደግሞ እስልምና ይክዳል። ቁርአን የፈጣሪ ቃልነታቸውን ያረጋገጠላቸውን እነዚህን መጻሕፍት መቃረኑ እስልምና የውሸት ሀይማኖት፥ መሐመድም ሀሰተኛ ነብይ መሆኑን ያረጋግጣል። ስለዚህ ከመሐመድ ዘመን በኋላ ተበርዟል የሚለውም መልስ፥ እስልምናን አይታደግም። ሁለቱም ውሸት መሆኑን ይረጋገጣሉ

➣ መደምደሚያ

ከላይ በብዙ ማስረጃዎች "ኦሪትና ወንጌል ተበርዘዋል" የሚለው እይታ እስልምና ላይ ምን እንደሚያደርስ ለማየት ሞክረናል። በተለይም ተበርዘዋል ከተባለ፥ የተበረዙበት ግዜና አንድምታዎቹን ለመመልከት ሞክረናል። በሁለቱም ምርጫዎች፥ መሐመድ ሀሰተኛ ነብይ ከመሆን አልዳነም።

♦️ ስለዚህ ከመሐመድ ዘመን በፊትም ሆነ በኋላ ተበርዘዋል የሚለው መልስ የእስልምናን ውሸተኝነት ካሳየ፥ መቼ ነው ኦሪትና ወንጌል የተበረዙት?

እግዚአብሔር ከዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ከሆነ የውሸት ሀይማኖት ሙስሊሞችን አውጥቶ ወደ ልጁ መንግስት ያፈልሳቸው ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው!
Forwarded from Isaiah 48 Apologetics
🚩 የማን አምላክ ነው ጾታ ያለው?

ሰሞኑን ሙስሊሞች "ክርስቶስ አምላክ ከሆነ እንዴት ጾታ ሊኖረው ይችላል?" የሚለውን የአቡ ሐይደርን አስቂኝ ጥያቄ ሲቀባበሉት ነበር። የጥያቀው አመክንዮ እጅግ ደካማ ሲሆን ከመሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮዎች መካከል አንዱ የሆነውን የስጋዌን (incarnation) ትምህርት ችላ ያለ ነው።

ክርስቶስ በመለኮት ጾታ አለው ብለን አናምንም። ስጋን ከመንሳቱ በፊት ወይንም ደግሞ በስጋ ከመምጣቱ በፊት ሲኖርበት በነበረው ባህርይው መለኮት ነበር። መለኮት መንፈስ ነው (ዮሐ 4:24) በቦታ (ኤር 23:24) በጊዜ (ራዕ 22:13) እና በቁስ (ኢሳ 31:3) አይገደብም፥ አይወሰንም። ስለዚህ ጾታ የለውም። ክርስቶስም በስጋ ከመምጣቱ በፊት መለኮት ስለነበር (ዮሐ 1:1-3 ኤር 23:5-6) ጾታ አልነበረውም።

ጾታ የኖረው፥ ቀድሞ የእርሱ ያልነበረውን የሰውን ባህርይ የራሱ ሲያደርግ ነው (ፊሊ 2:6-7) ይህን ባህርይ የራሱ ሲያደርገው፥ ከኀጢአት በቀር ጠቅላላ ባህሪያቱ (attributes) የእርሱ ሆኑ። ከሰውነት ባህሪያት ደግሞ አንዱ ጾታ ነውና ክርስቶስ ሲሰገው፥ ጾታ ኖረው። ከስጋዌው በኋላ ክርስቶስ የመለኮትም የስጋም ባህሪያት ያሉት ሲሆን፥ ጾታ ሊኖረው የቻለበትም ምክንያት ይህ ነው። በስጋ መገለጡ። እንጂ በስጋ የመጣው አምላክ ስላልሆነ አይደለም

♦️ አስተውሉ! በክርስትና አስተምህሮ መሰረት መለኮት ጾታ የለውም። እኛ ክርስቲያኖች መለኮት ጾታ አለው ብለን አናምንም። ክርስቶስ ጾታ ሊኖረው የቻለው፥ ሌላ ሁለተኛ ባህርይን የራሱ ስላደረገ እንጂ በአምላክነቱ ጾታ የለውም። ጾታ የመለኮት ባህርይ አይደለም።

✍️ እነርሱ ያነሱትን ጥያቄ በዚህ መልኩ ከመለስን ዘንድ፥ ወደ ተነሳንበት ርዕስ እንግባ። የማን አምላክ ነው ጾታ ያለው?

እጅግ በሚያስገርምና በሚያስደቅ መልኩ፥ ጾታ ያለው የሙስሊሞች አምላክ አላህ መሆኑን እንረዳለን! ለዚህ ማስረጃ የሆነውን የቁርአን አንቀፅ እንመልከት፦

"መጫወቻን (#ሚስትና #ልጅን) ልንይዝ #በሻን ኖሮ ከእኛ ዘንድ #በያዝነው ነበር፡፡ (ግን) ሠሪዎች አይደለንም" ሱራ 21:17

✏️ በዚህ ስፍራ የሙስሊሞች አምላክ አላህ ቢሻ ኖሮ ሚስትና ልጆችን ይይዝ እንደነበር ሲናገር እንመለከታለን። ብፈልግ ሚስትና ልጅን እይዛለሁ ማለት፥ ብፈልግ ሚስት አግብቼ ከዚያች ሚስት ልጅ መውለድ እችላለሁ ማለት ነው። ነገር ግን "ሰሪዎች አይደለንም" በማለት ይህን ነገር የማድረግ ፍላጎት እንደሌለው ይናገራል

ይህ ማለት የሙስሊሞች አምላክ አላህ ወንድ ነው ማለት ነው። ጾታ አለው። ሚስት አግብቶ ልጅ ያልወለደበት ምክንያት፥ ረቂቅ መለኮት ስለሆነ ሳይሆን ስላልፈለገ ነው። ጉዳዩ የፍላጎት እንጂ የባህርይ አይደለም። አላህ እንደ ወንድ ሚስት አግብቶ ልጅ የሚያስወልድ ባህርይ አለው። ነገር ግን ስላልፈለገ አያገባም። ልክ አንድ ሰው ከፈለገ ሚስት እንደማያገባው ልጅም እንደማይወልደው ማለት ነው። ታዲያ አግብቶ መውለድ የሚችል ወንድን እያመለኩ ለምንድነው ይህን አይነት ጥያቄ የሚያነሱት? ጾታ ያለው አምላክ እያመለኩ "እንዴት አምላክ ጾታ ሊኖረው ይችላል?" ብሎ ሌላውን በሀሰት መወንጀል ይቻላል እንዴ?

♦️ ነገሩን በይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ፥ ጾታ አለው ብለው ማመናቸው በመለኮት መሆኑ ነው። ሙስሊሞች እንደ ክርስቲያኖች መለኮት በስጋ ተገለጠ ብለው አያምኑም። ስለዚህ አላህ ጾታ አለው ሲሉ በስጋ አይደለም፥ ስጋ የለምና። ስለዚህ በትክክል አምላክ ጾታ አለው ብለው የሚያምኑት እነርሱ ናቸው ማለት ነው።

ይህ ደግሞ እስልምናን paganism ያደርገዋል። ምክንያቱም በመለኮት ጾታ አለው ብለው የሚያምኑት ፓጋኖች ናቸውና። ጣኦታዊ የነበሩት የጥንት ግሪካዊያን፥ ሮማዊያን፥ ከነዓናዊያን፥ ግብፃዊያን፥ ፋርሳዊያን፥ ባቢሎናዊያን፥ አሦራዊያን እና የሙስሊሞች ነብይ ሕዝቦች የነበሩት ጣኦታዊ አረባዊያን በሙሉ አማልክቶቻቸው በመለኮት ጾታ እንደነበራቸው ያምኑ ነበር። መለኮት ጾታ አለው በማለታቸው ወንድና ሴት አማልክት እንደነበሩ፥ እነዚህም አማልክት እንደሚጋቡና እንደሚወልዱ ያምኑ ነበር። እስልምናም አላህ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ ነው በማለቱ፥ ሳይወድ በግድ ከፓጋኖቹ ምድብ ይመደባል።

▶️ የቁርአን ተንታኞች (ሙፈሲሮች) ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምን አሉ?

ሙፈሲሮቹም ከቁርአኑ ጋር በመስማማት፥ አላህ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ መሆኑን ይመሰክራሉ። ከዚያ በተጨማሪም፥ ቢፈልግ እነ ማንን እንደሚያገባም ይናገራሉ፦

"Had We desired to find some diversion, that which provided diversion, in the way of a partner or a child, we would have found it with ourselves, from among #the_beautiful_eyed_houris or #angels were we to do {so}. But We did not do so, thus We never desired it"

✍️ Tafsir Al Jalalayn:- https://quranx.com/Tafsir/Jalal/21.17

የቁርአን ተንታኞች ሁለቱ ጃላላዎች እንዳስቀመጡት፥ አላህ ብንሻ ሚስትና ልጅ ብንይዝ ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ አብራርተውታል። እርሱም፥ ከፈለገ ከመላእክትና ከሁሪዎች (በእስላማዊ ጀና ያሉ እንግዳ እንስት ፍጥረታት ናቸው) ሚስት አግብቶ መውለድ ይችላል ማለት ነው ብለዋል። ስለዚህ አላህ በሰማይ ከሁሪዎችና ከመላእክት ጋር ሊጋባ የሚችል ወንድ ነው ማለት ነው

"Then Allah revealed the following, when they said that the angels are Allah's daughters: (if we had wished to find a pastime) if we wished to #have #daughter; and it is said that it means: if we wished to #have a #wife; and it is also said that this means: if we wished to #have #children, (we could have found it in our presence) from us from among #the_maidens of paradise (if we ever did) and we will never do this"

✏️ Tafsir ibn abbas:- https://quranx.com/Tafsir/Abbas/21.17

የሙስሞች ነብይ የአጎት ልጅ የነበረውና፥ "ኻብራል ኡማ/የኡማው የብዕር ቀለም" ተብሎ የሚጠራው ኢብን አባስ እንደተረጎመው፥ አላህ ሚስትና ልጅ ብፈልግ ኖሮ እይዝ ነበር ሲል፥ ከፈለኩ በሰማይ ያሉ ሁሪዎችን ማግባት እችላለሁ ማለቱ ነው ብሏል። ይህ ማለት አላህ አንዲትን እንስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ ነው ማለት ነው። ከሁሪዎቹ ጋር ተገናኝቶ ልጅ የሚያስወልድ ባህርይ አለው። ስለዚህ ጾታ ያለው የሙስሊሞች አምላክ ነው ማለት ነው።

