ewca_eth
115 subscribers
1.26K photos
33 videos
2 files
29 links
Develop and conserve scientifically Ethiopia's Wildlife resources and protected areas through active participation.
Download Telegram
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት መመዝገቡን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የማብሰሪያ መርሀግብር በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ አከናወነ፡፡
ህዳር 25/2016 ዓ.ም ( ባሌ ሮቤ) ፡- በመርሀ ግብሩ ላይ የፌድራል፣ የክልል እና ዞን አመራሮች ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዛሬ ኢትዮጵያ ሀገራችን ፣ የባሌ ህዝብ እና የባሌ ተራሮች ብሐየራዊ ፓርክ እንዲሁም በዙሪያው ያሉ አካባቢዎች በዓለም አደባባይ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ይህ ደግሞ የሆነው በባሌ ህዝብ ፣ ለ24 ሠዓታት ደከመን ሰለቸን ሳይሉ በፍፁም ፍቅር እና ትጋት ፓርኩን በሚጠብቁ ሬንጀሮች እና የባለስልጣኑ ሠራተኞች እንዲሁም አጋር አካላት ርብርብ ነው በማለት መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌድሪ ቱሪዝም ሚንስቴር ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ናቸው ፡፡
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተፈጥሮው ልዩ የሆነ መልካ ምድራዊ ውበት እና የብዝሀ ህይዎት ባለቤት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለብሔራዊ ፓርኩ ልዩ በረከት ነው፡፡ ይህን በረከት ከኛ በፊት ከነበረው ትውልድ በአደራ የተረከብነው እኛ ነን ያሉት ሚንትሯ ይህን ብሔራዊ ፓርክ ከዚህ በተሻለ ጠብቆ የላቀ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን ማስቻል እና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አሁን ካለበት በተሻለ ተጠብቆ እና ለምቶ ለቀጣይ ትውልድ ይተላለፍ ዘንድ ባጋራ እና በኃላፊነት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ የዓልም ቅርስነት መመዝገብ እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ፣ እንደ ክልል ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፣ እንደ ዞን ለባሌ ዞን እንደ ህዝብ ደግሞ በተለይ ለባሌ ህዝብ እጅግ ትልቅ ስኬት ነው ያሉት የእለቱ የክብር እንግዳ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምክትል ፕሬዝዳንት መዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱረሀማን አብደላ ናቸው፡፡
ብሔራዊ ፓርኩ በተፈጥሮ ሀብት የታደለ ነው፡፡ ይህ ሥፍራ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማድረግ ለበርካታ ዓመታት የተደረጉ ጥረቶች ወደ ውጤት ተቀይረው በማየታቸው የተሰማቸውን ልባዊ ደስታ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሥም የገለፁት አቶ አብዱረሀማን ጥረቶቹ ፓርኩን በመጠበቅ እና ወደተሻለ የቱሪዝም መዳረሻነት ማሳደግ ላይ አትኩረው በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡ በተለይ በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ የሚከናወኑ ህገወጥ ድርጊቶን በአፋጣኝ ማስቆም ፣ ለቱሪዝም ምቹ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት እና የሰላም እና ፀጥታን ጉዳይ አስተማማኝ በማድረግ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ባሌ ተራሮች ብሐየራዊ ፓርክ ለዞኑ ህዝብ የቱሪዝም መስህብ ሥፍራ ብቻ አይደለም ፡፡ የህልውናው መሠረትም ጭምር ነው ያሉት የባሌ ዞን አስተዳደር አቶ አብዱልሃኪም አሊዪ ናቸው፡፡ በሔራዊ ፓርኩ አሁን ከባሌም፣ ከኦሮሚያም ፣ ከኢትዮጵያም አልፎ የዓለም አጀንዳ ሆንዋል ያሉት አስተዳዳሪው ይህ ደግሞ ለባሌና አጎራባች ዞኖች ሕዝብ ትልቅ ድል ነው እና እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በዞኑ ሥም ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡
የቱሪዝም መስፋፋት ለአንድ አካባቢ እድገት እና ስልጣኔ ከስተዋጽኦው የጎላ ነው ያሉት አቶ አብዱልሃኪም የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ ሌሎች በዞኑ የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን በተሸለ መልኩ በማልማት እና ምቹ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆኑ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የባሌ ህዝብ ከፓርኩ ሠራተኞች ጋር በመተባበር ብሔራዊ ፓርኩን ጠብቆ ለዚህ ደረጃ አብቅቷል በማለት የገለፁት ኃላፊው በቀጣይም በተለይ የማህበረሰቡን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት እና የጥበቃ ሥራዎችን ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር እንሠራለን ሲሉም ቃል ገብተዋል፡፡
