Eureka Academy
125 subscribers
172 photos
1 video
3 files
61 links
Learn Smart, Score High!
Helping Grade 12 students excel in their national exams. Check out our educational YouTube & TikTok channels for more!
Download Telegram
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም አዲስ እና ነባር የመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

የመደበኛ ፕሮግራም ነባር ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በሪሚዲያል እና በፍሬሽማን ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች፤ የ2018 ዓ.ም ምዝገባ መስከረም 05 እና 06/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የ2018 ዓ.ም ትምህርት የሚጀመረው መስከረም 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል፡፡

በሪሚዲያል እና ፍሬሽማን ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ እና ብርድ ልብስ እንዲሁም ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉትን የትምህርት ማስረጃ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

# tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና የማታ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት አሳውቋል፡፡

በዚህም፦
በ2017 ዓ.ም Freshman እና በ2016 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ተማሪዎች የነበራቸሁ ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት መስከረም 05 እና 06/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡ (ሪፖርት ምታደርጉበትን ካምፓስ ለማወቅ ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ፡፡)

ሌሎች ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 08 እና 09/2018 ዓ.ም፤ ፕሮግራሞቹ በሚገኙበት ካምፓሶች ይካሔዳል፡፡

ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ የማታ (Extension) ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 15 እና 16/2018 ዓ.ም፤ ፕሮግራሞቹ በሚገኙበት ካምፓሶች ይከናወናል፡፡

በሁሉም ፕሮግራሞች የግብርና ኮሌጅ፣ የእንስሳት ሀክምና፣ የስነ-ምድር እና የአደጋ መከላከል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉት በዘንዘልማ ካምፓስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

🔔 በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል፡፡

#tikvahuniversity
Forwarded from Tikvah-University
#SamaraUniversity

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

የሁሉም ነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የ2018 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ቀን መስከረም 07/2018 ዓ.ም ሲሆን፤ ምዝገባ መስከረም 08 እና 09/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ትምህርት መስከረም 12/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

🔔 በ2017 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

@tikvahuniversity
Forwarded from Tikvah-University
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ መስከረም 08 እና 09/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት በየምትማሩበት ግቢ (ደሴ ግቢ፣ ኮምቦልቻ ግቢ እና ልዕለ ህክምና ግቢ) ሪፖርት ማድረግ እንዳለባችሁ ተገልጿል።

በ2018 ዓ.ም አዲስ ለምትመደቡ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ጥሪ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

@tikvahuniversity
🌼መልካም አዲስ አመት🌼

2018 የሰላም ፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆናልቹ እንመኛለን!
1
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቋል።

የፈተና ውጤቱን አስመልክቶ ነገ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ መግለጫ ይሰጣል።

#MoE
#Learn_at_AAU – Notice to All Applicants
Undergraduate Admission (Regular & Extension Programs)
Academic Year 2025/26 (2018 E.C.)

Addis Ababa University is pleased to announce that applications are now open for admission to its Undergraduate Regular and Extension Programs for the 2025/26 Academic Year (2018 E.C.). Interested candidates—whether applying under government sponsorship (cost-sharing) or self-sponsorship, are invited to apply by fulfilling the requirements and procedures outlined below.

#Requirements for Self-Sponsored Applicants

1. Applicants must have completed the Ethiopian Secondary School Leaving Certificate Examination (ESSLCE) administered by the Ministry of Education (MoE) and achieved passing marks, as required by the MoE, for the academic years 2014–2017 E.C.
2. Applicants must take the Undergraduate Admission Test (UAT) of Addis Ababa University and obtain the required minimum passing score of 50 percent.
3. Applicants with previous enrollment in other government universities (2015–2017 E.C.) must submit official proof of cost-sharing payments along with their academic credentials.
4. Applicants who pursued remedial education at any recognized institution must successfully pass the remedial qualifying examination.
5. Applicants must pass any additional assessments required by the University for specific programs, including health-related, law, and other fields of study.
6. If an applicant’s ESSLCE and UAT results do not meet eligibility for their preferred program, they must consent to placement in an alternative field of study as determined by the University.