🔊 ታዲያ እንዴት ክርስቲያኖች ጾታ ያለው አምላክ አላቸው ይላሉ? ራሳቸው በመለኮት ጾታ ያለው አምላክ እያመለኩ???
Forwarded from Obadiah Apologetics
በእስላማዊ ምንጮች መሰረት የቀደሙት መጻሕፍት አሁን ያሉት አይደሉምን? (ክፍል 1)

እንደሚታወቀው ቁርአን በመሰረታዊ አስተምህሮ የእርሱን ትምህርት የሚቃወሙትን የክርስቲያኖችን እና የአይሁዶችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ፈጣሪ ቃል ያጸድቃል።

ይህ ማለት መጽሐፍ ቅዱስ እውነትም ሆነ ሀሰት እስልምና ከሀሰተኝነት አያመልጥም ማለት ነው። በዚህም ምክንያት ቁርአን የፈጣሪ ቃል አለመሆኑ ይረጋገጣል

ሙስሊም ወገኖችም ይህንን ተረድተው ሀይማኖታቸውን ከሀሰተኝት ለመታደግ የተለያዩ መልሶችን ለመስጠት ይሞክራሉ። ዛሬ በክርስቶስ ፈቃድ መልስ ይሆነናል ከሚሏቸው ምላሾች አንዱን እንዳስሳለን

ነጥቡ ይህ ነው " አላህ በቁርአኑ ውስጥ "ተውራት" እና "ኢንጅል" ሲል፥ አሁን በአይሁዶችና በክርስቲያኖች እጅ ያሉትን መጻሕፍት አይደለም። ጨርሶ ሌሎች መጻሕፍት ናቸው" ይላሉ

ከሞላ ጎደል ይህኛው መልስ እንደዚህ ነው። ግን እውነት ነውን?

በመጀመሪያ ደረጃ፥ አሁን ካለው ኦሪትና ወንጌል ወጪ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች በይፉ ሲጠቀሙበት የነበረ ሌላ ኦሪት ወይንም ወንጌል የለም። ታሪክ የሚያውቀውና በይፋ ክርስቲያኖች እና አይሁዳውያን ይጠቀሙባቸው የነበሩት መጻሕፍት አሁን በእጃችን ያሉትን መጻሕፍት ነው።

ሲቀጥል እንደ ቁርአኑ ምስክርነት ኦሪቱና ወንጌሉ በክርስቲያኖችና በአይሁዳውያን ዘንድ ነበሩ። በእነሱ እጅ ያሉትን መጻሕፍት ነው እንደ ፈጣሪ ቃል ያጸደቃቸው። (ሱራ 7:157 3:3-4 2:75 ወዘተ)

በመሐመድ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች እና አይሁዶች ደግሞ የነበራቸው ወንጌልና ኦሪት የትኞቹ እንደሆኑ እናውቃለን። በዛን ዘመን የተጻፉ ዕደ-ክታባት (manuscripts) አሉን። አሁን በእጃን ያሉት መጻሕፍት ናቸው። ስለዚህ በመሐመድ ዘመን የነበሩት ኦሪትና፥ ወንጌል አሁን ያሉት አይደሉም ማለት ፈጽሞ አይቻልም

ሲቀጥል ደግሞ ቁርአን ስለ አይሁዳውያን እና ስለ ክርስቲያኖች እምነት የሚናገረው ነገር አለ። "ይህንን፥ ይህንን ያምናሉ" በማለት ይወቅሳቸዋል። ነገር ግን ቁርአኑ ስለ እነሱ እምነት የሚናገረው ነገር እውነት የሚሆነው፥ በነሱ ዘንድ የነበሩት መጻሕፍት፥ አሁን በእኛ እጅ ያሉት ከሆኑ ብቻ ነው።

ለምሳሌ

" አይሁድ ዑዘይር የአላህ ልጅ ነው አለች፡፡ ክርስቲያኖችም #አልመሲሕ የአላህ #ልጅ ነው አሉ፡፡ ይህ በአፎቻቸው (የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፡፡ የእነዚያን ከነሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፡፡ አላህ ያጥፋቸው፡፡ (ከእውነት) እንዴት ይመለሳሉ! " ሱራ 9:30

በዚህ ስፍራ አላህ ክርስቲያኖች ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለው ያምናሉ በማለት ሲከሰን እንመለከታለን። ይህ አያ በመሐመድ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች መሲሁ የአላህ ልጅ ነው በማለት ያምኑ እንደነበር በግልጽ ያሳያል።

ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚለው ትምህርት የወንጌል ምሰሶ ነው። የወንጌል መሰረታዊ ጭብጥ የኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት ነው።

" በታንኳይቱም የነበሩት። በእውነት የእግዚአብሔር #ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት።"
(የማቴዎስ ወንጌል 14:33)

" በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ። ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር #ልጅ ነበረ አለ።"
(የማርቆስ ወንጌል 15:39)

" መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር #ልጅ ይባላል።"
(የሉቃስ ወንጌል 1:35)

" የእግዚአብሔር #ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን። ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?"
(የዮሐንስ ወንጌል 10:36)

ታዲያ በመሐመድ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች መሲሁ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የሚለውን እምነት ከየት አመጡት? በእነሱ ዘንድ የነበረው መጽሐፍ ጨርሶ ያንን የማያስተምር ከሆነ?

ሌላ ምሳሌ

" እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና፡፡ " ሱራ 2:208

በዚህ ስፍራ አላህ ወደ እስልምና የሚገቡ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንዲገቡ ያዛል። ይህ አያ የወረደበት ታሪካዊ ዳራ አብደላህ ኢብን ሰላማ የተባለ አይሁዳዊ፥ ከይሁዲነት ወደ እስልምና ከገባ በኋላ እንኳ የይሁዲነት ልምምዱን ባለማቆሙ ነው። በተለይም ኦሪት የግመል ስጋን መብላት ይከለክላል ብሎ የግመል ስጋን አልበላም አለ። ለዚህ ነገር መልስ ይሆን ዘንድ፥ አላህ ይህንን "አወረደ"

[ asbab al nuzul al wahidi, tafsir ibn kathir, ibn abbas, al jalalayn, qurtubi ]

ይህ አያ በመሐመድ ዘመን የነበሩ አይሁዶች ኦሪት የግመል ስጋን መብላት ይከለክላል ብለው ያምኑ እንደነበር በግልጽ ያሳያል። አሁን በእጃችን ላይ ያለው ኦሪትም ደግሞ የግመል ስጋን መብላት ይከለክላል

" ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም፤ #ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ #ርኩስ ነው።"
(ኦሪት ዘሌዋውያን 11:4)

" ነገር ግን ከሚያመሰኩ ወይም ሰኮናቸው ከተሰነጠቀ እነዚህን አትበሉም፤ #ግመልን፥ ጥንቸልን፥ ሽኮኮን #አትበሉም። ያመሰኳሉና፥ ነገር ግን ሰኮናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ #ርኩሶች ናቸው። "
(ኦሪት ዘዳግም 14:7)

ታዲያ በመሐመድ ዘመን የነበሩ አይሁዶች፥ ኦሪት የግመል ስጋን መብላት ይከለክላል የሚለውን ሀሳብ ከየት አመጡት? በነሱ ዘንድ የነበረው ኦሪት ጨርሶ ያንን የማያስተምር ከሆነ?

አንድ የመጨረሻ ምሳሌን እንመልከት፦

" አይሁዶችና ክርስቲያኖችም «እኛ የአላህ #ልጆችና ወዳጆቹ ነን» አሉ፡፡ «ታዲያ በኃጢአቶቻችሁ ለምን ያሰቃያችኋል አይደላችሁም እናንተ ከፈጠራቸው ሰዎች ናችሁ» በላቸው፡፡ ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ይቀጣል፡፡ የሰማያትና የምድርም በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፡፡ መመለሻም ወደርሱ ብቻ ነው፡፡ " ሱራ 5:18

በዚህ ስፍራ አላህ አይሁዶችና ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ልጆች ነን በማለታቸው ሲወቅሳቸው እንመለከታለን። ይህ አያ በመሐመድ ዘመን የነበሩ አይሁዶችና ክርስቲያኖች የአላህ ልጆች ነን ብለው ያምኑ እንደነበር በግልጽ ያሳያል

ወደ ኦሪትና ወንጌል ስንመጣ፥ አይሁዶችና ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸው ተደጋግሞ ተነግሯል

"1 እናንተ የአምላካችሁ #የእግዚአብሔር #ልጆች ናችሁ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ "
(ኦሪት ዘዳግም 14:1)

" ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ #የእግዚአብሔር #ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 1:12)

ታዲያ በመሐመድ ዘመን የነበሩ አይሁዶችና ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ልጆች ነን የሚለውን እምነት ከየት አመጡት? በእነሱ ዘንድ የነበሩት መጻሕፍት በፍጹም ያንን ካላስተማሩ?

