Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25K subscribers
41K photos
338 videos
7 files
5.81K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ለቦይንግ 737 አውሮፕላን ሰለባዎች የሙት አመት መታሰቢያ ተደረገ
************************
(ኢ.ፕ.ድ)

መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ET302 ማክስ 8 አውሮፕላን የተከሰከበት ቦታ ላይ ዛሬ የሙት አመት መታሰቢያ ስነስርአት እየተከናወነ ይገኛል።

ስነስርአቱ የተዘጋጀው በአካባቢው ነዋሪዎች ሲሆን በሚልኪ የማስታወቂያ ስራዎች አስተባባሪነት የሚከናወን መሆኑን የሚልኪ አድቨርታይዚንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ቀልቤሳ መገርሳ ተናግረዋል።

በስነስርአቱ ለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ጸሎት ያደረጉ ሲሆን የአካባቢው ፈረሰኞች ዛሬ ለአመት የዘለቀው ሀዘን የሚያበቃበት ቀን መሆኑን ለማሣወቅ ጥቁርና ነጭ ሰንደቅ አላማዎየችን በመያዘ ተገኝተዋል። አባ ገዳዎችም ምስጋና አቅረበዋል።

በአውሮፕላኑ ተሣፍረው የነበሩ የ33 አገር ዜጎች በሙሉ ህይወታቸው ማለፉና ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታውጆ እንደ ነበር ይታወሳል።

ዘገባ እና ፎቶ በራስወርቅ ሙሉጌታ
የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ የተሰራጨባቸው ሃገሮች
/ የካቲት 30, 2012 / ከቀኑ 10:00 ሠዓት /

★ ጣሊያን (Italy)
※ 7,424 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 1,541 ሰዎች አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ናቸው።
※ 366 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። ከእነዚህ መካከል 133 ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ ሞተዋል።

★ ኢራን (Iran)
※ 7,161 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 595 ሰዎች አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ናቸው።
※ 237 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። ከእነዚህ መካከል 43 ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ የሞቱ ናቸው።

★ ደቡብ ኮሪያ (South Korea)
※ 7,478 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከነዚህ መካከል 165 ሰዎች አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ናቸው።
※ 53 ሰዎች በቫይረሱ ሞተዋል። ከእነዚህ መካከል 2 ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ የሞቱ ናቸው።

የሌሎች ሃገሮች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት

★ ስፔን (Spain)
※ በስፔን 235 አዲስ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በአጠቃላይ 909 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

★ ጀርመን (Germany)
※ በጀርመን 200 አዲስ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በአጠቃላይ 1,112 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

★ አልባኒያ (Albania)
※ አልባኒያ 2 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ስዎች እንዳገኘች ሪፖርት አድርጋለች።

★ ግብጽ (Egypt)
※ ግብጽ በቫይረሱ የመጀመሪያ ሰው (1 ሰው) እንደሞተባት ሪፖርት አድርጋለች።

መልካም ጤንነት!!

EthioTena - ኢትዮጤና
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ (face mask) አጠቃቀምና እነማን መጠቀም እንዳለባቸው ልብ ይበሉ::
***********************
(ኢ.ፕ.ድ)

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (face mask) አጠቃቀሙና እነማን መጠቀም እንዳለባቸው በቅጡ ባለመረዳት ሰዎች ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ሲዳረጉ ይስተዋላል፡፡

ለመሆኑ ማስክ መጠቀም ያለባቸው እነማን ናቸው?

ጤና ሚኒስቴር መልስ አለው ....

1. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም የሚያስፈልገን በበሽታው የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ሰው አጠገብ ወይም እየተንከባከብን ከሆነ ብቻ፣

2. ሳልና ትኩሳት ካለብን ለሌላው ጥንቃቄ በማድረግ ሲያስለን ወይም ሲያስነጠሰን ነው። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ለምሳሌ ሰው የሚበዛበት ቦታ ከመሄድ ራስን መቆጠብ ፣ እጅ በደንብ መታጠብ ፣ መጨባበጥ ማቆም እና ማስኩን በስርዓት ማስወገድ እና ለባለሙያ ማሳወቅ ያስፈልጋል::

3. የማስክ አጠቃቀምም ውጤታማ የሚሆነው እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትሮ መታጠብ ሲቻል እና አወገገዱም ጥንቃቄ የተሞላበት ሲሆን ብቻ ነው፡፡

