እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
8.72K subscribers
121 photos
16 videos
40 files
403 links
“እውነት ለሁሉ” በዓለም ዙርያ በሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ክርስቲያኖች የተመሠረተ ድረ-ገፅ ሲሆን እስልምናንና ክርስትናን የተመለከቱ መጣጥፎችን፣ መጻሕፍትን፣ ዜናዎችንና የመሳሰሉትን ያስነብባል፡፡ የኦዲዮና የቪድዮ መረጃዎችንም ያቀርባል፡፡ የበለጠ ለማወቅ http://www.ewnetlehulu.org ይጎብኙ።
Download Telegram
እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
https://vm.tiktok.com/ZMhBb3tPT/
🚩 ሐዋርያው ጳውሎስ እንደ እስልምና አስተምህሮ ሀሰተኛ ሐዋርያና አሳች ሳይሆን ትክክለኛ የአላህ መልእክተኛ መሆኑ እንደሚታመን ለመዳሰስ ሞክረናል (ክፍል 3)

Share!
እየሱስ እንዴት ከመጥምቁ ዮሐንስ ቀድሞ Exist አደረገ?

ዮሃ 1:30
አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ #ከእኔም #በፊት #ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።

#ነበር የሚለው የግሪክ ቃል፣ "ኤን" የሚልው imperfect verb ሲሆን፣ Aspectቱ ያልተገደበ Continuous past existence የሚገልፅ ነው።

አሁን፣ ከኢየሱስ በፊት ዮሃንስ ቀድሞ ተወልዶ ሳለ፣ እንዴት እየሱስ ከሱ ቀድሞ ነበር ተባለለት?

መልስህ፣ አይ፣ በአምላክ አእምሮ ውስጥ እንጂ በገሃድ አይደለም ካልክ፣ ጥያቄው የሚሆነው፣ በአምላክ አእምሮ ውስጥ አንዱ ከሌላው ቀድሞ ይታወቃል እንዴ? አምላክ ስለ እየሱስ አስቀድሞ አውቆ፣ ስለ ዮሃንስ ያላወቀበት ጊዜ ነበር እንዴ? ይህ ማለት፣ አምላክ ሁልጊዜም ሁሉን አዋቂ አልነበረም ብሎ የሚያምን ሰው የሚያመጣው ትርጉም ስለሆነ ደካማ ሙግት ነው።