ቁርአን በመሐመድ ዘመን የነበሩት ኦሪትና ወንጌል አሁን ያሉት ኦሪትና ወንጌል ከሆኑ ብቻ እውነት ሊሆን የሚችል ንግግርን ተናግሯል።

በተጨማሪም ቁርአን ስለ ክርስቲያኖችና አይሁዶች እምነት የተናገረው ነገር በዚህ ዘመን በሚገኙት ኦሪትና ወንጌል ተረጋግጧል። ከዚህ ተነስተን አላህ የቀደሙት መጻሕፍት ሲል አሁን በእኛ እጅ ያሉትን ማለቱ እንደሆነ እናረጋግጣለን

🚩 ይቀጥላል
Forwarded from Obadiah Apologetics
በእስላማዊ ምንጮች መሰረት የቀደሙት መጻሕፍት አሁን ያሉት አይደሉምን? (ክፍል 2)

ባለፈው ክፍል፥ እስላማዊ ምንጮች ተውራትና ኢንጅል ሲሉ፥ አሁን በአይሁዶችና በክርስቲያኖች እጅ ያሉትን መጻሕፍትን እንደሆነ ለማየት ሞክረን ነበር።

ዛሬም ከቁርአን ባሻገር፥ ሌሎች እስላማዊ ምንጮችን ጠቅሰን፤ ተውራትና ኢንጅል አሁን ያሉት ኦሪትና ወንጌል መሆናቸውን ለማየት እንሞክራለን

1. ተውራት

መሐመድ በሶስተኛው የጂሃድ ደረጃ ላይ በነበረበት ጊዜ፥ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፍርድን ለመስጠት ይቀመጥ ነበር። እንደተለመደው ፍርድን በሚሰጥበት ሰአት፥ ሁለት አይሁዳውያን በዝሙት ተይዘው ወደ እርሱ ለፍርድ ይመጣሉ።

በዚህም ሰአት አላህ ሱራ 5:43ን ያወርዳል፦

" እነርሱም ዘንድ ተውራት እያለች በውስጧ የአላህ ፍርድ ያለባት ስትኾን እንዴት ያስፈርዱሃል! ከዚያም ከዚህ በኋላ እንዴት ይሸሻሉ! እነዚያም በፍጹም ምእምናን አይደሉም፡፡ " ሱራ 5:43

አላህ "ከነርሱ ጋር ኦሪት እያለ ለምን ለፍርድ ወደ አንተ ይመጣሉ" ይላል። ይህ ማለት በአመንዝሮች ላይ የሚተላለፈው ቅጣት በኦሪቱ ላይ ተገልጾ እያለ ለምን ወደ አንተ ይመጣሉ ማለቱ ነው።

[ Tanwir al miqbas min tafsir ibn abbas, tafsir ibn kathir, asbab al nuzul al wahidi ]

ከዚያም መሐመድ በአይሁዳውያን እጅ የነበረው ኦሪት እንዲመጣ በማዘዝ፥ ፍርዱን እንደሚከተለው ያስላልፋል፦

Ibn ‘Umar said:

some jews came to the Messenger of Allah (ﷺ) and mentioned to him that a man and a women of their number had committed fornication. The Messenger of Allah (ﷺ) asked them: What do you find in the Torah about stoning? They replied: We disgrace them and they should be flogged. ‘Abd Allah b. Salam said: You lie; it contains (instruction for) stoning. So they brought the Torah and spread it out, and one of them put his hand over the verse of stoning and read what preceded it and what followed it. ‘Abd Allah b. Salam said to him: Lift your hand. When he did so, the verse of stoning was seen to be in it. They then said: He has spoken the truth, Muhammad, the verse of #stoning is #in *it*. The Messenger of Allah (ﷺ) then gave command regarding them, and they were stoned to death. ‘Abd Allah b. ‘Umar said: I saw the man leaning on the woman protecting her from the stones.

[ Sunan Abi Dawud 4446 ]

አሪቱ ለመሐመድ ከቀረበለት በኋላ አንዱ አይሁዳዊ እንዲገደሉ የሚያዘውን ጥቅስ በእጁ ይሸፍናል። ከዛም አንዱ የመሐመድ ሱሃባ እጁን እንዲያነሳ ይጠይቀዋል፥ ጥቅሱም ይገኛል። መሐመድም ቅጣቱን ተፈጻሚ በማድረግ ያስወግራቸዋል።

በሌላ ዘገባም፥ መሐመድ ያኔ በፊቱ በቀረበው ኦሪት እንደሚያምን ይናገራል (sunan abu dawud 4449)

ይህ ክስተት በመሐመድ ዘመን የነበረው ኦሪት አሁን በኛ እጅ ያለው መሆኑን በግልጽ ያሳያል፦

1. በሰባተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የኦሪት ዕደ-ክታባት አሁን በእጃን አሉ። አሁን ካለን ኦሪት ጋር ፍጹም አንድ አይነት ናቸው። ስለዚህ ያኔ የነበረው ኦሪት አሁን ካለው ጋር መሰረታዊ ልዩነት አለው ማለት አይቻልም

2. አመንዝሮቹን ለማስገደል በመሐመድ እና በሱሃቢዎቹ የተጠቀሰው የኦሪት ጥቅስ፥ አሁን በእጃችን ባለው ኦሪት ውስጥ መገኘቱ:-

" ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራይቱ ፈጽመው #ይገደሉ።"
(ኦሪት ዘሌዋውያን 20:10)

በመሐመድ ዘመን በነበረው ኦሪት ውስጥ ይህ ጥቅስ መገኘቱ፥ ያኔ የነበረው ኦሪት አሁን ያለው ለመሆኑ ሊታበል የማይችል መረጃ ነው

3. ይህ ሀቅ በሙስሊም ሊቃውንትም ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱ፦

Here it refers to a case of illicit relationship between a man and a woman who belonged to respectable families of the Jews of Khaibar. According to the Torah (Deut 22፥ 23-24), their punishment was that both of them should be stoned to death.

[ MaududiSayyid Abul Ala Maududi - Tafhim al-Qur'an ]

ማውዱዲ የተሰኘው የኢስላም ኡለማ፤ ዘዳ 22:24ን በመጥቀስ፥ በመሐመድ ዘመን የነበረው ኦሪት አሁን በእኛ እጅ ያለው መሆኑን መስክሯል

" ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመንዝራውና አመንዝራይቱ ሁለታቸው #ይሙቱ፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከእስራኤል ታስወግዳለህ። "
(ኦሪት ዘዳግም 22:22)

ይህንን ግልጽ መረጃ ለማስተባበል "ለሙሴ የተሰጠው ተውራት አንድ መጽሐፍ ነው። አሁን ያሉው ኦሪት ግን የአምስት መጻሕፍት ስብስብ ነው" ይላሉ

ይህ ቁርአንን ካለማወቅ የመነጨ ስሁት እሳቤ ነው። ምክንያቱም ቁርአን ኦሪትን #መጻሕፍት በማለት ይጠራዋልና

" ይልቁንም በዚያ በሙሳ #ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? " ሱራ 53:36

ጽሑፎች የሚለው የአረብኛ ቃል "صُحُفِ/ሱሁፊ" የሚል ሲሆን በሱራ 87:18 ላይ #መጻሕፍት ተብሎ ተተርጉሟል

ስለዚህ ከላይ በቀረቡት መረጃዎች መሰረት፥ ቁርአን "ተውራት" ሲል ታሪክ የሚያውቀውን ኦሪት አይደለም ማለት አይቻልም

2. ወንጌል

" ለእነዚያ ያንን እነሱ #ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)፡፡ በበጎ ሥራ ያዛቸዋል፡፡ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፡፡ መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፡፡" ሱራ 7:157

በዚህ ስፍራ አላህ፥ መሐመድ በኦሪትና በወንጌል ተተንብዮ እንደሚገኝ ይናገራል። በዘመናችን የሚገኙ ሙስሊም ወገኖች "መሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ተተንብዮአል" የሚሉት በዚሁ አንቀጽ የተነሳ ነው

በኦሪትና በኢንጅል መሐመድ ካልተተነበየለት ቁርአን ውሸታም ሊሆን ስለሆነ፥ የመሐመድ ጥንታዊ የግለ ታሪክ (Biography) ዘጋቢዎች መረጃ ብለው ወንጌልን ጠቅሰዋል። ምን ይሆን የጠቀሱት?

የመጀመሪያው የመሐመድ ግለ ታሪክ ዘጋቢ ኢብን ኢሻቅ ለ7:157 መረጃ ብሎ አንድ የወንጌል ክፍልን ጠቅሷል
Forwarded from Obadiah Apologetics
THE WORD APPLIED TO THE APOSTLE OF GOD IN THE GOSPEL

Among the things which have reached me about what Jesus the Son of Mary stated in the Gospel which he received from God for the followers of the Gospel, in applying a term to describe the apostle of God, is following.It is extracted from what #John the Apostle set down for them when he wrote the Gospel for them from the Testament of Jesus Son of Mary: 'He that hateth me hath hated the Lord. And if I had not done in their presence works which none other before me did, they had not.had sin:150 but from now they are puffed up with pride and think that they will over-come me and also the Lord.But the word that is in the law must be ful-filled, "They hated me without a cause" (i.e.withoutreason).But when the #Comforter has come whom God will send to you from the Lord's presence, and the #spirit of #truth which will have gone forth from the Lord's presence he (shall bear) #witness of #me and ye also, because ye have been with me from the beginning.I have spoken unto you about this that ye should not be in doubt." The Muna Memana(God bless and preserve him!) in Syriac is Muhammad; in Greek he is the paraclete

[ Ibn ishaq p.102-104 ]

በዚህ ስፍራ ኢብን ኢስሃቅ ለሱራ 7:157 መረጃ ብሎ የዮሐንስ ወንጌልን ሲጠቅስ እንመለከታለን። ይህ ዘገባ በኢብን ሂሻም ሀያሲነትም ተቀባይነት ያገኘ ዘገባ ነው።

ይህ ግለ ታሪክ የተዘገበው መሐመድ ከሞተ 90 አመታት በኋላ ሲሆን፥ ከአይነቱ የመጀመሪያው ነው። ስለዚህም የመጀመሪያው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ስለ ወንጌል ያለውን መረዳት ያሳያል

ይህ ዘገባ ቁርአን ኢንጅል ሲል በእኛ እጅ ያለውን መሆኑን በግልጽ ያሳያል:-

1. ዘጋቢው መረጃ ሊያቀርብለት የፈለገው የቁርአን አያ ሱራ 7:157 ነው። ያ አያ ደግሞ ተውራትና ኢንጅል በአይሁዶችና በክርስቲያኖች ዘንድ (with them) መሆኑን ይናገራል።

ከላይ እየተናገርን እንደመጣነው፥ በመሐመድ ዘመን የነበሩት አይሁዶችና ክርስቲያኖች የነበራቸው ኦሪትና ወንጌል ዕደ ክታባት አሉን። አሁን ካሉን መጻሕፍት የተለዩ አይደሉም

2. ሲቀጥል፥ ዘጋቢው በቀጥታ የዮሐንስ ወንጌልን በስሙ ይጠቅሳል። ሱራ 7:157ን ለመደገፍ የጠቀሰው ዮሐንስ ወንጌልን ነው። በታሪክ አሁን ካለው የዮሐንስ ወንጌል በቀር ሌላ የዮሐንስ ወንጌል የለም።

3. ዘጋቢው ለሱራ 7:157 ድጋፍ ብሎ የጠቀሰው የዮሐንስ ወንጌል ጥቅስ፥ አሁን በእኛ እጅ ባለው የዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ይገኛል

" ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ #አጽናኝ እርሱም ከአብ #የሚወጣ #የእውነት #መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ #እኔ #ይመሰክራል፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 15:26)

አሁንም የቀረበውን ግልጽ መረጃ ለማስተባበል "ለኢሳ የተሰጠው ኢንጅል አንድ መጽሐፍ ነው። የአሁኑ ወንጌል ግን የአራት መጻሕፍት ስብስብ ነው" ይላሉ

ይህ አባባል ፍጹም የተሳሳተ ነው። ምክንያቱም የታሪክ ዘጋቢው ለቁርአን መረጃ አድርጎ ያቀረበው ሐዋሪያው ዮሐንስ እንደ ጻፈው በማለት ነው። ይህ ስለ አራቱ ወንጌላት ያውቁ እንደ ነበር በግልጽ የሚያመለክት ነው። ለይቶ በስም አቅርቦታልና

ሲቀጥል፥ የመሐመድን ነብይነት ያጸደቀው "ክርስቲያኑ" ዋራቃ፥ #ወንጌላትን ያነብ እንደነበር መነገሩ ነው

Narrated `Aisha:

The Prophet (ﷺ) returned to Khadija while his heart was beating rapidly. She took him to Waraqa bin Naufal who was a Christian convert and used to read the #Gospels in Arabic Waraqa asked (the Prophet), "What do you see?" When he told him, Waraqa said, "That is the same angel whom Allah sent to the Prophet) Moses. Should I live till you receive the Divine Message, I will support you strongly."

[ Sahih al-Bukhari 3392 ]

ዋራቃ በሂራ ዋሻ ውስጥ ለመሐመድ የተገለጠለት አካል ጅብሪል ነው ብሎ ለመሐመድ ነብይነት ማረጋገጫ የሰጠ ሰው ነው። ለእሱ ወንጌል ማለት ከአንድ በላይ መጽሐፍ ነው።

መደምደሚያ

ከላይ በቀረቡት መረጃዎች መሰረት፥ ቁርአን ወንጌልና ኦሪት ሲል፥ ታሪክ የሚያውቃቸውን እና አሁን በእኛ እጅ ያሉትን መጻሕፍት መሆኑን እናረጋግጣለን
Forwarded from Isaiah 48 Apologetics
🚩 አልተሰቀለም?

ሙስሊሞች ክርስቶስ አልተሰቀለም ብለው ያምናሉ። በእነሱ እምነትና መረዳት መሰረት፥ አይሁዶች ኢየሱስን ሊገድሉት ሲሉ አላህ ወደ ራሱ አነሳው። ከዚያም የሌላ ሰውን መልክ የኢየሱስን እንዲመስል አድርጎ በመቀየር፥ በእርሱ ቦታ ሌላ ሰው ተሰቅሎ እንዲገደል አደረገ

ለዚህም እምነታቸው፥ የሚከተለውን የቁርአን አንቀጽ እንደማስረጃ ያቀርባሉ፦

"«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ #አልገደሉትም #አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) #ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም #አልገደሉትም፡፡" ሱራ 4:157

➣ አላህ ሌላ ሰውን በኢየሱስ ቦታ አስመስሎ በመለወጥ፥ አስገደለ የሚለው ሀሳብ እጅግ በጣም ብዙ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነገር ነው። በእውነቱ ከሆነ፥ እንደዚህ ጉዳይ አወዛጋቢና ብዙዎችን እያነጋገረ ያለ ነገር የለም

"ለምን ለ600 ዓመታት ዝም አለ? ይህ ተግባር አላህን አታላይና አጭበርባሪ አያደርገውም ወይ? የኢየሱስ ተከታዮች "ኢየሱስ ተሰቅሎልናል" ወደሚል እምነት የመጡት በራሱ በአላህ ምክንያት ሆኖ ሳለ (አላህ ያን ሰው ኢየሱስን እንዲመስል ስላደረገው፥ ተከታዮቹ ያዩት የእሱን መልክ ነው) እንዴት ተሳስታችኋል ተብለው ሊወቀሱ ይችላሉ? መሐመድ ከመምጣቱ በፊት የነበሩት ክርስቲያኖችስ ለዚህ እምነታቸው እውን መወቀስ አለባቸው?..." እነኚህንና የመሳሰሉት ብዙ ጥያቄዎች የሚያስነሳና፥ እያስነሳ ያለ ጉዳይ ነው

✎ እኛም ዛሬ፥ ሊመለሱ ይገባቸዋል ያልናቸውን የተወሰኑ ጥያቄዎችን እናንሳ:-

ሱረቱል ኒሳዕ፥ 157ን በተመለከተ የቁርአን ተንታኞች (ሙፈሲሮች) ወጥ የሆነ አቋም የላቸውም። ሁሉም የተለያዩና እርስ በራሳቸው የሚጋጩ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል

የተሰወኑት ተንታኞች፥ በኢሳ ፋንታ የተሰቀለው የኢሳና የሐዋርያቱ ወዳጅ (companion) ነው ይላሉ። ኢብን ከቲር፥ ቁሻዪሪ ለዚህ ተጠቃሽ ናቸው። በእነርሱ ትንተና መሰረት፥ አይሁዳውያን ኢየሱስን ሊይዙት ሲመጡ፥ ኢየሱስ "በእኔ ቦታ ማን ይሆናል" ብሎ ሐዋሪያቱን እና አብረውት ያሉትን ሰዎች ይጠይቃቸዋል። ከዚያም ከሐዋሪያቱ አንዱ፥ እኔ እሆናለሁ ብል በእርሱ ቦታ ይገባል። አላህም መልኩን በመቀየር በእርሱ ቦታ ተሰቅሎ እንዲገደል ያደርጋል። እንደውም ኢብን ከቲር፥ ኢየሱስን በአንተ ቦታ እሆናለሁ ያለው ከሁሉም ትንሹ ነበር ይላል። ከዚያም ኢየሱስ ሌላ በእርሱ ቦታ የሚገባ አለ ወይ ብሎ ጠይቆ፥ ማንም ፈቃደኛ አለመሆኑን ሲያይ፥ ትንሽየው ልጅ በእርሱ ፋንታ እንዲሆን ፈቀደለት ይለናል።

ሌሎቹ ተንታኞች ደግሞ፥ ከዚህ በተቃራኒ፥ በኢየሱስ ፋንታ የተሰቀለው ከአይሁድ ወገን የሆነ እና፥ የኢየሱስና የሐዋርያቱ ጠላት የሆነ ሰው ነው ይላሉ። ለዚህ ኢብን አባስ እና አል ጃለሌይን ተጠቃሽ ናቸው። በዚህ ትርጉም መሰረት፥ የኢሳ ጠላቶች ከሆኑት አይሁዳውያን መካከል አንዱን አላህ መልኩን ቀየረው። ከዚያም አይሁድ ኢየሱስን ያገኙ መስሏቸው እሱን ሰቀሉት። ሁለቱ ጃላላዎች እንደውም፥ በኢየሱስ ቦታ የተሰቀለው ሰው ኢየሱስን ይሳደብ የነበር ሰው መሆኑንም ዘግበዋል

ስለዚህ ጥያቄዎቻችንም ይህን ያማከሉ ይሆናሉ።

✍️ የተሰቀለው የኢየሱስና የሐዋርያት ወገን የሆነ ሰው ከነበር፦

1) እንዴት አይሁዶቹ የዚያን ሰው ሬሳ ማምጣት አቃታቸው?

እንደሚታወቀው ከክርስቶስ ስቅለት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሐዋሪያቱ ከሞት መነሳቱን መስበክ ጀምረው ነበር። በዚህ የትንሳኤ ስብከታቸው ብዙ ሕዝብ ወደ ክርስትና የመጣ ሲሆን (ሐዋ 2:24 ሐዋ 2:41) የወንጌሉ ተቃዋሚዎች ለዚህ የሐዋሪያት አዋጅ ምላሽ አልነበራቸውም ነበር። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የክርስቶስን ሙት ስጋ ማምጣት ባመቻላቸው ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ የተሰቀለው በገሃድ፥ በብዙ ሕዝብ ፊት ሲሆን (ማር 15:11-15) የተቀበረውም ቦታው በሚታወቅ መቃብር ነበር (ዮሐ 19:38-42) ነገር ግን በሶስተኛው ቀን የተቀበረበት መቃብር ባዶ ሆኖ ተገኝቷል። ስጋውም በዚያ አልነበረም (ሉቃ 24:2) በዚህም ምክንያት ፈሪሳዊያኑ ደቀመዛሙርቱ ሰርቀውታል የሚል የሀሰት ወሬ ፈጠሩ (ማቴ 28:13) ይህን ሊያደርጉ የቻሉት የክርስቶስን ሙት ስጋ አምጥተው ከሞት አለመነሳቱን ማሳየት ባለመቻላቸው ነው። በዚህም ምክንያት የክርስቶስን ትንሣኤ መቀልበስ ሳይችሉ ቀርተዋል። ይህ እውነት ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በሐዋሪያትና በመጀመሪያዎቹ ተከታዮቻቸው ይታመን የነበር እምነት ሲሆን፥ ቀዳማዊ ከሆነው ከራሳቸው የሐዋርያት ጽሑፍ ሊረጋገጥ የሚችል ሀቅ ነው።

በእስልምና የሚታመነው ነገር እውነት ነው ከተባለ ግን አንድ ወሳኝ ጥያቄ ይነሳል። ይኸውም በእርግጥም የተሰቀለው በክርስቶስ ኢየሱስ የተመሰለ የሐዋርያት ወገን ከሆነ፥ እንዴት አይሁዶቹ የእርሱን ሬሳ ማምጣት አቃታቸው? ሐዋሪያቱ ክርስቶስ ተነስቷል ብለው መስበክ ሲጀምሩ፥ አይሁዶቹ እንዴት ክርስቶስን እንዲመስል የተቀየረውን ሬሳ ማምጣት ተሳናቸው? ያ ሰው ከሞት ተነስቶ ነበር እንዴ? ካልተነሳ እንዴት አይሁድ በእጃቸው የነበረውን ሬሳ ማምጣት ሳይችሉ ቀሩ?