ህብረተሰባችን መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

የበለጠ መረጃ ሲያስፈልግ ነጻ በሆነው 8335 የስልክ መስመር ላይ መደወል ይቻላል፡፡
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ እንደሚወያዩ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ የኮሮና ቫይረስን መከላከል በሚቻልበት መንገድ ጨምሮ ስለ አንበጣ መንጋ እንዲሁም የክልል ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ::
ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ከፕሬዚዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተወያዩ
*****************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በድጋሚ መጡ ብለዋቸዋል።

ፕሬዚደንት ኢሳይያስ ለሁለት ቀናት በሚያደርጉት ቆይታ፣ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ዛሬ ሚያዚያ 25 ቀን 2012 ዓም
አንድ መቶ ሰባ ስድስት (176) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል
*******************
(ኢ ፕ ድ)

👉 3 ሰዎች አርፈዋል፤

👉 75 ሰዎች አገግመዋል

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5636 የላብራቶሪ ምርመራ 176 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3521 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 28 (17 ከጤና ተቋም እና 11 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በተጨማሪ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አምስት (75) ሰዎች (31 ከአዲስ አበባ፣ 28 ከሶማሊ ክልል፣ 10 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 1 ከአፋር ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 545 ነው።
ትንቢት በሚራዘምበት አገር ምርጫ ቢራዘም ምን ይገርማል?

ዘንድሮ “መራዘም” ብሎ ቃል ክብሪት ሆኗል። ባሳለፍነው ሳምንት የፌደሬሽን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የህዝብና ቤት ቆጠራው መራዘም ያልተዋጠላቸውና የተዋጠላቸው የምክር ቤቱ አባላት ተረት ተታኩሰዋል።

አንዲት የምክር ቤቱ አባል “እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ” በማለት ቆጠራው መራዘሙን ሲተቹ ፤ ሌላ የምክር ቤት አባል “ለማያቅሽ ታጠኚ” ብለው እርፍ አሉ።

ከዚህ ቀደምም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫውን ለማራዘም ባደረገው ውይይት ሃሳቡን የተቃወሙ የምክር ቤቱ አባል “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ነሽ ይሏታል” ብለው ተርተው ነበር። ለትችቱ ምላሽ የሰጡ ሌላ የምክር ቤቱ አባል ደግሞ “ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል” ብለው ተርተዋል። የመልስ ምቱ ይበልጥ ጠንክሮ “ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ” እና “አዛኝ ቅቤ አንጓች” ታክለዋል።

በርግጥ ምክር ቤቶቹ ለተረትና ምሳሌዎች አዲስ አይደሉም። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበር ተፈቅዶላቸው ፓርላማ የገቡ ጥቂት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በገዢው ፓርቲ ሰዎች በሚተኮሱ ተረቶች ሲቆስሉ ኖረዋል። ልዩነቱ ያኔ ተራች መንግስት ነበር። የያኔዎቹ የተቃውሞ ጎራ ሰዎች እንኳን ለብሽሽቅ ተረት የሚወክሉትን ህዝብ ጥያቄ ለማቅረብ የማትበቃ ሁለት ደቂቃ ነበር የሚሰጣቸው። ከዛ ሃሳባቸው ሳያልቅ ሰዓታቸው ያልቃል ፤ አይ ዴሞክራሲ !

ዛሬ ደግሞ ተረት ተራቹ ተቃዋሚው ቡድን ሆኗል። የፌዴራል መንግስቱን የተቆጣጠረው ገዢ ፓርቲም “እሾህን በእሾህ” አይነት ስትራቴጂ ቀይሷል። ሁኔታዎች በዚህ መልኩ የሚቀጥሉ ከሆነ የሁለቱ ምክር ቤት አባሎች ከሕገመንግስቱ እኩል ለተረት መጽሐፍት ትኩረት መስጠት መጀመራቸው አይቀሬ ነው። https://www.press.et/Ama/?p=34542
የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ዴዛማታሶን ( Dexamethasone) የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ከሞት መታደጉን አረጋግጠናል አሉ
*****************************
(ኢፕድ)
የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ርካሽና በቀላሉ በየትኛውም አካባቢ ሊገኝ የሚችለው ዴዛማታሶን( Dexamethasone) የተሰኘው መድሃኒት የኮሮናቫይረስ ህመምተኛን ከሞት ሊታደግ እንደሚችል አረጋግጠናል አሉ። ተማማሪዎቹ እንደሚሉት መድሃኒቱ እስካሁን ጥቅም ላይ ከዋሉት መድሃኒቶች ሁሉ ሞትን በመቀነስ ተወዳዳሪ የለውም።