#Requirements for Government-Sponsored Applicants (Cost-Sharing Scheme)

1. Applicants must have taken the 2017 E.C. ESSLCE and achieved the minimum cut-off score for higher education admission as determined by the Ministry of Education.
2. Applicants must take the UAT and obtain a minimum passing score of 50 percent.
3. Applicants must provide official proof of economic deprivation, obtained from their local administrative authority (Kebele/Woreda/Zone/District) or a recognized legal organization supporting their education.
4. Applicants must pass any additional assessments required by the University for health-related, law, and other specific fields of study.

#AAU Presidential Scholarship Requirements

Applicants wishing to be considered for the AAU Presidential Scholarship must:

1. Achieve a minimum score of 500 in the 2017 E.C. ESSLCE.
2. Successfully pass the UAT administered by AAU.
3. Provide consent to be placed in a department alongside government-sponsored students, based on merit and institutional placement guidelines.

#Application Steps

1. Open the AAU Admission Portal: [https://portal.aau.edu.et](https://portal.aau.edu.et)

2. Click Apply for Admission (left-hand side menu).

3. From the Undergraduate Student menu, select Apply.

4. Click Call for Undergraduate Regular Admission.

5. Click Apply Now after reviewing the programs.

6. Create an account using the Create Undergraduate Applicant Account form. Use a valid email address as your username and set your password.

7. Log in with your email and password to access your AAU application account.

8. Fill out the Personal Profile and Academic Profile forms, then click Update and Next.

9. Under Financing Your Study, select either:

   * Government Sponsorship: Upload supporting evidence for requesting sponsorship, then choose your freshman program (Natural Sciences or Social Sciences).
   * Self-Sponsorship: Select your top three program preferences, consent to placement conditions, and continue.

10. Upload the required documents:

* ESSLCE result certificate
* Remedial result certificate (if applicable)
* Grade 9–12 transcripts

11. Select your UAT Exam Location from the drop-down menu.
12. Read the Consent Statement, select Accept, and click Submit (review all information before submission).
13. Proceed to payment:

* Application fee: ETB 350
* UAT fee: ETB 750
* Total: ETB 1,100
* Payment via Telebirr (QR code scan or mobile number deduction).
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ እየጠበቀ መሆኑን ገልጿል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ መመዘኛና መስፈርት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር መጀመሩ ይታወቃል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመስከረም 05-09/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በዩኒቨርሲቲው ፖርታል (https://portal.aau.edu.et) አማካኝነት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ ሰዓት እና የፈተና ማዕከላት በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ማኅበራዊ መገናኛ ገፆች እና በተቋሙ ይፋዊ ድረገፅ እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
1
ማስታወቂያ

በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡-

1. የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ስሚቀበል ምርጫችሁ ውስጥ ማካተት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

2.አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑ እናሳውቃለን።
ማስታወቂያ

በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡-

1. የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ስሚቀበል ምርጫችሁ ውስጥ ማካተት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

2.አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑ እናሳውቃለን።
#MoE

በ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ለመማር ያለፋችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማይቀበል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ አመልካቾች መስፈርቶች

የመስማት/የማየት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች፦ ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና የማየት ወይም የመስማት ችግርን የሚገልጽ የህክምና ማስረጃ።

የሚያጠቡ እናት አመልካቾች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከወለዱበት የጤና ተቋም 6 ወር ያልሞላው የህጻኑ/ኗ የክትባት ካርድ።

ለተመሳሳይ ጾታ መንትያ አመልካቾች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከወሳኝ ኹነት የተገኘ የሁለቱም አመልካቾች የልደት ካርድ።

የአካል ጉዳት ላለባቸው አመልካቾች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከመንግሥት የጤና ተቋማት የቦርድ ወሳኔ የተሰጠበት የህክምና ማስረጃ።

የጤና ዕክል ያለባቸው አመልካቾች
ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እና ከመንግሥት የጤና ተቋማት የቦርድ ውሳኔ የተሰጠበት የህክምና ማስረጃ።