♦️ አስተውሉ! አላህ ይህን የሐዋርያትን ወገን ኢየሱስን እንዲመስል ስላደረገው አይሁዶቹ የገደሉት ኢየሱስን ገደልን ብለው ነው። ቁርአንም ኢሳን ገደልነው አሉ ማለታቸውን ይመሰክራል (ሱራ 4:157) በተጨማሪም በእስልምና ውስጥ ይህ በክርስቶስ ፋንታ የተሰቀለው ሰው ከሞት ተነስቷል ተብሎ አይታመንም። ስለዚህ ሐዋሪያቱ ኢየሱስ ከሞት ተነስቷል ብለው ሲሰብኩ፥ እንዴት አይሁዶቹ ኢየሱስን እንዲመስል የተለወጠውን የዚያን ሰው ሬሳ ማምጣት ተሳናቸው? ከሞት ካልተነሳ፥ በሚታወቅ መቃብር ከተቀበረ፥ ተነስቷል ተብሎ ሲሰበክ እንዴት ሬሳውን ማምጣት አልቻሉም?

አይሁድ ለምን የዚያን ሰው ሬሳ ማምጣት እንዳልቻሉ #በማስረጃ መልሱ

2) በቁርአን ውስጥ፥ ነቢያት በኢ-አማኒያን የግድያ ሙከራ ሲደረግባቸውና አላህ ሲያድናቸው፥ ኢሳ የመጀመሪያው አይደለም። ለምሳሌ፦ በቁርአን ውስጥ ጣዖት አምላኪያን ኢብራሂምን ሊገድሉት ወደ እሳት እንደጣሉትና፥ አላህም ከእሳቱ እንዳዳነው የሚናገር ታሪክ አለ።

👉 [ ሱራ 2:258 6:74-82 19:41-49 26:70-89 29:16-17 43:26-28 ]

ጥያቄው፥ አላህ ለምን ኢሳን አ
ኢብርሃምን እንዳዳነው አላዳነውም? ለምን በእርሱ ቦታ ሌላ ሰው ተካ?

ጣዖታዊያኑ ኢብራሂምን እሳት ውስጥ ሲጨምሩት፥ ሌላን ሰው እርሱን አስመስሎ በእርሱ ቦታ አልተካም። ከእሳቱ አዳነው፥ ጣዖታዊያኑም ከስረው ባዶ እጃቸውን ተመለሱ። ሌላ ሰው መሞት አላስፈለገውም።

በኢሳ ታሪክ ላይ ግን የሆነው ሌላ ነው። አይሁዳውያን ኢሳን ሊገድሉት ሲመጡ፥ አላህ ለኢብራሂም እንዳደረገው አላደረገም። ሌላ ሰውን በእርሱ ቦታ በመተካት፥ የንጹህ ሰው ሕይወት እንዲጠፋ አድርጓል። ለምን? ለኢብራሂም እንዳደረገው ለኢሳም ቢያደርግ ኖሮ፥ አይሁዳውያኑ ልክ እንደ ጣዖታዊያኑ ከስረው ይቀሩ ነበር፥ ኢሳም ከሞት ይድናል፥ ንጹህ ሰውም አይገደልም ነበር። አላህ ይህን ማድረግ እየቻለ፥ ለምን ሌላ ሰውን በእርሱ ቦታ አስገደለ? እንዲሁ ማዳን እየቻለ ሌላ ሰውን ማስገደሉ ምክንያቱ ምንድነው?? #በማስረጃ መልሱ

3) በኢሳ ቦታ የተሰቀለው ከሐዋርያት ወገን አንዱ ከሆነ፥ ለምንድነው ሐዋርያት "የተሰቀለው ኢየሱስ ነው" በሚለው እምነታቸው የቀጠሉት?
Forwarded from Isaiah 48 Apologetics
ኢየሱስ ከነበረበት ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ፥ የተላለፈው የሐዋርያትና የአይን እማኞች ምስክርነት "የተሰቀለው ኢየሱስ ነው" የሚለው ነው። ይህን ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ከመጣው የራሳቸው ጽሑፎች ማረጋገጥ እንችላለን። ሐዋርያት ራሳቸውም ያመኑት፥ ተከታዮቻቸውንም ያስተማሩት የተሰቀለው ኢየሱስ መሆኑን ነው። የትኛውም ሐዋሪያ "ኢየሱስ አልተሰቀለም" አላለም። ይህ ታሪካዊ ሀቅ ነው

ታዲያ እስልምና እንደሚለው በኢየሱስ ቦታ የተሰቀለው ከሐዋርያት ወገን አንዱ እንጂ ራሱ ኢየሱስ ካልሆነ፥ ለምን ሐዋርያት ኢየሱስ ነው የተሰቀለው አሉ? ለምንስ ተከታዮቻቸውንም የተሰቀለው ኢየሱስ ነው ብለው አስተማሩ?

በእሱ ቦታ የተሰቀለው ከእነርሱ አንዱ መሆኑን እያወቁ?? እስላማዊው ትርክት እውነት ከሆነ፥ ለምን በኢየሱስ ቦታ የተሰቀለው ከኛ መካከል አንዱ ነው አላሉም? ለምንስ በዚህ እምነት አልቀጠሉም? ለምንስ ለተከታዮቻቸው እንዲህ ብለው አላስተማሩም? ሐዋሪያቱ ዋሽተዋል ብሎ መከራከር አይቻልም። ምክንያቱም በቁርአን መሰረት፥ ሐዋርያት ሙስሊሞች ናቸው (ሱራ 3:52) እስከ መጨረሻው ቀንም የበላይ እንደሚሆኑ አላህ ቃል ገብቶላቸዋል (ሱራ 3:55) አሸናፊ ይሆኑ ዘንድም አበረታታቸው ይላል (ሱራ 61:14) ስለዚህ ውሸት የሰበኩ ሀሰተኞች ናቸው ብሎ መከራከር አይቻልም። ታዲያ ለምን "የተሰቀለው ራሱ ኢየሱስ ነው" በሚለው እምነት ቀጠሉ? ለምንስ ተከታዮቻቸውን እንደዚያ ብለው አስተማሩ? #በማስረጃ መልሱ

✍️ የተሰቀለው የኢየሱስና የሐዋርያቱ ጠላት፥ ከአይሁድ ወገን የሆነ ሰው ከነበር፦

1) እንዴት አይሁዶቹ የዚያን ሰው ሬሳ ማምጣት አቃታቸው?

ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርነው፥ ከክርስቶስ ስቅለት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሐዋሪያቱ ከሞት መነሳቱን መስበክ ጀምረው ነበር። በዚህ የትንሳኤ ስብከታቸው ብዙ ሕዝብ ወደ ክርስትና የመጣ ሲሆን (ሐዋ 2:24 ሐዋ 2:41) የወንጌሉ ተቃዋሚዎች ለዚህ የሐዋሪያት አዋጅ ምላሽ አልነበራቸውም ነበር። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የክርስቶስን ሙት ስጋ ማምጣት ባመቻላቸው ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ የተሰቀለው በገሃድ፥ በብዙ ሕዝብ ፊት ሲሆን (ማር 15:11-15) የተቀበረውም ቦታው በሚታወቅ መቃብር ነበር (ዮሐ 19:38-42) ነገር ግን በሶስተኛው ቀን የተቀበረበት መቃብር ባዶ ሆኖ ተገኝቷል። ስጋውም በዚያ አልነበረም (ሉቃ 24:2) በዚህም ምክንያት ፈሪሳዊያኑ ደቀመዛሙርቱ ሰርቀውታል የሚል የሀሰት ወሬ ፈጠሩ (ማቴ 28:13) ይህን ሊያደርጉ የቻሉት የክርስቶስን ሙት ስጋ አምጥተው ከሞት አለመነሳቱን ማሳየት ባለመቻላቸው ነው። በዚህም ምክንያት የክርስቶስን ትንሣኤ መቀልበስ ሳይችሉ ቀርተዋል። ይህ እውነት ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በሐዋሪያትና በመጀመሪያዎቹ ተከታዮቻቸው ይታመን የነበር እምነት ሲሆን፥ ቀዳማዊ ከሆነው ከራሳቸው የሐዋርያት ጽሑፍ ሊረጋገጥ የሚችል ሀቅ ነው።

በእስልምና የሚታመነው ነገር እውነት ነው ከተባለ ግን አንድ ወሳኝ ጥያቄ ይነሳል። ይኸውም በእርግጥም የተሰቀለው በክርስቶስ ኢየሱስ የተመሰለ የኢየሱስ ጠላት ከሆነ፥ እንዴት አይሁዶቹ የእርሱን ሬሳ ማምጣት አቃታቸው? ሐዋሪያቱ ክርስቶስ ተነስቷል ብለው መስበክ ሲጀምሩ፥ አይሁዶቹ እንዴት ክርስቶስን እንዲመስል መልኩ የተቀየረውን ሬሳ ማምጣት ተሳናቸው? ያ ሰው ከሞት ተነስቶ ነበር እንዴ? ካልተነሳ እንዴት አይሁድ በእጃቸው የነበረውን ሬሳ ማምጣት ሳይችሉ ቀሩ?

♦️ አስተውሉ! አላህ ይህን የኢየሱስን ጠላት ኢየሱስን እንዲመስል ስላደረገው አይሁዶቹ የገደሉት ኢየሱስን ገደልን ብለው ነው። ቁርአንም ኢሳን ገደልነው አሉ ማለታቸውን ይመሰክራል (ሱራ 4:157) በተጨማሪም በእስልምና ውስጥ ይህ በክርስቶስ ፋንታ የተሰቀለው ሰው ከሞት ተነስቷል ተብሎ አይታመንም። ስለዚህ ሐዋሪያቱ ኢየሱስ ከሞት ተነስቷል ብለው ሲሰብኩ፥ እንዴት አይሁዶቹ ኢየሱስን እንዲመስል የተለወጠውን የዚያን ሰው ሬሳ ማምጣት ተሳናቸው? ከሞት ካልተነሳ፥ በሚታወቅ መቃብር ከተቀበረ፥ ተነስቷል ተብሎ ሲሰበክ እንዴት ሬሳውን ማምጣት አልቻሉም?

አይሁድ ለምን የዚያን ሰው ሬሳ ማምጣት እንዳልቻሉ #በማስረጃ መልሱ

2) አላህ ለምን ይህን እውነታ ለሐዋርያቱ አልገለጠላቸውም?