ቬንትሌተር ለሚያስፈልጋቸው ህመምተኞች መድሃኒቱ ከ40- 28 በመቶ የሚሆኑትን የማዳን አቅም ያለው ሲሆን፣ ኦክስጂን በአጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ ለሚያስፈልጋቸው ህመምተኞች ደግሞ ከ25 -20 በመቶ የሚሆኑትን የማዳን አቅም አለው ተብሏል።

ዋና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፒተር ሆርቢ እንደሚሉት “ይህ መደሃኒት እስካሁን ከተገኙት መደሃኒቶች በሙሉ ሞትን በመቀነስ ረገድ ተወዳዳሪ የለውም፤ ሞትን ትርጉም ባለው ሁኔታ ቀንሷል፤ በዘርፉ በተካሄዱ የምርምር ሂደትም ትልቅ ዕምርታ ነው።”

ምርምሩን የመሩት ፕሮፌሰር ማርቲን ላንድሬይ በበኩላቸው “የመድሃኒቱ አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም፤ በዋጋም በጣም ርካሽ ነው፤ ለአንድ ሰው የሚያስፈልገው 35 ፓውንድ ብቻ ነው። ከዚህም በላይ ይላሉ ፕሮፌሰር ላንድሬይ መደሃኒቱ በየትኛውም አካባቢ በቀላሉ ሊገኝ የሚቻል ነው” ብለዋል።

ፕሮፌሰር ላንድሬይ መድሃኒቱ በራሳቸው ለመተንፈስ ለሚችሉ ህመምተኞች አያስፈልጋቸውም፤ መድሃኒቱ የሚያስፈልጋቸው በሆስፒታል ለተኙ ጽኑ ህመምተኞች ብቻ ነው። ማንም መድሃኒቱን ገዝቶ እቤቱ መጠቀም ይችልም ሲሉ ፕሮፌሰሩ ተናገረዋል።
ምልክት የማያሳዩ የኮሮና ታማሚዎችን ጭምር ለመለየት የሚያስችል የምርመራ መሳሪያ ተሰራ

ምልክት የማያሳዩትን ጨምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን በቀላሉ ለመለየት የሚያስችል የምርመራ መሳሪያ መስራታቸውን በእንግሊዝ የበርሚንግሃም ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡

አብዛኞቹ የቫይረሱ ታማሚዎች በቫይረሱ መያዛቸው የታወቀው ከታመሙ በኋላ መሆኑ አሳሳቢ ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ ግኝታቸው በስፋት ለመመርመር እና ምልክት የማያሳዩትን የቫይረሱን ተጠቂዎች ጭምር ለመለየት እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

የሚሰበሰቡ የቫይረሱን ናሙናዎች 98 በመቶ ያህል የመለየት አቅም አለውም ተብሏል፡፡

ዴይሊ ሜይል ጨዋታ ቀያሪ ያለው አዲሱ ግኝት በቫይረሱ ስንያዝ ሰውነታችን ሊያዘጋጅ የሚችለውን የጸረ እንግዳ አካል (antibodies) ሁኔታ በማጤን የሚሰራ ነው፡፡

1 ሺ የሚጠጉ የእንግሊዝ የጤና ሰራተኞች በተሳተፉበት የጥናት ሂደትም ውጤታማነቱ ተረጋግጧል፡፡

በቫይረሱ ሊጠቁ እንደሚችሉ ከሚታሰቡ 10 ሰዎች 8 ምልክቶቹን ላያሳዩ እንደሚችሉ የመስኩ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ምንጭ -አልአይን
በዚህ ወሳኝ ወቅት መከላከያን አንስቶ ማብጠልጠል የለየለት የሀገር ክህደት ወንጀልና ባንዳነት ነው።

👉ምሁራን ለሀገራቸው የሚሰጡት ትልቁ ስጦታ እውቀታቸውን ነው። ከተራ ወታደር እስከ ጀነራል መኮንኖች ድረስ የሚሰጡት መተኪያ የሌላትን ሕይወታቸውን ነው። ለሀገር ከዚህ በላይ ታላቅ ስጦታ የለም።

👉ሀገሬን ወገኔን እወዳለሁ የሚል ማንኛውም ዜጋ የሀገሩን ሰላም ጸጥታና ደህንነት ለመጠበቅና ለማስከበር ሁልግዜም ከሠራዊቱ ጎን መቆም መሰለፍ ይገባዋል ብለን እናምናለን።