Unless of course, the Son of God LITERALLY existed from eternity 🙂
የድረ-ገጻችን አምደኛ የሆነው ወንድም ሚናስ ሌላ አዲስ ጽሑፍ ይዞልን መጥቷል። ይህንን ግሩም ጽሑፍ ለማንበብ አስፈንጣሪውን ይከተሉ https://ewnetlehulu.net/carmen-christi/
አራት ዓይነት አፈጣጠር? በሚል ርዕስ የተጻፈውን ይህንን አዲስ ጽሑፍ ያንብቡ። የኢየሱስን ከድንግል መወለድ እንደ አራተኛ የሰው አፈጣጠር መንገድ ለሚቆጥሩት ሙስሊሞች የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ ነው https://ewnetlehulu.net/four-creation/
ኢትዮጵያን የአረብ ሊግ አባል የማድረግ እንቅስቃሴ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዕድገት ፋይዳ የሌለው በአንጻሩ ግን ጎጂ የሆነ እንቅስቃሴ ነው። ሊጉ ሃይማኖታዊ እንጂ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዓላማ የሌለው ከንቱ ስብስብ ነው። የሊጉ አባል ሀገራት ምን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አገኙ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ምንም የሚል ነው። በፖለቲካውም ረገድ አባል ሀገራቱን ከመበታተን አልታደገም። ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ሶርያ፣ የመን፣ ሊብያ እና ኢራቅ አባላት በመሆናቸው ምን አተረፉ? በሊጉ ስር የተጠለሉት የእርዳታ ድርጅቶች በብዙ ሀገራት ይንቀሳቀሳሉ። መስጊዶችንና መድረሳዎችን ከማስገንባት የዘለለ ለሰው ልጆች የሚጠቅም ምን የረባ የልማት ሥራ ሠርተው ያውቃሉ? አባላቱን ለመቀላቀል በመንግሥት እየተሰጠ ያለው ሰበብ የግብፅን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያስችላል የሚል ነው። ነገር ግን አዋጭነቱ ምን ያህል ነው? ጉዳቶቹስ ታስበውባቸዋል ወይ? ብሎ መጠየቅ አስተዋይነት ነው። ግብፅ ከምዕራባውያን የምትቀበላቸውን አጀንዳዎች በአረብ ሀገራት ላይ የምትጭነው በዚህ ሊግ አማካይነት መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ሌሎቹ ሀገራት የሊጉ አባላት መሆናቸው የግብፅ ተገዢ ካደረጋቸው አባል መሆን ኢትዮጵያን ሰተት አድርጎ የግብፅ ብብት ስር የሚከት እርምጃ ላለመሆኑ ምን ዋስትና አለ? የግብፅን ጫና ለመቋቋም አዋጭ የሆነው መንገድ ሌሎች ሀገራትን ጠቅልሎ የግብፅ ተገዢ ያደረገ ማሕበር ውስጥ መግባት ሳይሆን የውስጥ አንድነት ማስጠበቅና በኢኮኖሚም ሆነ በፖለቲካ ረገድ የሀገራችንን ፍላጎት ከሚጋሩ ሀገራት ጋር የጋራ ሕብረት መፍጠር ነው። ግብፅ ሁል ጊዜ እኛን አጀንዳ አድርጋ በሊጉ ስብሰባዎች ላይ ማቅረቧ ሊጉን ለመቀላቀል በቂ ሰበብ አይሆንም። የግብፅን ክስና ሀሜት መስማት ካስፈለገ የግድ አባል መሆን አይጠበቅም። ሕንድን የመሳሰሉት ሀገራት በታዛቢነት እንደሚገኙት ሁሉ ታዛቢ ሆኖ መቅረብ ይቻላል። አረቦችና የአረብ ባሕል እንዳላቸው የሚያስቡ ሀገራት የፈጠሩት ማሕበር አባል መሆን አረባዊ ላልሆነችና አብዛኛው ሕዝብ ክርስቲያን ለሆነባት ሀገር ጠቃሚ አይደለም። ይሁን ከተባለም መዘዙ ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ውሳኔ እንጂ የጥቂት ፖለቲከኞችና የጥቂት ሙስሊም መሪዎች ውሳኔ ሊሆን አይገባውም።
የሶርያ ዋና ከተማ ደማስቆ በአማፅያን እጅ ገብታለች። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በሽር አል-አሳድ ዋና ከተማውን ለቀው ወደ ኢራን ሄደው ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለ። ነገር ግን የተሳፈሩበት ጀት እዚያው ሶርያ ውስጥ ሁምስ አካባቢ አርፎ ሊሆን ይችላል ምናልባትም ተከስክሶ ሊሆን ይችላል የሚሉ መረጃዎችም እየተሰሙ ነው። ለሶርያ ክርስቲያኖች እንጸልይ። የአሳድ መንግሥት አምባገነን ቢሆንም ለክርስቲያኖች ደህንነት የተሻለ ጥበቃ ያደርግ ነበረ። አማፂያኑ የፖለቲካ ታጋዮችና የሽብርተኞች ድብልቅ ናቸው። ምዕራባውያንና የእስራኤል መንግሥት ለገዛ ጥቅማቸው እንጂ ለክርስቲያኖች ምንም ግድ የላቸውም። ከ2003 በፊት በኢራቅ አገር ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ክርስቲያኖች ነበሩ፣ ነገር ግን ይህ አሃዝ በአሁኑ ጊዜ ከ150,000 በታች መውረዱ ይነገራል። ከ 2013 ጀምሮ ከ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑ የኢራቅ ክርስቲያኖች አገሪቱን ለቀው ተሰደዋል።
በሀገር ውስጥና በውጪ ያላችሁ አገልግሎታችንን መደገፍ ለምትፈልጉ ወገኖች በብዙ አማራጮች የቀረበ የድጋፍ ማሰባሰብያ ገጽ ነው። ጎራ ብላችሁ እግዚአብሔር በረዳችሁ መጠን ደግፉን። ምስጋናችን ከልብ ነው! https:santimfundme.com/campaigns/8d340f3d6454-94752dcba126
I just saw some of you asking me about the letter 360 of St. Basil, specifically on invocation of saints