አላህ ይህን ሰው ሲያስገድል፥ መልኩ የኢየሱስን እንዲመስል አድርጎ ነው። በዚህም ምክንያት እርሱ ኢየሱስ አለመሆኑን ከአላህ በቀር አይሁዳውያኑም፥ ሮማውያኑም፥ ሐዋሪያቱም አላወቁም። ከአላህ በቀር ማንም ይህን አላወቀም።

ለሙግት ያህል አይሁዳውያኑ የአላህ መልእክተኛ የኢሳ ጠላቶች ስለሆኑ አታለላቸው ብንል እንኳ፥ ለምን ሐዋሪያቱን አታለላቸው? ለምን ያ ሰው ኢየሱስ አለመሆኑን አላሳወቃቸውም? ለምን እነሱም ተከታዮቻቸውም በስህተት "የተሰቀለው ኢየሱስ ነው" ሲሉ ዝም አለ?

በቁርአን መሰረት፥ ሐዋርያት ሙስሊሞች ናቸው (ሱራ 3:52) እስከ መጨረሻው ቀንም የበላይ እንደሚሆኑ አላህ ቃል ገብቶላቸዋል (ሱራ 3:55) አሸናፊ ይሆኑ ዘንድም አበረታታቸው ይላል (ሱራ 61:14) ታዲያ እንዴት ሊያታልላቸው ቻለ? ኢየሱስ አለመሆኑን ሳያሳውቃቸው፥ እነሱም ተከታዮቻቸውም በተሳሳተ እምነት እንዲሄዱ ለምን ፈቀደ? #በማስረጃ መልሱ

3) አይሁዶች ሊሰቅሉት ሲመጡ፥ ለምን "እኔ ኢየሱስን አይደለሁም" ብሎ አልተቃወመም?

እነዚህ ተንታኞች እንደሚሉት፥ የኢየሱስ ተቃዋሚ የሆነ አይሁዳዊ ከሆነ በኢየሱስ ቦታ መልኩ ተቀይሮ የተሰቀለው፥ አይሁዶች ሊሰቅሉት ሲመጡ ለምን "እኔ ኢየሱስን አይደለሁም" ብሎ አልተቃወመም? ለምን ያለ ምንም ተቃውሞ ተሰቀለ?

♦️ አስተውሉ! ይህ ሰው ክርስቶስን ሲቃወም፥ ሲሳደብ የነበር ሰው ነው። አሁን ባላወቀው ሁኔታ፥ የራሱ ወገን የሆኑት አይሁዳውያን "አንተ ኢየሱስ ነህ" ብለው ሲይዙትና ሲሰቅሉት፥ ያለ ምንም ተቃውሞ ዝም ብሎ ተገደለ? ይህ አዕምሮ ሊቀበለው የሚችለው ነገር ነው? ያ ሰው "እኔ ኢየሱስ አይደለሁም" ብሎ ሳይቃወም እንዴት ሊሰቀል እንደቻለ #በማስረጃ መልሱ

ለእነዚህ ጥያቄዎች በማስረጃ የተደገፈ አመክንዮአዊ መልስ እስካልተሰጠ ድረስ "ኢየሱስ አልተሰቀለም" የሚለው እስላማዊ ትርክት በይበልጥ አጣብቂኝ ውስጥ ይገባል። ሀሰተኝነቱም እየተጋለጠ ይመጣል

መደምደሚያ

የብሉይ ኪዳን ነቢያት ሆነ የአዲስ ኪዳን ሐዋርያት፥ የክርስቶስን ስቅለት ተናግረዋል። ከ600 አመት በኋላ፥ በሌላ ሀገር የኖረ፥ ሌላ ቋንቋ የተናገረ፥ የክርስቶስ አይን እማኞችን የማያውቅ፥ እርሱን የሚደግፍ ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የሆነ ቀዳማዊ ምንጭ (primary source) የሌለው ሰው "አልተሰቀለም" ቢል ምንም አይነት ተቀባይነት የለውም።

በዚህም ምክንያት ትርክቱ፥ ሊመለሱ የማይችሉ ጥያቄዎች ይነሱበታል። እውነታው ግን ግልፅ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሏል፥ ሞቷል። ሞቶ ግን አልቀረም፥ ተነሥቷል። ይህ ዘላለማዊ ሀቅ ነው

" #ኢየሱስ እንደ #ሞተና እንደ #ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።"
(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4:14)

ጌታ ይርዳን!
Forwarded from Obadiah Apologetics
🐋መሬትን ተሸካሚው ፍጡር🐋
("አል-ኑን/النون")

በእስልምናው አስተምህሮት ውስጥ አፈታሪካዊ እና ተረታዊ ከሆኑት ታሪኮች መካከል አንደኛው ግዙፉ እስላማዊው አሳ ነባሪ ( الحوت الإسلامي ፣ አል-ሁት አል-ኢስላሚ) ይሄም ፍጡር ምድርን በጀርባው እንደሚሸከም የተገለጸለት አፈታሪካዊው ፍጡር ነው፡፡ ታዳ ይሄ እስላማዊው አውሬ/አሳነባሪ(አል-ሁት/ٱلْحُوتِ) በቁርአን ላይ "ምድር ተሸካሚ አሳ" ወይም "አል-ኑን/النون" ተብሎ ተጠርቷል። ቁርአኑ ስለዚህ ፍጡር ግልጽ በሆነ ሁኔታ አላስቀመጠልንም። በዚህም ምክንያት በአንዳንድ የሙስሊም ሊቃውንቶች መካከል እስካሁኑ ሰአት ድረስ ያልተፈታ ትልቅ ንትርክን የፈጠረ ለዘመናዊው ሳይንስ ጥናቶች እንግዳና አጠያያቂ የሆነ ጉዳይ ነው። እኔም ስለዚህ ፍጡር ጉዳይ በስፋት በመመልከት አንዳንድ እስላማዊ ጽሁፎችን ማለትም ሐዲሳትን እና የተለዩ ተፍሲራትን እያገላበጥን ለማሳየት ቀርቤያለሁ።

🔍ከላይ በጨረፍታ ለመመልከት እደሞከርነው "አል-ኑን/النون" በውሀ ውስጥ ከሚኖሩ የአሳ ዝርያዎች መካከል አንዱ ነው። በቁርአን በሱረቱል አል-ቀለመ በአንደኛው አያት ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። ይሄንን አያት በእስልምናው ማህበረሰብ ውስጥ እጅጉን እውቅና ካላቸው የቁርአን ተፍሲሮች (ኢብን-ከሲር፣ አል-ቁርጡቢ፣ ጃለለይን እና አት-ጠበሪ) እንደሚያስረዱን ከሆነ "ኑን" የሚባለው ግዙፍ አሳ ነባሪ እንደሆነና ምድርን የተሸከመ ፍጡር እንደሆነ ይነግሩናል።

አል-ቀለም 68:1
نٓۚ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ
ነ.( #ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡

ኢብን ከሲር አል-ቀለም 68:1 ተፍሲር፦
ታላቁ ሙፈሲር ኢብን ከሲር በተፍሲሩ ላይ ስለ ኑን ሲናገር፦ አላህ ‹ #ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ምድር #በኑን ጀርባ ላይ እንደዘረጋ ይናገራል፡፡ ከዛም ተረቱ ይቀጥላል #ኑን የሚባለው ፍጡር ደነበረ ወይም ተረበሸ ይለናል። በዚህ መሀል ምድር ማረግረግ ወይም መንቀጥቀጥ ጀመረች። አላህ ለዚህ ችግር ሲል ተራሮችን ፈጠረ። እነዚህም ተራሮች ምድር እንዳትነቃነቅ እንደ ችካል ቸከላቸው ይለናል። እንደውም በቁርአን 78:7 ላይ "...ጋራዎችንም(ተራሮችን) ችካሎች አላደረግንምን(وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادًا)?)..." አላህ ተራሮችን የቸከላቸው የመሬትን መንቀጥቀጥ ለማስተካከል እንደሆነ ተፍሲራት ይነግሩናል(ጃላለይን, ኢብን ከሲር ተፍሲር)። ምን ይሄ ብቻ አሁም አፈታሪካዊ ተረቱ አላበቃም አል ባግሃዊ እና ሌሎች የሙስሊም ሙህራኖች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት #ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ #ሰባቱ_መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል ብለው ያስባሉ። እስቲ ይሄን ታሪክ ከኢማም ኢብን ከሲር ተፍሲር በተወሰነ መልኩ እንመልከት፦

"...ከዚያም አላህ ‹ #ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ሰማይ የተፈጠረበት ጭስ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ከዚያም ምድር #በኑን ጀርባ ላይ ተዘረጋች፡፡ ከዚያም ኑን ስለደነበረ ምድር ማረግረግ ጀመረች፤ ነገር ግን (አላህ) ምድርን እንዳትንቀሳቀስ አድርጎ በተራሮች ቸከላት…

"ኢብን አቡ ኑጃኢህ እንደተናገረው ኢብን አቡ በኪር በሙጃሂድ እንዲህ ተብሎ ተነግሮት ነበር፣ “ኑን ከሰባቱ መሬቶች በታች የሚገኝ ታላቁ አሣ እንደሆነ ይነገራል፡፡” በተጨማሪም አል ባግሃዊ (አላህ ነፍሱን ያሳርፋትና) እንዲሁም ሌሎች ሐታቾች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል፡፡..."[1]

#ኑን ለሚለው ቃል ትርጓሜ ሲያስቀምጥ ደግሞ "...ኑን የሚባለው ትልቅ አሳነባሪ ነው(Nun is a big whale/نۤ حوت عظيم)..." በማለት ኢብን ከሲር ትንታኔውን አስቀምጧል።[2]

አል-ቁርጡቢ ተፍሲር 68:1 
نۤ> الحوت الذي تحت الأرض السابعة>
"...<ኑን>ከሰባተኛው(السابعة) መሬት(الأرض) በታች(تحت) የሚገኘው አሳ ነባሪ(الحوت) ነው...."[3]
በአል-ቁርጡቢ ተፍሲር መሰረት " #ኑን" የሚባለው ከሰባተኛው መሬት በታች የሚገኝ አሳ ነባሪ እንደሆነ ይነግረናል። ልብ በሉ "...ከሰባተኛው(السابعة)..." ሰባት ምድር እንዳለም ከላይ በኢብን ከሲር ተፍሲር ላይ ተመልክተናል። እነርሱም ተደራራቢ እንደሆኑ "ታሐት(تحت)" ወይም "ከታች/ከስር" የሚለው ቃል ያስረዳናል።

♦️ተፍሲር አት-ጠበሪ 68:1
አት-ጠበሪ በሱረቱል አል-ቀለም 68:1 ላይ ማብራሪያ ሲያስቀምጥ እንዲህ ብሏል፦
"...هو الحوت الذي عليه الأرَضُون..."
"...ሰባቱ ምድሮች የተቀመጡበት ፍጡር አሳ ነባሪ(الحوت) ነው..."[4]

በእስልምናው ኮስሞሎጂ መሰረት አላህ ሰባት ሰማያትን እንደፈጠረ ሁሉ ሰባት ምድሮችንም ፈጥሯል(Quran 65:12)።
እነዚህም ጠፍጣፋ ምድሮች በአሳ ነባሪው ላይ ተደራርበው ተቀምጠው እንደሚገኙ ጥንታዊ የሙስሊም ሊቃውቶች ይነግሩናል።

♦️ተፍሲር አል-ከቢር(አር-ረዚ)/tefsir Al kabir(by Ar-Razi)፦

"...بالحوت الذي على ظهره الأرض وهو في بحر تحت الأرض السفلى..."