👉በለውጡ መጀመሪያ አካባቢ ሲጻፉ የነበሩ የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት የሚነኩ፤ መረጃን አሳልፈው ለጠላቶቻችን ሲሰጡ የነበሩ ለምሳሌነት የሠራዊቱ ሞራል ደካማ ነው ፤ ሠራዊቱ በጎሣ የተከፋፈለ ነው ብሎ መጻፍና መናገር ትልቅ ወንጀል ነው።

👉ሠራዊቱና አመራሩ እንዲጋጭ እንዳይግባባ መተማመን እንዳይኖረው ለሀገር ጠላት በር ለመክፈት ሆን ተብሎ ሲሰራ የነበረ ምናልባትም ከጀርባ በጠላቶቻችን ፋይናንስ የተደረገ በሀገር ክህደት ወንጀል የሚያስጠይቅ ነው።

👉ከሠራዊቱ ውስጥ መረጃ አግኝቻለሁ በሚል የራሳቸውን መረጃ ፈጥረውና ፈብርከው ወይም ከሠራዊቱ የለቀቁና ቅሬታ የነበራቸው ሰዎች የሚሰጡትን የጥላቻ መረጃ ያለአንዳች የጎንዮሽ ማረጋገጥ እውነት አስመስለው በመጻፍ ለገንዘብ ማግኛ ሲጠቀሙበት የነበረ የሚዲያ እንቅስቃሴ አይተናል።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5274 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ (129) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3759 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (11 ከጤና ተቋም እና 7 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም። ከዚህ ባለፈ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ሶስት (63) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ አንድ (111) ሰዎች (109 ከአዲስ አበባ እና 2 ከድሬዳዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 849 ነው።
ዴክሳሜታሶን በኮሮናቫይረስ ታማሚዎች ላይ ያስገኘውን ውጤት መልካም ነው፣
.የመድሃኒቱ ጠቀሜታ በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባላቸው ላይ አይደለም - የዓለም ጤና ድርጅት
****************************
(ኢፕድ)
በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ዴክሳሜታሶን በተባለው መድኃኒት ላይ የተደረገው ሙከራና ያስገኘውን ውጤት በበጎ እንደሚመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም እንዳሉት "ይህ ኦክስጂንና የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማን ላይ የሚያጋጥምን ሞት የሚቀንስ የመጀመሪያው መድኃኒት ነው" ብለዋል።

በሙከራው ይህ መድኃኒት በኮሮናቫይረስ በጽኑ ከታመሙ ሰዎች የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት አመልክቷል።

ድርጅቱ እንዳለው የዴክሳሜታሶን ጠቀሜታ በኮቪድ-19 በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባለቸው ላይ እንዳልሆነ አመልክቷል።

ዴክሳሜታሶን ከ1960ዎቹ (እአአ) ጀምሮ በተለያዩ ህመሞች ምክንያት የሚያጋጥሙ እብጠቶችን ለመቀነስና የተወሰኑ አይነት የካንስር ህመሞችን ለማከም ጥቅም ሲውል ቆይቷል።
‹‹የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በወቅቱ ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል አድራጊ ፈጣሪነት በፍጥነት ተዳክሞ ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርጓል›› ሲሉ የቀድሞው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትርና፤ በሩሲያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ አስታወቁ፡፡

አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት ፣ የህዳሴ ግድቡ አቶ መለስ በህይወት እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ በየወሩ ይገመገም የነበረ ሲሆን ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ በየወሩ መገምገሙ ቀርቷል፡፡

የወቅቱ የቦርድ ሰብሳቢ በክላስተር አደረጃጀት በሁለት ወር አንድ ጊዜ እንዲታይ ብለው አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን አስታውሰው ፣ ሰብሳቢው አሠራሩን ተግባራዊ ሳይደርጉ መቅረታቸውንም አመልክተዋል። በዚህ ሁኔታ የህዳሴ ግድቡን ፕሮጀክት የመብራት ኃይል ቦርድ አካልም ይገመግመው እንዳልነበር ጠቁመዋል::