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተፈጥሮ የታደላቸው እና ከሌሎች ብሔራዊ ፓርኮች ልዩ የሚያደርጉት የከፍተኛ ቅዝቃዜ መገለጫ ከሆነው ውርጭ እስከ ሞቃታማው የቆላማ የአየር ንብረት ባለቤት መሆኑ እና ከዚህ የአየር ንብረት ጋር ተስማምተው የሚኖሩ በኢትዮጰያ ብቻ የሚገኙ የበርካታ ብርቅዬ የዱር እንስሳትና አእዋፍት መገኛ መሆኑ ነው በማለት በመርሀ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ናቸው፡፡፡፡
ዛሬ ይህ ብሔራዊ ፓርክ እነዚህን እና ሌሎች መገለጫዎችን መሰረት አድርጎ በዮኔስኮ የዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ ይህ ስኬት በተለይም ብሔራዊ ፓርኩን በመጠበቅ ሂደት ውስጥ ዋጋ ለከፈሉ ሠራተኞቻችን እና የባሌ ህዝብ የተሰጠ ልዩ ሽልማት እና የትጋት ውጤት ነውያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ስኬቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ብሔራዊ ፓርኩን አሁን ካሉበት የተለያዩ ሰው ሠራሽ ጫናዎች በአፋጣኝ ልንታደገው ይገባል በማለት ገልፀዋል፡፡
የባሌ ህዝብ ይህን እጅግ ውብ እና በብዝሀ ህይወት ስብጥሩ በዓለም ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ያለውን ተፈጥሯዊ ጥቅም ተገንዝቦ እና ጠብቆ እዚህ አድርሷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይ በብሔራዊ ፓርኩ ላይ በየጊዜው የተከሰቱና የዱር እንስሳቱን ህልውና ስጋት ላይ የጣሉ ህገ-ወጥ ሰፈራ እና ልቅ ግጦሽን የመሳሰሉ ተግዳሮቶች በጋራ ሆነን አፋጣኝ መፍትሄ ልንሰጥ እና የአከባቢው ማህበረሰብ ፓርኩን በመጠበቅ እና በማልማት ሂደት የጋራ ተሳታፊናተጠቃሚ የሚሆንባቸውን የተሻሉ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ ችግሮቹን በአፋጣኝ መፍታት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የብሄራዊ ፓርኩን እና በውስጡ ያሉ የዱር እንስሳትን ህልውና ለመታደግ ከምንም በላይ የሆነች ህይወታቸውን ለገበሩ እንደ ቢንያም አድማሱ ያሉ ጀግኖቻችንን ሁሌም ስንዘክራቸው እንኖራለን ያሉት የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶንጋቱ ሞቱማ ናቸው ፡፡
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አሁን ያለበት ስኬት የበለጠ ጎልብቶ እና ፓርኩ ከዚህ በተሻለ በቱሪዝም ኢንዳስትሪው ከፍ ያለ ቦታ ላይ ለማድረስ ለቱሪስቶች ምቹ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት ጊዜ ማይሰጠው ጉዳይ ነው እና ባለሀብቶችና አጋር አካላት የሮቤ ከተማን ለቱሪስቶች እንቅስቃሴ የተመቸች እና ሠላሟ የተጠበቀ ለማድረግ አብራችሁን ልትሠሩ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ኢዱጥባ
ህዳር 2016 ዓ.ም
The Czech Republic Ambassador in Ethiopia and the Ethiopian Wildlife Conservation Authority Director General had a discussion.
The Czech Republic Ambassador in Ethiopia H.E. Miroslav Kosek and the Director General of the Ethiopian Wildlife Conservation Authority, Mr. Kumera Wakjira, had a bilateral discussion about future cooperation and support for capacity building and research in wildlife conservation.
ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን 18ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በፓናል ውይይት አከበሩ
ህዳር 28/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ‹‹ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት አከበሩ፡፡
መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት ክቡር አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የሙዚየም ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው ይህ ዓመት ለቱሪዝም ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ የተለየ አመት እንደሆነ ገልፀው ባለፈው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክንና የጊዲዮ ባህላዊ መልክዓ ምድርን በማስመዝገብ ሀገራችን ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር መሆኗን ጠቅሰው ሰሞኑን ቦትስዋና ላይ በተካሄደው የዬኒስኮ ጉባኤ የሸዋልኢድ በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ የትምህርት ተቋም (ዩኒስኮ) አገራችን ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች በ5ኛነት በመመዝገቡ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ህብረ ብሔራዊ አንድነትና የሰላም ግንባታ በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ሠነድ ያቀረቡት የተቋሙ የቅርስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ህይወት ኃይሉ በኅብረብሔራዊ ፌዴራሊዝምና የሰላም ግንባታ፣ በፌዴራሊዝም ሥርዓት ምንነት፣ የፌዴራሊዝም ጥቅሞችና ተግዳሮቶች፣ ኅብረብሔራዊ ፌዴራሊዝምን ከመተግበር አንፃር ገለጻ አቅርበዋል፡፡
በቀረበው የውይይት መነሻ ሠነድ ላይ የተለያዩ ሃሳቦችና አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተካሄዷል፡፡
#ከቱሪዝም ሚኒስቴር ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