በዚህም ተፍሲር ላይ በጀርባው ምድር የሚሸከመው ዓሳ ነባሪ እንሆነና
አል-ከቢር እዚህ ዓሳ ነባሪ ጀርባ ላይ ሚዛናዊ የሆኑ ጠፍጣፋ መሬቶች እንዳሉ ይነግረናል፡፡[5]

ተፍሲር አል-ቃዲር/ِTafsir Al-Qadir (by Shawkani)

ይህ ተፍሲር ከ 18 ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ዓለም ዓሳ ነባሪ ጀርባ ላይ ተሸክሟል የሚል ሀሳብን በመደገፍ ያረጋግጣል።
"....هو الحوت الذي يحمل الأرض..."
"....ምድርን የተሸከመው ፍጡር አሳ ነባሪ/الحوت ነው....."/Fath Al-Qadir on 68:1______[6]

ሐዲስ ከኢብን አባስ (ቱርጁማን ኡል-ቁርአን/ترجمان القرآن)
(ሐዲስ ከአት-ጠበሪ)

ኢብን አባስ እንደተናገረው፦አላህ የፈጠረው የመጀመሪያ ነገር ብእርን ስለነበረ “ጻፍ!” አለው፡፡ እናም እስከ ሰዓቱ (የፍርድ ቀን) ድረስ ምን እንደሚሆን ጽፏል፤ ከዚያም #ኑንን_ከውሃ_በላይ #ፈጠረ ከዚያም ምድርን በእርሱም ላይ ተጫነች፡፡(ታሪኽ አት-ታባሪ) [7]

ይህም ሀዲስ(ትረካ) በሀዲሳት ሰንሰለት #ትክክለኛ(ሰሒህ/صحيح) ትረካ ተደርጎ ተቆጥሯል፡፡[7] መሐመድ ለኢብን አባስ ዱዓ (ጸሎት) ስላደረገ አላህም የቁርአንን ትክክለኛ አተረጓጎም ያስተምረው ነበር፡፡እንዲሁም ኢብን አባስ (ቱርጁማን ኡል-ቁርአን/ترجمان القرآن) “የቁርአን ተርጓሚ” ተብሎ ተጠርቷል ፣ ምክንያቱም ስለ ራእዮች ትርጓሜ (ቃል በቃል መተርጎም) የሚሰጥና ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው ነበር።

ኢብኑ ዐባስ (ራአ) እንደተናገሩት፦
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) አቅፈውኝ “አሏህ ሆይ! የመጽሐፉን (ቁርአን) እውቀት አስተምሩት ፡፡ ”(ሳሂህ ቡኻሪ 9:92:375)
Forwarded from Obadiah Apologetics
ታዳ ይህ በቁርአን ጥልቅ እውቀት ያለው አሊም ተራራዎቹ በቁርአን ውስጥ እንደ ችካል እንዴት እንደተደረጉ የእርሱ ትረካ ያስረዳል፡፡ ምክንያቱም በባህላዊው እስላማዊ የኮስሞሎጂ መሠረት ምድር ከዓሣ ነባሪው ጀርባ ላይ ትነቃነቅ (ትንቀጠቀጥ) ስለነበረ አላህ ምድርን ዓሣ ነባሪው ላይ ተረጋግታ እንድትቀመጥ ተራሮችን እንደ ችካል እንዳደረጋቸው በግልጽ ሁኔታ ተርኮልናል፡፡
📌በመጨረሻም ከዚህ ሁሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች የምንረዳው ነገር ቢኖር አላህ ሰባት መሬቶችን ፈጥሮ በአሳ ነባሪው("አል-ኑን/النون" ) ጀርባ ላይ ደራረቦ በማስቀመጥ ከዛም አሳ ነባሪው("አል-ኑን/النون" ) ሲደነብር መሬት እዳትነቃነቅ በተራሮች በመቸከል እንድትረጋጋ አድርጓል። ይባስ ብሎም በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል ብለው በማሰብ ይህ ለሳይንስና ለእውነታ ሆድና ጀርባ የሆነን ነገር ከአንዳንድ የመሰለኝን ልናደርግ ከሚሉ ፈላስፋዎች ቀጥታም ሆነ ተጨማምሮበት የተቀዳ አፈታሪክን የአምላክ መገለጥ ነው ብሎ መቀበል በጣም ሞኝነት ነው። አንዳንድ የዘመኔ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ስኮላሮችና ዳኢዎች ይሄ ነገር አልዋጥ ሲላቸው የውሸት የትረካ ሰነድ ወይም አምላካዊ ንግግር የሆነ ሀሳብ አይደለም ይሉናል።[8] ነገር ግን አይኑ የፈጠጠ በድሮ ዘመን በነበሩት የእስልምና ሊቃውንቶች መካከል ተቀባይነትን ያተረፈ ታሪክ እንደሆነ ከተፍሲራትና ከሐዲስ ለመመልከት ችለናል። ይሄን የመሰለ ተረትና አፈታሪክ ታቅፈው ነው እነ ዶክተር ዛኪር ናይክና ቢጤዎቹ ቁርአን ከሳይንስ ጋር አይጣረስም የሚሉን። በመሰናበቻዬም አንድ ነገር ተናግሬ ልደምድም፦ እውነት ቁርአን የፈጣሪ ንግግር ነውንከሆነስ ለምን ከሐቅና ከሳይንስ ጋር ላይስማማ ሊጣረስ ቻለእውነትን ፈልጉ እውነትም አርነት ያወጣችኋል። ተባረኩ🙏

🔖ማጣቀሻዎችና ማስፈንጠሪያዎች
[1] Tafseer Ibn Katheer;Online Edition:http://quran.al-islam.com/Tafseer/DispTafsser.asp?l=arb&taf=KATHEER&nType=1&nSora=68&nAya=1
[2] altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=7&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1
[3] http://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=5&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1
[4]  http://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=1&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1
[5]  http://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=4&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1
[6] http://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=9&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1
[7]  http://hdith.com/?s=%D8%AB%D9%85+%D8%AE%D9%84%D9%82+%D8%A7%D9%84%D9%86%D9%88%D9%86+%D9%81%D9%88%D9%82+%D8%A7%D9%84%D9%85%D8%A7%D8%A1%D8%8C+%D8%AB%D9%85+%D9%83%D8%A8%D8%B3+%D8%A7%D9%84%D8%A3%D8%B1%D8%B6+%D8%B9%D9%84%D9%8A%D9%87
[8]  https://islamqa.info/en/114861

Jonathan (جوناثان)
Forwarded from Obadiah Apologetics
ኡስወቱን ሀሰነ/أُسْوَةٌ حَسَنَة

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ነብያቸው መሐመድ ከሚጠራባቸው ስሞች መካከል <<"ኡስወቱን ሀሰነ/أُسْوَةٌ حَسَنَة">> ማለትም ጥሩ ስነምግባር ያለው ወይም ደግሞ ለሌሎች በባህሪው አርአያ ሊሆን የሚችል ሰው በመባል የሚታወቅ ግለሰብ ነበር። በቁርአኑ "ረኡፍ/رَءُوف" ሩህሩህ ወይም ደግሞ "ረሒም/رَّحِيمٌ" አዛኝ በማለት ይጠራዋል።
አት-ተውባህ 9:128
لَقَدْ جَآءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِٱلْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ
ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) #ርኅሩኅ #አዛኝ_የኾነ_መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡

ከእስምና እምነት አሉ ከሚሏቸው ነብያቶች መካከል እጅጉን ከፍ ያለ ከበሬታ ያገኘው ነብይ ሙሐመድ ነው። እንደእርሱ ክብር ያገኘ ነብይ ያለ አይመስለኝም ኧረ እንደውም አምላካቸውን "አሏህ" እንደሱ ከበሬታ አላገኘም። ሰሞኑን በሙስሊም ማህበረሰብ ያልበረደውን ቁጣ የሚዘነጋ አይደለም። "ነብዩ/ሐቢቢ" ለምን ተነኩ ብለው የፈረንሳዩን መሪ ማብጠልጠል ከማብጠልጠላቸውም አልፎ ከሀገረ ፈረንሳይ የሆኑ ምርቶች ወደ ሀገራችን አይገባም በማለት ማመጻቸው አላቆሙም። እንደውም በሀገረ ፓኪስታን እና በአንዳንድ ቦታዎች "በነብዩ ላይ ለሚቀልዱ ሰዎች ምህረት አይገባም" በማለት መዛታቸውን ተያይዘውታል። ቆይ እስቲ መሀመድ ተብዬው ነብይ አላህ ረኡፍ/رَءُوف" #ሩህሩህ እና "ረሒም/رَّحِيمٌ" አዛኝ ካለው እና እውነት ይሄም እርሱን የሚገልጽ እውነተኛ ምግባሩ ከሆነ ታዳ ለምን የእርን ፈለግ ሙስሊሞች አልተከተሉትም??? ለምን እነሱም ለሰዎች መልካም ቸር ደግ አሳቢ አልሆኑም???ምክንያቱም #ሱና ስለሆነ ማለቴ ነው። ነገር ግን ስለዚህ ነገር አንድ ጥያቄ መጠየቅ ይኖርብናል፦