ፕሮጀክቱን በሚመለከት በየጊዜው ለቦርዱ ጥያቄ እናቀርብ ነበር ያሉት አምባሳደር አለማየሁ፣ ቦርዱም ገምግሞ ወደ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የግምገማውን ውጤት አይልክም ነበር ብለዋል፡፡ የዘርፉ ባለቤት ብንሆንም ተገልለን ነበር፤ ሪፖርትም ከመብራት ኃይል እየወሰድን ጉድለቶቹን እንናገር ነበር ሲሉም ተናግረዋል::

እንደ አምባሳደሩ ገለጻ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከመብራት ኃይል የሚያገኘውን መረጃ ይዞ እንደ ዘርፍ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት እንኳን ‹‹ምን አግብቷችሁ ነው መግለጫ የምትሰጡት›› በማለት በቦርድ ሰብሳቢው በኩል ቁጣ ይደርስባቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ሁኔታም ፕሮጀክቱ ከህዝብ ፕሮጀክትነቱ ወርዶ የአንድ ግለሰብ ፕሮጀክት ሆኖ እንደነበር አመልክተዋል። ይህም የግድቡን ግንባታ ለውድቀት ከመዳረጉ ባለፈ ‹‹በአገራችን ታሪክ የሚያሳዝን ድርጊት ሆኖ አልፏል›› ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሱዳኑን ሉዐላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሌፍተናንት ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳልጎን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደኅና መጡ በማለት ከተቀበሉ በኃላ የሱዳኑ ጀነራል ለጉብኝት አዳማ ይዘዋቸው ሲሄዱ በመንገድ ላይ የባቡር ሀዲድ ላይ ፎቶ በመነሳት ደስታቸውን እየገለፁ የነበሩ ሙሽሮችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋቸዋል::
‹‹ግብፅ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ ያላት ምርጫ ከኢትዮጵያጋር መተባበር ብቻ ነው››
‹‹በአባይ ውሃ የኢትዮጵያ መብት፣ ከግብፅ የተረፈ መሆን የለበትም›› ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በአአዩ መምህርና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ
*****************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- ‹‹ዛሬም ሆነ ወደፊትም ግብፅ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ ያላት ምርጫ ከኢትዮጵያ ጋር መተባበር ብቻ ነው›› ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የአባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪና ተደራዳሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ገለጹ፡፡

ፕሮፌሰር ያዕቆብ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ለግብፅ ሌላ አማራጭ ማማተር ከንቱ ነው፡፡ ግብፅ፣ ሱዳን ወይም የትኛውም ሌላ ወገን ማወቅ ያለበት እ.ኤ.አ ከ2015 የመርህ መግለጫ ሰነድ በስተቀር ኢትዮጵያ ከግብፅም ሆነ ከሱዳን ጋር አስገዳጅ ውለታ እንደሌላት ነው፡፡

‹‹በአባይ ውሃ የኢትዮጵያ መብት፣ ከግብፅ የተረፈ መሆን የለበትም›› ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ይህ ከሆነማ ኢትዮጵያ የውሃ መብት ሉዓላዊ ባለቤትነት አይኖራትም ማለት ነው›› ብለዋል፡፡

እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ እስከዛሬም ድረስ ግብፅ የምትሄድበት አካሄድ የማይገባት አካሄድ መሆኑ መታወቅ አለበት። የአባይ ውሃ ከኢትዮጵያ ይነሳል። ለወደፊቱም እንዲሁ ይቀጥላል። ድንበር ተሻጋሪ ሀብት ስለሆነ በመተሳሰብና በመተባበር በውሃ ሀብቱ ሁሉም መጠቀም ይችላል። ስለዚህም የግብፅ ፍላጎት የሌሎች ውሃ ተጋሪዎች ጥቅም፣ መብትና የልማት ፍላጎት ሊረመርም አይገባም፤ አይችልምም። ምንጊዜም ቢሆን የግብጽፅ ፍላጎት በጉልበት ሌሎች ላይ ሊጫን አይችልም። በጦርነትም አይሆንም።

‹‹ኢትዮጵያውያን ለግብፅ የተሳሳተ ፍላጎት ሲባል ጥቅማቸውን ዘንግተው እጃቸውን አጣጥፈው መብታቸውን ጥለው ይቀመጣሉ ተብለው አይታሰብም።›› ሲሉም ጠቅሰው፤ ግብፅ በጦርነት ፍላጎቷን ለመጫን ስንት ጦርነት ትዋጋለች? ስንት ጊዜስ ትዋጋለች? የግብፅን ጦርነት በትህትና የሚያስተናግድ ማንን ታገኛለች።›› ሲሉም አብራርተዋል።