🔔https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ድረስ ያመልክቱ።
በትምህርት ሪፎርሙ የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል የተወሰዱ እርምጃዎች እና ከታች ጀምሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና ስራዎች
በሀገራችን የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል ከተወሰዱት እርምጃዎች አንዱ በትምህርት ፖሊሲው የተቀመጠውን አንድ ተማሪ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ወይም እርከን ለመሸጋገር ቢያን 50 ከመቶና በላይ አማካይ ውጤት ማስመስመዝገብ አለበት በሚል የተደነገገውን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው። በዚህም በሪፎርሙ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችም ይሁኑ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ያሉ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ሲያመጡ ወደ ሚቀጥለው ክፍል/እርከን እንዲሸጋገሩ እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ተማሪዎች 50 ከመቶ በታች አማካይ ውጤት አምጥተው ወደ ሚቀጥለው ክፍል እንዲዛወዱ ወይም በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ይደረግ እንደነበር የሚታወስ ነው። አሁን ባለው አሰራር ይህንን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በየትኛውም የክፍል ደረጃ 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያላመጣ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ወይም እርከን አይዛወርም።
በተጨማሪም በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች  በነዚህ ፈተናዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል እንዲዛወሩ እየተደረገ ይገኛል። ይህም በየደረጃው የትምህርት ጥራቱ ያለበትን ደረጃ እየለኩ ለመሄድ ትልቅ አስተዋጻኦ ይኖረዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/17CF2bPKAt/
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመማር ላመለከታችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው መስከረም 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ለፈተና የተመረጣችሁ ስም ዝርዝር፣ ፈተናውን የምትፈተኑበት ቦታ እና የመፈተኛ ሊንክ ለክልል ትምህርት ቢሮዎች የተላከ በመሆኑ ከዛ ማወቅ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

ፈተናው የሚሰጠው በኦንላይን በመሆኑ፣ በሚሰጣችሁ ሊንክ የመለማማጃ ፈተና የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
‎Dear AAU  2018 Entry Students,

‎Welcome to AAU!  Get ready to connect and explore all AAU has to offer!

‎Use the WiFi passwords below for your respective campus:


‎AAU campus wifi passwords

‎Use the WiFi passwords below for your respective campus:

👉 Sefereselam
‎AAU-SSC Student
‎    --SSC@Student!
‎AAU-SSC Staff
‎    -SSC@Staff!
‎AAU-SSC Super
‎    --SSC@ICT!

‎4kilo
👉Wifi name: AAU-CNCS-Staff
‎   Password:  CNCS@Staff!
👉Wifi name: AAU-CNCS-Student
‎     Password: CNCS@Student!

‎5kilo
👉Wifi name: AAU-AAiT-Staff
‎      Password:  AAiT@Staff!
👉Wifi name: AAU-AAiT-Student
‎      Password:  AAiT@Student!

‎6kilo
👉Wifi name: AAU-Main-Staff
‎      Password:  AAU@Staff!
👉Wifi name: AAU-Main-Student
‎     Password:  AAU@Student!

‎CBE
👉WiFi Name: AAU CBE Student
‎    Password : CBE@Student!
👉Wifi Name: AAU CBE Staff
‎  Password: FBE@Staff!

‎Lideta Eiabc
password  pass@eiabc!

‎Tikur anbesa
👉Wifi name: AAU-CHS-Staff
‎      Password:  CHS@Staff!
👉Wifi name: AAU-CHS-Student
‎      Password:  CHS@Student!

‎Enjoy your time at AAU!

‼️i advice all of you to turn on your VPN while you are using public wifi because VPN adds a vital layer of security and privacy when you're connected to a public Wi-Fi network.
ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ባስጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ጥቂት ክፍት ቦታዎች ተጨማሪ ተማሪዎችን (አሁን 9ኛ ክፍል ገብተው እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች መካከል በማወዳደር) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም በነዚህ ውስን ክፍት ቦታዎች ተማዝግባችሁ ለመማርና የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች https://sbs.moe.gov.et/apply  በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።