<< #በውኑ_ኡስወቱን_ሐሰነ_መሀመድን #ይገልጸዋል>>

መጠየቅ የሚገባው ትክክለኛ ጥያቄ!!!በእውነት መሀመድ ለተከታዮቹ ጥሩ ስነምግባር ያለው ወይም ደግሞ ለሌሎች በባህሪው አርአያ ሊሆን የሚችል ቢሆን ተከታዮቹ የእርሱን ፈለግ በተከተሉ ነበር። በእርግጥ የእርሱን ስራ አሁንም እየተከተሉ ነው። የመሀመድን እና የተከታዮቹን ትክክለኛ ባህሪ ሐዲሳቱን እና ሱናቸው ምን እንደሚመስል መመልከት ይኖርብናል። የመሀመድ ባህሪያት በሐዲሳቱ ሲመረመር፦

#መሀመድ_እና_ዝሙት
አንድ ቀን መሀመድ ወደ ሚስቶቹ ተራ በተራ ይሄድ ነበርና እርሱም ወደ ሀፍሷ ቤት መጣ ሐፍዛ አባቷን ልታይ ሄዳለችና አጣት። ከዛም መሀመድ የሀፍሷ ገረድ የሆነችውን ግብጻዊት ማርያምን አስጠራና በሐፍሷ መኝታ ላይ ከእርሷም ጋር አንሶላ ተጋፈፈ(had intercourse) ሐፍሷም በመጣች ጊዜ ባየችው ነገር በጣም አዘነች። መሀመድም ከአሁን በኋላ ለኔ እርም(የተከለከለች) ነች አላት። ከዛም ለማን እዳትናገር አዘዛት። ከዛም አላህ ወሒይን አት-ተህሪም 66፥1 አወረደለት ይለናል። [ተፍሲር ኢብን ከሲር እና ጃለለይን]
At-Tahrim 66:1

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَۖ تَبْتَغِى مَرْضَاتَ أَزْوَٰجِكَۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ #የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትኾን (ባንተ ላይ) ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህም እጅግ #መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

ተመልከቱ ይሄ ሐቀኛ ታማኝ (أَلْصَّدِيق አስ-ሰዲቅ,33:22) ጻድቅ ተብዬ ነብይ ህጋዊ ባለቤቱ በሌለችበት ጊዜ ከገረዷ ጋር መዘሞት ምን የሚሉት ስነምግባር ነው?
👉በተጨማሪም Sunan an-Nasa'i ሐዲስ ቁጥር 3411 ይመልከቱ፦
أَخْبَرَنِي إِبْرَاهِيمُ بْنُ يُونُسَ بْنِ مُحَمَّدٍ، حَرَمِيٌّ - هُوَ لَقَبُهُ - قَالَ حَدَّثَنَا أَبِي قَالَ، حَدَّثَنَا حَمَّادُ بْنُ سَلَمَةَ، عَنْ ثَابِتٍ، عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَتْ لَهُ أَمَةٌ يَطَؤُهَا فَلَمْ تَزَلْ بِهِ عَائِشَةُ وَحَفْصَةُ حَتَّى حَرَّمَهَا عَلَى نَفْسِهِ فَأَنْزَلَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ ‏}‏ إِلَى آخِرِ الآيَةِ ‏.‏

It was narrated from Anas, that the Messengerof Allah had a female slave with whom #he_had_intercourse, but 'Aishah and Hafsah would not leave him alone until he said that she was forbidden for him. #Then_Allah, the Mighty and Sublime, #revealed:

"O Prophet! Why do you forbid (for yourself) that which Allah has allowed to you.' until the end of the Verse.

#Sahih (Darussalam)
Sunan an-Nasa'i 3959
In-book : Book 36, Hadith 21
English translation : Vol. 4, Book 36, Hadith 3411
Sunan an-Nasai
#መሀመድ_እና_አታላይነቱ
መሀመድ እና ከድጃን ለበጋባት የዘየዱት ሴራ ከአንድ በባህሪው ምስጉን(አህመድ) ከተባለ ነብይ ቀርቶ ከአንድ ሰብአዊነት ካለው ተራ ሰው የሚጠበቅ ተግባር አልነበረም። ከድጃ አባት ስለመሀመድ ሊድራት አልፈለጉም ነበር። ምክንያቱም መሀመድ የቲም(ወላጅ አልባ)ነበርና አባቷ ለእንደዚህ አይነት ሰው ጋር በአማችነት መተሳሰር አይፈልጉም ነበር። ስለዚህ መሀመድ እና ከድጃ ተመካክረው አነስተኛ ድግስ ነገር ጥቂት ምግብ እና መጠጥ አዘጋጅተው የተወሰኑ የቁረይሽ ሰዎችን ጠራች አባቷና ሰዎቹ በልተው እስኪሰክሩ ድረስ ደግሞ ጠጡ፡፡ ከዛም ከድጃ ለአባቷ "መሐመድ ቢን አብደላህ ሊያገባኝ ይፈልጋል ለእርሱ ስጠኝ (ዳረኝ)" አለችው። አባቷም በስካር መንፈስ ነበርና በስካር ለየቲሙ ነብይ ለጋብቻ ሰጣት፡፡ እርሷም አባቷንም ሀላል ልብስ ማለትም የጋብቻ ልብስ አልብሳ ነበርና ከስካሩ ሲያገግም ተመለከተና ሽቶ ተቀብቶ እና የሀላላ ልብስ ለብሶ ተመለከተ፡፡ እርሱም "ምን ነካኝ?" ይሄ ምንድን ነው? አላት እርሷም ለመሐመድ ቢን አብደላህ በጋብቻ ሰጠኸኝ ፡፡ እርሱም "ከአቡ ጣሊብ ወላጅ አልባ አባት ጋር ለጋብቻ ሰጥቻለሁን?! ምንም ሁኔታ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም!" አላት ከዲጃህ አለች "በቁረይሽ ፊት ሞኝ መስለህ ለህዝቦችህ እንደ ሰከርክ መንገር አታፍርም?" ብላ ከሀቀኛ እና በምግባሩ ለሌሎች አርአያ ነው ከሚባለው ነብይ ጋር እንደዚህ አይነት ወንጀል መፈጸም ምን የሚሉት ተግባር ነው!??? ተግባሩና እና ስሞቹ የማይገጣጠሙለት ነብይ፦
ሙስናድ አህመድ ጁዙዕ 1 ገፅ 312 ክፍል 2846 ላይ ይገኛል ::
Forwarded from Obadiah Apologetics
2846 حدثنا أبو كامل حدثنا حماد بن سلمة عن عمار بن أبى عمار عن ابن عباس فيما يحسب حماد أن رسول الله صلى الله عليه وسلم ذكر خديجة وكان أبوها يرغب أن يزوجه فصنعت طعاما وشرابا فدعت أباها وزمرا من قريش فطعموا وشربوا حتى ثملوا فقالت خديجة لأبيها إن محمد بن عبد الله يخطبني فزوجني إياه فزوجها إياه فخلعته وألبسته حلة وكذلك كانوا يفعلون بالآباء فلما سري عنه سكره نظر فإذا هو مخلق وعليه حلة فقال ما شأني ما هذا قالت زوجتني محمد بن عبد الله قال أنا أزوج يتيم أبي طالب لا لعمري فقالت خديجة أما تستحي تريد أن تسفه نفسك عند قريش تخبر الناس أنك كنت سكران فلم تزل به حتى رضي حدثنا عفان حدثنا حماد قال أخبرنا عمار بن أبي عمار عن ابن عباس فيما يحسب أن رسول الله صلى الله عليه وسلم ذكر خديجة بنت خويلد فذكر معناه

#መሀመድ_እና_የአክራሪ_ጽንፈኝነት #ጭፍጨፋ

የእስልምና አክራሪ ቡድኖች የነብዩን ሱና በመከተል አንዳንድ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን እየፈጸሙ ይገኛሉ። እንደውም አንዳንዶቹ ተግባሮቻቸውን ከሀዲሳት፣ ከቁርአን እና ከሲራዎች በማጣቀስ የነቢዩን ተግባራት ከድርጊቶቻቸው ጋር እያጋመዱ ትክክለኝነታቸውን ለማሳየት ይሚናገሩም አልጠፉም። የሚማርኳቸውን የጠላቶቻቸውን ወታደሮችን፣ ሲቪሎችን እና እና ዲነል ኢስላምን ያልተቀበሉ ማህበረሰቦችን በማሰር ከዛም አልፎ ተርፎም የእስረኞች ግድያ ቪዲዮን በማዘጋጀት ለብዙሃን ሀይላቸውን ያሳያሉ፡፡ ይሄ ተግባራቸው ዝም ብሎ የመነጨ አልያም ከመሬት ተነስተው የፈጸመው ተግባር ይመስላችኋል??? አይደለም በሙስሊም ማህበረሰቡ ዘንድ "ሐቢቢ" ተብሎ የሚጠራውም ነብይ በዘመኑ እንዲሁ አድርጎ አልፈዋል። በነብዩ መሀመድ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ቁጥራቸው ከ 800 እስከ 900 የሚሆኑ አይሁዳውያን መሀመድ ነፍሰ በላዎችን ወደ እነርሱ ልኮ በተቆፈረ ቦይ ውስጥ አንገታቸውን እንዲቆርጡ ያደረገ ግለሰብ ነው፡፡
📌ኢብን ኢሳቅ 464

🔖ኢብን ኢሳቅ ሐዲስ በሐዲሳት ጥናት ዘገባ ሰንሰለት ጥሩ(ሐሰን) የሚባል ነው(see M. R. Ahmad (1992). Al-sīra al-nabawiyya fī dhawʾ al-maṣādir al-aṣliyya: dirāsa taḥlīlīyya (1st ed.). Riyadh: King Saud University.)

ታዳ እኚህ ነብይ ተግባራቸው እና ስማቸው ለምን ተለያየ??<<#በውኑ_ኡስወቱን_ሐሰነ_መሀመድን #ይገልጸዋል>> የኛ ጥያቄ ነው በክፍል ሁለት የመሀመድን በሴቶች ላይና በግድያ ላይ ያላቸውን አቋም ለመዳሰስ እንሞክራለን እስከዛው ቸር ሰንብቱ🙏

Jonathan (جوناثان)