That letter, including letters after that 361,362,..of Basil are spurious. They are forgeries. Even the catholics know this and admit it.

Back when I was looking at EO theology, I came across that letter and thought it is a big claim by Basil until I found out it is certainly spurious which someone forged after the 7th ecumenical council. Both internal and external evidences are against Basil's authorship.
የዐዲስ ኪዳን ቀኖና ተኣማኒነት በሚል ርዕስ በወንድማችን ሚናስ የተጻፈ ጽሑፍ በዌብሳይታችን ላይ ተለቋል። ያንብቡት ለሌሎችም ያጋሩ https://ewnetlehulu.net/nt-canon-p-1/
ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሑር ስርግው ሀብለ ሥላሴ በጻፉት ታሪክ መሠረት በኡሑድ ጦርነት ላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከመካ ተዋጊዎች ጎን ተሰልፈው ሙሐመድና ወታደሮቹን ተዋግተዋል። በዚህ ውጊያ ሙስሊሞች ክፉኛ የተሸነፉ ሲሆን ሙሐመድ ራሱ ቆስሎ ሁለት የፊት ጥርሶቹ ረግፈዋል (Sergew Hable Selassie, Ancient and Medieval Ethiopian History to 1270, p. 188.)። የእስልምና ውድቀትና የካዕባ መፍረስ በኢትዮጵያውያን እጅ እንደሚከናወን ሙሐመድ በትንቢት መልኩ ተናግሯል። ይህ በአረብ ሙስሊሞች ዘንድ ኢትዮጵያውያንን የመፍራትና በጥርጣሬ የመመልከት ስሜት መነሻው ከእስልምና ልደት እንደሚጀምር መረዳት ይቻላል። ከዚህ ጋር አያይዘን በየመን የኢትዮጵያ ጀነራል የነበረው አብርሃ ካዕባን ለማፍረስ ያደረገውን ዘመቻ ማንሳት እንችላለን። "መጥፊያችን በኢትዮጵያውያን እጅ ነው" የሚለው የአረብ ሙስሊሞች ስነ ልቦናዊ ስጋት ተጨባጭ ታሪካዊ መነሻ አለው። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን እነርሱ እንደሚፈሩት በሰይፍ ሳይሆን በወንጌል እስልምናን ከምድረ ገጽ እናጠፋዋለን። መጥፊያው በኛ እጅ መሆኑን ራሱ አስቀድሞ አውቆታል።
በግራኝ አሕመድ ወረራ ዘመን ለኢትዮጵያ ክርስትና መትረፍ ሰበብ የሆኑ በቀድሞ ሕይወታቸው ሙስሊም የነበሩና ክርስትናን የተቀበሉ ሁለት ሰዎች ነበሩ። አንደኛዋ የሐዲያዋ ተወላጅ ጥበበኛዋና ውቧ ንግሥት እሌኒ (በሌላ ስሟ የዘይላ ንግሥት) ስትሆን ሁለተኛው ደግሞ የመናዊው ባለ ብሩህ አእምሮ በቀድሞ ስሙ አቡ አል-ፈት በክርስትና ስሙ አባ ዕንባቆም ነበሩ። ንግሥት እሌኒ በፖለቲካና በወታደራዊው መስክ፣ አባ ዕንባቆም ደግሞ በመንፈሳዊ መስክ የሠሩት ሥራ የኢትዮጵያን ክርስትና ከጥፋት ታድጓል። በተለይም አባ ዕንባቆም የግራኝን ሠራዊት ያሸነፈውን ንጉሥ ገላውዴዎስን ከልጅነቱ ጀምሮ በማስተማር፣ ከዚያም በጦርነቱ ዘመን የእስልምናን ሐሰተኝነት የሚገልጡ ጽሑፎችን (ለግራኝ ለራሱ ደብዳቤዎችን መጻፍን ጨምሮ)፣ በኋላም በጦርነቱ የወደሙ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመተካት እንዲሁም ከክርስትና የወጣውን ሕዝብ ወደ እምነቱ በመመለስ ረገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ የሚረሳ አይደለም። የእነዚህ ሁለት ሰዎች በወቅቱና በቦታው መገኘት የእግዚአብሔር ተዓምራዊ ሥራ እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም። የአባ ዕንባቆምን የሕይወት ታሪክና ጽሑፎች በተመለከተ አንድ ብዙ ዓመታትን የፈጀ ምሑራዊ ጽሑፍ በቅርቡ በሀገራችን ለሕትመት እንደሚበቃ መረጃው አለኝ።
የኢትዮ ፅንፈኛ ሙስሊሞች እፎይ የተሰኘው ወንድማችን ላይ ዘመቻ ከፍተዋል። ነፍሱን ለማጥፋት በየ ሚድያው ቅስቀሳ እያደረጉ ነው። ከትላንት ወዲያ ተሰብስበው ጥቃት ሊያደርሱበት ሞክረው ነበር። አንደኛ ነገር:- ኢትዮጵያ በሸሪአ ሕግ የምትተዳደር ሀገር አይደለችም። ሃይማኖት ላይ ጥያቄ አነሳ በሚል አንድን ሰው ተጠያቂ የሚያደርግ ሕግ የለንም። ሁለተኛ:- ልጁ ራሱ ጥፋተኛ ቢሆን በደቦ ፍርድ ጥቃት እንዲደርስበት መቀስቀስ በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው። ጥፋተኛን የሚቀጣ መንግሥት ባለበት ሀገር ከሕጋዊ ሂደት ውጪ አንድ ግለሰብ ላይ ጥቃት እንዲፈፀም መቀስቀስ ተጠያቂነትን ያስከትላል። ሦስተኛ:- ክርስትናን እንደ ልባቸው ሲሳደቡና ሲያንጓጥጡ የኖሩት የሀገራችን ሙስሊም ሰባኪያን በምን አንደበታቸው ሃይማኖታቸው እንደ ተነካ ስሞታ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ ማሰብ ያዳግታል። የሰው ሃይማኖት መንቀፍ ጥፋት ከሆነ የመጀመሪያዎቹ ተጠያቂዎች እነርሱ ናቸው። የሆነው ሆኖ ይህ ወጣት እምነቱን ከመከላከል ውጪ ምንም ዓይነት ጥፋት አልፈፀመም። በእስላማዊ መጻሕፍት ውስጥ ያልተጻፈ ምንም ነገር ተናግሮ አያውቅም። ተናግሯል የሚል ሰው ካለ እስኪ አንዲት ነጥብቅ ይጥቀስ። ችግሩ እስላማዊ መጻሕፍት ሲገለጡ ብዙ አሸማቃቂ ጉዶችን የተሸከሙ በመሆናቸው ሳብያ ያለ ምንም ተጨማሪ ማብራርያ እንኳ የገዛ መጻሕፍታቸን ማንበብ ብቻውን በብዙ ሙስሊሞች ዘንድ እንደ ስድብ መቆጠሩ ነው። ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው እንዲከበርላቸው ከፈለጉ አንደኛ:- የገዛ ነቢያቸውን የሚያንቋሽሹትን እነዚህን መጻሕፍት ሰብስቦ ማቃጠል፤ ሁለተኛ:- የሰው ሃይማኖት ሳይነኩ ዝም ብሎ መቀመጥ ያዋጣቸዋል። ችግሩ እዚያው እነርሱ ጋር በሆነበት ሁኔታ ሌላውን መወንጀል መፍትሄ አይደለም። ደግሞ ድሮ ድሮ ክርስቲያኖች እስልምናን ሳይጠቅሱ የራሳቸውን ሕይወት ሲኖሩ በነበሩባቸው ዘመናት ክርስትናን ሲሰድቡና ሲተቹ ኖረው መልስ ሲመለስላቸው ማለቃቀስ ምን የሚሉት ነው? ልጁ ዋሽቶ ከሆነ በአደባባይ ውይይት ገጥሞ ማሸነፍ፣ ያንን ማድረግ ከፈሩ ደግሞ በቪድዮ መልስ መስጠት። ሁለቱንም ማድረግ ካልቻሉ ሽንፈትን አምኖ መቀመጥ እንጂ የሰው ደም ለማፍሰስ መሯሯጥ የሃይማኖታቸውን ሐሰተኝነት ከመግለጥ የዘለለ ፋይዳ የለውም።
ወንድማችን Minas ይህንን ምሑራዊ ጽሑፍ አዘጋጅቶልናል። በተለይም ከሙስሊሞችና ከስህተት መምህራን ጋር በክርስቶስ አምላክነት ዙርያ የምትወያዩ ወገኖች በደንብ ብታጠኑት ይመከራል። አብሮ የተያያዘውንም መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ጽሑፍ ያላነበባችሁ ወገኖች እንድታነቡ አበረታታለሁ። ካነበብን በኋላ ለሌሎች ማካፈል አንዘንጋ። መልካም ንባብ! https://ewnetlehulu.net/the-name-above-all-names/
ሙሐመድ የኢየሱስን አምላክነት በመካዱ ምክንያት ተቀስፎ እንደ ሞተ ያውቃሉን? ነገሩ እንዲህ ነው። ሙሐመድ ሃይማኖቱን ከመሠረተ በኋላ በአረብያና በዙርያው የነበሩ የተለያዩ ማሕበረሰቦች እንዲሰልሙ የቻለውን በጂሃድ የማስገደድና ያልቻለውን ደግሞ ደብዳቤዎችን በመላክ ጥሪ የማድረግ ዘዴዎችን ይጠቀም ነበር። የሙሐመድ ደብዳቤ ከደረሳቸው ማሕበረሰቦች መካከል በደቡብ አረብያ የሚኖር ነጅራን የተሰኘ ክርስቲያን ማሕበረሰብ ይገኝበታል። ከሙሐመድ የደረሳቸውን ደብዳቤ ምክንያት በማድረግ ከሙሐመድ ጋር ለመወያየት የማሕበረሰቡ ተወካዮች ወደ መዲና እንደ ተጓዙ ከእስላማዊ ምንጮች እንረዳለን። ውይይቱ የክርስቶስ አምላክነትና ሥላሴን በመሳሰሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙርያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ እነዚሁ ምንጮች የሚናገሩ ሲሆን ባለመግባባት እንደተጠናቀቀ ተዘግቧል።

የውይይቱን ባለመግባባት መጠናቀቅ ተከትሎ ሙሐመድ “ሐሰትን የተናገረው ወገን እንዲቀሠፍ” በሚል እርስ በርስ የመረጋገም ስርዓት (ሙባሃላ) እንዲፈፅሙ ክርስቲያኖቹን የጋበዛቸው ሲሆን የክርስቲያኖቹ ምላሽ ግን አዎንታዊ አልነበረም። በዚህም ምክንያት ሙሐመድ ቤተሰቡን ሰብስቦ በማምጣት ብቻውን ተራገመ፤ እርግማኑም ደርሶበት በአንድ ዓመት ውስጥ በከባድ ህመም ሞተ። እነሆ ሙሉ ታሪኩ እዚህ ሊንክ ውስጥ ይገኛል
https://ewnetlehulu.net/mubahalah/