ፕሮፌሰር ያዕቆብ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ሌሎች የናይል ውሃ አመንጪ አገሮች የራሳቸውን

ጥቅምና መብት ጥለው ግብፅን በትህትና አያስተናግዱም። የጦርነት ሐሳብ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን የቂል አስተሳሰብም ጭምር ነው። በተለይ ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ በጦርነት የውሃ ፍላጎቷን ለማሟላት ማሰቧ በዲፕሎማሲና በመተሳሰብ የመሽራት ሐሳቡም ሆነ እውቀቱ ርቋታል ማለት ነው።

ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=34609
የፀሐይ ግርዶሹን ለመመልከት ሊመጡ የሚችሉ 20ሺህ ቱሪስቶችን እና ሳይንቲስቶችን በኮሮና ሳቢያ ኢትዮጵያ እንዳጣች ተገለጸ
***************************
(ኢፕድ)
አዲስ አበባ፡- በመጪው እሁድ የሚጠበቀውን የፀሐይ ግርዶሽ ክስተት ለመመልከት ብለው ሊመጡ የሚችሉ 20ሺህ ቱሪስቶችን እና ሳይንቲስቶችን ኢትዮጵያ በኮሮና በሽታ ምክንያት ማጣቷን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ከጎብኚዎች ሊገኝ የሚችለው ገቢ በበሽታው ምክንያት ቢቀርም የሀገርን ገጽታ ከማስተዋወቅ አንጻር ግን ክስተቱን በቀጥታ በማህበራዊ ድረገጽ እና የቴሌቪዥን ስርጭት ለዓለም ህዝብ ለማስተላለፍ የባለሞያዎች ቡድን ወደላሊበላ እና ባህርዳር ከተሞች መላኩን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ሰኔ 14 ቀነ 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሚታየውን የፀሐይ ግርዶሽ ለገቢ ማስገኛ፣ ለመልካም ገጽታ ግንባታ እና ለወጣት ኢትዮጵያውያን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማነቃቂያነት እንዲውል ታስቦ ቅድመ ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቷል። ተመሳሳይ ክስተቶች በሌሎች ሀገራት ሲታዩ በአንድ ቀን 20ሺህ ቱሪስት እንደሚገኝ በመታወቁ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ቁጥር ያለው የውጭ ዜጋ እንደሚገኝ ተገምቶ ነበር። ይሁንና ኮሮና በመከሰቱ የአንድ ቀኑን ተፈጥሯዊ ክስተት ለመመልከት ብለው ይመጡ የነበሩ ቱሪስቶችን ኢትዮጵያ አጥታለች።

እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ቱሪስቶችንና የተለያዩ ሳይንቲስቶችን በኢትዮጵያ ለማስተናገድ ባይቻልም የግርዶሹን ክስተት በቀጥታ በማህበራዊ ድረገጽ እና በቴሌቪዥን በማስተላለፍ የሀገርን ገጽታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ዝግጅት ተደርጓል። ለሥራውም ባህርዳርን እና ላሊበላ ከተሞችን ጨምሮ ወደሦስተ ቦታዎች አነስተኛ ቴሌስኮፖች እና የተለያዩ የፀሐይ ግርዶሹን መመልከቻ

መሳሪያዎች ተልከዋል። መሳሪያዎቹን የሚቆጣጠሩ እና የቀጥታ ስርጭቱን ሥራ የሚያሳልጡ ባለሙያዎችም ወደአካባቢዎቹ ተንቀሳቅሰዋል። በዚህምተግባር መላው ዓለም ክስተቱን እንዲከታተለው ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በሳይንሱ ረገድ እያበረከተችው ያለውን አስተዋጽኦ ለዓለም ለማሳየት ጥረት ይደረጋል።

ኢንስቲተዩቱ ከዓለም አቀፉ እና ከአፍሪካ የአስትሮኖሚ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት የፀሐይ ግርዶሹን በተመለከተ የሚደርሱ መረጃዎችን ለዓለም ለማሳወቅ እየሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ አብዲሳ፤ ይህም ኢትዮጵያ በሳይንሱ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎ የምታሳድግበት አንዱ መንገድ መሆኑን ተናግረዋል።

ለተጨማሪ https://www.press.et/Ama/?p=34639
"ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል፡፡ የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን አነስተኛ መጠን ያለው ዴክሳሜታዞን እንደ ድኝገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል። ህክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ ይወጣል"
- ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር